ተገቢው ዳኝነት ክፍያ ሳይፈጸም በፍ/ቤት በቀጠለ ክርክር ስለሚፈፀም ስርዓት (ዋዜማ የልብስና ሸራ ምርቶች ኃ/የተ/የግ/ማህበር እእና የነገው ሰው ትምህርት አአክስዮን ማህበር)
No summary available.
የመ/ቁ. 17352 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ አበዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ አቶ መስፍን እቁበዮናስ አመልካች፡- ዋዜማ የልብስና ሸራ ምርቶች ኃ/የተ/የግ/ማህበር መልስ ሰጭ፡- የነገው ሰው ትምህርት A/ማ ለዳኝነት ስለሚከፈል ገንዘብ - ከስነ ስርዓት ውጭ ስለሚቀርብ ክስ /የግባኝ/ - የፍትሐበሕር ሥነሥርዓት ህግ ቁጥሮች 215፣ 320/2/፣ 207፣ 211/2/ አመልካች ከስር ፍ/ቤት በመ/ሰጭ እንዲከፍለው የጠየቀው ወለድ በመ/ሰጭ ላከፈለው የማገባ ቢሆንም አመልካች ክሱን ሲያቀርብ ለወለድ ጥያቄው የዳኝነት ክፍያ ያልከፈለ በመሆኑ ወለድን በሚመለከት ያቀረበው ጠያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመወሰኑና ከዚህ አንፃር የቀረበውን መስቀለኛ ይገባኘ የፍድሪል ጠቅላይ ፍ/ቤተ ውድቅ ስላደረገው የቀረበው አቤቱታ ው ሳ ኔ፡- የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትና የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በጉዳዩ የወለድ ከፍያን በሚመለከት የሰጧቸው ውሳኔዎች ተሽረዋል።
አንድ ፍ/ቤት በሰጠው ትእዛዝ ወይም ውሳኔ የስነ ስርዓት ስህተት የፈጸመ እነደሆነ ከተከራካሪ ወገኖች ጥያቄ ሲቀርብለት ወይም በራሱ አነሳሽነት ስህተቱን ማረም አለበት።
የስነ ስርዓት ስህተት ፈጽሞ እንደሆነ ጥያቄው ለፍ/ቤቱ ሳየቀርብ ይግባኝ ማቅረብ አይቻልም።
የመ/ቁ. 17352 ሐምል 28 ቀን 1997 ዓ.ም ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ አበዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ አቶ መስፍን እቁበዮናስ አመልካች፡- ዋዜማ የልብስና ሸራ ምርቶች ኃ/የተ/የግል ማኀበር መልስ ሰጭ፡- የነገው ሰው ትምህርት A/ማ
የሰበር ችሎቱ በዚህ መዝገብ የቀረበለትን ጉዳይ መርምሮአል። ለጉዳዩ መነሻ የሆነው የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁኑ አመልካች እንዲከፈለው የጠየቀው ወለድ በስር ተከማሽ ላከፍል የሚገባው ቢሆንም ከሣሹ ክሱን ሲያቀርብ ከነሐሴ 16/91 ጀምሮ ክሱ እስከቀረበበት ጥቅምት 27 ቀን 1994 ድረስ ያለውን ወለድ አስቦ ዳኝነት ስላልከፈለበት በዚህ ጊዜ ውስጥ የቀረበውን የወለድ ሂሣብ ፈ/ቤቱ አልተቀበለውም በማለት በመወሰኑ ነው። ጉዳዩ ለፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት መስቀለኛ ይግባኝ ቢያቀርብም ተቀባይነት ባለማግኙቱ ጉዳዩ ለሰበር ቀርቧል።
