ጉዳዩ መልስ ለመቀበል በተቀጠረ ቀን የከሳሽ አአለመቅረብ ሰለሚኖረው ውጤት (ውርጌሣ ታደሰ እእና እእነ መለሰ ተካ)
No summary available.
የመ/ቁ. 14184 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሥሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ አቶ መስፍን እቁበዮናስ ወ/ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- አቶ ውርጌሳ ታደሰ መልስ ሰጪ፡- አቶ መለሰ ተካ አቶ ፍሬሰንበት አዝማች አቶ በቀለ ድልኬራ አቶ አለሙ ደልላቦ አቶ ከተማ ኢብሣ አቶ ወ/ሰማያት ዲማ አቶ ፍቃዱ ራህመቶ አቶ አማረ ተሰማ አቶ ኤፍሶን መጋቢ በከሣሽነት ወይም በተከሣሽነት በሙግት ተወካይ ለመሆን ስለ ባለጉዳዩ /ከሳሽ/ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ መቅረብ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር ቁጥሮች 73 አመልካች ጉዳዩ መልስ ለመቀበል በተቀጠረበት እለት በችሎቱ ባለመገኘታቸው ምክንያት ያቀረቡትን ክስ የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍትሐብሐር ሥነ/ሥርዓት ሕግ ቁጥር 73 መሰረት በመዝጋቱ እና ይህንኑ ትእዛዝ የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ጉዳዩ በይግባኝ ቀርቦለት በአብላጫ ድምጽ በማጽናቱ የቀረበ አቤቱታ ው ሳ ኔ፡- የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትና የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጣቸው ትእዛዞች ተሽረዋል።
ክስ ያቀረበ ሰው ክሱ የሚዘጋበት ክርክሩን እንዲሰማ ቀጠሮ በተያዘበት ቀን ያልቀረበ እንደሆነ ነው።
ከተከሣሹ መልስ ለመቀበል የሚያዝ ቀጠሮ ተከሣሹ እንጂ ሕጉ እንደሚያዘው ጉዳዮ የሚሰማበት ቀጠሮ አይደለም
መልስ ለመቀበል ቀጠሮ በተያዘበት ቀን ከሳሽ ባይቀርብ ፍ/ቤቱ የተከሳሹን መልስ ተቀብሎ ጉዳዮን ለተከታዩ ክንውን ማዘጋጀት እንጅ ክሱን መዝጋት የለበትም።
ሐምል 29 ቀን 1997 ዓ.ም የመ/ቁ. 14184 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሥሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ አቶ መስፍን እቁበዮናስ ወ/ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- አቶ ውርጌሳ ታደሰ ጠበቃ ህይሉ አግዘው መልስ ሰጪ፡- አቶ መለሰ ተካ አቶ ፍሬሰንበት አዝማች አቶ በቀለ ድልኬራ አቶ አለሙ ደልላቦ አቶ ከተማ ኢብሣ አቶ ወ/ሰማያት ዲማ ሁሉም አልቀረቡም አቶ ፍቃዱ ራህመቶ አቶ አማረ ተሰማ አቶ ኤፍሶን መጋቢ
በዚህ መዝገብ የቀረበው የህግ ነጥብ አንድ ጉዳይ በይግባኝ ፍ/ቤት በሚታይበት ወቅት ከተከራካሪዎቹ የአንዱ መቅረት የሚያስከትለው በሕጉ የተደነገገ ውጤት ምንድነው; የሚል ነው። ለዚሁ የሕግ ነጥብ መነሣት ምክንያት የሆነው ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን አመልካቾች ጉዳዩ መልስ ለመቀበል በተቀጠረበት እለት በችሎት ባለመገኘታቸው ምክንያት አመልካቾችን በሚመለከት ቀርቦ የነበረውን ይግባኝ በፍትሀብሐር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁ.73 መሰረት በመዝጋቱ ነው።
አመልካች መዝገቡ ተመልሶ እንዲከፈት ጥያቄ ቢያቀርብም ለባለጉዳዩ መቅረትም ሆነ ለጠበቃው መቅረት የቀረበው ምክንያት በቂ ስላልሆነ የተዘጋው ይግባኝ አይከፈትም በማለት ትእዛዝ ሰጥቷል፣ ጉዳዩ በይግባኝ ለፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤትም የቀረበ ቢሆንም የከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ትእዛዝ በድምጽ ብልጫ ፀንቷል።
አመልካች ጠበቃ የሰበር አቤቱታ በመቅረቡና ጉዳዩ ያስቀርባል በመባሉ መልስ ሰጪ እንዲቀርቡ ታዞ በጉዳዩ መልስ ቀርቦአል። የመልስ መልስም እንደዚሁ ቀርቦ ከማኅደሩ ጋር ተያይዞአል።
የሰበር ችሎት በዚሁ የቀረበው የሰበር ማመልከቻ መነሻነት መታየት ያለበት ትልቁ የሕግ ትርጉም አንድ ፍርድ ቤት በይግባኝ ደረጃ ይግባኝ ባይ አልቀረበም በማለት የይግባኝ መዝገቡን ለመዝጋት የሚችለው መቼ ነው; የሚለው ሆኖ አግኝተነዋል። የፍትሐብሕር የሙግት ሂደት የሚመራው በፍትሀብሕር ሥነ 47 48 ሥርዓት ሕግ ጥያቄ መመለስ የሚኖርበት ሕጉ የሚያስቀምጠው ሥርዓት መሰረት ብቻ መሆን ይገባዋል። የአንዱ ወይም የልላው ተከራካሪ ፍርድ ቤት በያዘው ቀነ ቀጠሮ አለመገኘት የሚያስከትለው ውጤት ምንድነው; የሚለው ነጥብም መሰረታዊ ከሆነ ከመክሰስ መብትና ክስ ከመከላከል መብት ጋር እጅጉን የተያያዘ በመሆኑ መስተናገድ የሚኖረበት ሕጉ የሚያስቀምጠው መስፈርት መሰረት ብቻ መሆን የኖረበታል።
የከፍተኛ ፍርድ ቤት የአመልካችን ይግባኝ በከፊል ውድቅ የደረገው የፍትሀብሕር ሥነ ሥርህት ሕጉን ቁጥር 73 በመጥቀስ ስለሆነ የትእዛዙን ትክክል መሆን አለመሆ ለመመርመር በዚህ ቁጥር የሰፈረው ድንጋጌ ስለተከራካሪዎች መቅረብና አለመቅረብ የሚደነግጉትን ተዛማጅ ቁጥሮች መመልከት ያስፈልጋል፣ በቁጥር 73 የሰፈረው ድንጋጌ ባንድ ነገር ክስ ያቀረበ ሰው ክርክሩ እንሲማ በተወሰነው ቀነ ቀጠሮ ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነና ተከሣሹ ቀርቦ የተከሰሰበትን ነገር በሙሉ ወይም በከፊል ያመነ እንደሆነ ከሣሹ በልለበት ቢሆን የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ይችላል። ከሣሹ የካደ እንደሆነ ግን መዝገቡን በመዝጋት ያሰናብተዋል።
