No summary available.
ሚያዚያ 18 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ አሰግድ ጋሻው አቶ መስፍን እቁበዮናስ ወ/ት ሂሩት መለሰ አቶ ተሻገር ገ/ስላሴ አመልካች፡- በምስራቅ ቀጠና ጉምሩክ የሐረር ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ተጠሪ፡- አቶ አብዲ አላ ሳዬ የጉምሩክ ክርክር - ኮንትሮባንድ - የተቋረጠ ጥቅም ክፍያ - አዋጅ ቁ. 60/89 አንቀጽ 5 - 6 የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 2010/2/ የOሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የOሮሚያ ም/ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች የ393 ቀናት የተቋረጠ ገቢ ለተጠሪ እንዲከፍልና መኪናውን ወይም ዋጋውን እንዲተካ የሰጠውን ውሳኔ በማፅናቱ በተቃውሞ የቀረበ አቤቱታ ነው።
ውሣኔ፡ - የOሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የOሮሚያ ም/ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የጉምሩክ ባለሥልጣን በኮንትሮባንድ ወደ አገር የሚገቡትን ወይም ከአገር የሚወጡትን እቃዎች እንቅስቃሴ የመቆጣጠር፣ የሚንቀሳቀሱ እቃዎችንና ማጓጓዣዎችን የመያዝና አስፈላጊ እርምጃዎችን የመውሰድ ስልጣን ተሰጥቶታል።
የጉምሩክ ባለሥልጣን በሕገ ወጥ መንገድ መገልገያ የሆኑ መጓጓዣዎችን ጭምር ይዞ ለምርመራ በጥበቃ ሥር ለማቆየት ግልፅ ስልጣን ተሰጥቶታል።
የመንግሥት መ/ቤት ባለሥልጣን ራሱ የመረመራቸውን ሰነዶች ቃላት መቃወም የሚቻለው ዳኞች በተለይ ከፈቀዱ ብቻ ነው።
ሚያዚያ 18 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡-
ተጠሪ፡- አቶ አብዲ አላ ሳዬ - ቀረበ።
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ሰጥተናል።
መዝገቡ ለሰበር ችሎት ላቀርብ የቻለው የአሁኑ አመልካች በ12/4/98 ጽፎ ባቀረበው የሰበር ቅሬታ ማመልከቻ መነሻነት ነው። በዚህ ጉዳይ የአሁኑ ተጠሪ በሥር ፍ/ቤት በአመልካች ላይ ባቀረበው ክስ የአሁኑ አመልካች የኮንትሮባንድ እቃ ሳልጭን ጭነሀል በማለት መኪናዬን ከሕግ ውጭ ይዞ ስላቆመብኝ በቀን አገኘው የነበረው ገቢ ብር 25A /ሁለት መቶ ሀምሳ/ ብር በ15A ቀኖች ተባዝቶ የአሁን አመልካች ብር 37,500 /ሰላሣ ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር/ እንዲከፍለው በተጨማሪም የመኪናውን ዋጋ ብር 50,000 ወይም መኪናውን እንዲያስረክበው ጠይቋል። የሥር ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ክርክር አድምጦ ጥር 27 ቀን 1997 በዋለው ችሎት የአሁኑ አመልካች የ393 ቀናት የተቋረጠ ገቢ ለተጠሪ እንዲከፍልና መኪናውን ወይም ዋጋውን ብር 50,000 እንዲተካ ታዟል። ጉዳዩን በይግባኝ ያየው የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት መኪናው በመያዙ ምክንያት የአሁኑ ተጠሪ ጠይቆ የነበረው የተቋረጠ ገቢ የ150 ቀናት ብቻ ሆኖ እያለ የሥር ፍ/ቤት የ393 ቀናት መወሰኑ ትክክል ባይሆንም ይግባኝ ባይ በዚህ በኩል ያቀረበው አቤቱታ ስለልለ ታልፏል ብሎ የይግባኝ መዝገቡን ዘግቶ መልሶታል።
