በህግ ግምት የሚሸፈንን የፍሬ ነገር ክርክር በሚመለከት ተከራካሪ ወገኖች ባያነሱትም ፍርድ ቤቱ በህግ ግምቱን ተፈፃሚ ስለማድረጉ /ዶ/ር ዳንኤል አአለሙ እእና እእነ ሮማን ወርቅ የማነብርሃን/
No summary available.
የመ/ ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሰሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ ወ/ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡-- ዶ/ር ዳንኤል አለሙ መልስ ሰጪዎች፡- 1. ወ/ሮ ሮማነወርቅ የማነብርሃን 2. ወ/ሮ በቀለች ወረደ 3. ወ/ሮ ምስለአበባ ውቤ ውል - የግድታ ዎች መቅረት - ሰለ ይርጋ - የውልን ጉዳይ ስለሚመለከት ማስረጃገንዘቡ እንደተከፈለ የሚያስቆጥሩ የህልና ግምቶች - የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥሮች 1856፣2024 አመልካች ታህሳስ 1 ቀን 1981 ዓ.ም ከመ/ሰጭዎች ጋር ባደረጉት የጥብቅና ውል መሰረት ለሰጡት የጥብቅና አገልግሎት ክፍያ (አርባ ስድስት ሺህ) እንዲከፈላቸው በ1988 ዓ.ም ያቀረቡትን ክስ የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክሱ ክፍያው መጠየቅ ከነበረበት ጊዜ ሁለት ዓመት በኋላ የቀረበ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2024(ለ) መሰረት እንደተከፈለ ይቆጠራል በሚል ውድቅ ስላደረውና ውሣኔውን ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለት የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ስላጸና የቀረበ አቤቱታ፣ ውሣኔ፡- የሰበር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ጸንቷል።
በፍብ/ሕ/ቁ 2024 በተደነገገው የሕግ ግምት ተጠቃሚ ያልሆነ ወገን (ከሣሽ) ክፍያው እንዳልተፈጸመ የማስረዳት ሸክም ያለበት ሲሆን ይኸን ሸክሙን መወጣት የሚችለው መሃላ በማውረድ ብቻ ነው።
የሕላና ግምት ድንጋጌዎች ከይርጋ ደንብ ድንጋጌዎች የተለዩ ናቸው።
የመ/ ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሰሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ ወ/ት ሂሩት መለሰ አመልካች፣- ዶ/ር ዳንኤል አለሙ መልስ ሰሰጪዎች፡-1ኛ. ወ/ሮ ሮማነወርቅ የማነብርሃን በክርክሩ አልቀረቡም 2ኛ. ወ/ሮ በቀለች ወረደ 3ኛ. ወ/ሮ ምስለአበባ ውቤ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ውሣኔ ተሰጥቷል።
ውሣኔ አመልካች ለሰበር አቤቱታ ያቀረቡት የፍድራል የመጀመሪሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰጠውና የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ባፀናው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ነው።
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዳዩን አይቶ ውሣኔ የሰጠው አመልካች መልስ ሰጭዎች በፍርድ ቤት ያላቸውን የተለያዩ ጉዳዮች በተለየዩ መዝገቦች እነሱን ወክዬ እንድከራከር ወክለውኛል፣ የጥብቅና ውሉም ታህሳስ 1 ቀን 1981 ተፈርሟል፣ በውሉ መሰረት ለፈፀምኩት የጥብቅና አገልግሎት በአጠቃላይ ብር 46.000 (አርባ ስድስት ሺህ) ይከፈለኝ በማለት ባቀረቡት ክስ መነሻነት ነው። መልስ ሰጭዎች ለክሱ በሰጡት መልስ ውሉ የተፈፀመው በ1981 ሲሆን ክሱ ግን የቀረበው በ1988 ነው፣ ይሄውም የተጠቀሰውን ክፍያ ሳንጠየቅ ሁለት ዓመት ያለፈ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2024(ለ) መሰረት ክፍያው እንደተፈፀመ ይቆጠራል በማለት የተከራከሩ ሲሆን ልሎች ክርክሮችንም አንስተዋል። ፍርድ ቤቱም መልስ ሰጭዎች ክፍያውን በጽሁፍ አላመኑም፣ ክሱ ከሁለት አመት ገደቡ በኋላ በመቅረቡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2024(ለ) መሰረት የህላና ግምት እንዳይወሰድ መልስ ሰጭዎች የመሃላ ቃል እንዲሰጡ አልጠየቁም በመሆኑም ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2024(ለ) መሰረት ክፍያው መፈፀሙን የህላና ግምት ወስዷል። በማለት የአመልካችን ክስ ውድቅ አድርጎታል። ይህንኑ ውሣኔ የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ ተመልክቶ አጽንቶታል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በተሰጠው ውሣኔ ላይ ሲሆን ይዘቱም ሲጠቃለል አመልካች የጥብቅና አገልግሎት የሰጠሁት በተለያዩ መዝገቦች