በህግ የተደነገገው የውል አአፃፃፍ /ፎርም/ የተሰጠ ደንብ አአለመፈጸም ስለማያስከትለው ውጤት /የኪራይ ቤቶች አአስተዳደር ድርጅት እእና ሶስና አአስፋው/
No summary available.
የመ/ ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሰሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ ወ/ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት መልስ ሰጪ፡- ወ/ት ሶስና አስፋው ውል- ስለውል አፃፃፍ/ ፎርም/- ስለ ውል አፃፃፍ ነፃነት- ስለ ውል አጻጻፍ /ፎርም/ የተሰጠ ደንብ አለመፈጸም የሚያስከትለው ውጤት - የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን ስለሚመለከቱ ውሎች፣- የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ስለሚመለከቱ ውሎች በስምምነት ስለሚሆን ያጻጻፍ አይነት - የግድታዎች ቀሪ መሆን - ስለ ይርጋ - የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥሮች 1719፣1720/1/ 1723፣ 1726 ፣1727፣ 1845 በአመልካችና በመልስ ሰጭ መካከል የተደረገው የኪራይ ውል በሁለት ምክንያት ያልተረጋገጠ በመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥሮች 1726/1/ እና 1727/1/ መሰረት የውል ረቂቅ እንጅ አስገደጅነት የለውም፣ አመልካች ከጠየቀው ኪራይ ውስጥ እስከ 8/2/89 ያለው መጠየቅ ከሚችልበት ጊዜ ጀምሮ ሁለት አመት ያለፈው በመሆኑ በይርጋ ይታገዳል በማለት የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በማጽናቱ የቀረበ አቤቱታ፣ 65 66 ው ሳ ኔ፡- የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውና የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያፀናው ውሳኔ ተሽሯል።
በኢትዮጵያ የውል ህግ ውል አመሰራረት ደንቦች መሰረት በህግ ወይም በተዋዋዮች በራሳቸው የተለየ ፎርም ካልተፈለገ በቀር ለውል መመስረት በሁለት ተዋዋዮች መካከል የስምምነት መኖር ብቻ በቂ ነው።
የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሚመለከት የሚደረግ ውል ባለቤትነትን /ownership/፣ የአላባ ጥቅምን /usufruct/፣ መያዣን /mortgage/ ወይም ልላ አገልግሎትን /servitude/ ለማቋቋም ወይም ለማስተላለፍ የተደረገ ካልሆነ በቀር የግል በህግ በተመለከተው አጻጻፍ /ፎርም/ መከናወን የለበትም። የኪራይ ውል ከነዚህ ውሎች ውጭ በመሆኑ ከተዋዋዮች ስምምነት ካልሆነ በቀር በህጉ የተለየ አጻጻፍ /ፎርም/ የሚጠይቁት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ አይሆኑበትም።
የህግ ግምት ድንጋጌዎች ከይርጋ ድንጋጌዎች የተለዩ ናቸው።
የመ/ቁ. 15992 ሐምል 19 ቀን 1997 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሥሐ ወርቅነህ አቶ አብድልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ ወ/ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት መልስ ሰጪ፡- ወ/ት ሶስና አስፋው በዚህ መዝገብ የቀረበውን ጉዳይ መርምሮ ችሎቱ የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥቷል።
