የሰበር መ/70 /የአስር አአለቃ ተሻገር አአስታጥቄ እእና አአቶ አአዊስ አአው አአበዲ/ በከተማ ቦታ ላይ ስለሚኖር መብት/
No summary available.
መ/ቁ. 1541A ጥቅምት 1 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡-
ውሣኔ የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
የአሰሪ አጠቃላይ የደመወዝ ጭማሪ አወሳሰን ሥርዓት ሕገ ወጥ ነው በሚል የሚቀርብን ስክ የማየት ሥልጣን የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ነው።
የግል ጥቅምን መሰረት አድርጎ የሚቀርብን የደመወዝ ጭማሪ ክስ የማየት ስልጣን የሥራ ክርክር ችሎት ነው፡ ጥቅምት 1 ቀን 1998 ዓ.ም.
የመ.ቁ. 15410 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ ወ/ሮ ስንዱ ዓለሙ አቶ አሰግድ ጋሻው ወ/ሮ ደስታ ገብሩ አመልካች፡- አቶ ተሾመ ጅፋር - ቀረበ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ቴልኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን - ግርማ ማርቆስ ቀረበ
በዚህ መዝገብ የተያዘው የአመልካች እና የተጠሪ ክርክር የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄን የሚመለከት ነው። አመልካች ተጠሪው የተጠቀሰውን ክፍያ ይክፈለኝ ሲል ከአሰሪ እና ሰራተኛ ቦርድ ዘንድ ክስ ይመሰርታል። ቦርዱም በሁለቱ መካከል በነበረ ክርክር አስቀድሞ የተሰጠ ፍርድ እንደነበር ጠቁሞ ይህም ጥያቄ አብሮ ፍርድ እንዳገኘ 25 26 የሚቆጠር ነውና በአፈፃፀም እንጂ በክስ ላጠየቅ የሚገባው አይደለም በማለት ይወስናል።
ከዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ደግሞ የደመወዝ ጭማሪን አስመልክቶ የተሰጠ ፍርድ ስለልለ ጥያቄው በክስ እንጂ በአፈፃፀም ላጠየቅ አይገባም በማለት የቦርዱን ውሣኔ ሳይቀበለው ቀርቷል።
እንደዚሁም ቦርዱ የደመወዝ ጭማሪውን ክርክር አይቶ ውሣኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዳዩን መልሶለታል። ጉዳዩን ወደ ቦርድ የመለሰውም ይህን ክርክር የመዳኘት ስልጣን ያለው ቦርድ እንጂ ፍ/ቤት አይደለም በሚል እምነት መሆኑን በውሣኔው አመላክቷል።
በመቀጠል ጥያቄው በቀጥታ ክስ አይነት ለአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ ቀርቦለታል። ቦርዱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዳዩን ለመዳኘት ስልጣን የለኝም ሲል መዝገቡን ዘግቶታል። የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ደግሞ አስቀድሜ ፍርድ የሰጠሁበት ጉዳይ ስለሆነ ደግሜ ላየው የምችልበት ሥርዓት የለም በማለት በአሁን አመልካች የቀረበለትን ይግባኝ ውድቅ አድርጎታል።
ይህም ችሎት በግራ ቀኙ የቀረበለትን ክርክር መርምሯል።
ምላሽ ላያገኝ የሚገባው የጉዳዩ ጭብጥም ቦርድ ይህን የደመወዝ ጭማሪ ክርክር ለመዳኘት ሥልጣን አለው? ወይስ የለውም? የሚለው መሆኑን ተገንዝቧል።
ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው የአመልካች የደመወዝ ጭማሪ ይገባኛል ክርክር ተጠሪው በዚህ ረገድ የወሰደው አጠቃላይ እርምጃ የሰራተኞችን መብትና ጥቅም የሚጎዳ ነው የሚል ይዘት ያለው አይደለም። አለያም የተጠሪው የደመወዝ ጭማሪ አወሳሰን ሕገ ወጥ ነውና ላሰተካከል ይገባዋል በሚል አይነት የቀረበ አይደለም። ይልቁንም ክርክሩ የግል ጥቅምን ወይም መብትን ከማስከበር አኳያ የቀረበ መሆኑን በግልጽ መረዳት የሚቻል ነው። ይህም ይህ ችሎት በመ.ቁ.
