የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የዳኝነት ስልጣን የሰራተኛ ቅነሳ ጉዳይን በሚመለከት ስለሚነሳ ክርክር /የኬኬ ብርድ ልብስ ፋብሪካ መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር እእና የኬኬ ጨርቃ ጨርቅ ኢኢንዱስትሪ/
No summary available.
የመ/ቁ. 18180 ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሥሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ ዓለሙ አቶ መስፍን እቁበዮናስ አመልካች፡- የኬ.ኬ ብርድ ልብስ ፋብሪካ መሰረታዊ የሰራተኞች ማህበር መልስ ሰጪ፡- የኬ.ኬ ጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ስለ ስራ ክርክር- የስራ ክርክር ችሎቶች ሰልጣን - የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ስልጣን /የሰራተኞች ቅነሳ ጉዳይ በሚመለከት የሚነሳ የስራ ክርክር ለማየት/ -የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ.42/85 አንቀጽ 138/1/፣ 147 አመልካች በሰራተኛ ማህበራችን አማካኝነት የተወሰደብን የቅነሳ እርምጃ ህገ ወጥ በመሆኑ የተቋረጠብን ክፍያ ተሰጥቶን ወደ ስራችን እንመለስ በማለት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ያቀረቡትን ጥያቄ ቦርዱ በመቀበል የተደረገው ቅነሳ በአዋጅ ቁ.42/85 አንቀጽ 28 እና 29 ድንጋጌዎችን የሚጥስ በመሆኑ አመልካቾች ወደ ስራ ላመለሱ ይገባል በማለት የሰጠውን ውሳኔ ከስልጣኑ ውጭ የሰጠው ነው በሚል የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ስለሻረው የቀረበ አቤቱታ ው ሣ ኔ ፡- የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የመዳኘት ስልጣን የተሰጠው የወል የስራ ክርክር ጉዳዮችን የሚመለከቱ ክርክሮችን ሲሆን የስራ ክርክር ችሎቶች ደግሞ የግል የስራ ክርክሮችን እንዲዳኙ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል።
ህጉ የስራ ክርክር ጉዳዮችን የወል ወይም የግል ብሎ ለመለየት የተከራካሪ ሰራተኞችን ቁጥር እንደ መስፈርት መውሰድ እንዳለበት አያመላክትም።
ከአጠቃላይ የህጉ መንፈስ እና ድንጋጌዎች በመነሳት አንድ የስራ ክርክር ጉዳይ የወል ነው የሚባለው ጉዳዩ በጋራ የሆነ የሰራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አሉታዊ ሆነ አዎንታዊ ውጤት የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ ብቻ ሲሆን አንድን የስራ ክርክር ጉዳይ የግል የሥራ ክርክር ጉዳይ የሚያደርገው ደግሞ ጉዳዩ ከግል አልፎ በጋራ መብት ላይ የሚያመጣው ለውጥ የልለ እንደሆነ ነው።
የሰራተኛ ቅነሳ ጉዳይ የጋራ በሆነ የሰራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያለው በመሆኑ የወል የስራ ክርክር ጉዳይ ነው። ጉዳዩን የማየት ስልጣንም የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ነው።
የአሰሪና ሰራተኛ ፍ/ቤት ቦርዱ የህግ ስህተት ፈጽሟል ብሎ ሲያምን ጉዳዩን ከመመሪያ ጋር ወደ ቦርዱ ከመመለስ አልፎ የቦርዱ ውሳኔ መሻር አይችልም።
1 2 የመ/ቁ.18180 ሐምል 29 ቀን 1997 ዓ.ም ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍሥሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ/ሮ ስንዱ ዓለሙ አቶ መስፍን እቁበዮናስ አመልካች፡- የኬኬ ብርድ ልብስ ፋብሪካ መ/ሰ/ማ /56/ ሰዎች ወኪል ሰይድ ሀሚድ ቀረበ ተጠሪ፡- የኬኬ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ የቀረበ የለም መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገቡ የተያዘው ክርክር ከአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ የተጀመረ ነው። ጉዳዩ አሰሪ የሆነው የአሁን ተጠሪ ሰራተኛ በሆኑት በአሁን አመልካቾች ላይ የወሰደውን የቅነሣ እርምጃ የሚመለከት ነው።