ጉዳዩ ለሰበር በመቅረቡ መልስ ሰጪ መልሱን፣ አመልካች ደግሞ የመልስ መልሱን በጽሁፍ አቅርበዋል። የአመልካች የሰበር ማመልከቻ በተከሣሽ እንዲከፈል የተጠየቀው ብር 562,966.74 /ምስት መቶ ስልሣ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሣ ስድስት ከሰባ አራት ሣንቲም/ የወለድ ሂማብ ዳኝነት አልተከፈለበትም ተብሎ መታለፉ የሕግ ስህተት መፈፀሙን ያሳያል የሚል ሲሆን መልስ ሰጪ በበኩሉ በስር ፍርድ ቤት የተፈፀመ መሰረታዊ የሕግ ሰህተት ተፈጽሟል የሚልበትን ምክንያት ዘርዝሮ አቅርቧል። በዚህም መሰረት ለተጠየቀው ወለድ ዳኝነት ያልተከፈለበት መሆኑ፣ በልላው ጉዳይ የተከፈለ የዳኝነት ያልተከፈለበት መሆኑ፣ በልላው ጉዳይ የተከፈለ የዳኝነተ ሂሣብ ለወለድ ጥያቄው ይያዝልኝ ማለት የማይቻል መሆኑ፣ በሰበር በቀረበው ጥያቄ የመጨረሻ ውማኔ የሰጠው ጥቅምት 5 ቀን 97 ሲሆን በዚህም ላይ የቀረበ የሰበር አቤቱታ አለመኖሩ፣ አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረበበት ጉዳይ በመስቀለኛ ይግባኝነት 17 18 ቀርቦ ውድቅ የተደረገው በመሆኑ ተቀባይነት ላኖረው እንደማይገባ በመግለጽ ተከራክሯል። የመልስ መልስም ቀርቦ ዘመዝገቡ ጋር ተያይዟል።
የሰበር ችሎቱ በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዳይ አንድ ተሟጋች መክፈል የሚገባውን የዳኝነት ሂሣብ ገቢ ሳያደርግ ክርክሩ እንደቀጠለ ፍ/ቤቱ የተገነዘበ እንደሆነ መፈፀም ያለበት ሕጋዊ ሥርዓት ምንድነው? የሚለውን ጭብጥ የማያስነሣ ሆኖ አግኝቶታል።
የሕግ ትርጉም ወደሚያሰፈልገው ዋናው ጉዳይ ከመሄዱ በፊት ፍርድ ቤቱ መልስ ሰጪ በመልሱ ላይ ያቀረባቸውን ነጥቦች ተመልክቷል።
መልስ ሰጪው በስር ፍርድ ቤት የሂሣብ ይቀናነስልኝ ጥያቄ ስላልተነሣ ለልላ ጉዳይ የተከፈለው ዳኝነት ለወለዱ ይጣጣልኝ የሚለው ጠያቄ በሰበር ላታይ አይገባውም ብሐል። ለፍርድ ቤት የሚከፈል ዳኝነት በአጠቃላይ ከሣሽ በሚጠይቀው ዳኝነት የሚታሰብ እንጂ ለእያንዳንዷ ርእስ እየተለየ የሚጠየቅ ባለመሆኑ ክርክሩ የሚያስኬድ አይደለም። ከዚህም በተጨማሪ ጉዳዩ ለፍርድ ቤት ገቢ መሆን ያለበትን ሂሣብ የሚመለከት እንጂ በሁለቱ መካከል ያለውን ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከት ባለመሆኑ በአንዱ ወገን መነሣት አለመነሣቱ የሚያመጣው ለውጥ የለም።
