አአንድ ተወካይ በወካዩ ላይ ባቀረበው ክስ ወካዩን ወክሎ መከራከር ስላለመቻሉ (ማህልት ገ/ስላሴ እእና እእነ መንግሥቱ ኃብቴ)
No summary available.
የመ/ቁ. 14974 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሥሐ ወርቅነህ ወ/ሮ ስንዱ ዓለሙ አቶ መስፍን እቁበዮናስ ወ/ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- ወ/ት ማህልት ገ/ስላሴ መልስ ሰጪ፡- 1. አቶ መንግሥቱ ኃብ 2. አቶ ዮሴፍ ገ/ሥላሴ ስለ እንደራሴነት - ከገዛ ራስ ጋር ስለሚደረግ ውል ፍጹም ስለሆነ እንደራሴነት - ጥብቅ የሆነ ቅን ልቡና- የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥሮች 2188፣2189፣2209፡- በከሳሽነት ወይም በተከሳሽነት የሙግት ተካፋይ ስለመሆን - ስለ ወኪሎች - ስለ ባለጉዳዩ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ መቅረት- ተከሳሽ በልለበት የተሰጠውን ውሳኔ ስለማንሳት የፍትሐብሕር ሥነሥርዓት ህግ ቁጥሮች 57፣78 2ኛ መ/ሰጭ የአመልካች ወኪል ሆኖ ከ1ኛ መ/ሰጭ ጋር በአመልካች ላይ ባቀረበው ክስ በአመልካች ወኪልነቱ 2ኛ መ/ሰጭ መልስ ሰጥቶ ጉዳዩ ውሳኔ እንዲነሳ ያቀረበችውን ጥያቄ የም/ሽ/ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ወኪልሽ መልስ ሰጥቷል በሚል ውድቅ በማድረጉና ጉዳዩን በይግባኝ ያለው የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ በማድረጋቸው የቀረበ አቤቱታ ው ሳ ኔ፡- የም/ሽ/ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት፣ የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት የOሮሚያ ሰበር ችሎት የሰጡት ትእዛዝ ተሽሯል።
አንድ ተወካይ ፍጹም ታማኝ መሆን ያለበት ሲሆን በወካዩ ጥቅምና በራሱ ጥቅም መካከል ግጭት ባለበት ጊዜ ለወካዩ የማሳወቅ ግድታ አለበት።
አንድ ተወካይ በወካዩ ላይ ባቀረበው ክስ ወካዩን ወክሎ መከራከር አይችልም።
41 42 የመ/ቁ. 14974 ሃምል 28 ቀን 1997 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሥሐ ወርቅነህ ወ/ሮ ስንዱ ዓለሙ አቶ መስፍን እቁበዮናስ ወ/ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- ወ/ት ማህልት ገ/ስላሴ ተጠሪ፡-
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ብይን የተሰጠው በም/ሽ/ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን በአሁኑ ተጠሪዎች የአሁኗን አመልካች ጨምሮ ሶስት ሰዎች ላይ ክስ መስርተው ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ የአሁኗ አመልካች በልለሁበት የተሰጠው ውሳኔ ተነስቶ ወደ ክርክሩ ልግባ በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 78 መሰረት ታመለክታለች። ፍርድ ቤቱም የአመልካች አቤቱታ ለአሁኖቹ ተጠሪዎች እንዲደርሳቸው አድርጐ ተጠሪዎቹም በክርክሩ ወቅት ለአመልካቿ ወኪል መጥሪያ ደርሶ መልስ የሰጠች ስለሆነ አቤቱታው ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተቃውመዋል።