አመልካቾች በሰራተኛ ማኀበራቸው አማካኝነት የተወሰደብን የቅነሣ እርምጃ ሕገ ወጥ በመሆኑ የተቋረጠብን ክፍያ ተሰጥቶን ወደ ሥራችን እንመለስ ሲሉ በተጠሪው ላይ ክስ መስርተዋል። ተጠሪም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የቅነሣውን ተገቢነት ይገልጻል የሚለውን መልስ አቅርቦ ተከራክሯል። ክሱ የቀረበለት ቦርድ ደግሞ የተደረገው ቅነሣ አዋጅ ቁ. 42/85 አንቀጽ 28 እና 29ን የሚጥስ በመሆኑ አመልካቾቹ በአንቀጽ 42/2/ መሰረት ወደ ሥራቸው ላመለሱ ይገባል በማለት ወስኗል።
ከዚህ ውሣኔ ላይ በተጠሪ አማካኝነት በመ/ቁ.30769 ይግባኝ የቀረበለት የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በበኩሉ ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ቦርዱ ይህን የማየት ሥልጣን የለውም በማለት ከፍ ሲል የተጠቀሰውን የቦርዱን ውሣኔ ጥቅምት 25/1997 ዓ.ም ሽሮታል።
በመቀጠል አመልካቾች ይህ የፍ/ቤቱ ውሣኔ የአዋጅ ቁ.42/85 አንቀጽ 147/2ን እና 154/2ን የሚጥስ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነውና ይሻርልን በማለት አቤቱታቸውን ለዚህ ችሎት አቅርበዋል። ተጠሪም የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት ላያገኝ አይገባም የሚልበትን ምክንያት የሚዘረዝር መልስ አቅርቦ ተከራክሯል።
ይህም ችሎት ክርክሩን ላያስነሣ በቻለው አወዛጋቢ የህግ ነጥብ ላይ ብቻ በማተኮር መዝገቡን መርምሯል። በዋነኛነት ላፈቱ የሚገባቸው የነገሩ ጭብጦችም፡- 1ኛ. የሰራተኛ ቅነሣን አስመልከቶ የቀረበውን የህን ክርክር የመዳኘት ሥልጣን የማነው? የፍርድ ቤት ነው? ወይስ የቦርድ?
2ኛ. ፍ/ቤት በቦርድ የተሰጠን ውሣኔ ለመሻር ሥልጣን አለው? የሚሉት መሆናቸውን ተገንዝቧል።
ለመጀመሪያው ነጥብ ምላሽ የማግኘቱ ጉዳይ ስለ ሰራተኛ ቅነሣ፣ ስለ ቦርድ እና ስለ ፍርድ ቤት ሥልጣን የሚገልጹትን የአዋጅ ቁ. 42/85 ድንጋጌዎችን ተመስርቶ ጭብጡን መመርመርን ይጠይቃል። ቦርድ ላቀርቡ የሚገባቸው ጉዳዮች ፍ/ቤት ላቀርቡ ከሚገባቸው የሚለዩበትን ምክንያት መረዳትን ይፈልጋል። በዚህ ረገድ ግንዛቤ እንድናገኝ የሚያደርገን ደግሞ ስለ ቦርድ ሥልጣን የሚደነግገው የአዋጅ ቁ.147/1/ እና ስለ ፍ/ቤት ስልጣን የሚደነግገው የአዋጁ አንቀጽ 138/2/ ይሆናል።
ስለ ቦርድ ሥልጣን ከተደነገገበት የአዋጅ ቁ.42/85 አንቀጽ 147/1/ ውስጥ ለዚህ ጉዳይ አግባብነት የሚኖረው በንኡስ አንቀጽ /1/ /ሀ/ ላይ ቦርዱ በአንቀጽ 142/1/ ላይ የተመለከቱትን የሥራ ክርክሮች የመዳኘት እና ተከራካሪዎቹን የማስታረቅ ሥልጣን አለው በሚል የተመለከተው የሕጉ ክፍል ነው። እነዚህ ሁለት ድንጋጌዎች ተጣምረው ሲነበቡ ቦርዱ በአንቀጽ 142/1/ ስር በተዘረዘሩትና በልሎች የወል የሥራ ክርክሮች ላይ ውሣኔ የመስጠት ሥልጣን እንደተሰጠው መገንዘብ ይቻላል። በልላ በኩል ደግሞ በአዋ አንቀጽ 138/1/ የተዘረዘሩትንና መሰል የግል የሥራ ክርክሮችን የመዳኘት ሥልጣን ለፍ/ቤት መስጠቱን ከዚህ ድንጋጌ መረዳት ይቻላል።
የወል የሥራ ክርክሮች ለቦርድ፤ የግል የሥራ ክርክሮች ደግሞ ለፍ/ቤት የሚቀርቡ ናቸው ማለት ብቻውን ግን ሁለቱ ተቋማት በዚህ ረገድ ያላቸውን የዳኝነት ሥልጣን ክፍፍል በግልጽ እንድንለየው የሚያደርገን አይደለም። ይልቁንም የወል የሥራ ክርክር ማለት ምን ማለት ነው? የግል የሥራ ክርክር ማለትስ ምን ላሆን ይገባል?
