በአንዳንድ ውሎች የተመለከተ የአገልግሎት ክፍያ መጠን ለመቀነስ ፍርድ ቤት ስላለው ስልጣን /አአስቴር አአርአያ እእና ግርማ ወዳጆ/ ............................... 75 የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
No summary available.
የመ/ ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሰሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ ወ/ት መስፍን አቁበ ዮናስ አመልካች፡- አስቴር አርአያ መልስ ሰጭ፡- አቶ ግርማ ወዳጆ ውል - የውል ጉዳይ አወሳሰን - ስለ ውሎች ውጤት ውለን በመተርጐም ሰበብ ደኞች አንድ ውል ላፈጥሩ ስላለመቻላቸው - ስለ አንዳንድ ውሎች የተጻñ ለዩ ለዩ ደንቦች የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥሮች 1711፣1731፣1676/2/፣2635፣2640፣2646 የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካከ ባቀረበችው ክስ በጠየቀችው መሰረት ተጠሪ አመልካች ከከፈለው ብር 35,000/ ሰላሣ አምስት ሺህ/ በተጨማሪ በፍርዱ ከተገኘው ጥቅም 20% ብር 124,188.59 /አንድ መቶ ሃያ አራት ሺህ አንድ መቶ ሰማኒያ ስምንት ብር ከሃምሣ ዘጠኝ ሣንቲም/ ለአመልካች እንዲከፍል ሲወስን ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበበት የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በበኩሉ አመልካች ለሰጠችው አገለግሎት ካገኘችው መደበኛ ክፍያ በተጨማሪ በፍርድ ከሚገኘው ጥቅም 20% ታስቦ እንዲከፈላት በውል የተደረገው ቃል በፍትህ ሆነ በርትእ የሚደገፍ አይደለም በሚል የከፍተኛውን ፍ/ቤት ውሣኔ በመሻሩ የቀረበ አቤቱታ ውሳኔ፤- የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ ተሻሽሐል።
ህግ ከወሰናቸውና ከከለከላቸው ነገሮች ውጭ ተዋዋይ ወገኖች የሚዋዋሉበትን ጉዳይ እንደፈለጋቸው የመወሰን መብት ያላቸው ሲሆን በዚህ መሰረት የሚደረጉ የውል ስምምነቶች በተዋዋይ ወገኖች መካከል እንደ ህግ ሆነው ይቆጠራሉ።
ሆኖም ልዩ የእውቀት ያላቸውን የስራ ውሎች የሚያደርጉ ተዋዋዮች ስምምነት ላይ የደረሰባቸው የስራ ዋጋዎች ከመጠን በላይ መሆናቸው ግልፅ በሆነ ጊዜና ለሙያ ስራ ተግባሩም ክብር ተቃራኒ ሆኖ በተገኘ ጊዜ መጠኑን ዳኞች በመሰላቸው ላቀንሱት ይችላሉ።
የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት የመ/ቁ17191 ሐምል 29 ቀን 1997 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሰሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ አቶ መስፍን እቁበ ዮናስ አመልካች፡- ወ/ሮ አስተር አርአያ ተጠሪ፡- አቶ ግርማ ወዳጆ መዝገቡን መርመረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በሰበር ችሎቱ ለቀረበው ጉዳይ መነሻ የሆነው ክስ የተጀመረው በፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኗ አመልካች ለተጠሪ በሰጡት የጥብቅና አገልግሎት ሥራ የካቲት 3 ቀን 1987 በተደረገው የጥብቅና ሙያ አገልግሎት ውል መሰረት በማድረግ ተጠሪ ለአመልካች ከከፈለው ብር 35,000 (ሰላሣ አምስት ሺህ ብር) በተጨማሪ “ከፍርዱ ከሚገኝ ጥቅም 20% ላከፍል የተስማሙበትን ብር 520,000 (አምስት መቶ ሃያ ሺህ ብር) አመልካች በክሱ ምክንያት ካወጣው ወጭና የጠበቃ አበል ጋር ይከፈል በማለት ክስ መስርቷል።