ጉዳዩን በመጀመሪያ ያየው የም/ሸ/ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ህዳር 17/1995 ዓ.ም በዋለው ችሎት በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁጥር 78 መሰረት አንድ ሰው ክርክሩ ውስጥ ገብቶ መከራከር የሚችለው በልለበት እና ሳይከራከር ውሳኔ ወይም ትእዛዝ ወይም ብይን ሲሰጥ ነው። አመልካች ግን በተወካይዋ በኩል መጥሪያ ደርሷት መልስ ሰጥታ የተከራከረች በመሆኑና ውክልናው የተነሳ ለመሆኑም የቀረበ ነገር ስለልለ አቤቱታዋ ተቀባይነት የለውም በማለት የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል። በይግባኝ ያየው የOሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ውሳኔ ስህተት የልውም በማለት ይግባኙን በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 337 መሰረት የዘጋው ሲሆን የዚሁ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎትም ውሳኔው መሰረታዊ የህግ ስህተት የለውም ሲል የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ አድርጓል።
የአሁኑ አቤቱታም የቀረበው በዚሁ ብይን ላይ ሲሆን የአመልካችዋ ዋና ቅሬታም፣ 2ኛ ተጠሪ ራሱ ክስ አቅራቢ እራሱ መልስ ሰጪ ሆኖ ያቀረበው ክርክር ከህጉ መንፈስ ውጪ ነው የሚል ነው።
ተጠሪዎች ለቀረበው አቤቱታ መልስ እንዲሰጡ ተጠርተው ስላልቀረቡ ጉዳዩ በልሉበት ታይቷል።
ይህ ችሎትም መዝገቡን መርምሯል። ከመዝገቡ የስር 2ኛ ከሳሽ (የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ) የአመለካች (የስር 3ኛ ተከሳሽ) ወኪል በመሰረተው ክስም በአመልካች ስም መከላከያ መልስ መስጠቱን መረዳት ይቻላል። በመሆኑም አንድ ተወካይ በወካይ ላይ በመሰረተው ክስ በወካዩ ስም መልስ ላያቀርብ ይችላል ወይ; አቅርቦስ ከሆነ ክርክሩ ወካዩ እንዳቀረበው ላቆጠር ይችላል ወይ; የሚሉ ነጥቦች የህግ ትርጉም የሚያስፈልጋቸው ሆነው ተገኝተዋል።
አንድ ባለጉዳይ ፍ/ቤት መቅረብ የማይፈቅድ ከሆነ ነገሩን ለማስረዳት፣ ለመከራከር፣ ለሚጠይቀው ሁሉ በቂ መልስ ለመስጠት የሚችል ሰው በዋናው ባለጉዳይ ተተክቶ በነገረ-ፈጅነት፣ በወኪልነት፣ በጠበቃነት ላከራከር እንደሚችል በፍ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 57 ስር ተገልጿል። በመሆኑም አንድ ባለጉዳይ በሚከሰስበት ሆነ በሚከስበት ጉዳይ ፍ/ቤት መቅረብ ካልፈለገ ወይም ካልቻለ እሱን በመወከል እንዲከራከር ለልላ ሰው ውክልና መስጠት የሚችል ሲሆን ይህም ውክልና የሚሰጠው ስለውክልና የሚመለከቱትን የፍ/ብ ሕር ህጉ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ነው። በመሆኑም አንድ ወኪል የውክልናውን ስራ የሚፈጽምበት ጊዜ እነዚህን የህጉን ድንጋጌዎች በመከተል ይሆናል። ወኪሉም ከተሰጠው የውክልና ስልጣን ክልል ሳይወጣ በህጉ መሰረት የሚፈጽሟቸው ተግባራት ወካዩ ራሱ እንደሚፈጽማቸው ተደርገው ይቆጠራሉ (የፍ/ህ/ቁ 2189 (1))። በመሆኑም አንድ ወኪል ስለልላው ሰው ሆኖ በፍ/ቤት ክርክር እንዲቀርብ በተሰጠው የውክልና ስልጣን መሰረት የሚያቀርበው ክርክር ባለጉዳዩ እንዳቀረበው ተደርጐ ይቆጠራል። ይህ አጠቃላይ መርህ ሲሆን አንድ ሰው ስለልላ ሰው ሆኖ ክርክር እንዲያቀርብ የውክልና ስልጣን ተሰጥቶት እንኳን ቢሆን ወኪሉ ራሱ ወካዩን በከሰሰበት ጉዳይ ግን በወካዩ ስም ክርክር ላያቀርብ ይችላል ወይ; የሚለው ነጥብ ውክልናን ከሚመለከቱት አጠቃላይ የህጉ ድንጋጌዎች እና ከህጉ አላማ ጋር አገናዝቦ ማየቱ ተገቢ ነው፡ 43 44 ውክልና ማለት ተወካይ የሆነ ሰው ወካዩ ለሆነው ልላ ሰው እንደራሴ ሆኖ አንድ ወይም ብዙ ህጋዊ ስራዎች በወካዩ ስም ለማከናወን የሚገባበት ውል ነው።