የሥራ ክርክሮችን በምንና እንድት የወል ወይም የግል የሥራ ክርክር ብለን ልንመድባቸው እንችላለን? የሚሉና ልሎቹንም መሰል ጥያቄዎችን እንድናነሣ የሚያደርገን ነው። ለእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠታችን ደግሞ የሚቀርቡ የሥራ 3 4 ክርክሮችን ከየትኛው እንደምንፈርጃቸው የሚያመለክተንና በዚህ ተጨባጭ ጉዳይ ለተያዘውም የመጀመሪያ ጭብጥ መፍቻ እንድናገኝለት የሚረዳን ነው።
ስለ የወል እና የግል የሥራ ክርክር አይነቶች የአዋጅ ቁ.42/85 ለወልም ሆነ የግል የሥራ ክርክር የሰጠው ትርጓሜ የለም። የሥራ ክርክር በዚህ አዋጅ የተተረጎመ ቢሆንም ትርጓሜው የወልና የግል የሥራ ክርክርን እንድንለይ የሚያስችለን አይደለም። ስለሆነም በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት በግርድፉ ለማስቀመጥ ልላ መለኪያ እንድናበጅ የሚጠይቀን ነው።
እንደሚታወቀው ከአሰሪ ጋር የሚደረግ የሥራ ክርክር በሰራተኞች ማኀበር ወይም ቁጥራቸው ከአንድ በላይ በሆነ ሰራተኞች ወይም በአንድ ሰራተኛ ብቻ የሚካሄድ ነው። የወል የሚለው ቃል አገላለጽ የጋራ የሆነ ጉዳይ መኖሩን ለማመልከት ያህል የሚበቃ መሆኑም እርግጥ ነው። ይሁን እንጂ የወሉን ከግል ለመለየት የተከራካሪዎቹን ሰራተኞች ቁጥር እንደመለያ መስፈርት መውሰድ እንደምንችል የሚጠቁመን የሕግ ድንጋጌ የለም። ይህ ደግሞ ሕጉ ሁለቱን ክርክሮች ለመለየት የፈለገበትን ልላ መንገድ እንድንፈትሽ ያደርገናል። ለዚህም ሁለቱ የክርክር አይነቶች በምሣልነት በተናጥል የተዘረዘሩበትን የአዋጅ ቁ.42/85 አንቀጽ 142/1/ን እና 138/1/ን መሰረት ማድረጉ አሣማኝነት ያለው መደምደሚያ ላይ እንድንደርስ ይጠቅመናል።
አዋጅ ቁ.42/85 አንቀጽ 142/1/ ሀ. ስለደመወዝና ልሎች ጥቅሞች አወሳሰን፣ ለ. አዲስ የሥራ ሁኔታዎችን ስለመመስረት፤
ሐ. የሕብረት ስምምነት ስለመዋዋል፣ ስለማሻሻል፣ ፀንቶ ስለሚቆይበት ጊዜና ስለሚፈርስበት፣ መ. አዋጁን፣ የሕብረት ስምምነት ወይም የሥራ ደንብ ድንጋጌዎችን በሚመለከት የሚነሣ የትርጉም ክርክር፣ ሰ. ስለሰራተኛ አቀጣጠርና እድገት አሰጣጥ ሥርዓት፣ ረ. አጠቃላይ ሰራተኞችንና የድርጅቱን ሕልውና የሚነኩ ጉዳዮች፣ ሰ. እድገት ዝውውር እና ሥልጠናን በሚመለከት አሰሪው በሚወስዳቸው እርምጃዎች ምክንያት የሚቀርቡ ክሶች፣ ሸ. የሰራተኞች ቅነሣ እና የመሳሰሉት የሥራ ክርክሮች የወል የሥራ ክርክሮች መሆናቸውን ደንግጓል።
እንደዚሁም አብዛኛዎቹ የድንጋጌው ከፍሎች በውጤታቸው የሁሉንም ሰራተኞች መብትና ጥቅም የሚመለከቱ ጉዳዮችን ያቀፉ መሆናቸውን በግልጽ አመላክተውናል።