ፍርድ ቤቱም ግራቀኙን አከራክሮ የአሁኑ ተጠሪ #ጥቅም$ አላገኘሁም በሚል በሙያ አገልግሎት ውሉ የተስማማበትን ክፍያ አልከፍልም ማለቱ አግባብ አለመሆኑን ገልጾ፣ የቤቱን ሸያጭ ዋጋ ግምት መሰረት በማድረግ 124,188.59 (አንድ መቶ ሃያ ራት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ስምንት ብር ከሃምሣ ዘጠኝ ሣንቲም) የዳኝነቱንና የጠበቃ አበሉን ጨምሮ ይከፈል በማለት ወስኗል።
ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለት የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በበኩሉ፣ አንድ የጥብቅና ሙያ አገልግሎት የሚሰጥ ሙያተኛ ለአገልግሎቱ እንዲከፈለው ከተወሰነለት መደበኛ የክፍያ በተጨማሪ #ከፍርድ ከሚገኘው ጥቅም$ ታስቦ እንዳከፈለው የሚደረግ የውል ቃል በርትእም ሆነ በፍትህ የሚደገፍ አይደለም በማለት የሥር ፍቤትን ውሣኔ ሙሉ በሙሉ ሸሮታል።
የአሁን አመልካች በሰበር እንዲታይላት ያቀረበችው ማመልከቻ የሕግ ትርጉም የሚያስነሱ ነጥቦች ያሉት መሆኑን በማመን ጉዳዩ ለሰበር እንዲቀር ተደርጓል። በዚህ መሰረት ተጠሪ መልሷን አመልካች ደግሞ የመልስ መልሱን እንዲያቀርቡ ተደርጐ ክርክሩ አብቅቷል።
ይህ የሰበር ችሎት ጉዳዩን መርምሯል። በዚህ ጉዳይ በዋናነት የሕግ ትርጉም የሚያስፈልገው ጭብጥ የእውቀት ጠባይ ያላቸው የሥራ ውሎችን አስመልከቶ በተዋዋይ ወገኖች መካከል ስምምነት በተደረሰባቸው የክፍያ መጠኖች ላይ አለመግባባቶች ሲነሱ የዳኞች ሚና ምን ይሆናል? የሚለው ነጥብ ነው።
እንደሚታወቀው ማንኛውም ውል በተዋዋይ ወገኖች ፈቃድ ላይ ተመስርቶ የማደረግ ስምምነት ነው። ሕግ ከወሰናቸውና ከከለከላቸው ነገሮች ውጭ ተዋዋይ ወገኖች የሚዋዋሉበትን ጉዳይ እንደመሰላቸው የመወሰን መብት ያላቸው መሆኑን የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1711 ያሰገነዝባበናል። ውሉን ለመዋዋል ሕጉ በሰጠው ነፃነት መሰረት የሚደረገው የውል ስምምነቶች በግራ ቀኝ ተዋዋይ ወገኖች መካከል መብትና ግድታዎች የሚጥሉ በመሆናቸው ባቋቋሟቸው ሰዎች ላይ እንደ ሕግ ሆነው የሚያገለግሉ መሆናቸውን ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1731 መገንዘብ ይቻላል።
በያዝነው ጉዳይ የአሁኗ አመልካችና ተጠሪ የካቲት 3 ቀን 1987 ዓ.ም የጥብቅና ሙያ አገልግሎት ውል ያደረጉ መሆኑን ተረድተናል። በዚህ ውል ስምምነት መሰረት ተጠሪ በሕገወጥ መንገድ ተይዞብኛል የሚለውን ቤት በማስመለስ ረገድ የአሁኗ አመልካች ለምታበረክተው ሙያዊ የጥብቅና አገልግሎት ብር 35,000 (ሰላሣ አምስት ሺህ ብር) ለመክፈልና ከፍርዱ ከሚገኘው ጥቅም 20% ለመክፈል የተስማሙ መሆኑን ከሥር መዝገቡ ተረድተናል። በዚህ የውል ስምምነት ቤት የተመለሰለት የአሁኑ ተጠሪ ብር 35,000 (ሰላሣ አምስት ሺህ) ለአመልካች የከፈለ ቢሆንም ከፍርድ ከሚገኘው ጥቅም ለመክፈል የተስማሙበትን 20% እንዲከፍል ክስ በቀረበበት ጊዜ #ጥቅም$ አላገኘሁም በሚል ሲከራከር የቆየ ቢሆንም ጉዳዩን የመረመረው የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሉን መሰት በማድረግ የንብረቱን ግምት አስልቶ ተጠሪ ብር 124,188.59 (አንድ መቶ ሃያ ራት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ስምንት ብር ከሃምሣ ዘጠኝ ሣንቲም) እንዲከፍል በማለት ወስኗል።
የፍድራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ከፍ ሲል የገለጽነውን የውል ሕግ መሰረታዊ መርህ የሆነውን #በፍቃደኝነት ወዶ መዋዋልን$ መሰረት አድርጐ ውሣኔ የሰጠ ቢሆንም 77 78 የዚህ መርህ አፈጻጸም በፍትሐብሕር ሕጉ ውስጥ አግባብ ካላቸው ልዩ ድንጋጌቻች ጋር እንድት መገናዘብ እንደሚገባው ሳይመረምር ከውሣኔ እንደደረሰ ለመገንዘብ ችለናል።
ጉዳዩን በይግባኝ ያየው የፍድራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት በበኩሉ በግራቀኙ መካከል በሕጋዊ መንገድና በፈቃደኛነት የተቋቋመን ግልጽ ውል ትርጉምንና ርትእን ምክንያት በማድረግ የፍትሐብሕር ሕግ ቁ.1711፣1714(2) እና 1733 ከሚደነግጉት ውጭ እና በወቅቱ በሥራ ላይ ያልነበረን ደንብ ዋቢ በማደረግ #ከፍርድ የሚገኘውን ጥቅም$ ለሙያዊ አገልግሎት በሚደረግ ስምምነት ውስጥ ላጠየቅ አይገባም በማለት ተዋዋይ ወገኖች በስምምነት ያስቀመጡትን ግልጽ የውል ቃል ያለምንም የዉል ማፍረሻ ምክንያት ውድቅ እንዲሆን ማድረጉ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከፍ ብለን ለማሳየት እንደሞከርነው የየትኛውም ሕጋዊ ውል መሰረቱ በፈቃድ መስጠት ላይ የተመሰረተ ስምምነት መሆኑ አያከራክርም። ተዋዋይ ወገኖች ሕጉ በሰጣቸው ነፃነት ተጠቅመው ንብረትነትን የሚመለከቱ ግድታዎችን ለማቋቋም ለመለወጥ ወይም ለማስቀረት ስምምነት ማድረግ እንደሚችሉ ይታወቃል። ይህ በጠቅላላ ክፍሉ የተነገረው የውል መሰታዊ መርህ እንደተጠበቀ ሆኖ እነዚህን ጠቅላላ ደንቦች የሚለውጡ ወይም የሚያሟሉ ስለ አንዳንድ ውሎች የተጻñ ልዩ የሆኑ ደንቦች ካሉ በፍትሐብሕር ሕግ 5ኛ መጽሐፍ እና በንግድ ሕጉ የሚመለከቱ ስለመሆኑ የፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 1776(2) ያስገነዝባል።
በዚህም መሰረት አሁን ግራቀኙ እየተከራከሩበት ያለው ሙያዊ የእውቀት ሥራ የሚመለከት ውል በፍትሐብሕር ሕጉ 5ኛ መጽሐፍ ውስጥ ከሚገኙት ልሎች መካከል አንደኛ እንደሆነ እንገነዘባለን። ልዩ የእውቀት ጠባይ ያላቸው የሥራ ውሎች ደግሞ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2632 እና በሚቀጥሉት ቁጥሮች ውስጥ በተመለከቱ ድንጋጌዎች የሚመሩ ናቸው። እነዚህ የውል አይነቶች ልዩ እውቀትን የሚመለከቱ በመሆናቸው የተለየ ስምምንት ከልለ በቀር የእውቀት ሥራውን የተዋዋለው ሰው ግድታዎቹን ራሱ መፈፀም እንደሚጠበቅበት ከሕጉ ቁጥር 2636(1) መገንዘብ ይቻላል።
ተዋዋይ ወገኖች ውሉን ፈቅዶ የመዋዋል መርህን ተጠቅመው እነዚህን አይነት መሰል ውሎች መዋዋል ቢችሉም በነዚህ ልዩ ውሎች መሰረት ስምምነት ላይ የተደረሱባቸው የሥራ ዋጋዎች ከመጠን በላይ መሆናቸው ግልጽ በሆነ ጊዜ እና ለሙያ ሥራ ተግባሩም ክብር ተቃራኒ ሆኖ በተገኘ ጊዜ የሥራ ዋጋ መጠኑን ዳኞች በመሰላቸው ላቀንሱት እንደሚችሉ ተደንግጓል። የዚህ ሕግ አይነተኛ ዓላማ የተለየ እውቀት በሚሻው ጉዳይ ዙሪያ አማራጭ የልለውን ወይም አማራጩ በእጅጉ ላጠብበት የሚችለውን ተዋዋይ ወገን የሙያውን ተግባር ከሚያከናውነውና ልዩ እውቀት ካለው ሙያተኛ ተዋዋይ ወገን ጋር ውልን ፈቅዶ በመዋዋል ረገድ የሚኖረውን ቦታ (position) በተቻለ መጠን ለማቀራረብ እንደሆነ ይገመታል። በዚህ ረገድ በአብነት ላጠቀሱ ከሚችሉት ጉዳዮች መካከል ከቀዳጅ ሀኪሞች፣ ከጥርስ ሐኪሞች ወይም ከአእምሮ በሽታ ሐኪምች እና ሰዎችን ከማከም ኪነጥበብ ጋር ተያይዘው የሙያቸውን ተግባር የሚያከናውኑ ሰዎች ከበሽተኞቻቸው ወይም ከወኪሎቻቹው ጋር ባደረጉዋቸው ውሎች መነሻነት ስምምነት የተደረሰባቸው የሥራ ዋጋዎች ከመጠን በላይ ሆነው በተገኙ ጊዜ እና ሕይወትን መታደግን ዋንኛ ሙያዊ መርህ አድርጎ ከተነሣው የዋጋውን መጠን ላያሻሽሉት እንደሚችሉ የፍት.ሕግ ቁጥር 2640 እና 2646 ይደነግጋሉ።