(ፍ/ህ/ቁ 2198)። በመሆኑም አንድ ተወካይ የውክልና ስራ በሚፈጽምበት ጊዜ የወካዩን ህጋዊ ሁኔታዎችን የመለወጥ ስልጣን ተሰጥቶታል። ይሕም በመሆኑ ተወካዩ ለወካዩ ፍጹም ታማኝ የመሆን እና የወካዩን ጥቅም ሙሉ ለሙሉ የማስጠበቅ ግድታ ተጥሎበታል። ስለሆነም ተወካዩ ስራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ቅድሚያ ላሰጥ የሚገባው የወካዩን ጥቅም ብቻ በመሆኑ የጥቅም ግጭት ባለበት ሁኔታ ተወካዩ በስራው አፈጻጸም ጥንቃቄ ላያደርግ ይገባል። ምክንያቱም የጥቅም ግጭት በሚፈጠርበት ጊዜ አንድ ተወካይ ከራሱ ጥቅም ይልቅ የወካዩን ጥቅም ላያስቀድም ይችላል ተብሎ አይታሰብም። ስለዚህም ተወካዩ የራሱን ጥቅም የሚመለከት ጉዳይ ሲያጋጥመው ሁኔታውን ለወካዩ ሳያሳውቅና ወካዩ ሳይስማማ ስራውን እንዳይፈጽም ይከላከላል። ስለወኪልነት የተደነገጉትን የፍ/ብሕር ድንጋጌዎች ስንመለከትም ተወካዩ ከወካዩ ጋር በሚኖረው ግንኙነት ጥብቅ የሆነ ቅን ልቦና ላኖረው እንደሚገባ እና የውክልና ስልጣኑን የሚያስቀሩ ምክንያቶች እንዳለበት (የፍ/ብ/ህ/ቁ 2208)፣ ተወካዩ ስራውን የሚፈጽመው በተለይ ለወካዩ ጥቅም ላሰጥ የሚችል መንገድ ብቻ መሆን እንዳለበት (ፍ/ብ/ህ/ቁ 2209(1))፣ እንዲሁም ተወካዩ በራሱ ስም ከወካዩ ጋር የሚያደርገው ውል ወካዩ ካላጸደቀው በቀር ላፈርስ እንደሚችል (የፍ/ህ/ቁ 2188) መደንገጋቸው ተወካዩ ለወካዩ ፍጹም ታማኝ መሆን እንዳለበት እና ለወካዩ ጥቅም ብቻ መስራት እንዳለበት፣ የጥቅም ግጭት ባለበት ጊዜ ሁሉ ሁኔታውን ለወካዩ የማሳወቅ ግድታ እንዳለበት የሚያስገነዝቡ ናቸው። በመሆኑም አንድ ተወካይ የጥቅም ግጭት ባለበት ጊዜ ለወካዩ ሳያሳውቅ የሚየከናውነውን ስራ ወካዩ ላቃወመው የሚችል መሆኑን እና በዚህ ሁኔታ የተከናወነው ስራም ወካዩ ካላፀደቀው በቀር ወካዩ ራሱ እንደፈጸመው ላቆጠር እንደማይገባ ከውክልና ግንኙነት አጠቃላይ ዓላማ እና ከፍ/ብ/ህጉ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል።
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስ የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ በአመልካች (በስር 3ኛ ተከሳሽ) ላይ የመሰረተው ክስ በወኪሉ እና በተወካዩ መሃከል ግልጽ የጥቅም ግጭተ ፈጥሯል። 2ኛ ተጠሪም ራሱ ከሳሽ ሆኖ የቀረበበትን ጉዳይ ለአመልካች የገለፀላት መሆኑ እና አመልካቿም ተጠሪው የቀረበውን መልስ የተስማማችበት ለመሆኑ የተረጋገጠ ነገር የለም። አመልካቿ እንዲያውም ወኪሐ የሰጠውን መልስ ተቃውማዋለች። በመሆኑም 2ኛ ተጠሪ ራሱ በመሰረተው ክስ ለአመልካች ሳያሳውቅ ያቀረበው መከላከያ መልስ ስለወኪልነት የተመለከቱትን መርሆች እና የህጉን ድንጋጌዎች የሚቃረን በመሆኑ አመልካች በወኪሐ በኩል ክርክር አቅርባለች ማለት አይቻልም። በዚህም ምክንያት አመልካች በወኪሐ በኩል መልስ ሰጥታ የተከራከረች በመሆኑ በልለሁበት የተሰጠው ውሳኔ ተነስቶ ወደ ክርክሩ ልግባ በማለት ልትጠይቅ አይገባም ተብሎ የተሰጠው ብይን የህግ ስህተት አለበት።
• አመልካች በልለችበት የተሰጠው ውሳኔ ተነስቶ ወደ ክርክሩ ገብታ ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የመሰለውን ይወስን።
• የም/ሽ/ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ-13/95 በ17/3/95 ዓ.ም፣ የOሮማያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ 464/95 በ20/6/95 ዓ.ም፣ የOሮሚያ ፍ/ቤት በመ/ቁ 532/95 በ3/5/96 ዓ.ም የሰጡት ትእዛዞች ተሽረዋል።
• መዝገቡ ተዘግቷል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.