ለምሣልነት በንኡስ አንቀጽ 1/ሀ/፣ /ለ/፣ /ሐ/፣ /ሰ/፣ /ረ/ እና /ሸ/ የተጠቀሱትን የሥራ ክርክር አይነቶች መመልከት ይቻላል። እነዚህ የድንጋጌው አብዛኛው ንኡስ አንቀጾች ክርክሩ የወል ለመባል የጋራ የሆነን የሰራተኞቹን መብትና ጥቅም የሚመለከት ላሆን እንደሚገባ በግልጽ ካሣዩን ደግሞ በቀሪዎቹ ንኡስ አንቀጾች ላይ የተጠቀሱትንና ልሎችንም በድንጋጌው ያልተካተቱትን ተመሳሳይ የሥራ ክርክሮችን የወልነት ፀባይ ከሰራተኞቹ የጋራ መብትና ጥቅም ጋር ካለው ግንኙነት አኳያ ልንመዝነው የሚገባን ይሆናል። ስለሆነም ጥያቄው የደመወዝም ሆነ የሥልጠና፣ የሕግ ትርጉም ነክም ሆነ ወይም ልላ የወል የሚሰኘው ጉዳዩ የጋራ በሆነ የሰራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አሉታዊም ሆነ አወንታዊ ውጤት የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ ብቻ ላሆን ይገባዋል።
በልላ በኩል ደግሞ የአዋጅ ቁ.42/85 አንቀጽ 138/1/ ሀ. ከሥራ ማስወጣትን ጨምሮ ልሎች የዲሲፕላን እርምጃዎችን የሚመለከቱ ክሶች፣ ለ. የሥራ ውል መቋረጥ ወይም መሰረዝን የሚመለከቱ ክሶች፣ ሐ. የሥራ ሰዓትን፤ የተከፋይ ሂሳብን፤ ፈቃድንና እረፍትን የሚመለከቱ ክሶች፣ መ. የቅጥር ማስረጃ ሰርቲፊኬት መስጠትን የሚመለከቱ ክሶች፣ ሰ. የጉዳት ካሣን የሚመለከቱ ክሶች እና ረ. በአዋጁ መሰረት የሚቀርብ ማንኛውም የወንጀልና ደንብ መተላፍ እንዲሁም ልሎች ተመሳሳይ ጉዳዮች የግል የሥራ ክርክሮች መሆናቸው ተደንግጓል። የዚህ ድንጋጌ ይዘት ከፍ ሲል እንደተጠቀሰው ድንጋጌ የጋራ የሆነን የሰራተኞች ጉዳይ እንደሚያጠቃልል የሚገልጽ አይደለም። ስለሆነም ሥራ ክርክሩ በእነዚህ በተዘረዘሩትም ሆነ በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ ተመስርቶ ሲቀርብ ከግል አልፎ በጋራ መብት ላይ የሚያመጣው ለውጥ ያለመኖሩ ጉዳይ ክርክሩን የወል ሳይሆን የግል የሥራ ክርክር እንዲሆን ያደርገዋል።
እንግዲህ አንድ የሥራ ክርክር በአንድ ወይም በብዙ ሰራተኞች መቅረቡ ጉዳዩ የወል ወይም የግል የሥራ ክርክር መሆኑን የሚያረጋግጥልን አይደለም። ይልቁንም ክርክሩ የወል መሆኑን የሚያሳየን ውጤቱ ከግል አልፎ የሰራተኞቹን የጋራ መብትና ጥቅም የሚነካ የመሆኑ ጉዳይ ሲሆን ክርክሩ የግል ነው የምንለው ደግሞ ውጤቱ በተከራካሪው ሰራተኛ ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሆኖ ስናገኘው ነው።
ወደ ጭብጣችን ስንመለስ አመልካቾች ተጠሪው የቅነሣ እርምጃ ለመወሰድ የሚያስችል ምክንያት የለውም፤ ቅነሣውም በአዋጅ ቁ.42/85 አንቀጽ 29 የተመለከተውን ቅደም ተከተል ያከበረ አይደለም በሚል አይነት መሟገታቸውን ያሳየናል። እንደሚታወቀው የሰራተኞች ቅነሣ መላውን የድርጅቱን ሰራተኞች ከግምት በማስገባት በሕግ አግባብ ላከናወን የሚገባ ተግባር ነው። ቅነሣው ህግን ተመስርቶ አለመደረጉን አሳያለሁ በሚል ሁኔታ የሚቀርብ አቤቱታም በውጤቱ ሁሉንም ሰራተኞች የሚመለከት መሆኑ የሚታመን ነው። የአመልካቾች ክርክር ደግሞ በዚህ መልኩ የቀረበ መሆኑ ከፍ ሲል ተመልክቷል። ስለሆነም ጉዳይ የወል እንጂ የግል የሥራ ክርክር የሚሰኝበት ምክንያት አይኖርም። ክርክሩን የመዳኘቱ ሥልጣንም በአዋጅ ቁ.42/85 አንቀጽ 142/1/ /ሸ/ መሰረት የቦርድ እንጂ የፍ/ቤት አይሆንም።
የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ በግራ ቀኙ መካከል የነበረው የሥራ ውል የተቋረጠ መሆኑን ምክንያት በማድረግ የቅነሣውን ህጋዊነት የመመርመር ሥልጣን የፍ/ቤት ነው ሲል ወስኗል። ይሁን እንጂ ከፍ ሲል እንደተገለፀው አንድ የሥራ ክርክር በቦርድ ወይም የግል የሥራ ክርክር መሆኑ እንጂ የሥራ ውሉ የመቋረጥ ወይም ያለመቋረጡ ጉዳይ አይደለም። ስለሆነም ፍ/ቤቱ ለውሣኔው መሰረት ያደረገው ምክንያትም ከሕጉ ጋር የሚጣጣም አልሆነም።
በሁለተኛው ደረጃ የተያዘው ጭብጥም አግባብነት ከአለው የአዋጅ ቁ.42/85 አንቀጽ 154/2/ ጋር ተገናዝቦ ተመርምሯል። በዚህ ድንጋጌ የቦርድ ውሣኔ የሕግ ስህተት ያለበትና የሕግ ስህተቱም የውሣኔውን ውጤት አዛብቶት የተገኘ እንደሆነ ይግባኝ የቀረበለት ፍ/ቤት ጉዳዩን ከዝርዝርና ከአጠቃላይ መመሪያ ጋር ለመጨረሻ ውሣኔ ወደ ቦርድ እንደሚመልሰው፤ ነገር ግን የቦርዱን ውሣኔ ለመሻርም ሆነ ለማሻሻል እንደማይችል ተደንግጓል።
በእርግጥ በዚህ ጉዳይ የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የቦርዱን ውሣኔ እራሱ መሻሩ የውሣኔ አሰጣጡ ከተጠቀሰው ሕግ ጋር አለመጣጣሙን ያሳያል። ይሁን እንጂ ፍ/ቤቱ የቦርዱን ውሣኔ የሕግ ስህተት ለማረም እንዲችል በዚሁ ሕግ ሰፊ ሥልጣን ተሰጥቶታል። ውሣኔውን በይግባኝ ላሽረውም ሆነ ላያሻሽለው ባይችልም የሕግ ስህተቱ ታርሞ በጉዳዩ እንደገና ውሣኔ ይስጥበት ዘንድ ክርክሩን ወደ ቦርድ እንዲመልሰው ሕጉ በግልጽ ፈቅዶለታል።
ስለሆነም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የቦርዱን ውሣኔ እራሱ ለመሻር ሥልጣን የልለው በመሆኑ የፍርድ አሰጣጡ ከተጠቀሰው ህግ አግባብ ላቃና የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ 1ኛ. ለዚህ ክርክር መነሻ የሆነው የሰራተኛ ቅነሣ የወል የሥራ ክርክር በመሆኑ ጉዳዩን የመዳኘት ሥልጣን የቦርድ እንጂ የፍርድ ቤት ላሆን አይገባም በማለት ተወስኗል።
2ኛ. ይግባኙ የቀረበለት የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይህንኑ ተገንዝቦ ወደ ክርክሩ በመግባትና በቦርዱ የተሰጠው ፍርድ ከሕግ አኳያ ስህተት ያለበት መሆን አለመሆኑን በመመርመር ጉዳዩ ከመመሪያ ጋር ወደ ቦርድ ላመለስ የሚገባው መሆን አለመሆኑ ረገድ ውሣኔ ላሰጥበት ይገባል በማለትም ተወስኗል።
3ኛ. የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክሩን ማየት እንዲቀጥል ያስችለው ዘንድም ጉዳዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.343/1/ መሰረት ተመልሶለታል።
7 8 የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
No topics extracted.