በማለት ይደነግጋል። በዚሁ ድንጋጌ ይዘት ለመገንዘብ እንደሚቻለው ክስ ያቀረበ ሰው ክሱ የሚዘጋበት የተከሣሽን መልስ ለመቀበል ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ በያዘበት ቀን ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ ሳይሆን ክርክሩ እንዲሰማ ቀጠሮ በተያዘበት ቀነ ቀጠሮ ያልቀረቡ እንደሆነ ነው። ከላይ እንደተገለፀው በመሰረቱ ማንም ሰው ክስ ላያጣ ወይም በከፊል ላቀርበት የሚገባው ሕግ በግልጽ ለይቶ ባሰፈረው ምክንያት ብቻ ነው። አንድን ጉዳይ ለማየት የተሰየመ ፍ/ቤት የተለያዩ ክንዋኔዎችን ለመፈፀም በርካታ ቀጠሮዎች እንደሚሰጥ የታወቀ ነው። ክስ ያቀረበ ሰው በሁሉም ቀጠሮዎች እንዲገኝ የሚጠበቅበት ቢሆንም በተያዘው ቀጠሮ ባለመገኘቱ ምክንያት ያቀረበው ክስ ላዘጋበት የሚችለው ግን ሕጉ ለይቶና ዘርዝሮ ባስቀመጣቸው ምክንያቶችና አጋጣሚዎች ብቻ ነው። እነዚህን ሁኔታዎች በቅጡ ለመንዘብ የፍትሐብሐር ሥነ ሥርዓት ሕጋችን የከሣሽና/ወይም የተከሣሽ አለመቅረብ (non appearance of parties) አስመልክቶ ያስቀመጠውን ሥርዓት ከአጠቃላይ የሙግት ሂደት ጋር አገናዝቦ መመልከቱ ጠቃሚ ነው።
ከላይ እንደተጠቀሰው በዚህ መዝገብ የሕግ ትርጉም የሚሻው ትልቁ ጥያቄ አንድ ከሣሽ ወይም ይግባኝ ባይ በቀነ ቀጠሮ አልቀረብክም ተብሎ ክሱ /ይግባኙ/ የሚዘጋበት መቼ ነው; የሚለው ነው። ከሕጉ ቁጥሮች 69፣70፣73 ለመገንዘብ እንደሚቻለው ሕጉ በተከራካሪ ወገኖች አለመቅረብ ምክንያት አንድ መዝገብ እንዲዘጋ ወይም ተከሣሹ በልለበት የነገሩ መሰማት እንዲቀጥል ትእዛዝ የሚሰጠው ከሣሽ ወይም ተከሣሹ ወይም ሁለቱም ጉዳዩ እንዲሰማ በተቀጠረው ቀን ሳይቀርቡ የቀሩ እንደሆነ ነው። ከጉዳዩ ጋር አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች የሚሉትን በቅደም ተከተል እንመልከት።
69(1) ነገሩን ለማየት ፍርድ ቤቱ በወሰነው ቀነ ቀጠሮ ከሣሽ ተከሣሾች ራሳቸው ወይም ወኪሎቻቸው ተሟልተው መቅረብ አለባቸው። የተከራካሪ ወገኖች መቅረብ እንደተረጋገጠም ክርክሩ መሰማት ይጀምራል።
70 የተከሣሽ ያለመቅረብ ክርክሩ እንዲሰማ በተወሰነው ቀነ ቀጠሮ ከሣሸ ቀርቦ ተከሣሹ ያልቀረበ አንደሆነ ለጉዳዩ ውሣኔ የሚሰጠው ከዚህ ቀጥሎ በተመለከተው ሥርዓት ነው።
73 ባንድ ነገር ክስ ያቀረበ ሰው ክርክሩ አንዲሰማ በተወሰነው ቀነ ቀጠሮ ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነና ተከሣሹ ቀርቦ የተከሰሰበትን ነገር በሙሉ ወይም በከፊል ያመነ እንደሆነ ከሣሹ በልለበትም ቢሆን ፍርድ ቤቱ ተከሣሹ በሙሉ ወይም በከፊል ላመነው ጉዳይ የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ይችላል። በከፊል ላመነው ጉዳይ የፍርድ ውሣኔ ለመስጠት ይችላል። ተከሣሹ የካደ እንደሆነ ግን መዝገቡን በመዝጋት ያሰናብተዋል።
አንድን ጉዳይ አይቶ ውሣኔ ለመወሰን በርካታ ቀጠሮዎችን ፍርድ ቤት እንደሚሰጥ የሚታወቅ ሲሆን ከነዚህ በርካታ ቀጠሮዎች መካከል በአንዱ ወይም በልላኛው ወይም በሁለቱም አለመቅረብ ምክንያት ፍርድ ቤት ከላይ በተጠቀሱት ድንጋጌዎች መሰረት ትእዛዝ ላሰጥ የሚችለው የባለጉዳዮቹ መቅረት የተከሰተው ጉዳይ ለመሰማት በተቀጠረበት ቀን እንደሆነ ብቻ ነው። ስለዚህ ጉዳዩ ለመስማት ቀጠሮ የተያዘበት ቀን ከልሎች ቀጠሮዎች በተለየ ሁኔታ እንዲታይ ሕግ አውጪው መፈለጉ ግልጽ ነው። በተለምዶ ብዙ ፍርድ ቤቶች መልስ ለመቀበል ከሣሽ ወይም ተከሣሽ ወምይ ሁለቱም ያልቀረቡ እንደሆነ ፍርድ ቤቶቹ እነዚህን ድንጋጌዎች 49 50 በመጥቀስ ጉዳዩ እንዲዘጋ ወይም ተከሣሹ በልለበት እንዲሰማ ትእዛዝ የሚሰጡ ቢሆንም የድንጋጌዎቹ ይዘት ይህን አሰራር የሚደግፍ አይደለም። መልስ ለመቀበል የሚያዝ ቀጠሮ ተከሣሹ የጽሁፍ መልሱን ለማቅረብ እንዲችል የሚያዝ ቀጠሮ እንጂ ሕጉ እንደሚያዘው ጉዳዩ የሚሰማበት ቀነ ቀጠሮ አይደለም።
በመሆኑም መልስ ለመቀበል ቀጠሮ በተያዘበት ቀን ከሣሹ ሳይቀርብ ቢቀር ጉዳዩ ለማሰማት በተቀጠረበት ቀን ሳይቀርብ ቀረ ተብሎ መዝገቡ ላዘጋበት የሚችልበት የሕግ መሰረት የለም። በመሰረቱ መልስ ለመቀበል ቀጠሮ የሚያዘው በአንድ ጉዳይ ክስ የተመሰረተበት ሰው በጉዳዩ ላይ የቀረበበትን ክስ ያምን ወይም ይክድ እንደሆነ ሃሣቡን በጽሁፍ እንዲያቀርብ ማስረጃም ካለው የማሰረጃውን ዝርዝር ለፍርድ ቤቱ እንዲያቀርብ ለማድረግ ነው። በመሆኑም ከከሣሹ የሚጠበቅ ክንዋኔ የለም። ከሣሹ ሳይቀርብ ቀረ እንኳን ቢባል በፍርድ ቤቱ የሥራ ሂደት ላይ የሚያስከትለው መስተጓጐል ላኖር አይችልም።
በመሆኑም መልስ ለመቀበል ቀጠሮ በተያዘበት ቀን ከሣሹ ባይቀርብ የተከሣሹን መልስ ተቀብሎ ለተከታዩ ክንውን ጉዳዩን ከማዘጋጀት አልፎ መዝገቡን ለመርዝጋት በቂ ምክንያት የለም፣ የመዝገብ መዘጋትን ያህል ትልቅ እርምጀ በአንድ ተከሣሽ ላይ ለመውሰድ ቢያንስ በከሣሹ በኩል መፈፀም የነበረበት ነገር ግን ሳይፈፀም የቀረ በህግ የተደገፈ በቂ ምክንያት መኖር አለበት። የተከሣሽን የጽሁፍ መልስ ለመቀበል ቀጠሮ በተያዘበት ቀን ከሣሽ ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ መዝገቡ እንደሚዘጋ የሚገልጽ ድንጋጌ በሥነ ሥርዓት ህጋችን የትኛውም ክፍል አይገኝም። የህግ ድጋፍ በልለበት ሁኔታ የአንድን ተከሣሽ ክስ መዝጋት ደግሞ አግባብ አይሆንም ተከሣሹ ባለመቅረቡ ምክንያት ክሱ እንዲዘጋ ህጉ የሚያዘው ጉዳዩ እንዲሰማ ቀጠሮ በተያዘበት እለት ከሣሹ ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ ኑው።
ከሕጉ አደረጃጀትም መገንዘበ እንደሚቻለው ክሱ የሚሰማው የክስና የመከላከያ ጽሁፎች (ከቁጥር 222-240 የፍትብሕር ሥነሥርዓት ህጉ ድንጋጌዎች መሰረት) ልውውጥ ከተከናወነ በኋላ ነው። የጽሁፉን ልውውጥ የሚመለከተው የሕጉ ክፍል "ስለክስና ስለመከላከያ ጽሁፍ" በሚል ርእስ ራሱን የቻለ አንድ ክፍል ሲሆን በዚህ የጽሁፍ ልውውጥ በኋላ የሚከተለው ክንውን ደግሞ "ክስን ስለመስማት" በሚል ርእስ ራሱን በቻለ ልላ ምእራፍ የምናገኘው ነው። (241-273) ከዚህ የህጉ አደረጃጀት የጽሁፍ መልስ የሚቀርብበት ቀነ ቀጠሮ በመርህ ደረጃ የክሱ መሰማት ከሚከናወንበት ቀነ ቀጠሮ የተለየ መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም። ከህጉ አደረጃጀት ባሻገር የክስ መሰማትን የሚመለከተው የሙግት ሂደት በሁለት የተከፈለ ሲሆን ሁለቱም የከሣሽና የተከሣሽን መገኘት የሚጠይቅ ነገር ነው። የመጀመሪያ ክስ የከሣሽና የተከሣሽን መገኘት የሚጠይቅ ነገር ነው። የመጀመሪያ ክስ ላከፈት የሚፈፀመውን ሥነ ሥርዓት (First hearing) ለአብነት መመልከት ይቻላል።
በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 24(1) መሰረት ክሱ መሰማት በሚጀምርበት ቀን ፍርድ ቤቱ የባለጉዳዮቹን ማንነት ካረጋገጠ በኋላ ክሱንና መልሱን እንደሚያነብና ተከሣሹ መልሱ ላይ የካደውን ነገር ያምን ወይም ይክድ እንደሆነ በቃል እንደሚጠይቀው ይገልጻል። የዚሁ ንኡስ ቁጥር 2 ደግሞ ወይም ስለሱ ሆኖ የቀረበውን ሰው ለክርክሩ መነሻ የሆኑት ጉዳዮች ወይም ልሎች ነገሮች አብራርቶ ለማስረዳት ጠቃሚና ተገቢ መስሎ በገመተው ዘድ የቃል ጥያቄ በማቅረብ ፍርድ ቤቱ ላመረምራቸው እንደሚችል ይደነግጋል። ከሣሽ ወይም ተከሣሹ እንዲብራራለት የሚፈልገው ጉዳይ ካለ በፍርድ ቤቱ በኩል እንዲጠየቅለት ማድረግ እንደሚችልም በዚሁ ድንጋጌ ላይ በግልጽ ሰፍሯል።
ይህ የሚያስገነዝበው የመሰማት ሂደት የከሣሽና የተከሣሽ መገኘት የግድ የሚል ተሟጋቾቹም ጭምር የሚሣተፉበት ሂደት መሆኑን ነው። ይህ ሂደት ፍርድ ቤቱ ባለጉዳዩችንም ጭምር በማነጋገር ጉዳዩን ለዋናው የሙግት ደረጃ የሚያዘጋጅበት በመሆኑ በከሣሹና የተከሣሹ (ወይም የወኪሎቻቸው) መገኘት በጣም አስፈላጊ ነው። ከሁለቱ የአንዱ አለመገኘት ለሂደቱ መስተጓጐል የሚኖረው ተጽአኖም ከፍተኛ ነው። በመሆኑም ከልሎች ቀጠሮዎች ይበልጥ ባለጉዳዩች ጉዳዩ እንዲሰማ ቀጠሮ በተያዘበት እለት ባይቀርቡ የሚከተለው ውጤት ከልላው የበለጠ ጠንካራ መሆኑ አስፈለጊ ነው። በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ምእራፍ 2 (ከቁጥር 241 - 273) ያሉት ሁሉም ድንጋጌዎች የተሟጋቾች አለመገኘት የሚያስከትለውን ውጤት ከመሰማት ሂደት ጋር አያይዘው የሚያቀርቡትም በከፊል በዚህ ምክንያት ነው።
ለማንኛውም የመሰማት ቀነ ቀጠሮ የተከሣሽን የጽሁፍ መልስ ለመቀበል የሚሰጠው ቀነ ቀጠሮ የተለየ ነው። በመሆኑም ክርክሩ የሚሰማበት ወቅት ተፈጻሚ እንዲሆኑ የተደነገጉትን ደንቦች የተለየ ባህርይና ዓላማ ባለው መልስ የመቀበል ቀነ ቀጠሮ ተፈጻሚ ማድረግ አግባብነት የለውም። በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ 51 52 ቁጥሮች 69፣70 እና 73 ሥር ያሉት ድንጋጌዎች ለመልስ በተቀጠረበት ቀን ተፈጻሚ ካልሆኑ ከሣሹ ወይም ተከሣሹ ወይም ሁለቱም ሳይቀርቡ የቀረ እንደሆነ አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች የትኞቹ ናቸው የሚል ጥያቄ መነሣቱ የማይቀር ነው። ከላይ እንደተገለፀው የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕጉን ቁጥር 67፣70፣73 እና ልሎች ተዛማጅ ድንጋጌዎች ከተከራካሪዎች አንዱ ወይም ሁለቱም ጉዳዩ ለመሰማት (hearing) በተቀጠረበት ቀን ያልቀረቡ እንደሆነ ብቻ ተፈጻሚ ስለሚሆኑ ጉዳዩ መልስ ለመቀበል በተቀጠረበት ቀን ከሳሽ (እንደነገሩ ሁኔታ ይግባኝ ባይ) ወይም ተከሣሹ (የይግባኝ መልስ ሰጪ) ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ለሚሰጠው ትእዛዝ መሰረት የሚሆን ልላ የህግ ድጋፍ መኖር ይኖርበታል። የፍትሐብሕር ሕግ ከ192 እስከ 199 ባሉት ቁጥሮች ፍርድ ቤት እንዲፈፀሙ ያዘዛቹው ጉዳዮች ሳይፈፀሙ ሲቀሩ ስለሚሰጡ ትእዛዞች የተለያዩ ድንጋጌዎችን አስቀምጧል። በቁጥር 199 ሥር ያለው ድንጋጌ አሁን ለያዝነው ጉዳይ በተለይ አግባብነት ያለው ነው። ቁጥር 199(1) ለቀጠሮው ምክንያት የሆነው ጉዳይ ሳይፈፀም የቀረው ከተከራካሪዎቹ ወገኖች በአንደኛው ጉድለት የሆነ እንደሆነ መፈፀም ይገባው የነበረው ጉዳይ ያልተፈፀመ ቢሆንም እንኳ ፍርድ ቤቱ የጉዳዩን መፈፀም ሳይጠብቅ በዚያው ቀነ ቀጠሮ የመሰለውን ውሣኔ ለመስጠት ይችላል በማለት ይደነግጋል። የዚሁ ቁጥር ንኡስ ቁጥር (2) ደግሞ ለቀጠሮው ምክንያት የሆነው ጉዳይ ሳይፈፀም የቀረው በተከራካሪዎቹ ወገኖች ጉድለት ያልሆነ እንደሆነ ግን ፈርድ ቤቱ ልላ ቀጠሮ ይሰጣል ይላል።
አንድ ጉዳይ የተከሣሽን መልስ ለመቀበል በተቀጠረበት ቀን ከሳሽ ወይም ተከሳሽ ያልቀረቡ እንደሆነ (እንደነገሩ ሁነታ ይግባኝ ባይ ወይም መልስ ሰጪ) ፍርድ ቤቶች ትእዛዝ መስጠት የሚገባቸው በዚህ ድንጋጌ መሰረት ነው።
ከድንጋጌው ንኡስ አንቀጽ አንድ ለማየት እንደሚቻለው ለቀጠሮ ምክንያት የሆነው ጉዳይ ሳይፈፀም በቀረ ቁጥር መዝገብ የሚዘጋበት ሁኔታ እንደልለ ግልጽ ነው። ከዚህም በተጨማሪ በዚህ ድንጋጌ መሰረት ትእዛዝ የሚሰጠው አንድ ጉዳይ እንዲፈጽም የታዘዘው ወገን ያን የታዘዘውን ጉዳይ ሳይፈጽም የቀረ እንደሆነ ነው። በዚህም መሰረት መልሱን እንዲያቀርብ የታዘዘ ተከሣሽ ይህን ክንውን ሳይፈጽም ቢቀር ፍርድ ቤቱ በዚህ ድንጋጌ መሰረት የመለሰውን ይወስናል።
ከሣሹ ከመልስ በተቀጠረበት ቀን ባይቀርብ ግን ከሣሹ እንዲፈጽመው የታነዘዘው ነገር ስለልለ ቀጣዩን ክንውን አስመልክቶ ትእዛዝ ከመስጠት ውጪ የከሣሹን መዝገብ መዝጋት የሚያስችል አይደለም። በመሆኑም የተከሣሽን መልስ ለመቀበል ቀጠሮ በተያዘበት ቀን ከሣሹ ያልቀረበ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ የተከሣሹን የጽሁፍ መልስ ከማህደሩ ጋር አያይዞ ጉዳዩ የሚሰማበትን ቀነ ቀጠሮ ወስኖ ለዚሁ አስፈላጊ ትእዛዞችን መስጠት አለበት እንጂ መዝገቡን መዝጋት የለበትም። ከላይ ተደጋግሞ እንደተገለፀው መዝገብ የሚዘጋው ከሣሹ ጉዳዩን ለመስማት በፍርድ ቤት ቀጠሮ በተያዘበት ቀነ ቀጠሮ ያልቀረበ እንደሆነ ነው።
