በህግ ግምት የሚሸፈንን የፍሬ ነገር ክርክር በሚመለከት ተከራካሪ ወገኖች ባያነሱትም ፍርድ ቤቱ ግምቱን ተፈፃሚ ስለማድረጉ /ጳውሎስ ሩምቾ እእና ጫልቱ መርዳሳ/
No summary available.
የመ/ቁ. 15493 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ አበዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ ወ/ሪት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- አቶ ጳውሎስ ሩምቾ መልስ ሰጭ፡- ወ/ሮ ጫልቱ መርዳሳ የውል ግደታዎች መቅረት - ስለ ይርጋ - የውልን ጉዳይ ስለሚመለከት ማስረጃገንዘቡ እንደተከፈለ የሚያስቆጥሩ የህላና ግምቶች - የፍትሐብሕር ህግ ቁጥሮች 1845፣ 2024 የOሮሚያ ብሕራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት አመልካች እንዲከፈለው የጠየቀው የጥብቅና አበል በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024 /ለ/ መሰረት እንደተከፈለ ስለሚቆጠር የሥር ተከሣሾች በአመልካች የተጠየቀውን ገንዘብ ላከፍሉ አይገባም በማለት ልሎች ፍ/ቤቶች የሰጡትን ውሣኔ በመሻሩ የቀረበ አቤቱታ ውሳኔ፡- የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት የሰጠው ውሳኔ ጸንቷል።
የሐላና ግምት ድንጋጌዎች ከይርጋ ደንብ ድንጋጌዎች የተለዩ ናቸው።
በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2024 በተደነገገው የሕግ ግምት ተጠቃሚ ያልሆነ ወገን /ተከሣሽ/ ከፍያውን በከፊል መክፈሉ ግምቱን በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2025 /1/ መሰረት ቀሪ አያደርግም።
ሐምል 29 ቀን 1997 ዓ.ም የመ/ቁ.15493 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሥሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ ዓለሙ ወ/ሪት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- አቶ ጳውሎስ ሩምቾ መልስ ሰጪ፡- ወ/ሮ ጫልቱ መርዳሳ
በዚህ መዝገብ የሰበር አቤቱታ የቀረበው የOሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት አመልካች እንዲከፈለው የጠየቀው የጥብቅና አበል በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024/ለ/ መሰረት እንደተከፈለ ስለሚቆጠር የሥር ተከሣሾች በአመልካች የተጠየቀውን ገንዘብ ላከፍሉ አይገባም በማለት ልሎች ፍ/ቤቶች የሰጡትን ውሣኔ በመሻሩ ነው።
አመልካች ባቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻነት ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ቀርቦ እንዲታይ በመወሰኑ መልስ ሰጪም በጉዳዩ ላይ ያላትን የጽሁፍ መልስ አቅርባለች።
አመልካች የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት መሰረታዊ የሕግ ስህተት ፈጽሟል የሚለው /1/ ከጥብቅና አበሉ ውስጥ የመጨረሻ ክፍያ የተፈፀመው ሰኔ 1990 ዓ.መ በመሆኑ ክስ እስከቀረበበት ታህሣሥ 18 ቀን 1992 ዓ.ም በፍትሐብሄር ሕግ ቁ.2024 /ለ/ የተጠቀሰው የሁለት ዓመት የጊዜ ገደብ አላለፈም /2/ መልስ ሰጪዎች ከፊል እዳውን በመፈፀማቸው እዳውን እንዳመኑ ስለሚቆጠር በ2024 የተቀመጠው የህግ ግምት በ2025/1/ መሰረት ቀሪ ሆኖአል። /3/ የጥብቅና ውሉ በጽሁፍ የተደረገ በመሆኑ የይርጋ ጊዜው መታሰብ ያለበት በ10 ዓመት እንጂ በ2024 መሰረት በሁለት ዓመት አይደለም የሚሉትንና ልሎችንም ተመሳሳይ ክርክሮች በማቅረብ የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት የሰጠው ውሣኔ እንዲፀናላት ጠይቃለች።
አመልካች በመልስ ሰጪ ላይ ጥር 1 ቀን 1992 ዓ.ም ክስ የመሰረተው ጥቅምት 7 ቀን 1988 ዓ.ም በአመልካችና በመልስ ሰጪ መካከል የተመሰረተውን የጥብቅና አገልገሎት ውል መሰረት በማድረግ ነው። የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር 9 10 ችሎት ተዋዋዮቹ በውላቸው ላይ ለጥብቅና ውሉ ምክንያት የሆነው ቤት መልስ ሰጪ እጅ በገባ በሁለት ወር የጥብቅና ክፍያ መጠናቀቅ እንዳለበት ስለሚገልጽና ቤቱ ሕዳር 1988 መልስ ሰጪ እጅ የገባ በመሆኑ ክስ የቀረበበት የገንዘብ መጠን ክስ በቀረበበት ጊዜ ከሁለት ዓመት በላይ ስለሆነው በ2024 መሰረት እንደተከፈለ ይቆጠራል ብሐል።
