የሰበር መ/24 (ወ/ት እእጅጋየሁ ተሾመ እእና የእቴነሽ በቀለ ሞግዚት ወ/ሮ እእታገኝ ዘነበ/ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.6/1 መሰረት ዳኝነት እእንደገና እእንዲታይ ጥያቄው የሚቀርበው ይግባኝ ከመቅረቡ በፊት ስለመሆኑ)
No summary available.
ጥቅምት 22 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡-
አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አቶ አብዱልቃድር መሐመድ
አቶ ተገኔ ጌታነህ
አቶ መስፍን እቁበዮናስ
ወ/ሪት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- ወ/ት አበራሽ ጉቱ መልስ ሰጭ፡- 1. የመካከለኛው አዋሽ እርሻ ልማት ድርጅት
አቦቦ እርሻ ልማት ድርጅት
ተንዳሆ እርሻ ልማት ድርጅት
የሰሜን Oሞ እርሻ ልማት ድርጅት ፍርድ እንዲፈጸም ስለማቀርብ ማመልከቻና ስለ አፈፃፀሙ ስነስርዓት - ለፍርድ አፈፃፀም ማመልከቻ የውሳኔ አሰጣጥ ስርዓት - ጉድለት ያለበት የፍርድ አፈጻጸም ማመልከቻ ተስተካክሎ እንዲቀርብ ፍ/ቤቱ ትእዛዝ 57 58 ስለማሰጥበት ስርዓት፡- የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 378፣ 384፣ 385/1/ የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መ/ሰጭዎች ለአመልካች ብር 167,831.94 እንዲከፍሉ፤ አመልካች በበኩላቸው ለመ/ሰጭዎች ብር 17,183.94 እንዲከፍሉ፤ ከሰጠው ውሳኔ አመልካች ለመ/ሰጪ ብር 17,182.5A እንዲከፍሉ የተሰጠውን ውሳኔ የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመለወጥ የተጠቀሰውን ገንዘብ/ብር 17,182.5A/ መ/ሰጭዎች ለአመልካች እንዲከፍሉ በመወሰኑ የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሳኔ ከመስጠቱ ቀደም ብሎ የአፈጻጸም ትእዛዝ ሲሰጥ አመልካች ለተጠሪዎች እንዲከፍሉ የተወሰነውን እና በጠቅላይ ፍ/ቤቱ በኋላ የተሻሻለውን ብር 17,182.5A ቀንሰው ቀሪውን ገንዘብ ተጠሪዎች ለአመልካች እንዲከፍሉ የተሰጠው ትእዛዝ እንዲስተካከልና በዋናው ገንዘብ ላይ ወለድ እንዲከፈል ትእዛዝ እንዲሰጥ በአመልካች የቀረበውን አቤቱታ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቱ አመልካች የጠቅላይ ፍ/ቤትን ውሳኔ ባለማያያዙ በውሳኔው መሰረት ትእዛዝ ሂሳብ ሲሰራ ይችል ስላልነበርና በዋናው ፍርድ ወለድ እንዲከፍል የተሰጠ ውሣኔ ባለመኖሩ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቱ የሰጠው ትእዛዝ ትክክል ነው በሚል ውድቅ በማድረጉና ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም ውሳኔውን በማጽናቱ የቀረበ አቤቱታ ውሳኔ፡- የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠው ትእዛዝና የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ተሻሽሐል።
በአንድ ውሣኔ ላይ በከፊል ባለመብት የሆነ ተከራካሪ ወገን ባለመብት የሆነበት የውሳኔ ክፍል እንዲፈጽም ማመልከቻ ከማቅረብ የሚከለክለው ነገር የለም።
የአፈፃፀም ማመልከቻው የቀረበለት ፍ/ቤትም ውሳኔው ካልታገደ በቀር አፈጻጸሙን ላቀጥል ይገባዋል።
ከፊል ባለመብት የሆነ ተከራካሪ ወገን ከፊል ባለመብት የሆነበት የውሳኔ ክፍል እንዲፈጸምለት የአፈፃፀም መዝገብ ከፍቶ ከፊል ባለእዳ በሆነበት የውሳኔ ክፍል ይግባኝ ካቀረበና ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ይግባኝ ባዩን የሚጠቅም ውሳኔ ከሰጠ ባለመብቱ አዲስ የአፈጻጸም መዝገብ መክፈት ሳያስፈልገው፤ ልላ የአፈጻጸም ማመልከቻ በማቅረብ ብቻ የቀድሞው የአፈጻጸም መዝገብ እንዲንቀሳቀስ እና የተሻሻለው ውሳኔ እንዲፈጸምለት ለማድረግ ይችላል።
59 60 4. የመጀመሪያው የአፈጻጸም ጥያቄ የቀረበበት ጉዳይ ተፈጽሞ ያለቀ ቢሆንም እንኳን የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጠው በቀድሞው የአፈጻጸም መዝገብ ላይ እንዳይቀጥል የሚከለክል ምክንያት የለም።
የአፈጻጸም መዝገቡ እንዲንቀሳቀስ የቀረበው ጥያቄ ትክክል ያልሆነ ህግ ተጠቅሶ የቀረበ ቢሆንም እንኳን ማመልከቻው እንዲስተካከል ፍ/ቤቱ ያዛል ወይም ፍ/ቤቱ ራሱ አግባብነት ያለውን ህግ መሰረት አድርጎ ጥያቄውን ይመረምራል እንጅ ማመልከቻውን ውድቅ ማድረግ አይገባም።
በአፈጻጸም ደረጃ ወለድ እንዲከፈል ፍ/ቤቱ ትእዛዝ መስጠት የሚችለው በዋናው ፍርድ ወለድ እንዲከፈል ውሳኔ ከተሰጠ ነው።
መ/ቁ. 1672A ጥቅምት 22 ቀን 1998 ዳኞች፡-
አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አቶ አብዱልቃድር መሐመድ
አቶ ተገኔ ጌታነህ
አቶ መስፍን እቁበዮናስ
ወ/ት ሒሩት መለሰ አመልካች፡- ወ/ሮ አበራሽ ጉቱ ወኪል ሚደቅሳ ጉቱ ቀረቡ ተጠሪ፡-
የመካከለኛ አዋሽ እርሻ ልማት ድርጅት - አልቀረቡም።
አቦቦ እርሻ ልማት ድርጅት አልቀረቡም።
ተንዳሆ እርሻ ልማት አልቀረቡም።
የሰሜን Oሞ እርሻ ልማት ድርጅት - አልቀረቡም።
ለዚህ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው የአሁኑ አመልካች ለፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በ7/7/93 ጽፈው ያቀረቡትን የአፈፃፀም ማመልከቻ መሰረት በማድረግ ፍ/ቤት የሰጠው ትእዛዝ ነው። የአሁኑ አመልካች ለሥር ፍ/ቤት በፃፉት አቤቱታ 61 62
No topics extracted.