የሰበር መ/10 /አአቶ ተሾመ ጅፋር እእና የኢትዮጵያ ቴልኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን/ አአጠቃላይ የአሰራን የደመወዝ ጭማሪ አአወሳሰን ስርዓትን ሳይሆን የግል ጥቅምን መሰረት አአድርጐ የሚቀርብን የደመወዝ ጭማሪ ክስ የማየት ስልጣን የስራ ክርክሮች ችሎት ስለመሆኑ/
No summary available.
ጥቅምት 22/98 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ ወ/ሮ ስንዱ ዓለሙ ወ/ሮ ደስታ ገብሩ አቶ አሰግድ ጋሻው አመልካች፡- የኢት/ቴልኮሙኒኬሽነ ኮርፖሬሽን ተጠሪ፡- አቶ ገንታ ገምአ ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ወስነናል።
አቤቱታው ላቀርብ የቻለው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ ሚያዚያ 21/96 ዓ.ም. በመ/ቁ. 3A3/A2/94 በሰጠው ውሣኔ እና የፍድ/ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሣኔውን በማፅናት በመ/ቁ. 3A835 ሰኔ 16/96 ዓ.ም. በሰጠው ትእዛዝ ላይ ነው።
31 32 ለአቤቱታው መነሻ ምክንያት የሆነው የአሁን ተጠሪ በአሁን አመልካች ላይ ለአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ ያቀረበው ክስ ሲሆን፣ የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡በድርጅቱ ውስጥ በጥበቃ ሥራ ተቀጥሬ በመሥራት ላይ የምገኝ ስለሆነና ሥራውም ዘላቂነት ያለው ሆኖ ሣለ የቋሚ ሰራተኛነት መብቴ ላጠበቅልኝ ባለመቻሉ በአዋጅ ቁጥር 42/85 አንቀጽ 9 መሰረት ቋሚ ሰራተኛ እንድሆን፣ ለቋሚ ሰራተኞችም የሚሰጠው ጥቅማጥቅም ክሱን ካቀረብኩበት ጊዜ ጀምሮ እንዲሰጠኝ እንዲወሰንልኝ የሚል ነው።
የአሁን አመልካችም ለቀረበበት ክስ በሰጠው መልስ፡- ተጠሪው የሻምበል ባሻ የውትድርና ማእረግ ያለው በጡረታ ላይ የሚገኝ እንደሆነ ጠቅሶ በወቅቱ ለተፈጠረ የፀጥታ ችግር ምክንያት ችግሩ እስኪወገድ ድረስ ጥበቃውን ለማጠናከር የቀድሞ ወታደሮችን ቀጥሮ ለመመደብ እንዲችል ኰርፖሬሽኑ ለበላይ አካል ጥያቄ አቅርቦ በተፈቀደለት መሰረት ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠረ እንጂ በቋሚነት በሥራ ላይ ላቀጥል የሚችል አለመሆኑን፤ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄውም በህብረት ስምምነቱ ለተወሰነ ጊዜ ለተቀጠረ ሰራተኛ ተፈፃሚ የሚሆን አይደለም በማለት ተከራክሯል።
ቦርዱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ ከሣሽ በአዋጅ ቁጥር 42/85 አንቀጽ 1A መሰረት የተቀጠረ መሆኑን ተከሳሽ በተጨባጭ በማስረጃ አስደግፎ ያላስረዳ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 42/85 አንቀጽ 9 መሰረት ከሣሽ ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠረ ነው።
ጥቅማጥቅምን በተመለከተም በህብረት ስምምነቱ መሰረት ውሣኔው ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ወደፊት እየታሰበ ላሰጠው ይገባል ሲል ወስኗል።
የአሁን አመልካች ውሣኔውን በመቃወም ለከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ ቢያቀርብም ይግባኙ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ይህ አቤቱታ ላቀርብ ችሐል።
በዚሁ መሰረት ቦርዱም ሆነ የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለት ነው ሲል ውሣኔው እንዲታረምለት አመልካች አቤቱታውን ለዚህ ችሎት ያቀረበ ሲሆን፣ ተጠሪውም ቀርቦ መልሱን በመስጠት የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ ስህተት ስለልለበት ውሣኔው ፀንቶ ልሰናበት በማለት ተከራክሯል።
33 34 ይህም ችሎት ከክርክሩ በመነሳት ጉዳዩ ምን የክስ ምክንያት /cause of action/ ቦርድስ ይህን ጉዳይ ለማየት የሚያስችለው ሕጋዊ ሥልጣን አለው ወይ?