ሲሆን የአገልግሎት ክፍያ ጥያቄውም እንደየችሎቱ የክርክር ሂደት ጉዳዮች ተጠቃልለው ውሣኔ ሲያገኙ መቅረብ የሚገባው በመሆኑ ጥያቄው በዚሁ መሰረት ቀርቧል። መልስ ሰጭዎች የጥብቅና ውሉ መፈፀሙን አልካዱም፣ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.2024 ላፈርስ የሚችል የህላና ግምት የያዘ ነው። በመሆኑም በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2025 እና ተከታታዮቹ የሕላና ግምቱ እንዳይወሰድ (ለማፍረስ) ያቀረብኩትን ክርክር ፍ/ቤቱ ላመለከትልኝ ይገባ ነበር፣ ስለሆነም የሰበር ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለፈፀመበት እንዲሻርልኝ የሚል ነው።
መልስ ሰጭዎች ቀርበው መልስ እንዲሰጡ የጋዜጣ ጥሪ ተደርጎ ባለመቅረባቸው ፍርድ ቤቱ በአመልካች በኩል የቀረበውን ማመልከቻ ብቻ መሰረት በማድረግ ውሣኔ ሰጥቷል።፡ በቀረበው ጉዳይ በሰበር መታየት ያለበት ነጥብ የሥር ፍርድ ቤቶች በፍ.ብ.ሕ.ቁ 2024 የሰፈረውን የሕላና ግምት አመልካች በመሰረተው ክስ ተፈፃሚ ያደረጉት በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚል ነው። አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ1981 ዓ.ም ከመልስ ሰጪዎች ጋር በመሰረትነው የጥብቅና ውል መነሻነት ላበረከትኩት አገልግሎብ ብር 46.000 (አርባ ስድስት ሺህ) ይከፈለኝ የሚል ነው። ከክሱ ይዘት ለመመልከት እንደሚቻለው አመልካች ከመልስ ሰላዎች የሚፈልጉት ክፍያ የጥብቅና አገልግሎት ክፍያ ነው። አመልካች ክስ ያቀረቡት መልስ ሰጪዎች ከውሉ የሚመነጨውን የክፍያ ግድታቸውን አልተወጡም በሚል ነው። የጥብቅና አበል መከፈል አለመከፈሉ አከራካሪ በሆነ ጊዜ የማስረዳት ሸክሙ የማን ነው? የሚል ጥያቄ መነሳቱ የማይቀር ነው። በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024 (ለ) ከሁለት ዓመት በላይ የሆነውን የጥብቅና ክፍያ በሚመለከት የሕላና ግምት በማስቀመጥ በውል የመክፈል ግድታ ያለበት ወገን እንደከፈለ ይቆጠራል በማለት የሕግ ግምት ተጠቃሚ ያደርገዋል። በልላ በኩልም በሕጉ 2026(1) ይህን የሕላና ግምት ማፍረስ እንደማይቻልና የጥብቅና አገልግሎት ክፍያ አልተከፈለኝም የሚል ወገን ያለው ብቸኛ ግምቱን የማፍረሻ አማራጭ መሃላ እንዲወርድለት መጠየቅ ብቻ መሆኑን ያስቀምጣል።
በዚህ መሰረት መከፈል ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ያልተከፈለ ወይም ክፍያውን ያልጠየቀ ተዋዋይ በውሉ መሰረት የሚገባውን ክፍያ እንዳገኘ የሚገመትበት ብቻ ሳይሆን ክፍያው እንዳልተከፈለው የሚያስረዳው የማስረጃ አቀራረብ ሥርዓትም ልላ ፍሬ ነገርን ለማስረዳት ከሚከተለው ሥርዓት የተለየ ይሆናል። በመደበኛ የሙግት ሂደት የማስረዳት ሸክም ያለበት ወገን እንዲያስረዳ የሚጠበቅበትን ፍሬ ነገር ለማስረዳት ብዙም የሕግ ገደብ የለበትም። ፍሬ ነገሩን ያስረዳልኛል የሚለውን ማንኛውንም ዓይነት ማስረጃ ማቅረብ ይችላል። የጽሁፍ፣ የሰው ወይም የአካባቢ ማስረጃ በማቅረብ የማስረዳት ሽክሙን ላወጣ ይችላል።
በፍትሐብሄር ሕጉ 2024 የሚሸፈን ፍሬ ጉዳይ ባጋጠመ ጊዜ ግን የማስረዳት ሸክሙ ከአንዱ ወገን (ከተከሣሽ) ወደ ልላው (ወደከሣሽ) ከመዛወሩ በተጨማሪ የማስረዳት ሽክሙን መወጣት የሚቻልበት የማስረጃ አይነትም ውሱን ነው። በ2026 መሰረት የማስረዳት ሸክም የተሸጋገረበት ከሣሸ ይህን የማሰረዳት ሸክሙን መወጣት የሚችለው መሃላ በማውረድ ብቻ ነው። ልላ የትኛውም ዓይነት ማስረጃ ቢሆን የሕላናውን ግምት ላያፈርሰው አይችልም።
በዚህ ህግ የሰፈረው የህላና ግምት ከይርጋ ሕግ ጋር የሚያያዝ አይደለም።
በ2024 የሰፈረው የሕላና ግምት የማስረዳት ሸክም ከተከሣሽ ወደከሣሽ ያዞራል፣ የማስረዳት ሸክም የዞረበት ከሣሽ የሚያስረዳበትን መንገድ ይደነግጋል። በሆኑም በጊዜ ማለፍ ምክንያት ክሱ እንዲቋረጥ አያደርግም። የይርጋ ሕግ በልላ በኩል በጊዜ ማለፍ ምክንያት የመከሰስ መብትን ስለሚያስቀር ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የማስረዳት ሸክም ያለበት ወገን ማነው? የማስረዳት ሸክሙን ተወጥቷል አልተወጣም? ወዘተ- - ጥያቄዎችን በማንሣት ወደ ጉዳዩ ፍሬ ነገር ላገባ አይችልም። በመሆኑም የይርጋው ጊዜ በፍ.ብ.ሕ ቁ.1845 መሰረት 1A ዓመት የሆነ ጉዳይ በዚሁ ሕግ 2024 በተደነገገው የሕላና ግምት መሰረት ላስተናገድ ይችላል። የይርጋ ጊዜው ያላለፈን ጉዳይ በሕጉ ቁጥር 2024 መሰረት እንደተከፈለ መቁጠር እርስ በርሱ የሚጋጭ ነገር ማከናወን አይደለም።