ለዚህ ለሰበር ለቀረበው ጉዳይ ምክንያት የሆነው እዳ መከፈል ከነበረበት ሁለት ዓመት በላይ እንደሆነው በስር ፍርድ ቤት ተረጋግጦአል። ለጉዳዩ አግባብነት ያለው የፍ/ብ/ሕ/ቁ.2024 ሲሆን በዚህ ድንጋጌ መሰረት በሁለት ዓመት ውስጥ ያልተከፈለ እዳ እንደተከፈለ እንደሚቆጠር በዚህ ሰበር ችሎት በመ.ቁ.17068 ትርጉም ተሰጥቶበታል። የጥብቅና አበል ክፍያን የሚመለከተው የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2024/ለ/ም አንዱ የድንጋጌው አካል በመሆኑ በተጠቀሰው ትርጓሜ መሰረት እንደተከፈለ የሚቆጠር ነው። ስለዚህ የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በዚህ የፈፀመው የህግ ስህተት የለም።
አመልካች የሕግ ግምትና የይርጋ ህግን በማመሳሰል ጉዳዩ በፍ.ብ.ሕ.ቁ.1845 እንዲታይለት ቢጠይቅም የተያዘው ጉዳይ የክፍያ ግምት እንጂ የይርጋ ጉዳይ ባለመሆኑ ቅሬታው ተቀባይነት የለውም። የክፍያ ግምት ውሉ በጽሁፍ የተደረገ ሲሆን ተፈጻሚ አይሆንም የሚል ህግ ባለመኖሩ አመልካች ውላችን በጽሁፍ ስለሰፈረ 2024/ለ/ ተፈጻሚ ላሆንብኝ አይገባም ያለው ተቀባይነት የለውም። መልሰ ሰጪ በከፊል የጥብቅና አበል መክፈላቸውም ቢሆን አሁን ክስ የቀረበበትን ቀሪውን የጥብቅና አበል ማመናቸውን አያመለክትም። በመሆኑም የሕጉን ግምት ተፈጻሚነት በ2025/1/ መሰረት ቀሪ ለማድረግ በቂ ምክንያት አይደለም። በመሆኑም የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ክስ የቀረበበት ብር 71,000 /ሰባ አንድ ሺህ/ ሁለት ዓመት ካለፈው በኋላ የተጠየቀ ስለሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2024/ለ/ መሰረት እንደተከፈለ ይቆጠራል በማለት የሥር ፍ/ቤቶችን ውሣኔ መሻሩ ሕጉን በትክክል ተፈፃሚ ማድረጉን እንጂ የህግ ስህተት መፈፀሙን አያመለክትም።
ውሣኔ
የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችሎት በመዝገብ ቁ.00253 በ20/7/96 የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ።
የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የመ/ቁ. 17361 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ አለሙ ወ/ሪት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- ወ/ሮ ጋዲሴ ኢርጌ መልስ ሰጭ፡- ወ/ሮ ወርቅአንጥፉ በቀለ በከሣሽነት ወይም ተከሣሽነት በሙግት ተካፋይ ሰለመሆን - ስለተከራካሪ ወገን መሞትና ስለክሱ ያለመቋረጥ - ስለ ጊዜ አወሳሰንና አቆጣጠር- የፍትሐበሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 49 - ስለ ግድታዎች መቅረት - ሰለ ይርጋ - የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1856 አመልካች ከስር ከሳሽ የነበረችውን ወ/ሮ ብሪቱ ብሩን ተክታ ለመከራከር ያቀረበችው ጥያቄ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ቁጥር 49 የተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ካለፈ በኋላ የቀረበ መሆኑን በመግለጽ የስር ፍርድ ቤት ጥያቄዋን ውድቅ በማድረጉ እና የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይግባኙን ባለመቀበሉ መልስ ሰጭ ባነሳችው ክርክር ፍርድ ቤቶቹ ክሱን ውድቅ በማድረጋቸው የቀረበ አቤቱታ ው ሳ ኔ፡- የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ጸንቷል።
በሥረ ነገር /Substantive/ ህጎች የተደነገጉ የይርጋ ደንቦች በሥነ ሥርዓት ሕጎች ከተደነገጉት የጊዜ ገደቦች የተለዩ ናቸው።
በስነ ስርዓት ህጎች በግልጽ የሰፈረን ጊዜ ሳይጠብቅ የሚቀርብን ጥያቄ ፍ/ቤት በራሱ አነሳሽነትም ቢሆን ውድቅ ማድረግ አለበት።
11 12
No topics extracted.