የተከራካሪዎች መቅረብን አስመልክቶ በሰፊው ማየት የስፈለግን በያዝነው ጉዳይ ከፍተኛው ፍ/ቤት የይግባኝ ባይን መዝገብ የዘጋው መልስ ለመቀበል በተቀጠረበት ቀን ይግባኝ ባዩ አልቀረበም በማለት የፍ.ሥ.ሥ.ሕ.ቁ.73ን በመጥቀሱ ነው። ከመዝገቡ ለመረዳት እንደቻልነው የአሁኑ አመልካች ፍርድ ቤት ሳይቀርብ የቀረውን ጉዳዩን ለማሰማት በተያዘ ቀጠሮ አይደለም። በመሆኑም ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ለመዝጋት ምክንያት አድርጐ የጠቀሰው የሕግ አንቀጽ የሰጠውን ትእዛዝ ፈጽሞ የሚደግፍ አይደለም። መልስ ለመቀበል በተያዘው ቀጠሮ ከይግባኝ ባይ የሚጠበቅ ክንውን ስላልነበረም ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን መልስ ተቀብሎ ቀጣዩን ቀጠሮ (ክንውን) በማስመልከት ትእዛዝ ከሚሰጥ በስተቀር በተከሣሹ ላይ የፍ.ሥ.ሥ.ሕ.ቁ 199ን መሰረት በማድረግ የሚሰጠው ትእዛዝ ላኖር አይችልም።
በመሆኑም ከፍተኛው ፍ/ቤት የአመልካችን ይግባኝ የዘጋው እንዲፈጽም ትእዛዝ ተሰጥቶት ሳይፈጽመው የቀረ ክንውን ሳይኖርና መዝገብ እንዲዘጋ ሕግ ያስቀመጠውን ሥርዓት ሳይከተል በመሆኑ ይህ ፍርድ ቤት አልተቀበለውም።
መዝገቡን መልሶ ላለመክፈት የሰጠው ምክንያት ስህተት ባይሆንም ፍርድ ቤት የሰራውንና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማስተካከል ሲገባው ያለፈውን ግድፈት በሥ.ሥ.ሕ.ቁ 207 እና 211(2) መሰረት ማቀናት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቷል።
ውሣኔ (1) ከፍተኛው ፍ/ቤት በመ.ቁ.04000 ጥር 21 ቀን 1995 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እንዲሁም ፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ.ቁ.11523 ጥቅምት 6 ቀን 1996 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
(2) ከፍተኛው ፍርድ ቤት የአመልካችን ይግባኝ እንዲከፈት አድርጐ ካቆመበት እንዲቀጥል ታዟል።
(3) ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
53 54 ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የመ/ ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሰሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ ወ/ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡-- ዶ/ር ዳንኤል አለሙ መልስ ሰጪዎች፡- 1. ወ/ሮ ሮማነወርቅ የማነብርሃን 2. ወ/ሮ በቀለች ወረደ 3. ወ/ሮ ምስለአበባ ውቤ ውል - የግድታ ዎች መቅረት - ሰለ ይርጋ - የውልን ጉዳይ ስለሚመለከት ማስረጃገንዘቡ እንደተከፈለ የሚያስቆጥሩ የህልና ግምቶች - የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥሮች 1856፣2024 አመልካች ታህሳስ 1 ቀን 1981 ዓ.ም ከመ/ሰጭዎች ጋር ባደረጉት የጥብቅና ውል መሰረት ለሰጡት የጥብቅና አገልግሎት ክፍያ (አርባ ስድስት ሺህ) እንዲከፈላቸው በ1988 ዓ.ም ያቀረቡትን ክስ የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ክሱ ክፍያው መጠየቅ ከነበረበት ጊዜ ሁለት ዓመት በኋላ የቀረበ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2024(ለ) መሰረት እንደተከፈለ ይቆጠራል በሚል ውድቅ ስላደረውና ውሣኔውን ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለት የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ስላጸና የቀረበ አቤቱታ፣ ውሣኔ፡- የሰበር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ጸንቷል።
በፍብ/ሕ/ቁ 2024 በተደነገገው የሕግ ግምት ተጠቃሚ ያልሆነ ወገን (ከሣሽ) ክፍያው እንዳልተፈጸመ የማስረዳት ሸክም ያለበት ሲሆን ይኸን ሸክሙን መወጣት የሚችለው መሃላ በማውረድ ብቻ ነው።
የሕላና ግምት ድንጋጌዎች ከይርጋ ደንብ ድንጋጌዎች የተለዩ ናቸው።
የመ/ ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሰሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ ወ/ት ሂሩት መለሰ አመልካች፣- ዶ/ር ዳንኤል አለሙ መልስ ሰሰጪዎች፡-1ኛ. ወ/ሮ ሮማነወርቅ የማነብርሃን በክርክሩ አልቀረቡም 2ኛ. ወ/ሮ በቀለች ወረደ 3ኛ. ወ/ሮ ምስለአበባ ውቤ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ውሣኔ ተሰጥቷል።
ውሣኔ አመልካች ለሰበር አቤቱታ ያቀረቡት የፍድራል የመጀመሪሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰጠውና የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ባፀናው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ነው።
የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዳዩን አይቶ ውሣኔ የሰጠው አመልካች መልስ ሰጭዎች በፍርድ ቤት ያላቸውን የተለያዩ ጉዳዮች በተለየዩ መዝገቦች እነሱን ወክዬ እንድከራከር ወክለውኛል፣ የጥብቅና ውሉም ታህሳስ 1 ቀን 1981 ተፈርሟል፣ በውሉ መሰረት ለፈፀምኩት የጥብቅና አገልግሎት በአጠቃላይ ብር 46.000 (አርባ ስድስት ሺህ) ይከፈለኝ በማለት ባቀረቡት ክስ መነሻነት ነው። መልስ ሰጭዎች ለክሱ በሰጡት መልስ ውሉ የተፈፀመው በ1981 ሲሆን ክሱ ግን የቀረበው በ1988 ነው፣ ይሄውም የተጠቀሰውን ክፍያ ሳንጠየቅ ሁለት ዓመት ያለፈ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2024(ለ) መሰረት ክፍያው እንደተፈፀመ ይቆጠራል በማለት የተከራከሩ ሲሆን ልሎች ክርክሮችንም አንስተዋል። ፍርድ ቤቱም መልስ ሰጭዎች ክፍያውን በጽሁፍ አላመኑም፣ ክሱ ከሁለት አመት ገደቡ በኋላ በመቅረቡ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2024(ለ) መሰረት የህላና ግምት እንዳይወሰድ መልስ ሰጭዎች የመሃላ ቃል እንዲሰጡ አልጠየቁም በመሆኑም ፍ/ቤቱ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2024(ለ) መሰረት ክፍያው መፈፀሙን የህላና ግምት ወስዷል። በማለት የአመልካችን ክስ ውድቅ አድርጎታል። ይህንኑ ውሣኔ የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ ተመልክቶ አጽንቶታል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በተሰጠው ውሣኔ ላይ ሲሆን ይዘቱም ሲጠቃለል አመልካች የጥብቅና አገልግሎት የሰጠሁት በተለያዩ መዝገቦች ሲሆን የአገልግሎት ክፍያ ጥያቄውም እንደየችሎቱ የክርክር ሂደት ጉዳዮች ተጠቃልለው ውሣኔ ሲያገኙ መቅረብ የሚገባው በመሆኑ ጥያቄው በዚሁ መሰረት ቀርቧል። መልስ ሰጭዎች የጥብቅና ውሉ መፈፀሙን አልካዱም፣ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.2024 ላፈርስ የሚችል የህላና ግምት የያዘ ነው። በመሆኑም በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2025 እና ተከታታዮቹ የሕላና ግምቱ እንዳይወሰድ (ለማፍረስ) ያቀረብኩትን ክርክር ፍ/ቤቱ ላመለከትልኝ ይገባ ነበር፣ ስለሆነም የሰበር ፍ/ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለፈፀመበት እንዲሻርልኝ የሚል ነው።
መልስ ሰጭዎች ቀርበው መልስ እንዲሰጡ የጋዜጣ ጥሪ ተደርጎ ባለመቅረባቸው ፍርድ ቤቱ በአመልካች በኩል የቀረበውን ማመልከቻ ብቻ መሰረት በማድረግ ውሣኔ ሰጥቷል።፡ በቀረበው ጉዳይ በሰበር መታየት ያለበት ነጥብ የሥር ፍርድ ቤቶች በፍ.ብ.ሕ.ቁ 2024 የሰፈረውን የሕላና ግምት አመልካች በመሰረተው ክስ ተፈፃሚ ያደረጉት በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚል ነው። አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በ1981 ዓ.ም ከመልስ ሰጪዎች ጋር በመሰረትነው የጥብቅና ውል መነሻነት ላበረከትኩት አገልግሎብ ብር 46.000 (አርባ ስድስት ሺህ) ይከፈለኝ የሚል ነው። ከክሱ ይዘት ለመመልከት እንደሚቻለው አመልካች ከመልስ ሰላዎች የሚፈልጉት ክፍያ የጥብቅና አገልግሎት ክፍያ ነው። አመልካች ክስ ያቀረቡት መልስ ሰጪዎች ከውሉ የሚመነጨውን የክፍያ ግድታቸውን አልተወጡም በሚል ነው። የጥብቅና አበል መከፈል አለመከፈሉ አከራካሪ በሆነ ጊዜ የማስረዳት ሸክሙ የማን ነው? የሚል ጥያቄ መነሳቱ የማይቀር ነው። በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024 (ለ) ከሁለት ዓመት በላይ የሆነውን የጥብቅና ክፍያ በሚመለከት የሕላና ግምት በማስቀመጥ በውል የመክፈል ግድታ ያለበት ወገን እንደከፈለ ይቆጠራል በማለት የሕግ ግምት ተጠቃሚ ያደርገዋል። በልላ በኩልም በሕጉ 2026(1) ይህን የሕላና ግምት ማፍረስ እንደማይቻልና የጥብቅና አገልግሎት ክፍያ አልተከፈለኝም የሚል ወገን ያለው ብቸኛ ግምቱን የማፍረሻ አማራጭ መሃላ እንዲወርድለት መጠየቅ ብቻ መሆኑን ያስቀምጣል።
በዚህ መሰረት መከፈል ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ያልተከፈለ ወይም ክፍያውን ያልጠየቀ ተዋዋይ በውሉ መሰረት የሚገባውን ክፍያ እንዳገኘ የሚገመትበት ብቻ ሳይሆን ክፍያው እንዳልተከፈለው የሚያስረዳው የማስረጃ አቀራረብ ሥርዓትም ልላ ፍሬ ነገርን ለማስረዳት ከሚከተለው ሥርዓት የተለየ ይሆናል። በመደበኛ የሙግት ሂደት የማስረዳት ሸክም ያለበት ወገን እንዲያስረዳ የሚጠበቅበትን ፍሬ ነገር ለማስረዳት ብዙም የሕግ ገደብ የለበትም። ፍሬ ነገሩን ያስረዳልኛል የሚለውን ማንኛውንም ዓይነት ማስረጃ ማቅረብ ይችላል። የጽሁፍ፣ የሰው ወይም የአካባቢ ማስረጃ በማቅረብ የማስረዳት ሽክሙን ላወጣ ይችላል።
በፍትሐብሄር ሕጉ 2024 የሚሸፈን ፍሬ ጉዳይ ባጋጠመ ጊዜ ግን የማስረዳት ሸክሙ ከአንዱ ወገን (ከተከሣሽ) ወደ ልላው (ወደከሣሽ) ከመዛወሩ በተጨማሪ የማስረዳት ሽክሙን መወጣት የሚቻልበት የማስረጃ አይነትም ውሱን ነው። በ2026 መሰረት የማስረዳት ሸክም የተሸጋገረበት ከሣሸ ይህን የማሰረዳት ሸክሙን መወጣት የሚችለው መሃላ በማውረድ ብቻ ነው። ልላ የትኛውም ዓይነት ማስረጃ ቢሆን የሕላናውን ግምት ላያፈርሰው አይችልም።
በዚህ ህግ የሰፈረው የህላና ግምት ከይርጋ ሕግ ጋር የሚያያዝ አይደለም።
በ2024 የሰፈረው የሕላና ግምት የማስረዳት ሸክም ከተከሣሽ ወደከሣሽ ያዞራል፣ የማስረዳት ሸክም የዞረበት ከሣሽ የሚያስረዳበትን መንገድ ይደነግጋል። በሆኑም በጊዜ ማለፍ ምክንያት ክሱ እንዲቋረጥ አያደርግም። የይርጋ ሕግ በልላ በኩል በጊዜ ማለፍ ምክንያት የመከሰስ መብትን ስለሚያስቀር ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት የማስረዳት ሸክም ያለበት ወገን ማነው? የማስረዳት ሸክሙን ተወጥቷል አልተወጣም? ወዘተ- - ጥያቄዎችን በማንሣት ወደ ጉዳዩ ፍሬ ነገር ላገባ አይችልም። በመሆኑም የይርጋው ጊዜ በፍ.ብ.ሕ ቁ.1845 መሰረት 1A ዓመት የሆነ ጉዳይ በዚሁ ሕግ 2024 በተደነገገው የሕላና ግምት መሰረት ላስተናገድ ይችላል። የይርጋ ጊዜው ያላለፈን ጉዳይ በሕጉ ቁጥር 2024 መሰረት እንደተከፈለ መቁጠር እርስ በርሱ የሚጋጭ ነገር ማከናወን አይደለም።
አሁን በያዝነው ጉዳይ አመልካች ላቀረበው ክስ ምክንያት የሆነው ውል የተመሰረተው በ1981 ዓ.ም መሆኑን ግራ ቀኙ ተስማምተውበታል። የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከሣሾች የሕጉ ግምት ተጠቃሚዎች ናቸው ያለው የተጠየቀው ክፍያ በ1981 ዓ.ም መከፈል የነበረበት ነው በማለት ነው። ለዚሁ መነሻ ያደረገው ተጨማሪ ፍሬ ነገር አመልካች ከ1981 ዓ.ም ጀምሮ በዚህ መከፈል ነበረበት በተባለው መጠን ላይ ወለድ መጠየቁ ነው። አመልካች በልላ በኩል ክፍያው መከፈል የነበረበት ጊዜ ውሉ የተፈፀመበት 1981 ዓ.ም ሳይሆን ጉዳዩ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች የሚታይ በመሆኑ ውሣኔ የተሰጠበት ጊዜ መሆን ነበረበት ብሐል። ሆኖም ውሣኔ የተሰጠው መቼ እንደሆነ ለሰበር አቤቱታ ባቀረበው ማመልከቻ ላይ አልገለፀም። ሕጉ ከሚያዘው ከ2 ዓመት በታች መሆኑን ለማሣየት ክሱ ከቀረበበት ከ1988 ዓ.ም በፊት ባሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የተወሰነ መሆኑን ማስረዳት ሲኖርበት በዚህ ረገድ የቀረበ ነገር የለም።