ለሰበር ለቀረበው ጉዳይ መነሻ የሆነው ውሣኔ የተሰጠው በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን የውሣኔውም ይዘት የቤት ኪራይ ውል በሁለት ምስክሮች ፊት ካልተረጋገጠ በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1727/2/ እና 1726/1/ መሰረት የውል ረቂቅ እንጂ አስገዳጅነት አይኖረውም፣ በመሆኑም ከሣሽ ማስረጃዬ ነው ብሎ ያቀረበው ሰነድ ይህንን ስለማያሟላና በአመልካችና በተጠሪ መካከል የኪራይ ውል አለ ላባል ስለማይችል ከሣሹ የኪራይ ቤቶች አስተደደር ድርጅት የአሁን መልስ ሰጭ ከ23/5/70 ዓ.ም እስከ 30/1/91 ዓ.ም ያልተከፈለ የኪራይ ሂሣብ ብር 65,790.67 እና ወለድ ብር 168,785.90 በድምሩ ብር 234,576.57 እንድትከፍል ያቀረበውን ክስ ፍ/ቤቱ አልተቀበለውም የሚል ነው። ይኸው ፍ/ቤት ተከሣሽ ያቀረበችውን ይርጋን የሚመለከት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መሰረት በማድረግ ከሣሽ ከጠየቀው ክፍያ ውስጥ እስከ 8/2/89 ዓ.ም ድረስ ያለው በይርጋ ይታገዳል በማለት ቀደም ሲል በ23/10/92 ዓ.ም ብይን ሰጥቷል።
ኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ይህን ውሣኔ በመቃወም ለከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም ይግባኙ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ለሰበር ችሎቱ የሰበር ማመልከቻ አቅርቧል።
የሰበር ችሎት በዚህ የክርክር ሂደት 1ኛ. ይርጋን አስመልክቶ በሰጠው ትእዛዝ 67 68 2ኛ. የኪራይ ውል በሁለት ምስክሮች ፊት ካልተደረገ አይፀናም በማለት የሰጠው ውሣኔ የህግ ትርጉም የሚያስነሱ በመሆናቸው ጉዳዩ በሰበር ቀርቦ እንዲታይ አድርጓል፤ በዚህም መሰረት መልስ ሰጪ መልሱን፣ አመልካች ደግሞ የመልስ መልሱን እንዲያቀርቡ አድርጓል።
የሰበር ችሎቱ በቀረበለት ጉዳይ የህግ ትርጉም የሚሹትን ነጥቦች ከፍሬ ነገር ጉዳዮች በመለየት ተመልክቷል። በዚህም መሰረት፣ 1ኛ. የሚፀና የኪራይ ውል ለመመስረት መሟላት ያለበት የህግ መስፈርት ምንድን ነው?
2ኛ. በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024 የተመለከተውን የሕግ ግምት ክስን በይርጋ ከሚያግደው ድንጋጌ /1845/ ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? የሚሉትን የሕግ ነጥቦች መርምሮአል።
የሚፀና የኪራይ ውል ለመመስረት ሕጉ የሚጠይቀውን መስፈርት በተመለተ፤
ከላይ እንደተገለፀው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሣሽ ያቀረበውን ክስ ውድቅ ያደረገው በከሣሽ በኩል የቀረበው ሰነድ በሁለት ምስክሮች አልተፈረመም በማለት ነው።
የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1719/1/ በጠቅላላው ሥርዓት በሁለቱ ወገን ተዋዋዮች በማናቸውም ሁኔታ የተደረገ ስምምነት ውል ለማድረግ በቂ ነው በማለት ይደነግጋል። ከዚህ ድንጋጌ በግልጽ ለመገንዘብ እንደሚቻለው በሁለት ተዋዋዮች መካከል በህግ የሚፀና ሕጋዊ ውጤት ያለው ውል ለመመስረት በሁለቱም መካከል ስምምነት መኖሩ ብቻ በቂ ነው። ስለዚህ በኢትዮጵያ የውል ሕግ የውል አመሰራረት መሰረታዊ መርህ በህግ ወይም በተዋዋዮች በራሳቸው የተለየ ፎርም ካልተፈለገ በስተቀር ለውል መመስረት በሁለቱ ተዋዋዮች መካከል የስምምነት መኖር ብቻ በቂ ነው የሚለው ነው። በመሆኑም አንድ ውል ህጉ ያስቀመጠውን የፎርም መስፈርት አያሟላም ተብሎ ውድቅ ላደረግ የሚችለው ይህን ውል የሚመለከት በግልጽ የተቀመጠና የተለየ የአጻጻፍ ሥርዓት /ፎርም/ መኖሩ ሲረጋገጥ ብቻ ነው። ህጉ የተለየ ጽሁፍ የሚጠይቅ በሆነ ጊዜ ይኸው ሥርዓት እስካልተሟላ ድረስ ውሉ እንደረቂቅ ከሚቆጠር በቀር በተዋዋዮች መካከል የሚፀናና አስገዳጅነት ያለው ህጋዊ ግንኙነት ላመሰረት አይችልም (1720(1))። ለመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረት የሆነው ይኸው የሕግ ድንጋጌ አስገዳጅ የሕግ ድንጋጌ ነው። ሆኖም ይህ ድንጋጌ ተፈጻሚነት የሚኖረው ሕጉ የተለየ ፎርም የግድ የሚልባቸው ውሎች ብቻ ነው። በመሆኑም መጀመሪያ መታየት ያለበት ነጥብ የኢትዮጵያ ህግ ቤትን አስመልክቶ የሚደረግ የኪራይ ውል በተለየ ፎርም እንዲከናወን ይጠይቃል ወይስ አይጠይቅም የሚለው ነው?