አሁን በያዝነው ጉዳይ አመልካች ላቀረበው ክስ ምክንያት የሆነው ውል የተመሰረተው በ1981 ዓ.ም መሆኑን ግራ ቀኙ ተስማምተውበታል። የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከሣሾች የሕጉ ግምት ተጠቃሚዎች ናቸው ያለው የተጠየቀው ክፍያ በ1981 ዓ.ም መከፈል የነበረበት ነው በማለት ነው። ለዚሁ መነሻ ያደረገው ተጨማሪ ፍሬ ነገር አመልካች ከ1981 ዓ.ም ጀምሮ በዚህ መከፈል ነበረበት በተባለው መጠን ላይ ወለድ መጠየቁ ነው። አመልካች በልላ በኩል ክፍያው መከፈል የነበረበት ጊዜ ውሉ የተፈፀመበት 1981 ዓ.ም ሳይሆን ጉዳዩ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች የሚታይ በመሆኑ ውሣኔ የተሰጠበት ጊዜ መሆን ነበረበት ብሐል። ሆኖም ውሣኔ የተሰጠው መቼ እንደሆነ ለሰበር አቤቱታ ባቀረበው ማመልከቻ ላይ አልገለፀም። ሕጉ ከሚያዘው ከ2 ዓመት በታች መሆኑን ለማሣየት ክሱ ከቀረበበት ከ1988 ዓ.ም በፊት ባሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የተወሰነ መሆኑን ማስረዳት ሲኖርበት በዚህ ረገድ የቀረበ ነገር የለም።
በመሆኑም ውሉ የተፈረመበትና በከሣሽ መከፈል ከነበረበት ተብሎ ለወለድ ስልት መሰረት የሆነውን 1981 ዓ.ም መነሻ መደረጉ የሚነቀፍ አይደለም። ክሱ በ1988 ዓ.ም የቀረበ እንደመሆኑ ተከሣሾቹ የፍ.ብ.ሕ.ቁ 2024(ለ) #ለጠቀቆች፣ ለውል አዋዋዮች ለልሎችም የሕግ አማካሪዎች በሙያ ሥራቸው ወይም በሹመት ሥራቸው ላደረጉት 57 58 አገልግሎት የሚከፈል እዳ$ እዳው መከፈል ከሚገባበት ቀን ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ሳይከፈል የቀረ እንደሆነ እንደተከፈለ ይቆጠራል የሚለው የሕግ ግምት ተጠቃሚ ናቸው መባሉ በአግባቡ ነው።
የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሕግን ግምት ተፈጻሚ ከማድረግ አልፎ አመልካች ያቀረበው ክስ በይርጋ ይታገዳል የሚል ውሣኔ ባለመስጠቱ እንደአመልካች አባባል በፍ.ብ.ሕ.ቁ 1845 የሰፈረውን የይርጋ ሕግ አለቦታው ተጠቅሞበታል ላባል አይችልም። በመሆኑም የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበውን ክስ በፍ.ብ.ሕ. 2024(ለ)ን መሰረት አድርጐ ውድቅ ማድረጉም ሆነ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የአመልካችን ይግባኝ በፍ.ብ.ሥ.ሥ.ሕ.ቁ 337 መሰረት ውድቅ ማድረጉ የሕግ ስሀተት መፈፀሙን የሚያመለክት አይደለም።
መልስ ሰጪዎች የሕግ ግምት ተጠቃሚ እስከሆኑ ድረስ፣ የውሉን መኖሩን አለመካዳቸው፣ በውሉ መሰረት ለመክፈል መስማማታቸውና ማመናቸው፣ ውሉ ፈርሷል ብለው አለመከራከራቸው ወዘተ… የሙግቱን ውጤት የሚቀይረው አይደለም። ውሉ አለ እንኳን ቢባል ዞሮ ዞሮ ክስ የቀረበበት የገንዘብ መጠን እንደተከፈለ መቆጠሩ የሚቀር አይደለም። ይህ ላቀር የሚችለው መሃላ እንዲወርድ ተጠይቆ እንደሆነና መሃላው የከሣሽን ክስ ያረጋገጠ እንደሆነ ነው። ይህ ስለመሆኑ ከሰበር ማመልከቻውም ሆነ ከሥር ፍርድ ቤት መዝገቡ የተገነዘብነው ነገር የለም።
በመሆኑም አመልካች ያቀረበው የሰበር ማመልከቻ የሕግ መሰረት የልለው በመሆኑ አልተቀበልነውም።
ውሣኔ የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመቁ.5095 የካቲት 11 ቀን 1995 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ ፀንቷል። ይጻፍ።
ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የመ/ ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሰሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ አቶ መስፍን እቁበዮናስ አመልካቶች፡- ሼል ኢትዮጵያ A/ማ መልስ ሰጪ፡- ወ/ሮ አስቴር ብርሃነ ስላሴ በከሣሽነት ወይም በተከሣሽነት የሙግት ተካፋይ ስለመሆን
59 60
ተከሣሽ ከክሱ አስወጥቶ /Ex-parte/ ጉዳዩ መታየቱ የሚቀጥለው ተከሣሹ ጉዳዩ ላሰማ በተቀጠረበት ቀን ችሎት ያልቀረበ እንደሆነ ነው።
ጉዳዩ የተከሣሽን መልስ ለመቀበል በተቀጠረበት ቀን ተከሣሽ ያልቀረበ እንደሆነ መልሱን በጽሁፍ ከማቅረብ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥቅሞች ይቀረቡታል እንጂ በቀጣዩ ሂደት ከመሳተፍ አይከለከልም።
ሐምል 29 ቀን 1997 የመ/ ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሰሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ አቶ መስፍን እቁበዮናስ አመልካቶች፡- ሼል ኢትዮጵያ አክስዮን ማህበር መልስ ሰጪ፡- ወ/ሮ አስቴር ብርሃነ ስላሴ
በዚህ መሰረት ለቀረበው ክርክር መነሻ የሆነው የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውና የጠቅላይ ፍ/ቤት የተቀበለው ትእዛዝ ነው።
