በስነ-ሥርዓት ህጉ የጊዜ ገደብን በሚመለከት የተቀመጡ ድንጋጌዎች ፍርድ ቤት በራሱ አአነሳሽነት ተፈፃሚ ስለማድረጉ (ጋዲሴ ኢኢረጌ እእና ወርቅ አአንጥፉ በቀለ)
No summary available.
የመ/ቁ. 17361 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ ወ/ሪት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- ወ/ሮ ጋዲሴ ኢርጌ መልስ ሰጭ፡- ወ/ሮ ወርቅአንጥፉ በቀለ በከሣሽነት ወይም ተከሣሽነት በሙግት ተካፋይ ሰለመሆን - ስለተከራካሪ ወገን መሞትና ስለክሱ ያለመቋረጥ - ስለ ጊዜ አወሳሰንና አቆጣጠር- የፍትሐበሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 49 - ስለ ግድታዎች መቅረት - ሰለ ይርጋ - የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1856 አመልካች ከስር ከሳሽ የነበረችውን ወ/ሮ ብሪቱ ብሩን ተክታ ለመከራከር ያቀረበችው ጥያቄ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ቁጥር 49 የተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ካለፈ በኋላ የቀረበ መሆኑን በመግለጽ የስር ፍርድ ቤት ጥያቄዋን ውድቅ በማድረጉ እና የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይግባኙን ባለመቀበሉ መልስ ሰጭ ባነሳችው ክርክር ፍርድ ቤቶቹ ክሱን ውድቅ በማድረጋቸው የቀረበ አቤቱታ ው ሳ ኔ፡- የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ጸንቷል።
በሥረ ነገር /Substantive/ ህጎች የተደነገጉ የይርጋ ደንቦች በሥነ ሥርዓት ሕጎች ከተደነገጉት የጊዜ ገደቦች የተለዩ ናቸው።
በስነ ስርዓት ህጎች በግልጽ የሰፈረን ጊዜ ሳይጠብቅ የሚቀርብን ጥያቄ ፍ/ቤት በራሱ አነሳሽነትም ቢሆን ውድቅ ማድረግ አለበት።
11 12 የመ/ቁ. 17361 ሐምል 25 ቀን 1997 ዓ.ም ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ ወ/ሪት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- ወ/ሮ ጋዲሴ ኢርጌ መልስ ሰጭ፡- ወ/ሮ ወርቅአነጥፉ በቀለ
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዳይ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ የተመለከቱ የሥነሥርዓት ደንቦች አፈጻጸምን የሚመለከት ነው። ጉዳዩ ላቀርብ የበቃው አመልካች ከስር ከሣሽ የነበረችውን ወ/ሮ ብሪቱ ብሩን ተክታ ለመከራከር ያቀረበችው ጥያቄ የሥር ፍርድ ቤት በፍትሀብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 49 የተጠቀሰውን የጊዜ ገደብ ካለፈ በኋላ የቀረበ መሆኑን በመግለጽ ጥያቄዋን ውድቅ በማድረጉ ነው።
ጉዳዩን በይግባኝ ያየው የከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኙን ሳይቀበለው ቀርቷል። የአሁን አመልካች የሰበር አቤቱታ ዋነኛ የቅሬታ ነጥብም ፍርድ ቤቱ በፍትሐብሕር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 49(2) የተጠቀሰውን የጊዜ ገደብ ማንም ተከራካሪ ወገን ሳያነሳው ፍርድ ቤቱ በራሱ አነሣሽነት ተፈጻሚ ማድረጉ ሕጉ ይርጋን በማስመልከት ያስቀመጠውን ሥርዓት የሚጥስ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት ተብሎ ይሻልኝ የሚል ነው።