በመሆኑም ውሉ የተፈረመበትና በከሣሽ መከፈል ከነበረበት ተብሎ ለወለድ ስልት መሰረት የሆነውን 1981 ዓ.ም መነሻ መደረጉ የሚነቀፍ አይደለም። ክሱ በ1988 ዓ.ም የቀረበ እንደመሆኑ ተከሣሾቹ የፍ.ብ.ሕ.ቁ 2024(ለ) #ለጠቀቆች፣ ለውል አዋዋዮች ለልሎችም የሕግ አማካሪዎች በሙያ ሥራቸው ወይም በሹመት ሥራቸው ላደረጉት 57 58 አገልግሎት የሚከፈል እዳ$ እዳው መከፈል ከሚገባበት ቀን ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ሳይከፈል የቀረ እንደሆነ እንደተከፈለ ይቆጠራል የሚለው የሕግ ግምት ተጠቃሚ ናቸው መባሉ በአግባቡ ነው።
የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሕግን ግምት ተፈጻሚ ከማድረግ አልፎ አመልካች ያቀረበው ክስ በይርጋ ይታገዳል የሚል ውሣኔ ባለመስጠቱ እንደአመልካች አባባል በፍ.ብ.ሕ.ቁ 1845 የሰፈረውን የይርጋ ሕግ አለቦታው ተጠቅሞበታል ላባል አይችልም። በመሆኑም የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበውን ክስ በፍ.ብ.ሕ. 2024(ለ)ን መሰረት አድርጐ ውድቅ ማድረጉም ሆነ ከፍተኛው ፍርድ ቤት የአመልካችን ይግባኝ በፍ.ብ.ሥ.ሥ.ሕ.ቁ 337 መሰረት ውድቅ ማድረጉ የሕግ ስሀተት መፈፀሙን የሚያመለክት አይደለም።
መልስ ሰጪዎች የሕግ ግምት ተጠቃሚ እስከሆኑ ድረስ፣ የውሉን መኖሩን አለመካዳቸው፣ በውሉ መሰረት ለመክፈል መስማማታቸውና ማመናቸው፣ ውሉ ፈርሷል ብለው አለመከራከራቸው ወዘተ… የሙግቱን ውጤት የሚቀይረው አይደለም። ውሉ አለ እንኳን ቢባል ዞሮ ዞሮ ክስ የቀረበበት የገንዘብ መጠን እንደተከፈለ መቆጠሩ የሚቀር አይደለም። ይህ ላቀር የሚችለው መሃላ እንዲወርድ ተጠይቆ እንደሆነና መሃላው የከሣሽን ክስ ያረጋገጠ እንደሆነ ነው። ይህ ስለመሆኑ ከሰበር ማመልከቻውም ሆነ ከሥር ፍርድ ቤት መዝገቡ የተገነዘብነው ነገር የለም።
በመሆኑም አመልካች ያቀረበው የሰበር ማመልከቻ የሕግ መሰረት የልለው በመሆኑ አልተቀበልነውም።
ውሣኔ የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመቁ.5095 የካቲት 11 ቀን 1995 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ ፀንቷል። ይጻፍ።
ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የመ/ ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሰሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ አቶ መስፍን እቁበዮናስ አመልካቶች፡- ሼል ኢትዮጵያ A/ማ መልስ ሰጪ፡- ወ/ሮ አስቴር ብርሃነ ስላሴ በከሣሽነት ወይም በተከሣሽነት የሙግት ተካፋይ ስለመሆን
59 60
ተከሣሽ ከክሱ አስወጥቶ /Ex-parte/ ጉዳዩ መታየቱ የሚቀጥለው ተከሣሹ ጉዳዩ ላሰማ በተቀጠረበት ቀን ችሎት ያልቀረበ እንደሆነ ነው።
ጉዳዩ የተከሣሽን መልስ ለመቀበል በተቀጠረበት ቀን ተከሣሽ ያልቀረበ እንደሆነ መልሱን በጽሁፍ ከማቅረብ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጥቅሞች ይቀረቡታል እንጂ በቀጣዩ ሂደት ከመሳተፍ አይከለከልም።
ሐምል 29 ቀን 1997 የመ/ ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሰሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ አቶ መስፍን እቁበዮናስ አመልካቶች፡- ሼል ኢትዮጵያ አክስዮን ማህበር መልስ ሰጪ፡- ወ/ሮ አስቴር ብርሃነ ስላሴ
በዚህ መሰረት ለቀረበው ክርክር መነሻ የሆነው የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውና የጠቅላይ ፍ/ቤት የተቀበለው ትእዛዝ ነው።
የአሁኑ አመልካች ሁለቱም ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት በማለት የሰበር ማመልከቻ ያቀረበ ሲሆን ጉዳዩ በሰበር መታየት ይገባዋል ተብሎ በመታዘዙ መልስ ሰጪም ቀርቦ በጉዳዩ ላይ የጽሁፍ ክርክሩን አቅርቦአል።
የአመልካች አቤቱታ ከፍተኛ ፍ/ቤት የከሣሽ ክስ እንዲሻሻል ትእዛዝ መስጠቱን አውቆ ለተሻሻለው ክስ መልስ እንዲያቀርብ ሲጠይቅ ፍ/ቤቱ ቀደም ሲል በፍ.ብ.ሥ.ሥ.ሕ.ቁ 73 መሰረት ጉዳዩ አመልካች በልለበት እንዲታይ የተወሰነ መሆኑን በመግለጽ የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ በማድረጉ የሥነ ሥርዓት ሕጉን የጣሰ አሰራር ነው በማለት በሰበር እንዲስተካከልለት አመልክቷል። የአመልካች ዋና ክርክር የተሻሻለው ክስ እንደ አዲስ ክስ መቆጠር ስላለበት ቀደም ብሎ ክርክሩ በልለበት እንዲታይ የተወሰነ ቢሆንም ለተሻሻለው ክስ መልስ የመስጠት መብቱ ላቀርበት አይገባም የሚል ነው። መልስ ሰጪ በዚህ ጉዳይ ላይ መለሱን በጽሁፍ በማቅረብ የክሱ መሻሻል ቀደም ሲል የተሰጡትን ትእዛዞች የሚሽር ባለመሆኑ አመልካች ለተሻሻለው ክስ መልስ ለማቅረብ ያቀረበው ጥያቄ በሁለቱም ፍቤቶች ውድቅ መደረጉ የሕግ ስህተት መኖሩን አያሳይም በማለት ተከራክሯል።
ይህ የሰበር ችሎት በዚህ ጉዳይ ላይ አመልካች መልስ ለማቅረብ በተቀጠረበት ቀን መልሱን ይዞ ባለመቅረቡ ጉዳዩ በልለበት እንዲታይ መታዘዙን 6261 ተገንዝቧል፣ በተሻሻለው ክስ መልስ ላያቀርብ አይገባም የሚል ትእዛዝ የተሰጠውም ቀደም ብሎ የተሰጠውን ትእዛዝ መሰረት በማድረግ እንደሆነ ተረድቷል። በዚህም መሰት ጉዳዩን በአግባቡ ለማስተናገድ የአሁኑ አመልካች መልስ እንዲያቀርብ በተቀጠረበት እለት መለሱን ይዞ ባለመቅረቡ የሚከተለው ሕጋዊ ውጤት ምንድነው?