የአሁኑ አመልካች ሁለቱም ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት የሰበር ማመልከቻ ያቀረበ ሲሆን ጉዳዩ በሰበር መታየት ይገባዋል ተብሎ በመታዘዙ መልስ ሰጪም ቀርቦ በጉዳዩ ላይ የጽሁፍ ክርክሩን አቅርቦአል።
የአመልካች አቤቱታ ከፍተኛ ፍ/ቤት የከሣሽ ክስ እንዲሻሻል ትእዛዝ መስጠቱን አውቆ ለተሻሻለው ክስ መልስ እንዲያቀርብ ሲጠይቅ ፍ/ቤቱ ቀደም ሲል በፍ.ብ.ሥ.ሥ.ሕ.ቁ 73 መሰረት ጉዳዩ አመልካች በልለበት እንዲታይ የተወሰነ መሆኑን በመግለጽ የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ በማድረጉ የሥነ ሥርዓት ሕጉን የጣሰ አሰራር ነው በማለት በሰበር እንዲስተካከልለት አመልክቷል። የአመልካች ዋና ክርክር የተሻሻለው ክስ እንደ አዲስ ክስ መቆጠር ስላለበት ቀደም ብሎ ክርክሩ በልለበት እንዲታይ የተወሰነ ቢሆንም ለተሻሻለው ክስ መልስ የመስጠት መብቱ ላቀርበት አይገባም የሚል ነው። መልስ ሰጪ በዚህ ጉዳይ ላይ መለሱን በጽሁፍ በማቅረብ የክሱ መሻሻል ቀደም ሲል የተሰጡትን ትእዛዞች የሚሽር ባለመሆኑ አመልካች ለተሻሻለው ክስ መልስ ለማቅረብ ያቀረበው ጥያቄ በሁለቱም ፍቤቶች ውድቅ መደረጉ የሕግ ስህተት መኖሩን አያሳይም በማለት ተከራክሯል።
ይህ የሰበር ችሎት በዚህ ጉዳይ ላይ አመልካች መልስ ለማቅረብ በተቀጠረበት ቀን መልሱን ይዞ ባለመቅረቡ ጉዳዩ በልለበት እንዲታይ መታዘዙን 6261 ተገንዝቧል፣ በተሻሻለው ክስ መልስ ላያቀርብ አይገባም የሚል ትእዛዝ የተሰጠውም ቀደም ብሎ የተሰጠውን ትእዛዝ መሰረት በማድረግ እንደሆነ ተረድቷል። በዚህም መሰት ጉዳዩን በአግባቡ ለማስተናገድ የአሁኑ አመልካች መልስ እንዲያቀርብ በተቀጠረበት እለት መለሱን ይዞ ባለመቅረቡ የሚከተለው ሕጋዊ ውጤት ምንድነው?
የሚለውንና ተያያዥነት ያላቸውን ልሎች ነጥቦች መመርመር ተገቢ ሆኖ አግኝቶታል።
አንድ ተከሣሽ ጉዳዩ ለመልስ በተቀጠረበት እለት መልሱን ይዞ ካልቀረበ ክርክሩ በልለበት የሚሰማ መሆኑ ፍርድ ቤቱ በሚልክለት መጥሪያ ላይ እንደሚገልጽለት በፍሥ.ሥ.ሕ.ቁ 233 ላይ ተደንግጓል። በልላ በኩል የፍ.ሥ.ሥ.ሕ.ቀ 70 ክርክሩ እንዲሰማ በተወሰነው ቀነ ቀጠሮ ከሣሽ ቀርቦ ተከሣሽ ያልቀረበ እንደሆነ ተከሣሹ ያልቀረበው የተላከለት መጥሪያ ደርሶት ከሆነ ተከሣሹ በልለበት የነገሩ መሰማት እንደሚቀጥል ይደነግጋል። አነዚህ ሁለት ድንጋጌዎች ሁለት በተለያዩ ጊዜ የሚከናወኑ የሙግት ደረጃዎችን የሚመለከቱ ቢሆኑም የተከሣሽን መቅረት አስመልከቶ የሚያስከትሉት ውጤት ተመሳሳይ ይመስላል። የጽሁፍ መልሱን ሳያቀርብ የቀረ ተከሣሽ በ233 መሰረት በልለበት ጉዳዩ እንደሚሰማ ጉዳዩ ለመስማት በተቀጠረበት ቀን ያልቀረበ ተከሣሽም በተመሳሳይ ሁኔታ ጉዳዩ በልለበት እንደሚሰማ በቁጥር 70(ሀ) መሰረት ትእዛዝ የሚሰጥበት ይመስላል። የሁለቱም ድንጋጌዎች የአማርኛ ቅጂ ለመልስ በተቀጠረበት ቀን መቅረትና ጉዳዩ እንዲሰማ በተቀጠረበት ቀን መቅረት አንድ አይነት ውጤት ያላቸው እንደሆነ የሚገልጹ ቢሆኑም የሁለቱም የእንግላዝኛ ቅጂዎች ግን የተለየ ጽንሰ ሃሳብ የሚያስተላልñ ናቸው።
የእንግላዝኛ የ70(ሀ) የእንግላዝኛ ድንጋጌ ስለ Ex-part ሲናገር የ233 ግን የሚደነግገው ስለ default proceeding ነው።ሁለቱም የተለያየ ይዘት የተለያየ ውጤት ያላቸው ናቸው።
የ70(ሀ) የእንግላዝኛ ቅጂ 70 where the plaintiff appears and defendant does not appear when the suit is called on for hearing (a) if it is proved that the summons was duly served, the suit shall be heard ex-parte በማለት ሲደነግግ አግባብነት ያለው የ233 ክፈል ደግሞ …. The court shall cause… requiring him to appear with his statement of defense to be fixed in the summons and informing him that the case wile be proceeded withnotwithstanding that he does not appear or that he appears without his statement of defense. በማለት ይደገግጋል።
ሁለቱን የአንግላዝኛ ቅጂዎች በማነጻጸር ለመገንዘብ እንደሚቻለው ለመልስ በተቀጠረ ቀን ተከሣሽ መልሱን ይዞ ባይቀርብ የሚከተለው ውጤት ለመስማት በተቀጠረበት ቀን ባይገኝ ከሚከተለው ውጤት ጋር አንድ አይነት አይደለም። የ233 ድንጋጌ መለሱን ባያቀርብም የጉዳዩ መሰማት እንደሚቀጥል (default proceeding) ከሚይሳይ በቀር ተከሣሽ ከክርክር እንዲወጣ የሚያደርግበት ሥርዓት አለመኖሩን ያሳያል። በልላ በኩል በ70(ሀ) ስር ያለው ድንጋጌ ጉዳዩ ለመሰማት በተቀጠረበት ቀን የቀረ ተከሣሽ ጉዳዩ አሱ በልለበት መቀጠል(default proceeding) ብቻ ሳይሆን ከክርክሩ እንዲወጣ (ex-part) እንደሚደረግ በግልጽ ያስቀምጣል። ይህም በአማርኛ ቅጂ ላይ ያለው አገላለጽ በእንግላዝኛው ላይ ያለውን ሃሳብ በትክክል አለማስተላለñን ያመለክታል።