18180 ለግል እና ለወል የሥራ ክርክር አይነቶች ከሰጠው ትርጉም አኳያ ሲታይ የግል እንጂ የወል የሥራ ክርክር የሚሰኝ አይደለም። ጉዳዩን የመዳኘት ሥልጣንም የፍ/ቤት እንጂ የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ አይሆንም።
ስለሆነም ቦርዱ ጉዳዩን ለመዳኘት ሥልጣን የለኝም የሚል ውሣኔ መስጠቱ የሚነቀፍ አይደለም። በተጨማሪም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን ወደ ቦርድ ሲመልሰው ክርክሩን የመዳኘት ሥልጣን ያለው ቦርድ ነው በሚል እምነት እንጂ ይህን ነጥብ በጭብጥነት ይዞ ፍርድ ያልሰጠበት መሆኑን ከውሣኔው መገንዘብ ስለሚቻል ቦርዱ የሥልጣኑን ጥያቄ በጭብጥነት ይዞ ፍርድ መስጠቱ ጉዳዩን እንዲዳኝ ከመለሰለት የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ፍርድ ጋር አይጣጣምም ወይም ይቃረናል ላያሰኘው የሚችል አይሆንም። እንዲሁም ለሁለተኛ ጊዜ ይግባኝ የቀረበለት የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን እንደገና እንዳይ የሚፈቅድልኝ 27 28 ሥርዓት የለም ሲል የሰጠው ምክንያት የሕግ መሰረት ያለው ሆኖ ባይታይም ይግባኙን ውድቅ በማድረጉ ግን የፈፀመው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥህተት የለም።
ው ሣ ኔ የአሰሪ እና ሰራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ በመ.ቁ.14/01/93 የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ደግሞ በመ.ቁ. 21501 የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል።
ጥቅምት 22 ቀን 1998 ዓ.ም.
የመ/ቁ.16273 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ ወ/ሮ ደስታ ገብሩ አቶ አሰግድ ጋሻው አመልካች፡- የኢትዮጵያ ቴልኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ተጠሪ፡- አቶ ገንታ ገምአ የ ስራ ክርክር - የክስ ምክንያት መኖር -(በቋሚ ልሁን ጥያቄ ላይ) የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ስልጣን (የቋሚነት ጥያቄንና የግል የጥቅማጥቅምን አወሳሰን በተመለከተ)- የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 9፣1አ፣138 142 ፡- ከሳሽ ስለመሆን ችሎታ፡- የፍትሐብሕር ሥነ ስርዓት ህግ ቁጥር 33 አመልካች ያቀረበውን ጥያቄ በመቀበል አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ እንዲሁም የከፍተኛው ፍ/ቤት የአሁን ተጠሪ ቋሚ ሰራተኛ እንዲሆንና ጥቅማ ጥቅምም እንዲሰጠው በማለት ስለወሰኑ የቀረበ አቤቱታ።
29 30 ውሳኔ፡- የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ እና የፍድራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሳኔ በድምፅ ብልጫ ተሽሯል።
አንድ ሰራተኛ ከውሉና ከሕግ አንጻር ጐደለብኝ የሚለው መብት ካለ ከሚጠይቅ በቀር ቋሚ ልሁን በሚል የሚያቀርበው ጥያቄ የክስ ምክንያት /Cause of action/ የለውም።
የጥቅማ ጥቅም ክፍያን በተመለከተ ይህ ጥቅም ቀረብኝ የሚል ሰራተኛ የሚያቀርበው ክስ የዛን ሰራተኛ ጉዳይ ብቻ የሚመለከት በመሆኑ እንደግል የሥራ ክርክር የሚቆጠር እንጂ የወል የሥራ ክርክር አይደለም። ስለሆነም የጥቅማጥቅም ይከፈለኝ ጥያቄ የግል ክርክር በመሆኑ ለአሰሪና ሰራተኛ ወሳኝ ቦርድ ቀርቦ የሚስተናገድ አይሆንም፡
No topics extracted.