ከዚህ ልላ በአመልካች የቀረበው የሰበር ማመልከቻ የመጨረሻ ውሣኔ ያልተሰጠበት መሆኑን በመጥቀስ ጥያቄው ውድቅ እንዲሆን ጠይቋል። ሆኖም ለሰበር ችሎት የቀረበው ጥያቄ በመስቀለኛ ይግባኝ ለፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቦ ተቀባይነት ያጣ መሆኑን ከፍርድ ቤቱ ማኀደር ለመገንዘብ ተለናል። ስለዚህ የመጨረሻ ውሣኔ ያገኘ አይደለም ላባል አይችልም። የአሁኑ መልስ ሰጪ ይግባኝ ጠይቄ በፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሣኔ አግኝቻለሁ የሚለውም አሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበበትና ከክስ በፊት ያለውን የወለድ ሂሣብ የሚመለከት ሳይሆን ከውሣኔ በኋላ ያለውን ሂሣብ የሚመለከት መሆኑ #ተገቢው ዳኝነት ተከፍሉበት ሣይጠየቅ ወይም ወደፊት ይከፈልበት ሳይባል ክስ ከቀረበበት ጊዜ አንስቶ ዋናው ገንዘብ ተከፍሎ አለቀ ድረስ ወለድ ታስቦ ይከፈልበት በሚል መወሰኑ ትክክል ነው የምንለው አይደለም; ከሚለው መልስ ሰጪው ራሱ በመልሱ ካካተተው የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት የውሣኔ ክፍል መገንዘብ ይቻላል። ስለዚህ ሁለት የተለያዩ ጥያቄዎችንና ውሣኔዎችን በማምታታት ይኸው አሁን ለሰበር የቀረበው ጉዳይ የመጨረሻ ውሣኔ ያገኘ አይደለም በማለት የቀረበው ጉዳይ የመጨረሻ ውሣኔ ያገኘ አይደለም በማለት የቀረበው አስተያየት ተቀባይነት ያለው አይደለም።
ወደዋናው ጉዳይ ስንመለስ ይህ ችሎት የሕግ ትርጉም ያስፈልገዋል ብሎ የያዘው የሕግ ነጥብ የዳኝነት መክፈል የነበረበት ባለጉዳይ ሂሣቡን እንዳልከፈለ ፍ/ቤቱ ሲረጋገጥ ላሰጥ የሚገባው ውሣኔ ምንድነው? የሚለው ነው። አሁን በቀረበልን ጉዳይ የፍድራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች የጠየቀው የወለድ ሂሣብ ለአመልካች መከፈል ያለበት ስለመሆኑ በፍርዱ ተቀብዘለአል። ፍርድ ቤቱ ከነሐሴ 16/91 እስከ ጥቅምት 27/1994 ድረስ ያለውን የወለድ ሂሣብ ብር 562,966.74 ውድቅ ያደረገው ከሣሹ ወለድ አስበው ዳኝነት አልከፈሉበትም በማለት ነው።
ማንኛውም ለፍርድ ቤት ክስ የሚያቀርብ ሰው በሕጉ በተተመነው መሰረት የዳኝነት መከፈል እንዳለበት በሥነሥርዓት ሕጉ ቁጥር 215/1/ የተመለከተ ነው።
በመሆኑም ማንኛውም ጉዳይ ሕጉ በሚያዘው መሰረት ከመቀጠሉ በፊት የሚመለከተው የፍርድ ቤቱ ክፍል ይህ አስተዳደራዊ የሆነ ተግባር መከናወኑን ማረጋገጥ ይጠበቀበታል። በልላ በኩል በአንድ ወይም በልላ ምክንያት በሕጉ መሰረት የዳኘነት መከፈል የነበረበት ተከራካሪ ወገን ይህን ተግባር ሳይፈጽም ቢቀር ሕጉ ያሰቀመጠው መፍትሄ ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ መመልከት አስፈላጊ ነው።
የሥነ ሥርዓት ሕጉ በሙግት ሂደት የሚፈፀሙ ጉድለቶችን ለማረም የተለያዩ መፍትሄዎችን አስቀምጧል። በዋናነትና በተለምዶ በብዛት ሥራ ላይ የሚውለው ጉዳዮችን ለይግባኝ ፍ/ቤት እያቀረቡ ሰህተቶች እንዲታረሙ መጠየቅ ነው። ይህ የመፍትሄ አቅጣጫ አነድ በሙግት ሂደት የተፈፀመን ስህተት ስህተቱን ፈፀመ ለተባለው ፍርድ ቤት ሳይሆን በእርከን የበላዩ ለሆነው ልላ ፍርድ ቤት በማቅረብ የሚከናወን ሲሆን በሥነሥርዓት ሕግ ቁ. 320 እና ተከታዮቹ ቁጥሮች መሰረት የሚሰተናገድ ነው።
