በህግ ግምት የሚሸፈንን የፍሬ ነገር ክርክር በሚመለከት ተከራካሪ ወገኖች ባያነሱትም ፍርድ ቤቱ የሕግ ግምቱን ተፈፃሚ ስለማድረጉ /የኪራይ ቤቶች አአስተዳደር ድርጅት እእና በሮኒ አአቲክፖ/
No summary available.
የመ/ቁ. 17068 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሰሀ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ ወ/ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት መልስ ሰጪ፡- ሚ/ር ቢሮኒ አቲክፖ ውል የግድታዎች መቅረት - ስለ ይርጋ - የውልን ጉዳይ ስለሚመለከት ማስረጃ - ገንዘቡ እንደተከፈለ የሚያስቆጥሩ የህላና ግምቶች- የፍትሐብሕር ህግ ቁጥሮች 1856፣ 2024፡- ስለ አቤቱታ -ህጋዊ ስለሆኑ ግምቶች - የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 89 አመልካች በስር ፍ/ቤት መ/ሰጪ ያልከፈለው የኪራይ ገንዘብ እንዲከፍለው በመጠየቅ ባቀረበው ክስ መ/ሰጪ ሳይቀርብና ኪራዩ ተከፍሐል የሚል ክርክር ሳይነስ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ህ/ቁ. 2024 መሰረት ከሁለት አመት በላይ የሆነው የኪራይ ገንዘብ እንደተከፈለ ይቆጠራል በሚል የአመልካችን ክስ በከፊል ውድቅ ስላደረገውና የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ውሳኔውን ስላጸናው የቀረበ አቤቱታ ውሳኔ፡- የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ጸንቷል።
የሕላና ግምት ድንጋጌዎች ከይርጋ ደንብ ድንጋጌዎች የተለዩ ናቸው።
የቀረበላቸው ፍሬ ነገር በህግ ግምት ከተሸፈነ ተከሳሽ ፍሬ ነገሩን ካደም አልካደ ፍ/ቤቶች የህግ ግምቱን ተፈፃሚ ማድረግ አለባቸው።
የመ/ቁ. 17068 ሐምል 19 ቀን 1997 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሰሀ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ ወ/ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት መልስ ሰጪ፡- ሚ/ር ቢሮኒ አቲክፖ (ባለቤት)
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር ማመልከቻ መነሻ የሆነው የሥር ፍርድ ቤቶች አመልካች ክስ ካቀረበበት ገንዘብ መካከል ከሁለት ዓመት በላይ የሆነው ሂሣብ ተከሣሽ በፍ.ብ.ሕግ ቁጥር 2024 መሰረት እንደከፈለ ስለሚቆጠር ከሁለት ዓመት በላይ የሆነውን ሂሣብ በሚመለከት ከሣሽ ያቀረበው የክፍያ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት በመወሰናቸው እና ልሎችንም ክስ የቀተበባቸው ሂሣቦች ውድቅ በማድረጋቸው ነው።