የሰበር ችሉቱ ጉዳዩ በሰበር እንዲታይ በመወሰኑ መልስ ሰጪ በጉዳዩ ላይ መልስ እንዲያቀርብ ተደርጓል። የመልሱ መሰረታዋ ይዘት የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ምንም የሕግ ስህተት ሰለልለበት ላፀና ይገባዋል የሚል ነው። አመልካቿ የመልስ መልስ አቅርባለች። ይዘቱ ከሰበር ማመልከቻው የተለየ አይደለም።
በዚህ መዝገብ የቀረበው አቤቱተ በሥረ ነገር ሕጎች /Substantive Laws/ የተደነገጉ የይርጋ ደነቦች በሥነሥርዓት ሐጎች ከተደነገጉት የጊዜ ገደቦች ጋር ተመሳሳይ ናቸው ወይስ አይደሉም? በሥነ ሥርዓት ሕግ ውስጥ የሚገኙትን የጊዜ ገደቦች ፍርድ ቤቶች በራሳቸው አነሳሽነት ተፈጻሚነታቸውን ላከታተሉ ይችላሉ ወይስ እንደሥረነገር የይርጋ ህግ በተከራካሪ ወገን ካልተነሱ እንደተተው ይቆጠራል የሚሉትን የሕግ ነጥቦች የማያስነሳ ሆኖ አግኝተነዋል።
ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ መረዳት እንደቻልነው የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች ቀደም ብላ ክስ መስርታ የነበረችውን ወ/ሮ ብሪቱ ብሩን ተክታ የፍትሐብሄር ክሱን በወራሽነት እንድትቀጥል ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው ጥያቄው የቀረበው የፍትሀብሄር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 49 እንደሚያዘው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ አልቀረበም በማለት ነው።
የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 49(1) ከሣሽ ሲሞቱ የክሱ መብት ለልላ የሚተላለፍ የሆነ እንደሆነ የሟቹ ንብረት አስተዳዳሪ ተተክቶ ክሱን ላቀጥል እንደሚችል የሚፈቅድ ሲሆን የዚሁ ቁጥር ንኡስ ቁጥር ሁለት #ክሱን ለመቀጠል መብት አለን የሚሉት ወገኖች ዋናው ከሣሽ ወይም ከሣሾች በሞቱ በአንድ ዓመት ውስጥ ክሱን ለመቀጠል እንዲፈቀድላቸው ሳያመለክቱ የቀሩ እንደሆነ የተጀመረው ክርክር ውድቅ ይሆናል; በማለት ይደነግጋል።
የፍትሀብሕር ሥነሥርዓት ሕግ የሙግትን ሂደት ለመከታተል የሚያስችሉ የተለያዩ የጊዜ ገደቦችን አስቀምጧል። ይኸው ሕግ ያስቀመጣቸውን የጊዜ ገደቦች አፈጻጸም በሚመለከትም በሥነሥርዓት ሕጉ ምእራፍ ሰባት በርካታ ድንጋጌዎችን አስፍሮአል። የሕጉ ቁጥር 192 #በአንድ ክርክር ላይ መፈፀም ወይም መደረግ የሚገባው ነገር ሲኖርና ይህም የሚፈፀምበት ጊዜ በሕግ ያልተወሰነ ሲሆን የነገሩን አካባቢ ሁኔታ በሚመለከት ፍርድ ቤቱ ተገቢ መስሎ የሚተየውን ጊዜ ይወስናል; በማለት ይደነግጋል።