በሙግት ሂደት የሚከሰቱ ስህተቶችን ለማረም ግን ይግባኝ አንዱ ምናልባትም የመጨረሻው አማራጭ እንጂ ብቸኛው አማራጭ አለመሆኑን ከሕጉ አደረጃጀት ለመገንዘብ ይቻላል። በመሆኑም የኢትዮጵያ የሥነሥርዓት ሕግ ስህተቶችን ወደ የግባኝ ፍርድ ቤት መውሰድ ብቻ ሳይሆን ጉዳዩን ስህተቱን ፈፀመ ለተባለው ፍርድ ቤት ማቅረብ የሚቻልበትን ሥርዓት አስቀምጡል። ከፍትሀብሄር ሥነ ሥርዓት ሐግ ቁ.320/2/ መገንዘብ እንደሚቻለው አንድ ፍርድ ቤት የገዛ ትእዛዙን ለማሻሻል፣ ለማረም ወይም እንደገና ለማጣራት በሕግ ሥልጣን የተሰጠው ከሆነ ይግባኝ ማቅረብ የሚቻለው ይኸው ቅድመ ሁኔታ ከተሟላ ብቻ መሆኑ መረዳት ይቻላል። አግባብነት ያለው የሕጉ ክፍል እንዲህ ይላል በተሰጠው ፍርድ ወይም ትእዛዝ ላይ ይግባኝ ለማለት የሚቻል ቢሆንመ እንኳ ፍርድ ወይም ትእዛዝ የሰጠው ፍርድ ቤት በዚህ ህግ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ፍርዱን ለማረም ለማሻሻል ወይም እንደገና ለማጣራት የማችል ከሆነ ይኸው ሥርዓት አስቀድሞ ሳይፈፀም ይገባኙን ማቅረብ አይፈቀድም።
ይህ ድንጋጌ አንድ ፍርድ ቤት የሰጠውን ትእዛዝ ወይም ፍርድ ራሱ መልሶ የሚያይበት ሥርዓት መኖሩንና ቀዳሚው የመፍትሄ አቅጣጫ ማንኛውንም ጉዳይ ወደ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት መውሰድ ሳይሆን ጉዳዩን ለያዘው ፍርድ ቤት ለራሱ በማቅረብ ተሰራ የተባለው ስህተት እንዲታረም መጠየቅ መሆኑን በግልጽ ያስቀምጣል። ይህ አሰራር የይግባኝ ፍርድ ቤቶችን መጨናነቅ የሚቀንስ ከመሆኑ ባሻገር ተከራካሪ ወገኖች በአቅራቢያቸው ላለውና ጉዳዩን ለሚያውቀው ፍርድ ቤት ጥያቄያቸውን አቅርበው የተቀላጠፈ መፍትሄ የሚያገኙበትን ሁኔታ የሚያመቻች፣ ጉዳዮች ባነሳ ጊዜና ወጪ እንዲስተናገዱ እድል የሚሰጥ አሰራር ነው።
በሥነሥርዓት ሕጉ መሰረት ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው ፍርድ ቤት በዚህ ሁኔታ መልሶ ቀድሞ ያያቸውን ጉዳዮች የሚያስተናግድባቸው በርካታ መንገዶች ቢኖሩም /ለምሣል አንቀጽ 6፣ 74፣ 78፣ 358/ አሁን ከቀረበልን ጉዳይ ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነትና ተፈጻሚነት ያለው ግን በሥነሥርዓት ህጉ አንቀጽ 207 ላይ የሰፈረው መሰረተ ሃሣብ ነው። የዚሁ ሕግ ሙሉ ከፍል የሚከተለው ነው።
በህግ ተለይቶ ካልተደነገገ ወይም ፍርድ ቤቱ በልላ አኳኋን እንዲፈፀም ልዩ ተእዛዝ ካልሰጠ በቀር በዚህ ሕግ የተመለከቱትን ውሣኔዎች ወይም በውሣኔዎቹ መሰረት የሚወጣውን ደንብ ባለመፈፀም ከሥነሥርዓት ውጭ የሆነ ክስ ሲቀርብ ወይም በክሱ ውስጥ ደንብ ውጭ የሆኑ ተግባር ሲፈፀም፣ ከተከራካሪዎቹ ወገኖች አንዱ ባመለከተ ጊዜ ወይም ፍርድ ቤቱ በራሱ ሥልጣን ይህ ከሥነሥርዓት ውጪ የቀረበው ክስ በከፊል ወይም በሙሉ እንዲሰረዝ ወይም ክሱ ተሻሽሎ እንዲቀርብ በዚህም ምክንያት ስለሚደርሰው ኪሣራና ስለልላውም ወጭ ተስማሚ መስሎ የታየውን ትእዛዝ ይሰጣል።