የአሁኑ አመልካች ይግባኝ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም የቀረበው ይግባኝ ተቀባይነት በማጣቱ የሰበር ማመልከቻ አቅርቧል። የሰበር ማመልከቻው ይዘት በርካታ ነጥቦችን ያካተተ ሲሆን ዋና ዋና ነጥቦቹ የቤቱ ኪራይ በአሜሪካን ዶላር ላከፈለን ሲገባ ታልፎብናል፣ የውሃ ፍጆታና የአገልግሎት ሂሣብ ውድቅ ተደርጎብናል፣ ከሁለት ዓመት በላይ የሆነውን ሂሣብ አስመልክቶ ክሱ ውድቅ መሆኑ አግባብ አይደለም፣ የተወሰነልን ወጪና ኪሣራም ካወጣነው ወጪ በታች በመሆኑ ትክክለ አይደለም የሚል ነው።
አመልካች ካቀረባቸው ነጥቦች መካከል በሰበር ላታይ ይገባል የተባለው የሕግ ነጥብ የሥር ፍርድ ቤቶች ተከሣሽ ክሱን ለመከላከል ባልቀረበበት ሁኔታ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024 ላይ በሰፈረው የሕላና ግምት መሰረት ከሁለት ዓመት በላይ የሆነው የኪራይ ክፍያ እንደፈከፈለ ይቆጠራል በማለት የአመልካቹን ክስ በከፊል ውድቅ ማድረጋቸው አግባብ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ ነው። በመሆኑም አመልካች ያቀረባቸው ልሎች የቅሬታ ነጥቦች መሰረታዊ የሕግ ስህተት መኖሩን የሚያመለክቱ ስላልሆኑ ይህ ችሎት በነዚህ ቅሬታዎች ላይ ውሣኔ መስጠት አላስፈለገውም።
የሕላና ግምቱን በሚመለከት አመልካች መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለው፡- 31 32 ሀ. ‘’በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1856(2) ዳኞች በገዛ ስልጣናቸው የይርጋ ደንብን መከላከያ በራሳቸው አነሳሽነት ክሱ በይርጋ ውድቅ ነው በማለታቸው፣ ለ. ተከሣሹ ለቀረበበት ክስ መልስ ለመስጠት ካለመፈለጉም በላይ እዳውን አልካደም፣ ሐ. የሕላና ግምት ይወሰድልኝ ማስረጃ ማቅረብ አልችልም ጠፍቶብኛል ስለዚህ የሕግ ግምት ይወሰድልኝ በማለት ተከሣሹ ሳይከራከር፣ መ. የይርጋ ክርክር የሚያነሳው ወገን ግድታውን አለመውጣቱን ሳይክድ የተጣለበት ግድታ ግን በይርጋ ቀሪ ስለሚሆን ከኃላፊነት ነፃ ነኝ አልጠየቅም የሚል ክርክር ሲያቀርብ ነው’’ የሚሉ የክርክር ነጥቦችን በማቅረብ ነው።
መልስ ሰጭ መልስ ካለው ይዞ እንዲቀርብ ትእዛዝ ቢሰጥም ለዚሁ በተያዘው ቀጠሮ አልቀረበም፣ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ በሰበር እንዲታይ በተያዘው የሕግ ነጥብ ላይ የቀረበ የመልስ ሰጭ መልስ የለም።
ይኸው ችሎት አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ መነሻ በማድረግ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024 የሰፈረው የሕግ ግምት ተከሣሹ ቀርቦ እዳውን ባልካደበት ወይም ጭራሽ ባልቀረበበት ሁኔታ ተፈፃሚ ይሆናል አይሆንም በሚለው የሕግ ጉዳይ ትርጉም መስጠት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል።