ይህ ችሎት ሚያዚያ 2 ቀን 1998 ዓ.ም. መዝገቡ ለሰበር ይቀርባል በማለት ወስኖ ጉዳዩን ለመስማት በተያዘው ቀጠሮ ተጠሪን አግኝቶ መጥሪያውን ማድረስ ያልቻለ መሆኑን አመልካች በመግለፁ ይህ ችሎት ግንቦት 2 ቀን 1998 ዓ.ም. ተጠሪ የጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግለት ታዟል። የአሁኑ ተጠሪ ሰኔ 28 ቀን 1998 ሆነ በሚቀጥሉት ቀናት ባለመቅረቡ ፍ/ቤቱ በልለበት እንዲታይ ብይን ሰጥቷል።
በዚህ ጉዳይ የሥር ፍ/ቤቶች የአሁኑ አመልካች ለተጠሪ የተቋረጠ ገቢ ኃላፊ ነው ለማለት መሰረት ያደረጉት ምክንያት የአሁኑ አመልካች 111 112 የኮንትሮባንድ እቃ ዝርዝር የሚያሳያ የጽሁፍ ማስረጃ ቢያቀርብም የተባሉት እቃዎች ከተጠሪ መኪና ላይ መያዙን አይገልጽም፤ አመልካች ለሕግ ተቃራኒ በሆነ መንገድ መኪናውን ይዞ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ደግሞ ተጠሪን ሆነ ብሎ ለመጉዳት ነው በሚል መደምደሚያ እንደነበር ይህ ችሎት ተረድቶታል። በዚህ መሰረት ይህ ችሎት የተጠሪ መኪና ለህግ ተቃራኒ በሆነ መንገድ ተይዟል ተብሎ የአሁኑ አመልካች በውሳኔው የተመለከተውን ገንዘብ ይከፈል መባሉ በአግባቡ መሆን አለመሆኑን ይህ ችሎት መርምሯል።
አዋጅ ቁጥር 60/89 የጉምሩክ ባለሥልጣንን እንደገና ለማቋቋምና አሰራሩን ለመወሰን የወጣ አዋጅ ነው። በዚህ አዋጅ በአንቀጽ 6 ላይ የባለሥልጣኑን ሥልጣንና ተግባር በዝርዝር የተመለከተ ሲሆን በተለይ ለዚህ ጉዳይ አግባብነት ያለውን ንኡስ ቁጥር 5 ስንመለከት በኮንትሮባንድ ወደ አገር የሚገቡትን ወይም ከአገር የሚወጡትን እቃዎች እንቅስቃሴ የመቆጣጠር፣ የሚንቀሳቀሱ፣ እቃዎችንና ማጓጓዣዎችን የመያዝና አስፈላጊ እርምጃዎችን የመውሰድ ስልጣን የተሰጠው መሆኑ ተገልጿል።
አመልካች በዚህ በተሰጠው ሥልጣን ተጠቅሞ በኮንትሮባንድ ወንጀል ተግባር ይዞ በቁጥጥር ሥር ባቆየው መኪና ላይ በገቢ እቃ መመዝገቢያ ሞድል ላይ የተሞላውን ዝርዝር የኮንትሮባንድ እቃ በሰነድ ማስረጃነት አያይዞ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም የሥር ፍ/ቤት የቀረቡት የገቢ መመዝገቢያ ሞድሎችን ሕጋዊነት የተቀበለ ቢሆንም በመቀጠል ግን ማስረጃው የእቃዎች ዝርዝር የሚገልጽ እንጂ እቃው በከሳሽ መኪና ላይ መያዙን አይገልጽም ብቻ በማለት ውድቅ ማድረጉ ከማስረጃ ሕግ ዓላማና በፍ/ሕ/ቁ. 2010/2/ መሰረት በባለስልጣን ስለተረጋገጡ ሰነዶች ተቀባይነት የሚደረገውን ሕግ የሚጥስ አካሄድ ሆኖ አግኝተነዋል። ከዚህ በተጨማሪ የአሁን አመልካች በአዋጁ አንቀጽ 58/1/ /ለ/ መሰረት በሕገወጥ መንገድ መገልገያ የሆኑ መጓጓዣዎችን ጭምር ይዞ ለምርመራ በጥበቃ ሥር ለማቆየት ግልጽ ሥልጣን ተሰጥቶት እያለ የሥር ፍ/ቤት የተያዘ የኮንትሮባንድ እቃ ዝርዝር የቀረበ መሆኑን ተቀብሎ ከአሁኑ ተጠሪ መኪና ላይ ስለመያዙ ማስረጃ አልቀረበም በሚል የተቋረጠ ገቢ ይክፈል ብሎ ማለቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ብለናል።
ው ሣ ኔ የአሁኑ አመልካች በሕግ አግባበ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ተግባሩ ሲወጣ ይዞ ላቆየው ተሽከርካሪ የተቋረጠው ገቢ ይክፈል በማለት የምስራቅ ሐረርጌ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 271/96 በ22/04/97 እና የOሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት በመ/ቁ.