ይህ ድንጋጌ በሙግት ሂደት የሚከናወኑ ተግባራት በሕግ በተቀመጠው አላያም ፍርድ ቤቱ በሚወስነው የጊዜ ገደብ ውስጥ መከናወን የሚጠበቅባቸው መሆኑን የሚያመለክት ነው። የዚሁ ሕግ ቁጥር 195 #በዚህ ሕግ በቁጥር 196 የተመለከተው ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ አንድ ነገር እንዲፈፀም ከተወሰነው ጊዜ በኋላ ቢፈፀምም እንዳልተፈፀመ ሆኖ ይቆጠራል; በማለት በተወሰነ የጊዜ ገደብ መፈፀም ያለባቸው ተግባሪት ሕጉ ወይም ፍ/ቤቱ ባስቀመጠው ጊዜ ውስጥ ከተከናወኑ ብቻ ሕጋዊ ውጤት ላያስከትሉ እንደሚችሉ ይደነግጋል። የሥነ ሥርዓት ሕጎች ዋነኛ ዓላማ ለፍ/ቤት የሚቀርቡ ክርክሮች ባነሰ ወጪ በተቀላጠፈና ፍትሃዊ በሆነ ሥርዓት እልባት እንዲያገኙ ማድረግ ነው። በመሆኑም በሥነሥርዓት ህጎች የሰፈሩ የጊዜ ገደባች አፈጻጸም በአንድ ጉዳይ ካሉት ተከራካሪዎች ባሻገር የልሎች ተከራካሪዎች ጥቅም፣ በፍርድ ቤት መኖር 13 14 ያለበትን የሙግት አመራርና አጠቃላይ የሀብትና የጊዜ አጠቃቀምን የሚመለከቱ ናቸው። የጊዜ ገደቦች አለመከበር ለመዘግየት፣ ለጉዳዮች መከማቸትና መጨናነቅ ምክንያትም ስለሚሆን የሚጎዳው በአንድ ሙግት የሚሳተፉትን ብቻ ሳይሆን የልሎች የፍርድ ቤት ተጠቃሚዎች መብትና ጥቅምም ይነካል። ይህ ሁኔታ እንዳይፈጠር የሙግት ሂደት ሥርዓት እንዲይዝ ማድረግ ደግሞ ከተከራካሪዎችም የሚጠበቅ ቢሆንም በዋናነት ግን የፍርድ ቤቱ ሃላፊነት ነው። ይህን ሃላፊነት እንዲወጣ ከሚያደርጉት መንገዶች አንዱ ደግሞ በሰነ ሥርዓት ሕጉ የሰፈሩት የጊዜ ገደቦች በአግባቡ መፈፀማቸውን መከታተልና ያልተፈፀሙ ሆነው ሲገኙ ደግሞ ህጉ እንደሚያዘው ተመጣጣኝ የሆነ እርምጃ መውሰድ ነው።
በሥነሥርዓት ሕጉ የሰፈሩ ጊዜን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች ይዘትና ዓላማ ይርጋን አስመልከቶ በፈትሀብሄር ሕግ ቁጥር 1856/2/ ከሰፈረውና የይርጋ ጉዳይ በተከራካሪዎች ካልተነሣ በፍርድ ቤት አይነሳም ከሚለው ሕግ የተለየ ነው።
በፍትሐብሕር ሕግ የሰፈረው የይግርጋ ሕግ ዋነኛ ዓላማ የተዋዋዮችን ጥቅም መጠበቅ ነው። የዚህ መብት ተጠቃሚ የሆነ ተከሣሽ ይርጋውን ካላነሣም የሚጎዳው እሱ ብቻ ነው። ስለሆነም ተዋዋይ ወገን የተወውን መብት ፍርድ ቤት በራሱ አነሣሽነት እንዲያነሣው አይፈቀድም። በሥነሥርዓት ሕጉ የተቀመጡ የጊዜ ገደቦች መከበር አለመከበራቸውን ግን ፍርድ ቤቱ የመከታተል ሃላፊነት አለበት። በተከራካሪ ወገን ባይነሣ እንኳን በሥነ ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 195 እንደተደነገገው ጊዜው ካለፈ በኋላ የተከናወነው ነገር ሁሉ እንዳልተፈፀመ ሆኖ ስለሚቆጠር የሥነሥርዓት የጊዜ ገደቦች ተሟጋቾችን ብቻ ሳይሆን ፍርድ ቤቱንም ጭምር የሚመለከቱ ናቸው።
በመሆኑም በሥነሥርዓት ሕጉ በግልጽ የሰፈረው የጊዜ ገደብ ካለኝ በኋላ የሚቀርብን ማንኛውንም ጉዳይ ፍርድ ቤቱ በራሱ አነሳሽነትም ቢሆን ውድቅ ማድረጉ ትክክለኛው አካሄድ ነው።
አሁን በቀረበልን ጉዳይ የአሁኗ አመልካች ጥያቄዋን ለፍርድ ቤቱ ያቀረበችው የቀድሞዋ ተከራካሪ የወ/ሮ ብሪቱ ብሩ ወራሽ መሆንዋን ካረጋገጠች ከ3 ዓመት በኋላ ነው። ከመዝገቡ ለመረዳት እንደተቻለው የወራሽነት ውሣኔ ያገኘችው ሐምል 15/91 ሲሆን ለፍርድ በቱ ጥያቄዋን ያቀረበችው ደግሞ ጥር 20/1994 ነው። ይህም የሥነ ሥርዓት ሕጉ ቁጥር 49 ያስቀመጠው የአንድ አመት የጊዜ ገደብ ማለፉን የሚያረጋግጥ ነው። በሕግ የሰፈረውን ጊዜ ገደብ ያልጠበቀ ነገር የተሟጋችን ተቃውሞ ሳየጠብቅ ፍርድ ቤቱ ራሱ ውድቅ ማድረጉ ደግሞ ትክክለኛ የጉዳይ አመራር እንጂ ስህተት መፈፀሙን የሚያመለክት አይደለም።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.