ወደ ዋናው ነጥጥ ከመግባቱ በፊት አመልካች ያቀረባቸው የመከራከሪያ ነጥቦች የህላና ግምትን ከማመለከተው የሕግ ነጥብ ጋር ያላቸውን አግባብነት መርምሯል።
አመልካች በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024 የሰፈረው የሕግ ግምት ይርጋን ከሚመለከቱ ድንጋጌዎች ጋር አንድ እንደሆኑ በመቁጠር ፍርድ ቤት የሕላናውን ግምት በራሱ አነሳሽነት ላያነሳው አይገባም የሚል የሕግ ክርክር አቅርቧል። ሆኖም በፍትሐብሕር ሕጉ የሰፈረው የህላና ግምት በዚሁ ሕግ በአንቀጽ 1845 (ወይም በልሎች በርካታ አንቀጾች) ከሰፈረው የይርጋ ደንብ የተለየ በመሆኑ ፍ/ቤቱ ይህን መከራከሪያ የሚቀበለው አይደለም። የይርጋ ደንብ አንድ ክስ በፍርድ ቤቱ ቀርቦ በስረ ነገር እንዳይታይ የሚከለክል ሲሆን የሕላና ግምት (በ2024 የሰፈረው የመከፈል ግምትን ጨምሮ) በልላ በኩል የማስረዳት ሸክምን ከአንድ ወገን ወደ ልላው የማስተላለፍ ውጤት ብቻ ያለው በመሆኑ ከሣሽ ያቀረበውን ክስ ይዘት መርምሮ ውሣኔ መስጠትን የሚከለክል አይደለም። በፍትሐብሕር ሕጉ ውስጥ የሰፈረውን ይርጋ ተከሣሹ ወገን ካላነሳው ፍርድ ቤቱ በራሱ ላያነሳ እንደማይችል በፍትሐብሕር ሕግ ቁ.1856 የተጠቀሰ ቢሆንም ይህ ድንጋጌ ተፈጻሚነት የሚኖረው ለይርጋ ድንጋጌዎች እንጂ በሕግ ግምት የማስረዳት ሸክም ከአንድ ተሟጋች ወደ ልላው በሚዘዋወርባቸው ሁኔታዎች አይደለም። በመሆኑም የአመልካች ድርጅት ይርጋን (Period of limitation) ከሕግ ግምት (Presumptions) ጋር በማመሳሰል ለይርጋ ተፈፃሚ የሚሆነው ሕግ ለህግ ግምትም ተፈፃሚ መሆን ይገባዋል በማለት ያቀረበው ክርክር የህጉን መንፈስ፣ ዓላማና ግልጽ ይዘት ያልተከተለ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም።
ቀጥሎ መታየት ያለበትና በዚህ መዝገብ የህግ ትርጉም የሚሰጠው ዋነኛው ነጥብ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024 የሰፈረው የሕግ ግምት ተፈፃሚ የሚሆነው በምን ዓይነት ሁኔታ ነው? የሚል ሲሆን ተከሣሽ ቀርቦ የቀረበበትን ክስ ባልካደበት ሁኔታ ተፈፃሚ ይሆናል ወይስ አይሆንም? የሚለው ነጥብም ከዚሁ ተያይዞ የሚነሳ ነው።
የሕግ ግምት አፈፃፀም የስረነገር (Substantive) ሕግ እና የስነ ሥርዓት (Procedural) ህግ ገጽታዎች ያሉት ሲሆን ከላይ የተነሱትን ነጥቦች በአግባቡ ለመመለስ የኢትዮጵያ ሕግ በሁለቱም ረገድ ያለውን ዝርዝር ድንጋጌ መመልከትና መረዳት ያስፈልጋል።
በኢትዮጵያ የስሪነገር ሕጎች በርካታ የሕግ ግምቶች ያሉ ሲሆን አሁን ከቀረበልን ጉዳይ ጋር አግባብነት ያለው በፍትሐብሕር ሕጉ ቁጥር 2024 የሰፈረው ግምት ነው። ይህ የግህ ግምት ስለ ውሎች ማስረጃ በሚመለከተው ክፍል የሚገኝ ሲሆን በውል የሚጠየቅ ገንዘብ እንደተከፈለ ከሚያስቆጥሩ የሕላና ግምቶች አንዱ ነው።
ይህ ድንጋጌ እዳው እንዲከፈል ከሚገባበት ቀን ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ሳይከፈሉ የቀሩ በአንቀጹ ተዘርዝረው የተቀመጡትን እዳዎች እንደተከፈሉ ይቆጠራል። በዚህ ግምት ከሚሸፈኑ እዳዎች መካከል ለቤት ኪራል የሚከፈል እዳ አንዱ ነው።
(ቁ.2024/መ) የሕግ ግምቶች መሰረታዊ ውጤት የማስረዳት ሸክምን ከአንዱ ወገን ወደልላው እንዲሻገር ማድረግ ቢሆንም የማስረዳት ሸክሙ የዞረበት ወገን የሕግ ግምቱን ማፍረስ የሚችልበት የሕግ ሁኔታ ይለያያል። አንዳንድ የህግ ግምቶች የግምቱ ተጠቃሚ ያልሆነው ወገን ማንኛውንም ዓይነት ማስረጃ በማቅረብ የሚያፈርሳቸው ሲሆኑ (Reputable Presumption) ልሎች የሕግ ግምቶች ደግሞ ማንኛውም ዓይነት ማስረጃ 33 34 በማቅረብማፍረስን የማይፈቅዱ (Irrefutable Presumption) ናቸው። የፍትሐብሕር ሕጉ ከ2020 – 2024 ያሰፈራቸውን የህግ ግምቶች ለማፍረስ ማንኛውንም ዓይነት ማስረጃ ማቅረብ የማይቻል ስለመሆኑ ከሕጉ አንቀጽ 2026(1) ድንጋጌ መገንዘብ ይቻላል። ይኸው ድንጋጌ ‘’ከዚህ በላይ ባሉት ቁጥሮች ላይ ለተገለጠው የሕላና ግምት መቃወሚያ የሚሆን ማንኛውም ዓይነት ማስረጃ ለመቀበል አይቻል‘’ በማለት በሕጉ የሰፈሩትን ግምቶች ለማፍረስ አንደኛው ወገን ማንኛውንም ዓይነት ማስርጃ ማቅረብ እንደማይፈቅሉለት በመርህ ደረጃ በግልጽ አስፍሯል። ይህ አጠቃላይ መርህ ቢኖርም አንዱ ወገን ይህን አስገዳጅ የህግ ግምት ማፍረስ የሚችለው ልላው ወገን መሀላ እንዲፈጽምለት በመጠየቅ ብቻ ነው። በዚህ መልክ ልላው ወገን መሃላ እንዲወርድለት በመጠየቅ የማስረዳት ሸክሙን በመወጣት የሚሻ ወገን የፍትሐብሐር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 83 በሚያዘው መሰረት ይህን ማስረጃውን ክሱን በሚያቀርብበት ወቅት እንዲጠቅስ ይጠበቅበታል።
በውል ሕግ የሰፈሩት እነዚህ ድንጋጌዎች የስረ ነገር ሕግ ክፍሎች በመሆናቸው ፍርድ ቤቶች ላከተሉዋቸው የሚገባ አስገዳጅ የሕግ ድንጋጌዎች ናቸው።
እነዚህ ድንጋጌዎች የማስረጃን አቅራረብ የሚመለከቱ ከመሆናቸው በስተቀር እንደማንኛውም ልላ የውል ሕግ ድንጋጌዎች በባለጉዳዮች ቢጠቀሱም ባይጠቀሱም ፍርድ ቤቱ አግባብነት ባለበት ሁኔታ ሁሉ ተፈፃሚ ላያደርጋቸው የሚገቡ ድንጋጌዎች ናቸው። በመሰረቱ ወደ ፍርድ ቤት የሚቀርቡ ባለጉዳዮች ለጉዳያቸው አግባብነት ያለውን ፍሬነገርና የሚጠይቁትን ዳኝነት ከመግለጽ አልፈው በእያንዳንዱ ጉዳይ ላይ ተፈፃሚ የሚሆነውን ወይም የማይሆነውን ድንጋጌ እንዲጠቅሱ አይጠበቅባቸውም። በመሆኑም በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024 የተጠቀሰውን የሕግ ድንጋጌ ተፈፃሚ ለማድረግ የሚያበቃ ፍሬ ነገር የቀረበለት መሆኑን የተረዳ ፍ/ቤት በዚሁ ድንጋጌ መሰረት የሚሸፈነውን ፍሬ ነገር እንደተረጋገጠ የመቁጠር ግድታ አለበት።