የዚሁ ሕግ የእንግላዝኛ ቅጂ እንዲህ ይነበባል።
207 Principle Unless otherwise expressly provided by law of directed by the court, where irregularities arise from noncompliance with any provision of this code or regulation made there under the court, many of its own motion or on the application of either party, set aside such proceedings either party, set aside such proceedings either wholly or in part as irregular, or amend them or make, on such term as it thinks fit, such other order as may be appropriate.
ከዚሁ የሥነ ሥርዓት ህግ መንደርደሪያ መርህ መረዳት እንደሚቻለው በማንኛውም ፍ/ቤት በሚካሄድ ክርክር ሥነሥርዓቱን ያልተከተለ ክስ የቀረበ እንደሆነ ወይም በክሱ ሂደት ሕጉ ያስቀመጣቸው የሥነሥርዓት ደንቦች በአግባቡ ያልተፈፀሙ እንደሆነ ፍርድ ቤት ሥርዓቱ ከሚያዘው ውጪ የተሰራውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ላሰረዝ ይችላል። ይህም የሚከሃወነው በተከራካሪዎች አመልካችነት ብቻ ሳይሆን በፍርድ ቤቱ በራሱ አነሳሽነትም ጭምር ነው። በመሆኑም በዚህ መርህና ደንብ መሰረት በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ ዳኞች በሚያካሂዱት የዳኝነት ሥራ የሥነሥርዓቱን ደንብ ያልተከተለ ክንውን በራሳቸውም ሆነ በአስተዳደር ክፍሉ መፈፀሙን ሲያውቁ ወይም ሲደርሱበት ስህተቱን እንዲያርሙ ይጠበቅባቸዋል።
በፍርድ ቤቶች አካባቢ የሚታየው የተለመደው አሰራር ዳኛ የሰጠውን ትእዛዝ መቀየር አይችልም፣ መቀየር የሚችለው የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ብቻ ነው የሚል ቢሆንም ይህ በተለምዶ የዳበረው አሰራር የሥነሥርዓቱ ሕጉ ያስፈረደውን ከላይ የተጠቀሰውን መሰረታዊ መርህ የሚጻረር ነው። ሥነ ሰርዓት ነክ የሆነን ጉዳይ የሚመለከት እስከሆነ ድረስ ባለጉዳዮች ወደ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት መሄድ ሳያስፈልጋቸው ስህተቱን ለፈፀመው ፍርድ ቤት ማመልከት ይፈቀድላቸዋል፣ ዳኞችም እርግጥም ሰህተት መሰራቱን ካመኑበት ስህተቱን የማረም ሥልጣንም አላቸው። /የሥነ ሥርዓት ሕጉ ቁ.209/ ወደያዝነው ዋናው ጭብጥ ስንመለስ የከፍተኛ ፍ/ቤት ወለድን አስመልክቶ የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው ወለድ ላከፈለው አይገባም በሚል ምክንያት ሳየሆን ለፍርድ ቤት ገቢ መሆን የነበረበትን የዳኝነት ሂሣብ አልከፈለም በማለት ነው።