ስለ ውል አጻጻፍ /ፎርም/ የሚመለከተው የፍትሐብሕር ሕግ ክፍል /አንቀጽ 1719-1730/ የኪራይ ውል የተለየ ፎርም መከተል እንዳለበት የሚያስገድድ ድንጋጌ የለውም። በፍርድ ቤቱ በቀጥታ ባይጠቀስም ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ያለው ድንጋጌ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ስለሚመለከቱ ውሎች የሚደነግገው አንቀጽ 1723 ነው።
ሆኖም ይህም አንቀጽ የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ የሚደረጉ ውሎች የተለየ ፎርም እንዲኖራቸው የሚጠይቅ ቢሆንም የኪራይ ውልን ግን የሚያጠቃልል አይደለም። ከሕጉ ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለው በዚሁ ድንጋጌ መሰረት የተለየ ፎርም እንዲከተሉ የሚፈለጉት ውሎች የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከቱ ሁሉም ውሎች ሳይሆኑ በድንጋጌው ውስጥ ተለይተው የተቀመጡ ውሱን የውል ዓይነቶች ናቸው።
አግባብነት ያለው የቁጥር 1723 ድንጋጌ ይዘት የሚከተለው ነው።
1723/1/ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ባለቤትነት ወይም ባንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የአላባ ጥቅም መብት ወይም የመያዣ ወይም የልላ አገልግሎት መብት ለማቋቋም ወይም ለማስተላለፍ የሚደረጉት ውሎች ሁሉ በጽሁፍና በማገባ አኳኋን በፍርድ ቤት መዝገብ ወይም ውል የማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው ፊት መሆን አለባቸው።
ከዚህ ድንጋጌ በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ የሚደረግ ውል በተለየ ፎርም እንዲፈፀም ግድ የሚሆነው ውሉ
ከእነዚህ ውሎች በአንዱም ውስጥ ከማይካተቱና በዚህም ምክንያት የተለየ ፎርም ከማያስፈልጋቸው ውሎች መካከል የኪራይ ውል አንዱ ነው። የኪራይ ውል 69 7A የባለቤትነት መተላለፍን የሚመለከት አይደለም። የአላባ ጥቅምን፣ መያዣን ወይም ልላ አገልግሎት /servitude/ ለማቋቋም ወይም ለማስተላለፍ የሚደረግም አይደለም።
በመሆኑም የተለየ ፎርም የሚጠይቀው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1723/1/ የቤት ኪራይን ለሚመለከቱ ውሎች አግባብነት የለውም።
በልላ በኩል ሕጉ ከሚያስቀመጠው አስገዳጅ ፎርም ውጪ ተዋዋይ ወገኖች የውላቸው አፈፃፀም ልዩ በሆነ አጻጻፍ ሥርዓት ላወስኑት እንደሚችሉ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1719/3/ ይደነግጋል። በተመሳሳይ ሁኔታ ተዋዋዮቹ ሕጉ የማያስገድደውን ፎርም ለመፈፀም የተስማሙ እንደሆነ ውሉ ፍጹም የሚሆነው የተስማሙበትን የውላቸውን አፈጻጸም ሞልተው ሲዋዋሉ ብቻ እንደሆነ የሕጉ ቁጥር 1721 ይደነግጋል። በዚህ ህግ መሰረት የፎርሙን ዓይነትና ይዘት የሚወስኑት ተዋዋዮቹ ራሳቸው በመሆናቸው ላከተሉ ስለፈለጉት ፎርም በመካከላቸው ግልጽ የሆነ ስምምነት መኖር ይገባዋል።