የሚለውንና ተያያዥነት ያላቸውን ልሎች ነጥቦች መመርመር ተገቢ ሆኖ አግኝቶታል።
አንድ ተከሣሽ ጉዳዩ ለመልስ በተቀጠረበት እለት መልሱን ይዞ ካልቀረበ ክርክሩ በልለበት የሚሰማ መሆኑ ፍርድ ቤቱ በሚልክለት መጥሪያ ላይ እንደሚገልጽለት በፍሥ.ሥ.ሕ.ቁ 233 ላይ ተደንግጓል። በልላ በኩል የፍ.ሥ.ሥ.ሕ.ቀ 70 ክርክሩ እንዲሰማ በተወሰነው ቀነ ቀጠሮ ከሣሽ ቀርቦ ተከሣሽ ያልቀረበ እንደሆነ ተከሣሹ ያልቀረበው የተላከለት መጥሪያ ደርሶት ከሆነ ተከሣሹ በልለበት የነገሩ መሰማት እንደሚቀጥል ይደነግጋል። አነዚህ ሁለት ድንጋጌዎች ሁለት በተለያዩ ጊዜ የሚከናወኑ የሙግት ደረጃዎችን የሚመለከቱ ቢሆኑም የተከሣሽን መቅረት አስመልከቶ የሚያስከትሉት ውጤት ተመሳሳይ ይመስላል። የጽሁፍ መልሱን ሳያቀርብ የቀረ ተከሣሽ በ233 መሰረት በልለበት ጉዳዩ እንደሚሰማ ጉዳዩ ለመስማት በተቀጠረበት ቀን ያልቀረበ ተከሣሽም በተመሳሳይ ሁኔታ ጉዳዩ በልለበት እንደሚሰማ በቁጥር 70(ሀ) መሰረት ትእዛዝ የሚሰጥበት ይመስላል። የሁለቱም ድንጋጌዎች የአማርኛ ቅጂ ለመልስ በተቀጠረበት ቀን መቅረትና ጉዳዩ እንዲሰማ በተቀጠረበት ቀን መቅረት አንድ አይነት ውጤት ያላቸው እንደሆነ የሚገልጹ ቢሆኑም የሁለቱም የእንግላዝኛ ቅጂዎች ግን የተለየ ጽንሰ ሃሳብ የሚያስተላልñ ናቸው።
የእንግላዝኛ የ70(ሀ) የእንግላዝኛ ድንጋጌ ስለ Ex-part ሲናገር የ233 ግን የሚደነግገው ስለ default proceeding ነው።ሁለቱም የተለያየ ይዘት የተለያየ ውጤት ያላቸው ናቸው።
የ70(ሀ) የእንግላዝኛ ቅጂ 70 where the plaintiff appears and defendant does not appear when the suit is called on for hearing (a) if it is proved that the summons was duly served, the suit shall be heard ex-parte በማለት ሲደነግግ አግባብነት ያለው የ233 ክፈል ደግሞ …. The court shall cause… requiring him to appear with his statement of defense to be fixed in the summons and informing him that the case wile be proceeded withnotwithstanding that he does not appear or that he appears without his statement of defense. በማለት ይደገግጋል።
ሁለቱን የአንግላዝኛ ቅጂዎች በማነጻጸር ለመገንዘብ እንደሚቻለው ለመልስ በተቀጠረ ቀን ተከሣሽ መልሱን ይዞ ባይቀርብ የሚከተለው ውጤት ለመስማት በተቀጠረበት ቀን ባይገኝ ከሚከተለው ውጤት ጋር አንድ አይነት አይደለም። የ233 ድንጋጌ መለሱን ባያቀርብም የጉዳዩ መሰማት እንደሚቀጥል (default proceeding) ከሚይሳይ በቀር ተከሣሽ ከክርክር እንዲወጣ የሚያደርግበት ሥርዓት አለመኖሩን ያሳያል። በልላ በኩል በ70(ሀ) ስር ያለው ድንጋጌ ጉዳዩ ለመሰማት በተቀጠረበት ቀን የቀረ ተከሣሽ ጉዳዩ አሱ በልለበት መቀጠል(default proceeding) ብቻ ሳይሆን ከክርክሩ እንዲወጣ (ex-part) እንደሚደረግ በግልጽ ያስቀምጣል። ይህም በአማርኛ ቅጂ ላይ ያለው አገላለጽ በእንግላዝኛው ላይ ያለውን ሃሳብ በትክክል አለማስተላለñን ያመለክታል።
የትርጉም ልዩነት ሲኖር የአማርኛውን ቅጂ በመውሰድ እልባት መስጠት ይቻላል በማለት ጉዳዩ ማጠቃለል አንዱ አማራጭ ነው። ሆኖም ይህ አማራጭ አሁን በያዝነው ጉዳይ በግልጽ የሚታየውን የትርጉም ስህተት እንዲቀጥል የሚያደርግ በመሆኑ ትክክለኛ አማራጭ ነው አንልም። ይልቁም የተከሰተውን የትርጉም ልዩነት ከአጠቃላይ የሕጉ ዓላማ እንዲሁም ተከሣሽ በቀረበበት ክስ የመደመጥ መብትን ይበልጥ ላያስከብር በሚችል ሁኔታ መተርጐም በበለጠ የፍትህ አስተዳደርን ዓላማ በበለጠ ስለሚያሳካ የእንግላዝኛው ቅጂ መከተሉን መርጠናል።
በዚህም መሰረት አንድ ተከሣሽ ከክስ እንዲወጣ መደረግ ያለበት ጉዳዩ እንዲሰማ በተቀጠረበት ቀነ ቀጠሮ ሳይቀርብ የቀረ እንደሆነ እንጂ መልስ ለመቀበል ቀጠሮ በተያዘበት እለት ካልቀረበ መሆን የለበትም። ይህ አተረጓጐም ተከሣሹ መልስ ለመቀበል በተያዘ ቀጠሮ ሳይቀርብ ቢቀር ፍርድ ቤቱ ምን ያደርጋል የሚል ጥያቄ ማስከተሉ የሚቀር አይደለም። ይህን ጥያቄ ለመመለስ ፍርድ ቤት የሰጠው ቀጠሮ ሳይከበር ቢቀር ፍርድ ቤቱ ምን ያደርጋል ከሚል ልላ ጥያቄ ጋር ተያይዞ መመለስ ያለበት ነው።
በሙግት ሂደት ፍርድ ቤት የተለያዩ ጉዳዮች መከናወናቸውን ለማረጋገጥ የተለያዩ ቀጠሮዎችን ይሰጣል ሆኖም ፍ/ቤቱ የሰጠው ቀጠሮ በአንዱ ወይም በልላው ተሟጋች በተሰተጓጎለ ቁጥር ለመስተጓጎሉ ምክንያት የሆነው ወገን ከክርክ እንዲወጣ (Ex-parte) አይደረግም። የቀጠሮው አለመከበር ቀጠሮ ከተሰጠሰት ምክንያት ተነጥሎ የሚታይ ባለመሆኑ በየጉዳዩ የተለያየ ትእዛዝ የሚሰ ቢሆንም መሰረታዊው የጉዳዩ ሂደት የሚስተናገደው በሥነ ሥርዓት ሕግ ምእራፍ 7 በሚገኙት መርሆዎችና ድንጋጌዎች መሰረት መሆን አለበት። በፍ.ሥ.ሥ.ሕ.ቁ 194 እንደተገለፀው በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ መከናወን ያለበት ድርጊት በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ካልተከናወነ ዋጋ እንደልለው የገልጻል። በዚህም መሰረት በተወሰነ ጊዜ ውስጥ መልሱን እንዲያቀርብ የታዘዘ ተከሣሽ መልሱን ከማቅረብ ጋር ተያየዘው የሚነሱ ጥቅሞች ይቀሩበታል።
በቀጣዩ ሂደት ከመሳተፍ አይከለክልም።
63 64 ወደያዝነው ጉዳይ ስንመለስ አሁን አመልካች በተሻሻለው ክስ ላይ መልስ መስጠት አትችልም የተባለው ቀደም ብሎ ጉዳዩ መልስ ለመቀበል በተቀጠረበት ቀን መለሱን ይዞ አለመቅረቡን ምክንያት በማድረግ ነው። ሆኖም ጉዳዩ ለመልስ በተቀጠረ ቀን ተከሣሹ መልሱን ሳያቀርብ ቢቀር የጽሁፍ መልስና የማስረጃ ዝርዝር የማቅረብ እድሉን ከሚያጣ በቀር ከክርክሩ ውጪ እንዲሆን መታዘዝ አልነበረበትም።