የሕግ ግምቶችን አስመልክቶ በፍትሐብሕር ሕጉ የሰፈረው ይህ መሰረተ ሃሣብ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕጉም በተመሣሣይ መንገድ ተደንግጎ የምናገኘው ነው። በዚሁ ሕግ መሰረት ማንኛውም ተከሣሽ በመርህ ደረጃ ለፍርድ ቤቱ በሚያቀርበው መልስ ክስ የቀረበበትን ነገር በግልጽና በዝርዝር ማስተባበል ይጠበቅበታል። በክስ አቤቱታ ላይ የቀረበ ማንኛውም ነገር በግልጽ ካልተካደ እንደታመነ ላቆጠር እንደሚችልም ይደነግጋል። ይህ አባባል አጠቃላይ የፍትሐብሕር መደበኛ ሙግት አካሄድን የሚመለከት ቢሆንም ተከሣሹ የሕግ ግምት ተጠቃሚ ሲሆን በግምቱ የሚሸፈነውን ፍሬ ነገር በሚመለከት ይህ ግድታ እንደሚወርድለት የሕጉ አንቀጽ 89 በግልጽ ያስቀምጣል። ይህ ድንጋጌ ‘’አስቀድሞ በአንደኛው ወገን አቤቱታ ወይም ሙግት በግልጽ የተካደ ጉዳይ ካልሆነ በቀር አንዱ ወገን ተከራካሪ ህጋዊ በሆነ ግምት የሚደገፍበትን ነገር ወይም ልላው ወገን ማስረጃ እንዲያቀርብ ተገቢ የሆነበትን ጉዳይ ልላው ወገን በአቤቱታው ውስጥ መጥቀስ አይገባውም’’ በማለት የሕግ ግምት ተጠቃሚ የሆነ ተሟጋች በሚያቀርበው መልስ በህግ ግምት የተሸፈነውን ፍሬ ነገር በግልጽ የመካድ ግድታ እንደልለበት ያመለክታል። በመሆኑም አንድ ተከሣሽ በሕግ ግምት የተሸፈነውን ፍሬ ነገር በማስመልከት በመልኩ በግልጽና በዝርዝር መካድ አይጠበቅበትም። በመሆኑም በህግ ግምት የተሸፈነን ጉዳይ በማስመልከት ማንኛውም ፍርድ ቤት ቢሆን ተከሣሹ በግልጽ ስላልካደ እንዳመነ ይቆጠራል በማለት ፍርድ ላሰጥ አይችልም። ይህ መሰረተ ሃሣብ በፍትሐብሕር ሕጉ ካለው መሰረተ ሃሣብ ጋር ተመሳሳይ እና የሚጣጣም ነው።
የሕግ ግምትን አስመልክቶ ያለው የሕግ ማእቀፍ ይህ በመሆኑ ፍርድ ቤቶች የሚሰጡት ውሣኔ ይህንኑ መሰረት ያደረገ መሆን ይጠበቅበታል። ተከሣሹ የሕግ ግምት ተጠቃሚ በሚሆንበት ወቅት የሚከተሉት ሂደትና የሚሰጡት ውሣኔም በልሎች በመደበኛ የሙግት ሂደት ከሚተከሉዋቸው የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ደንቦች የተለዩ መሆናቸው የማይቀር ነው።
በመሆኑም የቀረበላቸው ፍሬ ነገር በህግ ግምት እስከተሸፈነ ድረስ ፍርድ ቤቶች ተከሣሽ ካደም አልካደ የሕግ ግምቱን ተፈፃሚ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ተከሣሹ በልለበት ጉዳዩ እንዲቀጥል መደረጉም አስገዳጅ በሆኑት የሕግ አንቀጾች አፈጻጸም ላይ የሚያመጣው ለውጥ አይኖርም። ተከሳሹ ፍርድ ቤት ቢቀርብም በግልጽ እንዲክድ የማይገደደውን ፍሬ ነገር ጉዳዩ እርሱ በልለበት በመቀጠሉ እንዳመነ የሚቆጠርበት በቂ ሕግ ምክንያት የለም።
አሁን በቀረበልን ጉዳይ ክስ በቀረበበት የኪራይ ክፍያ በከፊል መጠየቅ ከነበረበት ከሁለት ዓመት በላይ የሆነው ስለመሆኑ ከከሣሽ ክስ መረዳት ይቻላል። ይህ ከሆነ ደግሞ ተከሣሽ ባያነሳውም ወይም በልለበት ቢታይም በፍትሐብሕር ሕጉ ቁጥር 2024 ስር ያለውን የሕግ ግምት ተፈፃሚ በማድረግ እዳው እንደተከፈለ መቁጠር ተገቢ ነው።
35 36 የሥር ፍርድ ቤቶችም ያደረጉት ይህንኑ ነው። ስለዚህ ፍርድ ቤቶቹ ህጉን በትክክል ተፈፃሚ ያደረጉ ስለሆነ ውሣኔው የሚነቀፍ አይደለም።
ውሣኔ
የሥር ፍርድ ቤቶች ውሣኔዎች ፀንተዋል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ የሀሣብ ልዩነት በአብዛኛው ድምጽ በተሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2024 የተመለከተውም ሆነ ልሎች የሕላና ግምት ድንጋጌዎች ከይርጋ ደንብ የተለዩ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን እኛም ይህን የምንቀበለው ነው። የሕግ ግምት የሚያስከትለው ሕጋዊ ውጤት የማስረዳት ሸክምን በግምቱ ተጠቃሚ ከሆነው ወገን ወደ አልሆነው ተከራካሪ ማሻገር ብቻ መሆኑንም የምናምንበት ነው።
ይሁን እንጂ ፍርድ ቤት አንድን ሕግ ተመስርቶ ፍርድ ለማስፈር የቀረበለት ወይም የያዘው የፍሬ ነገር ክርክር ከተጠቃሹ ሕግ ጋር ግንኙነት ያለው እንዲሆን ያስፈልጋል። ፍ/ቤቱ ሕጉን መሰረት አድርጎ ውሣኔ ከመስጠቱ በፊትም ሕጉ ለክርክሩ አግባብነት ያለው መሆኑን ማረጋገጥ ይጠበቅበታል።
እኛም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2024 የተመለከተው የሕላና ግምት ከተያዘው ክርክር ጋር ያለውን አግባብነት መርምረናል። አብዛኛው ድምጽ እዳ እንዲከፍል የተጠየቀው ተከሣሽ ቀርቦ እዳውን ባይክድም ወይም ጭራሹን ባይቀርብም ፍ/ቤት ይህን ድንጋጌ ተመስርቶ በሕላና ግምቱ ተጠቃሚ ላያደርገውና እዳው እንደተከፈለ ላቆጠርለት ይገባል ሲል ለድንጋጌው በሰጠው ትርጓሜ እና በደረሰበት መደምደሚያ ግን ባለመስማማት እንደሚከተለው በሐሳብ ተለይተናል።
እንደሚታወቀው በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ያልተከፈለ እዳ እንደተከፈለ ይቆጠር ዘንድ ሕግ ግምት የወሰደበት የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2024 ማስረጃ ስለማቅረብ ግድታና ስለአቀባበሉ በተዘረዘረበት የፍ/ብ/ሕግ ምእራፍ ሰባት ክፍል አንድ ስር የሚገኝ ነው። በዚህ ምእራፍ ስር ያለ የሕላና ግምት ልክ እንደ ጽሑፍ፣ ምስክር፣ የእምነት ቃል ወይም መሐላ ሁሉ አንድ የማስረጃ አይነት ተደርጐ ላወሰድ የሚገባው መሆኑን ከፍ/ብ/ሕ/ቁ.2002 ላይ መገንዘብ የሚቻል ነው። ተቃራኒ ማስረጃ በማቅረብ እዳው እንደተከፈለ መቆጠሩን ቀሪ ማድረግ እንደሚቻል የሚደነግገው የፍ/ብ/ሕ/ቁ.2025 ደግሞ እነዚህ የሕላና ግምቶች እራሣቸው ማስረጃዎች መሆናቸውን ግልጽ የሚያደርግልን ነው። ስለሆነም የፍ/ብ/ሕ/ቁ.2024ን ጨምሮ በዚህ ምእራፍ ክፍል ሶስት ውስጥ የተደነገጉት ተጠያቂው ገንዘብ እንደተከፈለ የሚያስቆጥሩ የሕላና ግምቶች በሙሉ እንደ አንድ የክርክር ማስረጃ የሚወሰዱ እንጂ ሕግ በፍሬ ነገር ጉዳይ ላይ የሕላና ግምት የወሰደባቸው ናቸው ላሰኙ የሚችሉ አይደሉም። ለአንድ ውሣኔ መሰረት የመሆናቸውም ጉዳይ ከዚህ የሕጉ መንፈስና አላማ ጋር እየተዛመደ ላታይ የሚገባው ነው። ይህንንም ግልጽ ለማድረግ ጉዳዩን የፍትሐብሕር ሙግት ከሚመራበት የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች አኳያ ማየቱ አስፈላጊ ነው።
አንድ ክስ የቀረበበት ተከማሽ የተከሰሰበትን ነገር በግልጽ መካድ እንደሚገባውና ይህን ካላደረገ ደግሞ ክሱን እንደአመነ ላቆጠር እንደሚገባው በፍ/ብ/ሕ/ቁ.83፣ 334/1/መ/ እና 235 ላይ ተመልክቷል። እንበልና የሁለት ዓመት ጊዜ ያለፈው የኪራይ ሂሣብ እንዲከፍል ክስ የቀረበበት ተከሣሽ ቀርቦ አለመክፈሉን /እዳውን/ ቢያምን ወይም በግልጽ ባይክድ ፍ/ቤቱ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.242ን ተመስርቶ በእምነቱ መሰረት ፍርድ ላሰጥ እንጂ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2024 ወደ ተጠቀሰው የሕላና ግምት ላገባ የሚችልበት ሁኔታ አየታይም። የያዘውም ፍሬ ነገር የዚህን ስረ ነገር ሕግ ተፈፃሚነት የሚጠይቀው አይሆንም።
በልላ በኪል ደግሞ ይኸን የኪራይ ሂሣብ እንዲከፍል ክስ የቀረበበት ተከሣሽ ከፍያለሁ ቢልና የቀረበበትን ክስ ቢክድ ፍ/ቤቱ 1ኛ/ ተከሣሹ እዳውን ላከፍል የሚገባው ስለመሆን፣ አለመሆኑ ጭብጥ ላይዝ 2ኛ/ በተሹ ቢጠቀስም ባየጠቀስም የፍ/ብ/ሕ/ቁ.
2024ን ላመሰረትና ተከሣሹን በሐላና ግምት ማስረጀው ተጠቃሚ እንዲሆን ላያደርገው ይገባዋል። በሕላና ግምት ተጠቃሚው ተከሣሽ ልላ ማናቸውንም አይነት ማስረጃ ከማቅረብ ግድታ ነፃ የሚወጣ ሲሆን ከማሹ ግን ይህ የሕላና ግምት በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2026/2/ መሰረት በመሐላ ብቻ እንዲፈርስለት ለመጠየቅ ይችላል።
በተያዘው ጉዳይ ሁለት ዓመት ያለፈው የኪራይ ሒሣብ እንዲከፍል ክስ የቀረበበት ተከሣሽ ቀርቦ መልስ የሰጠ ወይም መከራከሪያውን ያሰማ አይደለም። ይህ ደግሞ አግባብነት ካላቸው የፍ/ብ/ሕጉ ድንጋጌዎች አኳያ ሲታይ ተከሣሹ እዳውን አለመክፈሉን ወይም ክሱን ማመኑን የሚያሳየን እንጂ በምንም መለኪያ ክሱን ክዷል ወደሚል መደምደሚያ ላይ ላያደርሰን የሚተል አይሆንም። ፍ/ቤቱም በፍሬ ነገርም ሆነ በሐጉ ረገድ ልዩነት የተፈጠረበት ክርክር ቀርቦለታል የሚያሰኝ ባለመሆኑም ውሣኔ 37 38 ላያሳርፍበት የሚገባ ጭብጥ ለመያዝ አይችልም። ይልቁንም ተከሣሹ የመከላከያ መልስ አላቀረበምና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.246 መሰረት በጉዳዩ ጭብጥ እንዲይዝበት የሚገደድበት አይሆንም። ይህ ደግሞ ተከሣሹ ክሱን እንዳመነ ተቆጥሮ በእምነቱ መሰረት ፍርድ ላሰጥበት እንደሚገባ የሚያመለክተን ነው። ከላይ እንደተገለፀው የእምነት መነሻ ተደርጐ ፍርድ ሲሰጥ ደግሞ ወደ ሕላና ግምት ማስረጃው መሄዱ አላሰፈላጊ ነው። በውጤቱም ተከሣሹ በሐላና ግምት ማስረጃው ተጠቃሚ መሆን እንደማይገባውና የፍ/ብ/ሕ/ቁ.2024ም እዳው ባልተካደ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ተከሣሹ ቀርባ መልሰ /መለላከያ/ ባቀረበ ጊዜም በፍ/ቤት አነሳሽነት ለውሣኔ መሰረት ላሆን እንደማይችል የሚያረጋግጥልን ነው።
በተጨማሪም አብዛኛው ድምጽ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.89ን በመጥቀስና ይህ ድንጋጌ የሕላና ግምቱ ተጠቃሚ የሆነው ወገን የፍሬ ነገር ክርክር የማቅረብ ግድታውን የሚያሰቀርለት ነው በማለት ድንጋጌው ከስረ ነገር ሕጉ ጋር ይጣጣማል የሚል ማጠቃለያ ላይ መድረሱን ተረድተናል። እኛም ምንም እንኳን የዚህ ድንጋጌ የአማርኛ ቅጅ በጣም ግልጽ ሆኖ ባናገኘውም ከእንግላዘኛው ቅጂ ጋር በአንድነት ሲታይ አንደኛ ድንጋጌው በፍሬ ነገር ጉዳይ ላይ የተደረገ የሕግ ግምትን እሳቤ አድርጐ የተደነገገ መሆኑን፤ ሁለተኛ የግራ ቀኙን ተሟጋቾች በክርክር ውስጥ መኖር የማጠይቅ መሆኑን፤ እንዲሁም ሶስተኛ አንደኛውን ወገን ተከራካሪ ባይከራከርበትም በሕግ ግምቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ጉዳዩ በልላው ወገን ያልተካደ ይሆን ዘንድ የሚፈልግ መሆኑን ለመረዳት ያህል ግን የሚበቃ መሆኑን ተገንዝበናል። እነዚህ ሕጉ የሚፈለጋቸው መስፈርቶች ደግሞ እንደ ማስማረጃ ከሚቆጠረው የፍ/ብ/ሕ/ቁ.2024 ጋርም ሆነ በጉዳዩ ከተያዘው ፍሬ ነገር ጋር የተያያዙ አይደሉም። ስለሆነም በእኛ እምነት ይህ ድንጋጌ ከመሰረቱም ከዚህ ጉዳይ ጋር የሚገናኝ አይደለም።
እንዲሁም የፍ/ብ/ሕ/ቁ.2024ን ጭምር በስረ ነገር ሕጉ ምእራፍ 7 ክፍል 3 ስር እንደተከፈሉ ይቆጠሩ ዘንድ የሕላና ግምት የተወሰደባቸውን እዳዎች አስመልክቶ ክስ ሲቀርብ ሙግቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ የተመለከተውን መደበኛ የሙግት ሥርዓት ተከትሎ የሚከናወን እንጂ የተለየ ደንብ ላከተል የሚገባው ሆኖ አላገኘነውም።
ተከሣሹ ቀርቦ እዳውን /ክሱን/ በመካድ እስከአልተከራከረም በሕላና ግምቱ ተጠቃሚ ላደረግና ከእዳው ነፃ ላሆን አይገባውም። ይልቁንም የሕላና ግምቱ ለፍርድ መሰረት ላደረግ የሚችልበት ሕጋዊ ምክንያት የለምና ክሱን በማሰረጃ አስደግፎ ያቀረበው ከሣሽ (አመልካች) ከሱን በመሰረትክበት ጊዜ ያልተከፈለህ ስለመሆኑ በመሐላ እንዲረጋገጥልህ አልጠየቅክም በሚል ምክንያት እዳው አይከፈልህም ላባል የሚገባው ሆኖ አላገኘውም።
በእነዚህ ምክንያቶች ስማችን በ2ኛ እና በ4ኛ ተራ የተጠቀሰው ዳኞች የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ፍርድ ተሽሮ አመልካቹ የጠየቀው የቤት ኪራይ እንዲከፈለው ላወሰን ሲገባ መጽናቱ ተገቢ ሆኖ ስላላገኘነው ፍርድ ላሻር ይገባው ነበር ስንል በሐሣብ ተለይተናል።
39 40 የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
No topics extracted.