በያዝነው ጉዳይ ግራቀኙ የልዩ እውቀት ፀባይ ያለው አገለግሎት ሥራ ውል ያደረጉ መሆኑ ይታመናል። ንብረቱ የተወሰደበት የአሁኑ ተጠሪ ለሚሰጠው ሙያዊ አገልግሎት በውሉ የተመለከተውን ብር 35,AAA እና በፍርድ ከሚገኘው ጥቅም 2A% ለመስጠት ተስመቶ የነበረ መሆኑን ይህ ችሎት በሚገባ ተገንዝቧል። ይህ ስምምነት ውልን ፈቅዶ በመዋዋል መርህ ላይ ተመስርቶ የተደረገ ውል አይደለም ለማለት እንኳን የሚያስችል ነገር ባይኖርም ከፍ ብለን ከላይ ሕጉ ላጠብበቃቸው ከተነሳው ዓላማ አኳያ ጉዳዩን በጥልቀት ስንመረምረው የአሁኗ አመልካች በሥር ፍ/ቤት ለሰጠችው ሙያዊ አገልግሎት 35,AAA (ሰላሣ አምስት ሺህ) የተከፈላቸው መሆኑ ታውቋል። ይህ ክፍያ ከንብረቱ ግምት አኳያ በመቶኛ ላሰላ 17% ይሆናል። አሁን አመልካች በተጨማሪ እንዲከፈላት እየጠየቀች ያለችው 2A% ከቀድሞ ክፍያ ጋር ሲደመር የጠቅላላ ቤቱን ግምት 37% መሆኑ ታውቋል። የተጠየቀው የገንዘብ መጠን ደግሞ ከንብረቱ ዋጋ ጋር ሲነጻጸር በተለምዶ ለአገልግሎቱ ከሚጠየቀው ክፍያ ጋር ሲታይ እጅግ በጣም የተጋነነና ለሙያውም ሥራ ክብር ቢሆን ተቃራኒ የሆነ መሆኑን አምነንበታል።
በመሆኑም ስምምነት የተደረሰበት የሥራ ዋጋ መጠን የበዛ እና ለሙያ ሥራ ክብርም ተቃራኒ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ዳኞች መጠኑን እንዲቀንሱ ሕጉ የሰጣቸውን ሥልጣን በመጠቀም የአሁኑ ተጠሪ ለአመልካች የንብረቱን ግምት ማለትም የብር 62A,942.98 79 80 (ስድስት መቶ ሃያ ሺህ ዘጠሀን መቶ አርባ ሁለት ብር ከዘጠና ስምንት ሣንቲም) 1A% (አሥር በመቶ) የሆነውን ገንዘብ እንዲከፍል ማድረጉ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካች ቀደም ሲል በውሉ መሰረት የወሰደው ብር 35,AAA ከክፍያው ገንዘብ ላይ ተቀናሽ ላሆን የሚገባ መሆኑን አምነንበታል።
ው ሣ ኔ • ተጠሪ ብር 27,094.30 (ሃያ ሰባት ሺህ ዘጠና አራት ብር ከሰላሣ ሣንቲም) ይህ ውሣኔ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ሕጋዊ ወለድ ጋር ለአመልካች ይከፈል፣ • የዚህ ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ ግራቀኙ ይቻቻሉ፣ • የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሐምል 8 ቀን 1996 ዓ.ም በፍ/ብ/ይ/ የሰጠው ውሣኔ ተሻሽሐል።
መዝገቡ ያለቀለት ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሣኔዎች ቅፅ 2 የኢትዮጵያ ፍድራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብላክ ፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ህዳር 1998 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
No specific laws extracted.
No topics extracted.