፡ በቁጥር 1719 እንደተገለፀው በመርህ ደረጃ ውል ለመዋዋል የስምምነት መኖር ብቻ በቂ በመሆኑ ውሉ እንዲፀና ተዋዋዮቹ እንዲፈፀም የፈለጉት ተጨማሪ ፎርማላቲ ምን እንደሆነ ማወቅ የሚቻለው ተዋዋዮቹ ባደረጉት ውል ብቻ ነው። ስለዚህ የፎርሙን አይነት የምስክሮቹን ብዛት፣ ስለመመዝገብ አስፈላጊነት፣ አዋዋይ ፊት ስለመቅረብ ወ.ዘ.ተ ተዋዋዮቹ በፍላጎት የጨመሩት ፎርም ስለመኖሩ በተዋዋዮቹ መካከል ከተደረገው ስምምነት መገንዘብ መቻል አለበት።
ተዋዋዮቹ ውላቸውን በጽሁፍ ካሰፈሩ የጽሁፉን ፎርማላቲ እንደፈለጉ መገመት ቢቻልም ይህ በጽሁፍ የሰፈረው ስምምነት በምስክሮች እንዲረጋገጥ ወይም እንዲመዘገብ፣ ወይም አዋዋይ ፊት እንዲቀርብ መፈለጋቸውን የሚያሳይ አይሆንም።
በጽሁፍ ከመሆኑ በተጨማሪ ልሎቹም ፎርማላቲዎች እንዲሟሉ መፈለጋቸው በጽሁፉ በራሱ ወይም በልላ መልክ ስምምነት መኖሩን የሚያሳይ ነገር መኖር አለበት።
በመሆኑም ተዋዋዮች በጽሁፍ መዋዋላቸውን ብቻ መሰረት በማድረግ ውሉ በምስክሮች ካልተረጋገጠ አይፀናም ማለት ተዋዋዮቹ ያልፈለጉትንና ያልተስማሙበትን ፎርም ከፍላጎታቸው ውጪ እንዲጫንባቸው ማድረግ ስለሚሆን ትክክለኛና ሕጉን የተከተለ አተረጓጎም አይደለም። ውሉ በሁለት ምስክሮች ፊት ካልተረጋገጠ አይፀናም የሚለው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1727/2/ ድንጋጌ ተፈጻሚ የሚሆነው ውሉ በጽሁፍ እንዲሆን ግድታ የተጣለ እንደሆነ ወይም ተዋዋዮቹ በስምምነት በሁለት ምስክር ፊት እንዲረጋገጥ ሲፈልጉ መሆን አለበት። ከዚህ ውጪ ተዋዋዮች የፈረሙትን ሰነድ በመካከላቸው የውል ግንኙነት ለመመሥረት በቂና ብቸኛ ፎርሙ አድርገው ከተቀበሉት ፍርድ ቤቶች ፍላጎታቸውን ከማስፈፀም ውጪ ልላ ተጨማሪ ፎርም ላጠይቁ አይገባም።
የማይንቀሳቀስ ንብረት ኪራይን የሚመለከተው የፍትሐብሕር ህጉ ልላው ክፍልም ቤትም የሚመለከት የኪራይ ውል የተለየ ፎርም እንዲከተል የሚያስገድድ ድንጋጌ የለውም። /ቁጥር 2896-3018/። ይልቁንም የዚሁ ክፍል አካል የሆነው አንቀጽ 2898 የሚደነግገው የኪራይ ውልን ለማረጋገጥ ስለሚያስፈልገው የማስረጃ አይነት እንጂ የሚፀና የኪራይ ውል ለመመሥረት መኖር ስለሚገባው ጽሁፍ /ፎርም/ አይደለም። የዚሁ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 3 “ቢሆንም የኪራዩ ውል የመከናወኑን ጊዜ ጀምሮ እንደሆነ ይህ ውል መኖሩን ምስክሮች በማቅረብ ወይም በግምት አስተያየት ለማስረዳት ይቻላል” በማለት ስለሚደነግግ የኪራይ ውል መኖሩን ለማረጋገጥ ምስክሮች ማቅረብ የሚቻልበት ሁኔታ እንዳለ ያመለክታል። ይህም ቀድሞውኑ የሚፀና የኪራይ ውል ለመመስረት የተለየ ፎርም መኖር አስፈላጊ አለመሆኑን ይበልጥ የሚያረጋግጥ ነው። በመሆኑም የፍድራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ህጉ የማይጠይቀውን የፎርም መስፈርት መሰረት በማድረግ አመልካች ያቀረበው ሰነድ ረቂቅ እንጂ የሚፀና ውል አይደለም ማለቱ የውል ህጉን በተሣሣተ መንገድ መተርጎሙን የሚያመለክት ነው።
