/የሰበር መ/73 /የኢትዮጵያ ቴልኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን እእና አአቶ ገንታ ገምአአ/ ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠርኩ እእንደሆንኩ ብቻ ይወሰንልኝ በሚል የሚቀርብ ጥያቄ የክስ ምክንያት የልለው ስለመሆኑ እእና የግል ጥቅምን መሰረት አአድርጐ የሚቀርብን የጥቅማጥቅም ክስ የማየት ስልጣን የስራ ክርክር ችሎት ስለመሆኑ/
No summary available.
ጥቅምት 18 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡-
ውሳኔ፡- የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ጸንቷል።
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.6/1/ መሰረት ዳኝነት እንደገና እንዲታይ ጥያቄው የሚቀርበው ይግባኝ ከመቅረቡ በፊት መሆን አለበት።
በውሳኔው ላይ ይግባኝ ከቀረበ የይግባኙ መዝገብ ቢዘጋም ዳኝነት እንደገና እንዲታይ የሚቀርብ አቤቱታ ተቀባይነት የለውም።
51 52
ጥቅምት 18 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ አብዱልቃድር መሐመድ ሐጐስ ወልዱ ዳኜ መላኩ መስፍን እቁበዮናስ አመልካች፡- ወ/ት እጅጋየሁ ተሾመ ጠበቃው ቀርቧል።
ተጠሪ፡- የእቴነሽ በቀለ ሞግዚት ወ/ሮ እታገኝ ዘነበ ቀርባለች።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ ይህ መዝገብ ተከፍቶ ለሰበር ችሎት ላቀርብ የቻለው የአሁኗ አመልካች ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው ፍ/ቤት በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 6 መሰረት እንደገና ዳኝነት እንዲታይ የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በሚል የሰጠው ብይን መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ሐምል 19 ቀን 1996 ዓ.ም. ተጽፎ እንዲቀርብ ባደረገችው ማመልከቻ መነሻ ነው።
ከመዝገቡ ለመመልከት እንደተቻለው ክርክሩን በመጀመሪያ ያየው የፍደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሟቹ ወታደር በቀለ መኩሪያ ሚያዝያ 8 ቀን 1989 ዓ.ም. አድርጓል በተባለው ኑዛዜ ላይ ግራ ቀኙን አከራክሮ ታህሣስ 17 ቀን 1994 ዓ.ም. ባቀረበው የኑዛዜ ሰነድ ላይ የተመለከተው ፊርማ ተመርመሮ የተናዛዡ አለመሆኑ ተረጋግጧል በሚል ውድቅ በማድረግ ወስኖ ከቆየ በኋላ የኑዛዜው ተጠቃሚ ነኝ የምትለው የአሁኗ አመልካች ግንቦት 30 ቀን 1995 ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ ፍ/ቤቱ ለሰጠው ውሣኔ መሰረት የሆነው ለፖላስ ቴክኒክ ምርመራ ተልኮ እንዲመረመር የተደረገው የኑዛዜ ሰነድ ከፍ/ቤቱ መዝገብ ጋር የተያያዘው ትክክለኛው ሰነድ ሣይሆን በሀሰት ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን ለመረዳት ተችሐል በሚል በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.6/1/ መሰረት እንደገና ዳኝነት እንዲታይ ባቀረበችው አቤቱታ ላይ የአሁኗ ተጠሪ መልስ እንድትሰጥበት ካደረገ በኋላ ሰኔ 29 ቀን 1996 ዓ.ም. በሰጠው ብይን በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.6/1/ መሰረት እንደገና ዳኝነት እንዲታይ አቤቱታ ላቀርብ የሚችለው የይግባኝ ቅሬታ ከመቅረቡ በፊት ነው።
በቀረበው ጉዳይ ግን አመልካች ቀድሞ በተሰጠው ውሣኔ ላይ ለይግባኝ 53 54 ሰሚ ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርባለች። የይግባኝ ቅሬታ አቅርባ ከቆየች በኋላ ይግባኙን በማቋረጥ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.6 መሰረት ዳኝነት ይታይልኝ የሚል ጥያቄ ልታቀርብ አትችልም በሚል ምክንያት ሣይቀበላት ቀርቷል።
አመልካች የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.6/4/ ዳኝነት እንደገና ላታይ ይገባል አይገባም በሚል ፍ/ቤት በሚሰጠው ውሣኔ ላይ ይግባኝ ለማለት አይቻልም ስለሚል ፍ/ቤቱ የሰጠው ብይን መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት የሚለውን በቀጥታ ለሰበር ችሎት ልታቀርብ ችላለች።
በአመልካች በኩል የቀረበው አቤቱታ ከተመረመረ በኋላ እንደገና ዳኝነት ይታይልኝ ጥያቄ ተቀባይነት ያጣው በሕጉ አግባብ መሆን አለመሆኑ ተጣርቶ መወሰን ያስፈልገዋል ተብሎ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ የተደረገ ሲሆን ማመለከቻውም ለአሁኗ ተጠሪ ተልኮ ደርሷት ቀርባ በጽሁፍ መልስ ሰጥታበት ተከራክራለች።
ይህ ችሎት በበኩሉ ዳኝነቱ እንደገና ላታይ አይገባም የተባለው በአግባቡ መሆን አለመሆኑን ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 6/1/ ማናቸውም ሰው ፍርዱን ወይም ውሣኔውን ለሰጠው ፍ/ቤት እንደገና ዳኝነት እንዲታይ አቤቱታ ላያቀርብ የሚችለው በተሰጠው ፍርድ ወይም ውሣኔ ወይም ትእዛዝ ላይ ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርቦ ከማሰማቱ በፊት እንደሆነ ያስረዳል። በቀረበው ጉዳይ የአሁኗ አመልካች ፍ/ቤቱ አስቀድሞ በሰጠው ውሣኔ ላይ ለከፍተኛው ፍ/ቤት የይግባኝ ቅሬታ አቅርባ በፍ/ቤቱ ለምርመራ እያለ ሲቀጥር መቆየቱ ተረጋግጧል። የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የይግባኙን መዝገብ አስቀርቦ በተመለከተበት ጊዜ ሁሉ ይግባኙ በእንጥልጥል ላይ ነበር።
አመልካች ይግባኙን አዘግቻለሁ የምትለው ፍ/ቤቱ የይግባኙን መዝገብ በማስቀረብ ለምርመራ ተበሎ መቀጠሩን በማረጋገጥ ከመለሰው በኋላ ነው። አመልካች ፍ/ቤቱ በሰጠው ውሣኔ ላይ የይግባኝ ቅሬታ አቅርባለች አላቀረበችም የሚለው ጥያቄ ተነስቶ ማቅረቧ ከተረጋገጠ በኋላ ይግባኙን ለሚሰማው ፍ/ቤት መዝገቡ እንዲዘጋላት ጠይቃ አዘግታ መቅረቧ የይግባኝ ቅሬታ አላቀረበችም ለማለት የሚያስችል አይደለም።
አመልካች ይግባኝ ማቅረቧ ከተረጋገጠ ከላይ በተጠቀሰው የሥነ ሥርዓት ሕግ መሰረት እንደገና ዳኝነት ይታይልኝ በሚል የምታቀርበው አቤቱታ ተቀባይነት 55 56 አይኖረውም። በመሆኑም ጉዳዩን በመጀመሪያ ያየው ፍ/ቤት ቀደም ሲል በተሰጠው ውሣኔ ላይ የይግባኝ ቅሬታ ቀርቦበታል በሚል ምክንያት እንደገና ዳኝነት ላታይ አይችልም በሚል በሰጠው ብይን ተፈጽሟል የሚባል የሕግ ስህተት የለም።
ው ሣ ኔ
የሰጠው ብይን በፍ/ሥ/ህ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
No topics extracted.