የትርጉም ልዩነት ሲኖር የአማርኛውን ቅጂ በመውሰድ እልባት መስጠት ይቻላል በማለት ጉዳዩ ማጠቃለል አንዱ አማራጭ ነው። ሆኖም ይህ አማራጭ አሁን በያዝነው ጉዳይ በግልጽ የሚታየውን የትርጉም ስህተት እንዲቀጥል የሚያደርግ በመሆኑ ትክክለኛ አማራጭ ነው አንልም። ይልቁም የተከሰተውን የትርጉም ልዩነት ከአጠቃላይ የሕጉ ዓላማ እንዲሁም ተከሣሽ በቀረበበት ክስ የመደመጥ መብትን ይበልጥ ላያስከብር በሚችል ሁኔታ መተርጐም በበለጠ የፍትህ አስተዳደርን ዓላማ በበለጠ ስለሚያሳካ የእንግላዝኛው ቅጂ መከተሉን መርጠናል።
በዚህም መሰረት አንድ ተከሣሽ ከክስ እንዲወጣ መደረግ ያለበት ጉዳዩ እንዲሰማ በተቀጠረበት ቀነ ቀጠሮ ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ እንጂ መልስ ለመቀበል ቀጠሮ በተያዘበት እለት ካልቀረበ መሆን የለበትም። ይህ አተረጓጐም ተከሣሹ መልስ ለመቀበል በተያዘ ቀጠሮ ሳይቀርብ ቢቀር ፍርድ ቤቱ ምን ያደርጋል የሚል ጥያቄ ማስከተሉ የሚቀር አይደለም። ይህን ጥያቄ ለመመለስ ፍርድ ቤት የሰጠው ቀጠሮ ሳይከበር ቢቀር ፍርድ ቤቱ ምን ያደርጋል ከሚል ልላ ጥያቄ ጋር ተያይዞ መመለስ ያለበት ነው።
በሙግት ሂደት ፍርድ ቤት የተለያዩ ጉዳዮች መከናወናቸውን ለማረጋገጥ የተለያዩ ቀጠሮዎችን ይሰጣል ሆኖም ፍ/ቤቱ የሰጠው ቀጠሮ በአንዱ ወይም በልላው ተሟጋች በተሰተጓጎለ ቁጥር ለመስተጓጎሉ ምክንያት የሆነው ወገን ከክርክ እንዲወጣ (Ex-parte) አይደረግም። የቀጠሮው አለመከበር ቀጠሮ ከተሰጠሰት ምክንያት ተነጥሎ የሚታይ ባለመሆኑ በየጉዳዩ የተለያየ ትእዛዝ የሚሰ ቢሆንም መሰረታዊው የጉዳዩ ሂደት የሚስተናገደው በሥነ ሥርዓት ሕግ ምእራፍ 7 በሚገኙት መርሆዎችና ድንጋጌዎች መሰረት መሆን አለበት። በፍ.ሥ.ሥ.ሕ.ቁ 194 እንደተገለፀው በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ መከናወን ያለበት ድርጊት በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ካልተከናወነ ዋጋ እንደልለው የገልጻል። በዚህም መሰረት በተወሰነ ጊዜ ውስጥ መልሱን እንዲያቀርብ የታዘዘ ተከሣሽ መልሱን ከማቅረብ ጋር ተያየዘው የሚነሱ ጥቅሞች ይቀሩበታል።
በቀጣዩ ሂደት ከመሳተፍ አይከለክልም።
63 64 ወደያዝነው ጉዳይ ስንመለስ አሁን አመልካች በተሻሻለው ክስ ላይ መልስ መስጠት አትችልም የተባለው ቀደም ብሎ ጉዳዩ መልስ ለመቀበል በተቀጠረበት ቀን መለሱን ይዞ አለመቅረቡን ምክንያት በማድረግ ነው። ሆኖም ጉዳዩ ለመልስ በተቀጠረ ቀን ተከሣሹ መልሱን ሳያቀርብ ቢቀር የጽሁፍ መልስና የማስረጃ ዝርዝር የማቅረብ እድሉን ከሚያጣ በቀር ከክርክሩ ውጪ እንዲሆን መታዘዝ አልነበረበትም።
በዚህም ምክንያት አንድን ተከሣሽ ሕጉ ከሚፈቅደው ሁኔታ ውጪ ከክርክር ውጪ ማድረግ በጉዳዩ ላይ የሥነ ሥርዓት ግድፈት መፈጸሙን ያመለክታል። ክሱ እንዲሻሻል ትእዛዝ ሲሰጥ ተከሣሸ መልስ ማቅረብ አትችልም የተባለው ከዚህ ሥነ ሥርዓት ግድፈት ጋር በተያያዘ ምክንያት ነው። አመልካቹ ከክርክሩ መውጣት ሳይኖርበት አውጥቶ ለተሻሻለው ክስ መለስ አታቀርብም መባሉ አግባብ አይደለም።
የጠቅላይ ፍ/ቤት የሥነ ሥርዓት ግድፈት መፈጸሙን በማመን ይህን ግድፈት ማስተካከል ሲገባው አልፎታል። በመሆኑም የሰበር ችሎት የተፈፀመውን የሥነ ሥርዓት ግድፈት በፍ.ሥ.ሥ.ሕግ ቁጥር 211 ስር በተደነገገው መሰረት ማሰተካከል አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል።
ውሣኔ
የአሁን አመልካች በከፈተኛ ፍ/ቤት በነበረው ክርክር ከክርክር ውጪ የተደረገው በአግባሱ ስላልሆነ ወደ ክርክሩ ይግባ።
ለተሻሻለው ክስ መልስ ማቅረብ እንዲችል በከፍተኛው ፍ/ቤት የተሻሻለው ክስ ግልባጭ ይሰጠው።
ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ።
ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የመ/ ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሰሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ ወ/ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት መልስ ሰጪ፡- ወ/ት ሶስና አስፋው ውል- ስለውል አፃፃፍ/ ፎርም/- ስለ ውል አፃፃፍ ነፃነት- ስለ ውል አጻጻፍ /ፎርም/ የተሰጠ ደንብ አለመፈጸም የሚያስከትለው ውጤት - የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን ስለሚመለከቱ ውሎች፣- የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ስለሚመለከቱ ውሎች በስምምነት ስለሚሆን ያጻጻፍ አይነት - የግድታዎች ቀሪ መሆን - ስለ ይርጋ - የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥሮች 1719፣1720/1/ 1723፣ 1726 ፣1727፣ 1845 በአመልካችና በመልስ ሰጭ መካከል የተደረገው የኪራይ ውል በሁለት ምክንያት ያልተረጋገጠ በመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥሮች 1726/1/ እና 1727/1/ መሰረት የውል ረቂቅ እንጅ አስገደጅነት የለውም፣ አመልካች ከጠየቀው ኪራይ ውስጥ እስከ 8/2/89 ያለው መጠየቅ ከሚችልበት ጊዜ ጀምሮ ሁለት አመት ያለፈው በመሆኑ በይርጋ ይታገዳል በማለት የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በማጽናቱ የቀረበ አቤቱታ፣ 65 66 ው ሳ ኔ፡- የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውና የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያፀናው ውሳኔ ተሽሯል።
በኢትዮጵያ የውል ህግ ውል አመሰራረት ደንቦች መሰረት በህግ ወይም በተዋዋዮች በራሳቸው የተለየ ፎርም ካልተፈለገ በቀር ለውል መመስረት በሁለት ተዋዋዮች መካከል የስምምነት መኖር ብቻ በቂ ነው።
የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሚመለከት የሚደረግ ውል ባለቤትነትን /ownership/፣ የአላባ ጥቅምን /usufruct/፣ መያዣን /mortgage/ ወይም ልላ አገልግሎትን /servitude/ ለማቋቋም ወይም ለማስተላለፍ የተደረገ ካልሆነ በቀር የግል በህግ በተመለከተው አጻጻፍ /ፎርም/ መከናወን የለበትም። የኪራይ ውል ከነዚህ ውሎች ውጭ በመሆኑ ከተዋዋዮች ስምምነት ካልሆነ በቀር በህጉ የተለየ አጻጻፍ /ፎርም/ የሚጠይቁት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ አይሆኑበትም።
የህግ ግምት ድንጋጌዎች ከይርጋ ድንጋጌዎች የተለዩ ናቸው።
የመ/ቁ. 15992 ሐምል 19 ቀን 1997 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሥሐ ወርቅነህ አቶ አብድልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ ወ/ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት መልስ ሰጪ፡- ወ/ት ሶስና አስፋው በዚህ መዝገብ የቀረበውን ጉዳይ መርምሮ ችሎቱ የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥቷል።
ለሰበር ለቀረበው ጉዳይ መነሻ የሆነው ውሣኔ የተሰጠው በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን የውሣኔውም ይዘት የቤት ኪራይ ውል በሁለት ምስክሮች ፊት ካልተረጋገጠ በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1727/2/ እና 1726/1/ መሰረት የውል ረቂቅ እንጂ አስገዳጅነት አይኖረውም፣ በመሆኑም ከሣሽ ማስረጃዬ ነው ብሎ ያቀረበው ሰነድ ይህንን ስለማያሟላና በአመልካችና በተጠሪ መካከል የኪራይ ውል አለ ላባል ስለማይችል ከሣሹ የኪራይ ቤቶች አስተደደር ድርጅት የአሁን መልስ ሰጭ ከ23/5/70 ዓ.ም እስከ 30/1/91 ዓ.ም ያልተከፈለ የኪራይ ሂሣብ ብር 65,790.67 እና ወለድ ብር 168,785.90 በድምሩ ብር 234,576.57 እንድትከፍል ያቀረበውን ክስ ፍ/ቤቱ አልተቀበለውም የሚል ነው። ይኸው ፍ/ቤት ተከሣሽ ያቀረበችውን ይርጋን የሚመለከት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መሰረት በማድረግ ከሣሽ ከጠየቀው ክፍያ ውስጥ እስከ 8/2/89 ዓ.ም ድረስ ያለው በይርጋ ይታገዳል በማለት ቀደም ሲል በ23/10/92 ዓ.ም ብይን ሰጥቷል።
ኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ይህን ውሣኔ በመቃወም ለከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም ይግባኙ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ለሰበር ችሎቱ የሰበር ማመልከቻ አቅርቧል።
የሰበር ችሎት በዚህ የክርክር ሂደት 1ኛ. ይርጋን አስመልክቶ በሰጠው ትእዛዝ 67 68 2ኛ. የኪራይ ውል በሁለት ምስክሮች ፊት ካልተደረገ አይፀናም በማለት የሰጠው ውሣኔ የህግ ትርጉም የሚያስነሱ በመሆናቸው ጉዳዩ በሰበር ቀርቦ እንዲታይ አድርጓል፤ በዚህም መሰረት መልስ ሰጪ መልሱን፣ አመልካች ደግሞ የመልስ መልሱን እንዲያቀርቡ አድርጓል።
የሰበር ችሎቱ በቀረበለት ጉዳይ የህግ ትርጉም የሚሹትን ነጥቦች ከፍሬ ነገር ጉዳዮች በመለየት ተመልክቷል። በዚህም መሰረት፣ 1ኛ. የሚፀና የኪራይ ውል ለመመስረት መሟላት ያለበት የህግ መስፈርት ምንድን ነው?