ከላይ እንደተብራራው የኪራይ ውል ልዩ ፎርም የሚጠይቅ ባለመሆኑ በአመልካች በኩል ቀረበ የተባለው ሰነድ በሁለት ምስክር አለመፈረሙ ብቻውን ውል የለም ወደሚል መደምደሚያ የሚወስድ አይደለም።
የፍትሐብሕር ሕጉ አንቀጽ 2898/1/ የኪራይ ውልን ለማስረዳት የጽሁፍ ማስረጃ እንደሚጠይቅ ግልጽ ነው። ሆኖም ለማስረጃነት የሚፈለገው ጽሁፍ ለውሉ መጽናት (validity) ከሚፈለገው ጽሁፍ ጋር ተመሳሳይ ፎርማላቲ እንዲኖረው ሕጉ አይጠይቅም። በመሆኑም ለማስረጃነት የሚፈለግ ሰነድ የግድ በሁለት ምስክሮች መፈረም አለበት ላባል አይችልም። ለማስረጃነት የሚፈለግ ሰነድ ያስረዳል የተባለውን ፍሬነገር ለማረጋገጥ የሚያስችል ተአማኒነት እስከአገኘ ድረስ ፍርድ ቤቱ የግድ በምስክሮች ፊት አልተፈረመም ወይም ለውል መጽናት የሚፈለጉትን ልሎች መስፈርቶች አላሟላም በማለት ዋጋ እንዲያጣ ለማድረግ የሚያስችለው የህግ ድጋፍ የለውም።
71 72 ስለዚህ 1ኛ. የኪራይ ውል በጽሁፍ መሆን እንዳለበት የሚያስገድድ ህግ ስለልለ 2ኛ.ተዋዋዮች በጽሁፍ መዋዋላቸው ብቻውን ምስክርም እንዲኖር መፈለጋቸውን ስለማያሳይ፣ 3ኛ.ለማስረጃነት የሚፈለግ ሰነድ የግድ በምስክር መረጋገጥ ስለልለበት የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካች ያቀረበውንና ማስረጃዬ ነው ያለውን የውል ሰነድ የፍትሐብሕር ሕጉን አንቀጽ 1720/1/ እና 1727/2/ በመጥቀስ ረቂቅ እንጂ አስገዳጅነት ያለው ውል አይደለም ማለቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት አተረጓጎም በመሆኑ ይህ ፍርድ ቤት አልተቀበለውም።
በሕግ ግምትና በይርጋ ድንጋጌዎች መካከል ያለው ግንኙነት በተመለተ ከዚህ ልላ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቀረበለትን ጉዳይ ሲመለከት አመልካች ከጠየቀው ክፍያ እስከ 8/2/89 ዓ.ም ድረስ ያለውን በይርጋ ታግዷል በማለት ብይን ሰጥቷል። በዚህም ረገድ ፍርድ ቤቱ በፍትሐብሕር ሕግ 2024 የተቀመጠውን የሕግ ግምት (presumption of payment) የተለየ ይዘትና ዓላማ ካለው የይርጋ ሕግ (Period of limitation) ጋር በማምታታት መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈፀሙን ያመለክታል።