የሚሉትን ጭብጦች በመያዝ ከሥር ውሣኔና አግባብ ካለው ሕግ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው መርመሮታል።
የክስ ምክንያት /cause of action/ አለ ወይም የለም የሚለውን ከማየታችን በፊት የዚህን ቃል ፅንሰ ሃሣብ ማየቱና መረደቱ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።
ስለ ክስ ምክንያት /cause of action/ ፅንስ ሀሳብ በ1958 ዓ.ም. በወጣው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ውስጥ መካተቱን ከሕጉ አንቀጽ 29፣8A/2/፣ 224/2/፣ 23/1//ሀ/ … ወዘተ መረዳት የሚቻል ሲሆን ለቃሉ የሰጠው ትርጉም ግን የለም።
በመሰረቱ ማንም ሰው በህግ ችሎታ ኖሮት በልላ ሰው ላይ ማናቸውንም ክስ ለማቅርብ እንዲችል አስቀድሞ ለክሱ መነሻ በሆነው ነገር ወይም ክሱ በተመሰረተበት ነገር ላይ ጥቅም ወይም መብት ያለው መሆኑ መረጋገጥ እንደሚገባው የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33 ይደነግጋል። በዚህም ከሣሽ ከተከሣሽ ላይ ላፈፀም የሚችል መብት አለኝ ብሎ ለማለት አስቀድሞ ለመብቱ መገኘት መነሻ የሆነውን ነገር በማረጋገጥ የተጠየቀውን ዳኝነት ለማግኘት ከሣሹ በሕግ መብት ያለው መሆን ይኖርበታል።
ከሕጉ አንቀፅ 8A(2) ላይም መረዳት የሚቻለው የክስ ምክንያት ሲባል አንድ ሰው አንድን ነገር ከአንድ ሰው ላይ ለማግኘት ፍ/ቤቱ እንዲወስንለት ክስ ለማቅረብ የሚያስችለው የፍሮ ነገር ሁኔታ ሲሆን፣ ይህም ፍሬ ነገር ዳኝነት ለማግኘት የሚያስችል መሆን ያለበት መሆኑን ነው።
ሮበርት አለን ሴድለር "Ethiopian civil procedure" በሚል ርእስ ባዘጋጁት መጽሀፍ ላይ "የክስ ምክንያት" አለ ብሎ ለመወሰን የሚቻለው በክሱ ላይ የቀረበው ነገር ቢረጋገጥ ከሣሹ የጠየቀውን ዳኝነት ለማግኘት ሕግ ይፈቅደሉታል ወይ? ለሚለው ጥያቄ አዎንታዊ ምላሽ መስጠት ሲቻል እንደሆነ ገልፀዋል።
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስም በግራ ቀኙ መካከል በቅጥር ላይ የተመሰረተ የሥራ ውል ግንኙነት መኖሩ አልተካደም። ተጠሪው በሥር ያቀረበው ክስ በአዋጅ ቁጥር 42/85 አንቀፅ 9 መሰረት ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ ልቆጠር ይገባል በማለት ሲሆን፣ ከዚሁ የቋሚ ልሁን ጥያቄው ጋር በተጓዳኝ ያቀረበው ለልሎች ቋሚ ሰራተኞች የተሰጠው 35 36 ጥቅማጥቅም ለእኔም ይሰጠኝ የሚል ነው። የአሁኑ ተጠሪ ለቦርዱ ያቀረበው ክስ የክስ ምክንያት ያለው መሆን አለመሆኑን ለመመርመር እነዚህን ጥያቄዎቹን ለያይቶ ማየት ያስፈልጋል። ተጠሪው ቋሚ ልሁን ሲል ያቀረበው ዋነኛው ጥያቄ ከአመልካች ጋር አድርጎት የነበረው ውል ባሕርይ እንዲተረጎምለት የጠየቀበት ሲሆን፣ ለልሎች ሰራተኞች የተጠሰው ጥቅማ ጥቅም ለኔም ይሰጠኝ የሚለው ጥያቄ ደግሞ በውሉ መሰረት ላያገኝ የሚገባውን ነገር ግን ቀረብኝ ያለውን ጥቅም ለማስከበር የቀረበ ጥያቄ ነው። የመጀመሪያው የውሉ ባሕርይ እንዲገለጽለት ከመጠየቅ የዘለለ ጥቅም የልለው ሲሆን ሁለተኛው ግን ውሉ አልተከበረምና ውሉን የጣሰው ወገን የውሉን ቃለ እንዲያከብር እንዲደረግለት የሚጠይቅ ነው።