2ኛ. በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024 የተመለከተውን የሕግ ግምት ክስን በይርጋ ከሚያግደው ድንጋጌ /1845/ ያለው ግንኙነት ምንድን ነው? የሚሉትን የሕግ ነጥቦች መርምሮአል።
የሚፀና የኪራይ ውል ለመመስረት ሕጉ የሚጠይቀውን መስፈርት በተመለተ፤
ከላይ እንደተገለፀው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሣሽ ያቀረበውን ክስ ውድቅ ያደረገው በከሣሽ በኩል የቀረበው ሰነድ በሁለት ምስክሮች አልተፈረመም በማለት ነው።
የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1719/1/ በጠቅላላው ሥርዓት በሁለቱ ወገን ተዋዋዮች በማናቸውም ሁኔታ የተደረገ ስምምነት ውል ለማድረግ በቂ ነው በማለት ይደነግጋል። ከዚህ ድንጋጌ በግልጽ ለመገንዘብ እንደሚቻለው በሁለት ተዋዋዮች መካከል በህግ የሚፀና ሕጋዊ ውጤት ያለው ውል ለመመስረት በሁለቱም መካከል ስምምነት መኖሩ ብቻ በቂ ነው። ስለዚህ በኢትዮጵያ የውል ሕግ የውል አመሰራረት መሰረታዊ መርህ በህግ ወይም በተዋዋዮች በራሳቸው የተለየ ፎርም ካልተፈለገ በስተቀር ለውል መመስረት በሁለቱ ተዋዋዮች መካከል የስምምነት መኖር ብቻ በቂ ነው የሚለው ነው። በመሆኑም አንድ ውል ህጉ ያስቀመጠውን የፎርም መስፈርት አያሟላም ተብሎ ውድቅ ላደረግ የሚችለው ይህን ውል የሚመለከት በግልጽ የተቀመጠና የተለየ የአጻጻፍ ሥርዓት /ፎርም/ መኖሩ ሲረጋገጥ ብቻ ነው። ህጉ የተለየ ጽሁፍ የሚጠይቅ በሆነ ጊዜ ይኸው ሥርዓት እስካልተሟላ ድረስ ውሉ እንደረቂቅ ከሚቆጠር በቀር በተዋዋዮች መካከል የሚፀናና አስገዳጅነት ያለው ህጋዊ ግንኙነት ላመሰረት አይችልም (1720(1))። ለመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረት የሆነው ይኸው የሕግ ድንጋጌ አስገዳጅ የሕግ ድንጋጌ ነው። ሆኖም ይህ ድንጋጌ ተፈጻሚነት የሚኖረው ሕጉ የተለየ ፎርም የግድ የሚልባቸው ውሎች ብቻ ነው። በመሆኑም መጀመሪያ መታየት ያለበት ነጥብ የኢትዮጵያ ህግ ቤትን አስመልክቶ የሚደረግ የኪራይ ውል በተለየ ፎርም እንዲከናወን ይጠይቃል ወይስ አይጠይቅም የሚለው ነው?
ስለ ውል አጻጻፍ /ፎርም/ የሚመለከተው የፍትሐብሕር ሕግ ክፍል /አንቀጽ 1719-1730/ የኪራይ ውል የተለየ ፎርም መከተል እንዳለበት የሚያስገድድ ድንጋጌ የለውም። በፍርድ ቤቱ በቀጥታ ባይጠቀስም ከዚሁ ጋር ተያያዥነት ያለው ድንጋጌ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ስለሚመለከቱ ውሎች የሚደነግገው አንቀጽ 1723 ነው።
ሆኖም ይህም አንቀጽ የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ የሚደረጉ ውሎች የተለየ ፎርም እንዲኖራቸው የሚጠይቅ ቢሆንም የኪራይ ውልን ግን የሚያጠቃልል አይደለም። ከሕጉ ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለው በዚሁ ድንጋጌ መሰረት የተለየ ፎርም እንዲከተሉ የሚፈለጉት ውሎች የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከቱ ሁሉም ውሎች ሳይሆኑ በድንጋጌው ውስጥ ተለይተው የተቀመጡ ውሱን የውል ዓይነቶች ናቸው።
አግባብነት ያለው የቁጥር 1723 ድንጋጌ ይዘት የሚከተለው ነው።
1723/1/ የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች ባለቤትነት ወይም ባንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የአላባ ጥቅም መብት ወይም የመያዣ ወይም የልላ አገልግሎት መብት ለማቋቋም ወይም ለማስተላለፍ የሚደረጉት ውሎች ሁሉ በጽሁፍና በማገባ አኳኋን በፍርድ ቤት መዝገብ ወይም ውል የማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው ፊት መሆን አለባቸው።
ከዚህ ድንጋጌ በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ የሚደረግ ውል በተለየ ፎርም እንዲፈፀም ግድ የሚሆነው ውሉ
ከእነዚህ ውሎች በአንዱም ውስጥ ከማይካተቱና በዚህም ምክንያት የተለየ ፎርም ከማያስፈልጋቸው ውሎች መካከል የኪራይ ውል አንዱ ነው። የኪራይ ውል 69 7A የባለቤትነት መተላለፍን የሚመለከት አይደለም። የአላባ ጥቅምን፣ መያዣን ወይም ልላ አገልግሎት /servitude/ ለማቋቋም ወይም ለማስተላለፍ የሚደረግም አይደለም።
በመሆኑም የተለየ ፎርም የሚጠይቀው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1723/1/ የቤት ኪራይን ለሚመለከቱ ውሎች አግባብነት የለውም።