በዚህም ምክንያት አንድን ተከሣሽ ሕጉ ከሚፈቅደው ሁኔታ ውጪ ከክርክር ውጪ ማድረግ በጉዳዩ ላይ የሥነ ሥርዓት ግድፈት መፈጸሙን ያመለክታል። ክሱ እንዲሻሻል ትእዛዝ ሲሰጥ ተከሣሸ መልስ ማቅረብ አትችልም የተባለው ከዚህ ሥነ ሥርዓት ግድፈት ጋር በተያያዘ ምክንያት ነው። አመልካቹ ከክርክሩ መውጣት ሳይኖርበት አውጥቶ ለተሻሻለው ክስ መለስ አታቀርብም መባሉ አግባብ አይደለም።
የጠቅላይ ፍ/ቤት የሥነ ሥርዓት ግድፈት መፈጸሙን በማመን ይህን ግድፈት ማስተካከል ሲገባው አልፎታል። በመሆኑም የሰበር ችሎት የተፈፀመውን የሥነ ሥርዓት ግድፈት በፍ.ሥ.ሥ.ሕግ ቁጥር 211 ስር በተደነገገው መሰረት ማሰተካከል አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል።
ውሣኔ
የአሁን አመልካች በከፈተኛ ፍ/ቤት በነበረው ክርክር ከክርክር ውጪ የተደረገው በአግባሱ ስላልሆነ ወደ ክርክሩ ይግባ።
ለተሻሻለው ክስ መልስ ማቅረብ እንዲችል በከፍተኛው ፍ/ቤት የተሻሻለው ክስ ግልባጭ ይሰጠው።
ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ።
ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የመ/ ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሰሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ ወ/ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት መልስ ሰጪ፡- ወ/ት ሶስና አስፋው ውል- ስለውል አፃፃፍ/ ፎርም/- ስለ ውል አፃፃፍ ነፃነት- ስለ ውል አጻጻፍ /ፎርም/ የተሰጠ ደንብ አለመፈጸም የሚያስከትለው ውጤት - የሚንቀሳቀሱ ንብረቶችን ስለሚመለከቱ ውሎች፣- የማይንቀሳቀሱ ንብረቶችን ስለሚመለከቱ ውሎች በስምምነት ስለሚሆን ያጻጻፍ አይነት - የግድታዎች ቀሪ መሆን - ስለ ይርጋ - የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥሮች 1719፣1720/1/ 1723፣ 1726 ፣1727፣ 1845 በአመልካችና በመልስ ሰጭ መካከል የተደረገው የኪራይ ውል በሁለት ምክንያት ያልተረጋገጠ በመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥሮች 1726/1/ እና 1727/1/ መሰረት የውል ረቂቅ እንጅ አስገደጅነት የለውም፣ አመልካች ከጠየቀው ኪራይ ውስጥ እስከ 8/2/89 ያለው መጠየቅ ከሚችልበት ጊዜ ጀምሮ ሁለት አመት ያለፈው በመሆኑ በይርጋ ይታገዳል በማለት የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በማጽናቱ የቀረበ አቤቱታ፣ 65 66 ው ሳ ኔ፡- የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውና የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያፀናው ውሳኔ ተሽሯል።
በኢትዮጵያ የውል ህግ ውል አመሰራረት ደንቦች መሰረት በህግ ወይም በተዋዋዮች በራሳቸው የተለየ ፎርም ካልተፈለገ በቀር ለውል መመስረት በሁለት ተዋዋዮች መካከል የስምምነት መኖር ብቻ በቂ ነው።
የማይንቀሳቀስ ንብረትን በሚመለከት የሚደረግ ውል ባለቤትነትን /ownership/፣ የአላባ ጥቅምን /usufruct/፣ መያዣን /mortgage/ ወይም ልላ አገልግሎትን /servitude/ ለማቋቋም ወይም ለማስተላለፍ የተደረገ ካልሆነ በቀር የግል በህግ በተመለከተው አጻጻፍ /ፎርም/ መከናወን የለበትም። የኪራይ ውል ከነዚህ ውሎች ውጭ በመሆኑ ከተዋዋዮች ስምምነት ካልሆነ በቀር በህጉ የተለየ አጻጻፍ /ፎርም/ የሚጠይቁት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ አይሆኑበትም።
የህግ ግምት ድንጋጌዎች ከይርጋ ድንጋጌዎች የተለዩ ናቸው።
የመ/ቁ. 15992 ሐምል 19 ቀን 1997 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሥሐ ወርቅነህ አቶ አብድልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ ወ/ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት መልስ ሰጪ፡- ወ/ት ሶስና አስፋው በዚህ መዝገብ የቀረበውን ጉዳይ መርምሮ ችሎቱ የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥቷል።
ለሰበር ለቀረበው ጉዳይ መነሻ የሆነው ውሣኔ የተሰጠው በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን የውሣኔውም ይዘት የቤት ኪራይ ውል በሁለት ምስክሮች ፊት ካልተረጋገጠ በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1727/2/ እና 1726/1/ መሰረት የውል ረቂቅ እንጂ አስገዳጅነት አይኖረውም፣ በመሆኑም ከሣሽ ማስረጃዬ ነው ብሎ ያቀረበው ሰነድ ይህንን ስለማያሟላና በአመልካችና በተጠሪ መካከል የኪራይ ውል አለ ላባል ስለማይችል ከሣሹ የኪራይ ቤቶች አስተደደር ድርጅት የአሁን መልስ ሰጭ ከ23/5/70 ዓ.ም እስከ 30/1/91 ዓ.ም ያልተከፈለ የኪራይ ሂሣብ ብር 65,790.67 እና ወለድ ብር 168,785.90 በድምሩ ብር 234,576.57 እንድትከፍል ያቀረበውን ክስ ፍ/ቤቱ አልተቀበለውም የሚል ነው። ይኸው ፍ/ቤት ተከሣሽ ያቀረበችውን ይርጋን የሚመለከት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መሰረት በማድረግ ከሣሽ ከጠየቀው ክፍያ ውስጥ እስከ 8/2/89 ዓ.ም ድረስ ያለው በይርጋ ይታገዳል በማለት ቀደም ሲል በ23/10/92 ዓ.ም ብይን ሰጥቷል።
ኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ይህን ውሣኔ በመቃወም ለከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም ይግባኙ ተቀባይነት ባለማግኘቱ ለሰበር ችሎቱ የሰበር ማመልከቻ አቅርቧል።
የሰበር ችሎት በዚህ የክርክር ሂደት 1ኛ. ይርጋን አስመልክቶ በሰጠው ትእዛዝ 67 68
No specific laws extracted.
No topics extracted.