በመካከላቸው የሥራ ውል የተፈፀመ ስለመሆኑ ግራ ቀኙ የተቀበሉበት ጉዳይ ነው። የሥራ ውል የራሱ ልዩ ባሕሪያት ያሉት ቢሆንም ከአጠቃላይ ውሎች ጋር የሚጋራቸው በርካታ ባሕሪያት እንዳሉትም መገንዘብ አስፈላጊ ነው። ከእነዚህ አንዱና ዋነኛው ውል ከተፈፀመ በኋላ ይኸው ውል በተዋዋዮች መካከል የአስገዳጅነት ባሕርይ ያለው መሆኑ ነው። ተዋዋዮቹ በውሉ የሚገደዱት በመርህ ደረጃ ሁለቱም ስምምነት ላይ ከደረሱበት ጊዜ ጀምሮ ነው። በመሆኑም ተዋዋይ ወገኖች ከውል የሚመነጭ መብት ለማግኘት የፍርድ ቤት ውሣኔ የግድ አያስፈልጋቸውም። ውሎች የፍርድ ቤቶች ይሁንታ ሳያስፈልጋቸው በአንዱ ወይም በልላው ተዋዋይ ወገን ላይ መብትና ግድታ የሚጥሉ በመሆናቸው ተዋዋዮች ወደ ፍርድ ቤቶች ላመጡ የሚገባው በውሉ መሰረት አልተፈፀመም የሚሉት ነገር ካለ ብቻ ወይም ውሉ ሕጉ ለይቶ ባስቀመጣቸው ምክንያቶች እንዲፈርስላቸው የፈለጉ እንደሆነ ብቻ ነው። ከዚሀ ውጪ በተዋዋዮቹ መካከል ያለው የውል ዓይነት እንዲነገር ወይም ውሉ እንዲፀድቅ ለፍርድ ቤቶች ጥያቄ ላቀርብ አይገባም።
ይህ አጠቃላይ የውሎች መሰረት ሃሣብ በሥራ ውልም ላይ ተፈጻሚነት አለው። በአዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 9 የሰፈረው መሰረት ሃሣብ በመርህ ደረጃ አንድ ሰራተኛ ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠረ የሚገመት መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው። የአዲሱ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 9 ድንጋጌም ተመሣሣይ ይዘት ያለው ነው። ማንኛውም በአዋጁ የሚሸፈን 37 38 ሰራተኛ የዚህ የህግ ግምት ተጠቃሚ ነው። ይህ የሕግ ግምት የሕግ ውጤት እንደመሆኑ የፍርድ ቤት ችሮታ ሳያስፈልገው ውሉ ከተፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ የሚሰራ የሕግ ግምት ነው። በመሆኑም አንድ ሰራተኛ ከውሉና ከዚህ ሕግ ግምት አንጻር ጎደለብኝ የሚለው ነገር ካለ ከሚጠይቅ በቀር ቋሚ ነህ ልባል የሚል ጥያቄ ላያቀርብ አይገባውም። በአሰሪውና በሰራተኛው መካከል የተፈፀመው ውል በሕጉ ግምት የሚሸፈን ሳይሆን አዋጁ በአንቀጽ 1A/በአዲሱም አዋጁ አንቀጽ 1A/ የሚሸፈን ነው የሚል ክርክር ላነሳ እንደሚችል ግልጽ ነው። ሆኖም ይህም ቢሆን ላነሣ የሚችለው ሰራተኛው ቀረብኝ የሚለው ጥቅም ወይም በአሰሪው ከሕጉና ከውሉ ውጪ ተፈፀመ የሚለውን በደል ማሳየት ሲችል ነው። በመሆኑም በኔና በአሰሪዬ መካከል ያለው የሥራ ውል ጊዜያዊ ሳይሆን ቋሚ ነው ተብሎ የተርጎምልኝ የሚለው ክስ የክስ ምክንያት ያለው ባለመሆኑ በቦርድም ይሁን በመደበኛ ፍርድ ቤቶች ላስተናገድ የሚገባው አይደለም። ከዚህም በተጨማሪ ቋሚ ልሁን የሚለው ጥያቄ የአንድን ሰራተኛ የውል ግንኙነት እንጂ አጠቃላይ የሥራ ሁኔታውን የሚመለከት ባለመሆኑ የግል የሥራ ክርክር እንጂ የወል የሥራ ክርክር አይደለም በመሆኑም ጉዳዩ የክስ ምክንያት የልለው ከመሆኑም በተጨማሪ ለአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የሚቀርብም ጉዳይ አይደለም። ቦርዱ ሥልጣን ያለው የወል የሥራ ክርክሮችን ለመመልከት እንጂ የግል የሥራ ክርክር ለመዳኘት አይደለም። በመሆኑም በሁለቱም ተደራራቢ ምክንያቶች ቦርዱ የቀረበለትን ይህን የመጀመሪያ ጥያቄ ማስተናገዱ አግባብ አይደለም።