በሥነሥርዓት ሕጉ ቁጥር 215/1/ እንደተደነገገው ለፍርድ ቤት የሚቀርቡ ክሶች ሁሉ ዳኝነት ካልተከፈለባቸው በቀር ተቀባይነት አያገኙም። ስለዚህ የዳኘነት ሂማብ ለፍርድ ቤት ገቢ ማድረግ በክስ ሂደት መከናወን ያለበት ተግባር ነው። የዳኝነት ክፍያ መጠናቀቅ ያለበት ክሱ ሲቀርብ እንደሆነ ከድነጋጌው ይዘት መገንዘብ ይቻላል።
በመሆኑም ይህን ሥራ እንዲያከናውኑ የተመደቡ የሚመለከታቸው የፍርድ ቤቱ ክፍሎች ይህ ህጉ የሚጠይቀውን ሥርዓት መከናወን ይጠበቅባቸዋል። በልላ በኩል ማከናወን ያለበት ይህ ተግባር ሳይከናወን ቀርቶ ክሱ ለፍርድ ቤት /ለዳኛ/ ቢቀርብ ክሱ ከሥነ ሥርዓት ውጪ የቀረበ /procedurally irregular/ ይሆናል። በፍትሐብሄር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 207 እንደተደነገገው የሥነሥርዓት ሕጉን ወይም በሱ መሰረት የሚወጡ ደንቦችን በመጣስ የቀረበን ከሥነሥርዓት ውጪ የተፈፀመን ተግባር የማቃናት ሃላፊነት ለፍ/ቤቱ የተሰጠ በመሆኑ የሥነሥርዓት ግድፈት የተፈፀመ መሆኑ ሲታወቅ በዚህ መሰረት መከናወን ይኖርበታል። በዚህ መሰረት ያልተከፈለ የዳኝነት ክፍያ ካለ የክሱን ሂደት አስመልከቶ የተፈፀመ የሥነ ሥርዓት ግድፈት መኖሩን ስለሚያመለከት ዳኞች በተጠቀሰው ሕግ መሰረት ግድፈቱን በማስተካከል ያልተከፈለ ሂሣብ ካለ ተሰልቶ እንዲከፈል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
በያዝነውም ጉዳይ የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማድረግ የነበረበት ይህንን ነው። አመልካች ወለድ እንዲከፈለው ጠይቋል። ይኸው የአመልካች ጥያቄ በሕግ ተቀባይነት ያለው መሆኑንም ፍ/ቤቱ ተቀብሎታል። በመሆኑም ያልተከፈለ ሂሣብ ካለ በሥነሥርዓት ሕጉ ቁጥር 207 መሰረት ማስከፈል ሲገባው ይህን አልፎ የቀረበውን 21 22 ክስ በዚህ ምከንያት ውድቅ ማድረጉ ሕጉ ያስቀመጠውን የሙግት አመራር የተከተለ አይደለም። በመሆኑም ይህ ፍርድ ቤት አልተቀበለውም።
የፍተሀብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 211/2/ #ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ይግባኝ በተባለበት ጉዳይ ላይ የተፈፀመውን ማንኛውንም የሥነ ሥርዓት ጉድለት በራሱ አስተያየት ላያርም ይችላል; በማለት ይደነግጋል። በዚህም መሰረት የሰበር ችሎት የዳኝነትን አከፋፈል አስመልክቶ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፈፀመውን የሥነ ሥርዓት ጉድለት ማቃናት እንዳለበት አምኖአል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.