በልላ በኩል ሕጉ ከሚያስቀመጠው አስገዳጅ ፎርም ውጪ ተዋዋይ ወገኖች የውላቸው አፈፃፀም ልዩ በሆነ አጻጻፍ ሥርዓት ላወስኑት እንደሚችሉ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1719/3/ ይደነግጋል። በተመሳሳይ ሁኔታ ተዋዋዮቹ ሕጉ የማያስገድደውን ፎርም ለመፈፀም የተስማሙ እንደሆነ ውሉ ፍጹም የሚሆነው የተስማሙበትን የውላቸውን አፈጻጸም ሞልተው ሲዋዋሉ ብቻ እንደሆነ የሕጉ ቁጥር 1721 ይደነግጋል። በዚህ ህግ መሰረት የፎርሙን ዓይነትና ይዘት የሚወስኑት ተዋዋዮቹ ራሳቸው በመሆናቸው ላከተሉ ስለፈለጉት ፎርም በመካከላቸው ግልጽ የሆነ ስምምነት መኖር ይገባዋል።፡ በቁጥር 1719 እንደተገለፀው በመርህ ደረጃ ውል ለመዋዋል የስምምነት መኖር ብቻ በቂ በመሆኑ ውሉ እንዲፀና ተዋዋዮቹ እንዲፈፀም የፈለጉት ተጨማሪ ፎርማላቲ ምን እንደሆነ ማወቅ የሚቻለው ተዋዋዮቹ ባደረጉት ውል ብቻ ነው። ስለዚህ የፎርሙን አይነት የምስክሮቹን ብዛት፣ ስለመመዝገብ አስፈላጊነት፣ አዋዋይ ፊት ስለመቅረብ ወ.ዘ.ተ ተዋዋዮቹ በፍላጎት የጨመሩት ፎርም ስለመኖሩ በተዋዋዮቹ መካከል ከተደረገው ስምምነት መገንዘብ መቻል አለበት።
ተዋዋዮቹ ውላቸውን በጽሁፍ ካሰፈሩ የጽሁፉን ፎርማላቲ እንደፈለጉ መገመት ቢቻልም ይህ በጽሁፍ የሰፈረው ስምምነት በምስክሮች እንዲረጋገጥ ወይም እንዲመዘገብ፣ ወይም አዋዋይ ፊት እንዲቀርብ መፈለጋቸውን የሚያሳይ አይሆንም።
በጽሁፍ ከመሆኑ በተጨማሪ ልሎቹም ፎርማላቲዎች እንዲሟሉ መፈለጋቸው በጽሁፉ በራሱ ወይም በልላ መልክ ስምምነት መኖሩን የሚያሳይ ነገር መኖር አለበት።
በመሆኑም ተዋዋዮች በጽሁፍ መዋዋላቸውን ብቻ መሰረት በማድረግ ውሉ በምስክሮች ካልተረጋገጠ አይፀናም ማለት ተዋዋዮቹ ያልፈለጉትንና ያልተስማሙበትን ፎርም ከፍላጎታቸው ውጪ እንዲጫንባቸው ማድረግ ስለሚሆን ትክክለኛና ሕጉን የተከተለ አተረጓጎም አይደለም። ውሉ በሁለት ምስክሮች ፊት ካልተረጋገጠ አይፀናም የሚለው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1727/2/ ድንጋጌ ተፈጻሚ የሚሆነው ውሉ በጽሁፍ እንዲሆን ግድታ የተጣለ እንደሆነ ወይም ተዋዋዮቹ በስምምነት በሁለት ምስክር ፊት እንዲረጋገጥ ሲፈልጉ መሆን አለበት። ከዚህ ውጪ ተዋዋዮች የፈረሙትን ሰነድ በመካከላቸው የውል ግንኙነት ለመመሥረት በቂና ብቸኛ ፎርሙ አድርገው ከተቀበሉት ፍርድ ቤቶች ፍላጎታቸውን ከማስፈፀም ውጪ ልላ ተጨማሪ ፎርም ላጠይቁ አይገባም።
የማይንቀሳቀስ ንብረት ኪራይን የሚመለከተው የፍትሐብሕር ህጉ ልላው ክፍልም ቤትም የሚመለከት የኪራይ ውል የተለየ ፎርም እንዲከተል የሚያስገድድ ድንጋጌ የለውም። /ቁጥር 2896-3018/። ይልቁንም የዚሁ ክፍል አካል የሆነው አንቀጽ 2898 የሚደነግገው የኪራይ ውልን ለማረጋገጥ ስለሚያስፈልገው የማስረጃ አይነት እንጂ የሚፀና የኪራይ ውል ለመመሥረት መኖር ስለሚገባው ጽሁፍ /ፎርም/ አይደለም። የዚሁ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 3 “ቢሆንም የኪራዩ ውል የመከናወኑን ጊዜ ጀምሮ እንደሆነ ይህ ውል መኖሩን ምስክሮች በማቅረብ ወይም በግምት አስተያየት ለማስረዳት ይቻላል” በማለት ስለሚደነግግ የኪራይ ውል መኖሩን ለማረጋገጥ ምስክሮች ማቅረብ የሚቻልበት ሁኔታ እንዳለ ያመለክታል። ይህም ቀድሞውኑ የሚፀና የኪራይ ውል ለመመስረት የተለየ ፎርም መኖር አስፈላጊ አለመሆኑን ይበልጥ የሚያረጋግጥ ነው። በመሆኑም የፍድራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ህጉ የማይጠይቀውን የፎርም መስፈርት መሰረት በማድረግ አመልካች ያቀረበው ሰነድ ረቂቅ እንጂ የሚፀና ውል አይደለም ማለቱ የውል ህጉን በተሣሣተ መንገድ መተርጎሙን የሚያመለክት ነው።
ከላይ እንደተብራራው የኪራይ ውል ልዩ ፎርም የሚጠይቅ ባለመሆኑ በአመልካች በኩል ቀረበ የተባለው ሰነድ በሁለት ምስክር አለመፈረሙ ብቻውን ውል የለም ወደሚል መደምደሚያ የሚወስድ አይደለም።
የፍትሐብሕር ሕጉ አንቀጽ 2898/1/ የኪራይ ውልን ለማስረዳት የጽሁፍ ማስረጃ እንደሚጠይቅ ግልጽ ነው። ሆኖም ለማስረጃነት የሚፈለገው ጽሁፍ ለውሉ መጽናት (validity) ከሚፈለገው ጽሁፍ ጋር ተመሳሳይ ፎርማላቲ እንዲኖረው ሕጉ አይጠይቅም። በመሆኑም ለማስረጃነት የሚፈለግ ሰነድ የግድ በሁለት ምስክሮች መፈረም አለበት ላባል አይችልም። ለማስረጃነት የሚፈለግ ሰነድ ያስረዳል የተባለውን ፍሬነገር ለማረጋገጥ የሚያስችል ተአማኒነት እስከአገኘ ድረስ ፍርድ ቤቱ የግድ በምስክሮች ፊት አልተፈረመም ወይም ለውል መጽናት የሚፈለጉትን ልሎች መስፈርቶች አላሟላም በማለት ዋጋ እንዲያጣ ለማድረግ የሚያስችለው የህግ ድጋፍ የለውም።
71 72
No topics extracted.