ከላይ እንደተመለከትነው ሰራተኛው ለልሎች ሰራተኞች የተሰጠው ጥቅም ለኔም ይጠበቅልኝ የሚል ጥያቄ አያይዞ ያቀረበ በመሆኑ ቦርዱ ጉዳዩን ማስተናገዱ የሚያመጣው ለውጥ መኖር አለመኖሩ ቀጥሎ የምንመለከተው ጉዳይ ነው። ከላይ እንደተመለከተው ይህ ጥያቄ አስፈሪው የውሉን ወይም የሕጉን ወይም የሁለቱን ድንጋጌ በመፃረር መብቴን ተጋፍቷል የሚል እንደምታ ያለው በመሆኑ የክስ ምክንያት የለውም ላባል የሚችል አይደለም። ውሉ የተጣሰበት ወገን 39 40 መፍትሄ ፍለጋ ወደሚመለከተው አካል ከሶ መቅረቡ ተገቢ ነው።
ውል ወይም ሕግ ተጥሶ የአንድ ወገን መብት የተጓደለ ከሆነ መብቱን ለማስጠበቅ ክስ ማቅረብ ትክክለኛ አሰራር ነው። ጥቅም ተጓደለብኝ የሚል ሰራተኛ በሕጉ አንቀጽ 9 መሰረት ቋሚ ነው የሚል የህግ ግምት ተጠቃሚ ስለሆነ ቋሚ መሆኑን ማስረዳት አያስፈልገውም። ሰራተኛ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እስካቀረበ ድረስ ጉዳዩን የሚያየው አካል ቋል እንደሆነ ግምት መውሰድ ይገባዋል፣ ቋሚ እንዳልሆነ ማስረዳት የልላኛው ወገን ኃላፊነት ነው።
ነገር ግን ይህ ጥቅም ቀረብኝ የሚል ሰራተኛ የሚያቀርበው ክስ የዛን ሰራተኛ ጉዳይ ብቻ የሚመለከት በመሆኑ በሕጉ አንቀጽ 138 መሰረት እንደግል የሥራ ክርክር የሚቆጠር እንጂ የወል የሥራ ክርክር አይደለም። ስለዚህ ከዚህ ጥያቄ የሚቀርበው ክስ የክስ ምክንያት የለውም ባይባልም ለቦርዱ ቀርቦ የሚስተናገድ ነጥብ ግን አይደለም። የወል የሥራ ክርክር ከግል የሥራ ክርክር የሚለየው በምንድነው የሚለው የሕግ ነጥብ ላይ ይህ ፍ/ቤት በመዝግብ ቁ.1818A በሐምል 29 ቀን 1997 ዓ.ም. ውሣኔ የሰጠበት በመሆኑ አሁን በዝርዝር መድገሙ አስፈላጊ አይደለም። ዋናው ነጥብ አንድ ሰራተኛ እሱን ብቻ የሚመለከትና የልሎችን ሰራተኞች የሥራ ሁኔታ የማይመለከት ክስ ያቀረበ እንደሆነ ጉዳዩ የግሉ የሥራ ክርክር እንጂ የወል የሥራ ክርክር ሆኖ ላታይ አይገባውም። የወል የሥራ ክርክር ካልሆነ ደግሞ ለቦርዱ ቀርቦ ውሣኔ ላሰጥበት የሚገባ አይሆንም። በአዋጃ ቁ. 42/85 አንቀጽ 1382 መሰረት በአዲሱም አዋጅ ቁ.377/96 አንቀጽ 138 የግል ሥራ ክርክርን የማየት ሥልጣን ያለው መደበኛ ፍርድ ቤት ነው። በመሆኑም በዚህም ረገድ ቦርድ የሄደበት አቅጣጫ ሕጉ ካስቀመጠው ሥርዓት ውጪ ነው። በመሆኑም ለልሎች ሰራተኞች የተሰጠ ጥቅማ ጥቅም ለኔ አልተጠበቀልኝም የሚለውን አጠቃላይ ክስ ቦርዱ የተመለከተው ከስልጣኑ ውጪ በመሆኑ ላሻር የሚገባው ነው።
ለማጠቃለል ቋሚ ሰራተኛ እንደሆንኩ ይወሰንልኝ የሚለው ክስ የክስ ምክንያት የልለው በመሆኑና የግል ጉዳይም በመሆኑ፣ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄውም የግል ክርክር በመሆኑ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ቀርበው መታየታቸው የጉዳዩ አመራር የህጉን ሥርዓት 41 42 ያልተከተለ በመሆኑ ትክክለኛውን የሕግ ትርጉም ተከትሎ እንዲሄድ ማድረግ አስፈላጊ ነው።
ውሣኔ
የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ሚያዝያ 21/96 ዓ.ም. በቁጥር 3A3/A2/94 የሰጠው ውሣኔና የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 3A835 ሰኔ 16/96 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብሥ/ሥ/ቁ. 348/1/ መሰረት በድምጽ ብልጫ ተሽረዋል።
ውሣኔዎቻቸው የተሻሩ መሆናቸውን እንዲያውቁት የፍርዱና የውሣኔው ቅጂ ይተላለፍላቸው።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ በየራሳቸው ይቻቻሉ
No topics extracted.