የይርጋ ሕግ አንድ ፍርድ ቤት የቀረበለትን ጉዳይ ፍሬ ነገር መመርመር ሳያስፈልገው አንድን ክስ ውድቅ የሚያደርግበት ሥርዓት ሲሆን የሕግ ግምት ግን ጉዳዩ ፍርድ ቤት ቀርቦ በተከራካሪዎች መካከል የቀረበው ማስረጃ ሲመዘን ተፈጻሚ የሚሆን ደንብ ነው። በመሆኑም አልፎ አልፎ የውጤት መመሳሰል የሚያጋጥም ቢሆንም የሕግ ግምትን ተፈጻሚ ለማድረግ ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ፍሬ ነገርና አግባብነት ያለውን ሕግ እንዲመረምር የግድ የሚል ሲሆን ይርጋ ግን ጊዜውን በመቁጠር ብቻ ክሱ በፍሬ ነገር ደረጃ እንዳይሰማ የሚያደርግ ሥርዓት ነው።
የፍትሐብሕር ሕጉ ከ2020-2024 ባሉት ድንጋጌዎች የተለያዩ የህግ ግምቶች አስቀምጧል። እነዚህ የሕግ ግምቶችን እንደብዙዎቹ የህግ ግምቶች አንድ ክስ ለችሎት ቀርቦ በሚታይበት ወቅት የማስረዳት ሸክም ያለበት ማነው? በሕግ የሰፈረውን ግምት ማፍረስ የሚቻለው እንድት ነው? ወ.ዘ.ተ. የሚሉትን ማስረጃን የሚመለከቱ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች እንጂ አንድ ጉዳይ በጊዜ ማለፍ ምክንያት ክስ እንዳይቀርብበት የሚከለክሉ የይርጋ ደንቦች አይደሉም። በመሆኑም ሁለት ዓመት ያለፈው እዳ እንደተከፈለ የሚቆጥረው አንቀጽ 2024 ሁለት ዓመት ካለፈው በጉዳዩ ላይ የሚቀርበውን ክስ በይርጋ የማገድ ውጤት የለውም። አንድ ክስ በይርጋ ይቋረጣል ወይስ አይቋረጥም የሚለውን በሚመለከት /ተከሣሹ በ2024 በተቀመጠው ድንጋጌ ተጠቃሚ በሆነባቸው ጉዳዮችም ጭምር/ ተፈጻሚ የሚሆነው የውልን ግንኙነት የሚመለከተው አጠቃላይ የይርጋ ሕግ ነው። አጠቃላይ የይርጋ ገደብ ደግሞ በ1845 ሥር እንደተደነገገው 10 ዓመት ነው። በዚህ መሰረት አንደ ክስ በይርጋ የሚታገደው ክሱ ከመቅረቡ ከአስር ዓመት በላይ ሲሆን እንጂ ሁለት ዓመት የሞላው እንደሆነ አይደለም። ከሁለት ዓመት በላይ እና ከአስር ዓመት በታች ባለው ጊዜ ውስጥ የሚገኘውና በክሱ የተጠቃለለው ክፍያ በቁጥር 2024 በተቀመጠው የሕግ ግምት የሚሸፈን በመሆኑ ከሣሹ የማስረዳት ሸክሙን መወጣት አለመወጣቱን በመመርመር ፍርድ ቤቱ በፍሬ ነገሩ ውሣኔ የሚሰጥበት እንጂ ከወዲሁ በይርጋ ታግዷል በማለት ወደ ሥረ ነገሩ ሳይገባ ከክርክር ውጪ የሚያደርገው አይደለም።
በመሆኑም በዚህም ረገድ ፍርድ ቤቱ ክስ የቀረበበትን ጊዜ መሰረት በማድረግ እስከ 8/2/89 ዓ.ም ድረስ ያለው ሂሣብ በይርጋ ይታገዳል ማለቱ ትክክል አይደለም።
ክሱ የቀረበው በ4/2/91 ዓ.ም በመሆኑ በይርጋ የሚታገደው ከ4/2/81 ዓ.ም በፊት ያለው ሂሣብ ብቻ ነው።
ውሣኔ
የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ.3993 በ9/10/95 እና ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁ.23335 የሰጧቸው ውሣኔዎች ተሽረዋል።
ፍ/ቤቱ ፍሬ ነገሩን መርምሮ የመሰለውን ውሣኔ እንዲሰጥ ጉዳዩ ወደ ፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ይመለስ።
ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ።
73 74 ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት