በመጓጓዝ ላይ የነበሩ እእቃዎች በጉዳት በሰው ላይ ላደርስ ይችል የነበረን የግጭት አአደጋ ለማስወገድ በተወሰደ ርምጃ የደረሰ የመኪና መገልበጥ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የደረሰ ጉዳት ስላለመሆኑ (የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት እእና እእነ ኮሜት ትራንስፖርት ድርጅት)
No summary available.
ጥቅምት 27/1994 ዓ.ም ያለውን የወለድ ክፍያ በሚመለከት በመዝገብ ቁ.11641 የሰጠውን ውሣኔ እና የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመዝገብ የሰጠውን ውሣኔ ሽሯል።
መልስ ሰጪ ከ16/12/91 እስከ 27/2/94 ላለው ጊዜ በዋናው ገንዘብ ላይ 9% ወለድ ይከፈል።
በዚሁ በተፈረደው የወለድ መጠን ያልተከፈለ የዳኝነት ገንዘብ አመልካቹ ለጠቅላይ ፍ/ቤቱ ገቢ ያድርግ። የውሣኔው ገልባጭ የሚሰጠው የዳኝነቱን ገንዘብ ገቢ ማድረጉ ከተረጋገጠ በኋላ ነው ተብሐል።
መልስ ሰጪ በዚህ ፍርድ ቤት ውሣኔ አመልካች ለዚህ ፍርድ ቤት ገቢ ያደረገውን የዳኝነት ሂሣብ ይተካለት፣ ልላው በዚህ ፍርድ ቤት ያለውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ።
ውሣኔያቸው ላይ ለውጥ መደረጉን እንዲያውቁት ለፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትና ለጠቅላይ ፍ/ቤት የዚህ ውሣኔ ግልባጭ ይላክ።
የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የመ/ቁ. 14605 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ አበዱልቃድር መሐመድ አቶ መስፍን እቁበዮናስ ወ/ሪት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት መልስ ሰጪዎች፡- 1. ኮሜት ትራንስዓርት ድርጅት 2. ሸበል ትራንስፖርት ድርጅት 3. በከልቻ ትራንስፖርት ድርጅት 4. ወይራ ትራንስፖርት ድርጅት 5. አዲስ ሜካኒካል ድርጅት 6. አቶ ዮሐንስ ተሰፋ ስለ ማጓጓዝ ስራ - የአጓዥ ኃላፊነት - የተመዘገቡ ጓዞች ወይም እቃዎች የጠፋ ወይም ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን - በተለያዩ ምክንያቶች ከኃላፊነት መዳን የንግድ ህግ ቁጥሮች 590፣ 591፣ ውል - ውልን ስላለመፈጸም- ከአቅም በላይ የሆነ ነይል - የፍትሐብሄር ህግ ቁጥር 1792 አመልካች በፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ ከ1ኛ-5ኛ በተጠቀሱት ተጠሪዎች መኪና አቅራቢነት ነጭ ጋዝ ናፍታ አሰጭኖ ከአሰብ ወደ ባህር ዳር በሚጓጓዝበት ወቅት መኪናው ተገልብጦ ዋጋው ብር 51,089.78 /ሃምሳ አንድ ሺህ ሰማንያ ዘጠኝ ብር ከሰባ ሰምንት ሳንቲም/ የሆነ ነዳጅ ስለፈሰሰ ይህንኑ ዋጋ ብር 51,089.78 /ሃምሳ አንድ ሺህ ሰማንያ ዘጠኝ ብር ከሰባ ሰምንት ሳንቲም/ ከ1-5 ያሉት ተጠሪዎ እንዲሁም የመኪናው ባለንብረት 6ኛ ተጠሪ በአንድነትና በነጠላ እንዲከፍሉት ያቀረበውን ጥያቄ ፍ/ቤቱ ነዳጁ 2423 የፈሰሰው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በመሆኑ ተጠሪዎች ኃላፊነት የለባቸውም በማለት ውሳኔ በመስጠቱና ውሳኔውን የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም በማጽናቱ የቀረበ አቤቱታ ው ሳ ኔ፡- የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት እና የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጡት ውሳኔ ተሽሯል።
አንድ አጓዥ በከፊል ወይም በሙሉ እቃዎች ወይም የተመዘገቡ ጓዞች ወይም ጉዳት ሲያገኛቸዉ ወይም የማስረከቢያ ጊዜው ቢዘገይ በኃላፊነት የሚጠቅ ሲሆን ከዚህ ኃላፊነት የሚነው እቃው የጠፋው ወይም ጉዳት የደረሰው ወይም የዘገየው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ወይም በተቀባዩ ጥፋት ሲሆን ነው።
ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ተከስቷል የሚባለው ባለእዳው /አጓዡ/ በቅድሚያ በምንም መልኩ ላያስበው ወይም ላገምተው የማይቻል ክስተት ሲፈጠር ነው።
ወደ መኪና ሮጦ የገባን ሰው ለማዳን በተወሰደ ርምጃ ምክንያት በመጓጓዝ ላይ የነበረ እቃ ላይ የደረሰ ጉዳት ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ ተከስቷል የሚባል አይደለም።
የመ/ቁ. 14605 ቀን ሐምል 29/1997 አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ አበዱልቃድር መሐመድ አቶ መስፍን እቁበዮናስ ወ/ሪት ሂሩት መለሰ የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት
ለአሁን አቤቱታ መነሻ የሆነው ፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት ጳጉሜ 3/1992 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ነው። አመልካች በዚያ ፍ/ቤት ከ1ኛ-5ኛ ድረስ ባሉት ተጠሪዎች መኪና አቅራቢነት A ላትር ነጭ ጋዝ ናፍታ አስጭኖ ከአሰብ ወደ ባህርዳር በሚጓጓዝበት ወቅት መኪናው በመገልበጡ የተጫነው ነዳጅ በሙሉ ስለፈሰሰ የፈሰሰውን ነዳጅ ዋጋ .78 /ሃምሳ አንድ ሺህ ሰማኒያ ዘጠኝ ብር ከሰባ ስምንት ሳንቲም/ ከነወለዱ አምስቱም ተጠሪዎች እንዲከፍሉ። 6ኛውም ተጠሪ የመኪናው ባለንብረት ስለሆነ በአንድነት እና በነጠላ በክሱ የተመለከተውን ገንዘብ ከነወለዱ እንዲከፍል ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኙን አቀራክሮ ነዳጁ የፈሰሰው ከአቅም በላይ በሆነ ከፍተኛ ሃይል ሰለሆነ ተጠሪዎቹ በሙሉ ለክሱ ሃላፊ አይደሉም በማለተ የአመልካችን ክስ ውድቅ አድርጎታል። ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የፍ/ከ/ፍ/ቤትም የስር ፍርድ ቤቱን ውሳፀነ አጽንቶታል።
25 26 የአሁኑ አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ ውሳኔ ላይ ሲሆን የአመልካተ ቅሬታ በአጭሩ ሲጠቃለል የስር ፍ/ቤቶች #ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታን; ሲተረጉሙ የህግ ስህተት ፈጽመዋል የሚል ነው ተጠሪዎችም ለቀረበው አቤቱታ መልስ አቅርበዋል።
ከ1ኛ-5ኛ ያሉት ተጠሪዎች በአንድነት በ17/10/96 በተጻፈ መልስ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ባላደራ ቦርድ በክሱ ይተካልን፣ ይህ ቢታለፍ ነዳጁ የፈሰሰው ከተባለም የቀድሞ የኢትዮጰያ ጭነት ማመላለሻ ኮርፖሬሽን ከአመልካች ጋር የማጓጓዣ ውል ስላልፈጸመ ለጥፋቱ ሃላፊ አንሆንም፣ በተመሳሳይ ጉዳይ ጭነት ማመላለሻ ኮርፖሬሽን የግለሰብ ተሽከርካሪዎች ለሚፈጽሙት ጥፋት ሃላፊነት እንደልለበት በመ/ቁ/9678 እና በመ/ቁ 6979 በሰበር ችሎት ውሳኔ ተሰጥቷል የሚል ነው።
6ኛ ተጠሪ በበኩሉ በ9/6/97 በተጻፈ መልስ ነደጁ የፈሰሰው ከፈቅም በላይ በሆነ መክንያት ስለሆነ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ አንዲጸናለት ጥቅቋል።
አመልካችም በመልስ መልሱ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እንዲሻርለት በመጠየቅ ተከራክሯል።
ከፍ ሲል የተገለጸው የግራ ቀኙ ክርክር ሲሆን ይህ ችሎትም መዝገቡን መርምሯል። ከላይ እንደተመለከተው አመልካች ያቀረበው ክስ ውድቅ የተደረገው አደጋው የደረሰው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ነው በሚል ነው። በመሆኑም፣
አደጋው የደረሰው ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ ነው? ወይስ አይደለም?
ካልሆነ ተጠሪዎች ለክሱ ሃላፊ ላሆኑ ይገባልን? የሚሉት ነጥቦች መታየት አለባቸው።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ አንድ አጓዥ በከፊል ወይም በሙሉ እቃዎች ወይም የተመዘገቡ ጓዦች ሲጠፉ ወይም ጉዳት ሲያገኛቸው ወይም የማስረከቢያው ጊዜ ቢዘገይ በሃላፊነት እንደሚጠየቅ የግን ህጉ ቁጥር 590 ሲያመለክት አጓዡ ከዚህ ሀላፊነት የሚድነው ደግሞ የጠፋው ወይም ጉዳት የደረሰው ወይም የዘገየው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ወይም በእቃው ውሳጣዊ ጉድለት ምክንያት ወይም በላኪና በተቀባዩ ጥፋት ምክንያት ሲሆን እንደሆነ የን/ህ/ቁ 591 ያመለከታል።
በመሆኑም አንድ አጓዥ የሚያጓጉዘው እቃ የጠፋ ወይም ጉዳት የደረሰበት ከሆነ ከሃላፊነት ለመዳን እቃው የጠፋው ወይም የተጎዳው ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ መሆኑን ወይም ከራሱ ከእቃው ጉድለት መሆኑን የማስረዳት ሸክም ያለበት ሲሆን ከምክንያቶቹ ውስጥም ከተያዘው ጉዳይ ጋር አግባብነት ያለው ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ የሚለው በመሆኑ ችሎቱም ይህ ሁኔታ ተከስቷል የሚባለው መቼ ነው የሚባለውን ከህጉ ጋር በማገናዘብ ተመልክቷል።
በንግድ ህጉ ውስጥ “ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ የተመለከተ ነገር ስለልለ ትርጉሙን ለማወቅ ወደ ፍ/ብ/ህጉ በተለይም ደግሞ ስለውሎች በጠቅላላው ወደሚመለከቱት ድንጋጌዎች ማምራቱ የግድ ይሆናል። በዚህ መሰረትም የፍ/ህ/ቁ 1792ን ስንመለከት ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ አለ ወይም የለም የሚባለው መቼ እንደሆነ ያሳያል።
የዚሁ ድንጋጌ ንኡስ ቁጥር 1 ከአቅም በላይ የሆነ ላመልሱት የማይቻል ሀይል ደርሷል የሚባለው ባለእዳ ባላሰበው ነገር ድንገት ደራሽ ሆኖበት ግድታውን እንዳይፈጽም ፍጹም መሰናክል በሆነ አይነት የሚያግደው ነገር ባጋጠመ ጊዜ መሆኑን ይገልጻል።
ከንኡስ ቁጥር 2 ደግሞ በአእምሮ ግምት ባለእዳው ቀደም ብሎ ላያስብበት የሚችል መሆኑ የታወቀ አንድ ድንገተኛ ደራሽ ነገር ወይም ለውሉ አፈጻጸም ከባድ የሆነ ወጪ በባለእዳው የሚደርስበት ቢሆን ከአቅም በላይ የሆነ ሃይል ነው ተብሎ እንደማይገመት መመልከት ይቻላል።
በመሆኑም በእነዚህ የሕጉ ድንጋጌዎች መሰረት ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ተከስቷል ላባል የሚችለው ባለእዳው በቅድሚያ በምንም መልኩ ላያስበው ወይም ላገምተው የማይችል ክስተት ሲፈጠር ነው። ነገር ግን ባለእዳው ሁኔታው ላፈጠር ወይም ላከሰት እንደሚችል ቀድሞ ላገምት ወይም ላያስብ እና ጥንቃቄ ላያደርግበት የሚችል ከሆነ ሁኔታው ድንገተኛ ደራሽ ነገር ቢሆን እንኳን ከአቅም በላይ የሆነ ነገር ተብሎ እንደማይገመት ማየት ይቻላል።
በአጠቃላይ ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ላባል የሚችለው ፈጽሞውኑ ላቋቋሙት ወይም ላቆጣጠሩት የማይቻል ወይም ማንኛውም ጠንቃቃ ሰው ላገምተው እና ላያስበው የማይቻለው ሁኔታ ነው። በፍ/ብ/ህ/ቁ 1793 የተዘረዘሩት ምክንያቶችም ይህንኑ የሚያሳዩ ናቸው።
ወደ ተያዘው ጉዳይም ስናመራ የስር ፍ/ቤቶች ተጠሪዎችን ከኃላፊነት ነጻ ያደረጓቸው ነዳጁ የፈሰሰው ወደ መኪናው ሮጦ የገባን ሰው ለማዳን በተወሰደ እርምጃ ስለሆነ ከአቅም በላይ በሆነ ድንገተኛ ደራሽ አደጋ ነው በማለት ነው። ነገር ግን አንድ 27 28 የመኪና አሸከርካሪ መኪያ በሚያሸከረክርበት ወቅት በመንገዱ ድንገት ሰው ላገባበት እንደሚችል፣ የተለያዩ የመጋጨት ወይም የመገልበጥ አደጋ ላያጋጥመው እንደሚችል ቀደም ብሎ ላገምት ወይም ላያስብ የሚችለው ነገር ነው። የመኪና አሽከርካሪ በሚያሽከረክርበት ጊዜ በመንገዱ ላይ ድንገት ሰው ላገባ ወይም ድንገተኛ አደጋ ላያጋጥም ይችላል ብሎ ፈጽሞ አያስብም ተብሎ አይገመትም። በመሆኑም 6ኛ ተጠሪ መኪናውን ሲያሽከረክር ድንገት ሰው ሮጦ ወደ መንገዱ መግባቱ ብቻ ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ መኖሩን አያሳይም። ስለዚህም የስር ፍ/ቤቶች ለነዳጁ መፍሰስ ምክንያት የሆነውን አደጋ ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ነው በማለት የሰጡት ትርጉም የህግ ስህተት ያለበት ነው።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ ከፍ ሲል እንደተገለጸው አንድ አጓዥ በከፊል ወይም በሙሉ እቃዎች ወይም የተመዘገቡ ጓዞች ሲጠፉ ወይም ጉዳት ሲያገኛቸው በኃላፊነት ይጠየቃል። ከኃላፊነቱ ነጻ ከሚሆንባቸው ምክንያቶች አንደኛው ደግሞ አደጋው ወይም ጉዳቱ የደረሰው ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ መሆኑ ነው። በተያዘው ጉዳይ 6ኛ ተጠሪ አጓዥ መሆኑ ክርክር አልተነሳበትም። ከላይ እንደተገለጸው ደግሞ አደጋው የደረሰው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንየት አይደለም። ስለዚህም 6ኛ ተጠሪ ለጉዳቱ በን/ህ/ቁ 590 መሰረት ኃላፊ ነው። ከ1ኛ-5ኛ ያሉትን ተጠሪዎችን ኃላፊነት ስንመለከት ተጠሪዎቹ አደጋው የደረሰው ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ ነው የማይባል ከሆነ የፈረሰው የኢትዮጵያ ጭነት ማመላለሻ ኮርፖሬሽን እቃውን ለማጓጓዝ ከአመልካች ጋር ያደረገው ውል ስለልለ ኃላፊነት የለብንም ሲሉ ተከራክረዋል። ይሁን አንጂ በስር ፍ/ቤት የፈረሰው ድርጅት የእቃ ላኪ ኮሚሲዮን እቃ አጓዡ ያለበት መብት እና ግድታ ያለበት በመሆኑ (የፍ/ህ/ቁ. 2252 (3)) ተጠሪዎቹ ለደረሰው ጉዳት በአንድነት አና በነጠላ ኃላፊ ላሆኑ ይገባል።
ከ1ኛ-5ኛ ያሉት ተጠሪዎች በተጨማሪ ያነሱት ክርክር በተመሳሳይ ጉዳት ጭነት ማመላለሻ ኮርፖሬሽን የግለሰብ ተሽከርካሪዎች ለሚፈጽሙት ጥፋት ኃላፊነት እንደልለበት ቀደም ሲል ተወስኗል የሚል ሲሆን እንደዚህ አይነት ውሳኔ ተሰጥቶ እንኳን ቢሆን በተያዘው ጉዳይ ተመሳሳይ ውሳኔ እንዲሰጥ የሚያስገድድ ይሆንም።
በመጨረሻም እነዚሁ ተጠሪዎች ወደ አክስዮንነት የተቀየርን ስለሆነ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ባለአደራ ቦርድ ተተክቶ ይከራከር ሲሉ የጠየቁ ቢሆንም ቦርዱ በኃላፊነታቸው መጠን እዳቸውን የመክፈል ግድታ ካለበት በአፈጻጸም ጊዜ እንዲተካ ላጠይቁ የሚችሉ በመሆኑ ጥያቄያቸው በዚሁ ታልፏል።
ውሣኔ ተጠሪዎች በአንድነት እና በነጠላ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ በመቶ ወለድ ጋር ለአመልካች ይክፈሉ።
አመልካች በክርክሩ ወቅት ለደረሰበት ወጪ እና ኪሣራ ዝርዝሩን በስር ፍ/ቤት አቅርቦ ያስወስን።
የፍ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ 349/87 በ3/13/92 ዓ.ም. እና የፍ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ 2317/93 በ14/3/96 ዓ.ም. የሰጧቸው ውሳኔዎች ተሽረዋል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.