25132 በ15/3/98 የሰጡትን የውሳኔ ክፍሎች ሽረናል፤ የአሁኑ አመልካች መኪናውን ለተጠሪ ያስረክብ ብለን የሥር ፍ/ቤት ውሳኔዎች አሻሽለን ወስነናል፤
መዝገቡ ያለቀለት ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
¡\iZ M/e. 12025
Mμióp 18/1999
ªƒu:- አቶ M}iUÍH¦ o¨
አቶ „\¶¬ μað
አቶ M^Ö} –ei§|^
ወ/ት BôVp MEQ
አቶ ma´Z ´/SF\ö
„MG‰u:- „q O|\ö „GNð
MG^ \¾:- 0fiö K¶
የወንጀል ጉዳይ ክርክር - ማታለል - የጥብቅና ፈቃድ ከተሰረዘ በኋላ የጥብቅና
ስራ እሰራለሁ ብሎ ገንዘብ መቀበል - የመከላከል መብት - የ1949 ወንጀለኛ
መቅጫ ህግ ቁ. 656(ሀ) ና (ለ)
አመልካች በቤንሻንጉል ጉምዝ ከፍተኛና ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰጠው
የጥፋተኝነትና የቅጣት ውሣኔ የህግ ስህተት ያለበት ነው በሚል የቀረበ
አቤቱታ ነው።
ውሣኔ፡ - የቤንሻንጉል ጉምዝ ከፍተኛና ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ጸንቷል።
የጥብቅና ፈቃድ ከተሰረዘ በኋላ ጉዳይ አስፈጽማለሁ ብሎ ገንዘብ መቀበል የማታለል ወንጀል ነው።
የመከላከል መብት ህገ-መንግሥታዊ መብት ነው።
113 114
¡\iZ M/e. 12025
Mμióp 18/1999
ªƒu:- 1. M}iUÍH¦ o¨
2. „\¶¬ μað
3. M^Ö} –ei§|^
4. BôVp MEQ
5. ma´Z ´/SF\ö
„MG‰u:- „q O|\ö „GNð „GdUiðO
MG^ \¾:- 0fiö K¶ „GdUiO
Ö Z ¬
¦C Mš´k E\iZ uEùp ¡dUið „MG‰u iSZ ÖZ¬ iöqu
¡m\¸ð ¡ºÔm‚{p| ¡g¹p ðR{ö ¡K¶ ^Cmp M~V} iNô¤MEŠp Að{öo
¡m\¸ iMD{ð ðR{ö“s ¦aVG‚ \óG iNMGˆn {ð::
¦C ÖZ¬ iöp ¡„MG‰u} „iöno ˆ^Z ÖZ¬ iöqu ðR{ö“u †}ªóAðO
i˜óC ÖZ¬ iöp ˆm¨U´ð ¡ËHðÖ ŠZŠZ| „¶jk{p ‰Frð EöEùu K´ùu μZ
iN´|˜k MZO[„G::
i˜óCO MQUp „MG‰u ¡mˆ\ð| ºÔm ¡mjEð ¡}®E Mg¿
K¶ eºZ 656(A) †| (E)} iMmFEÖ \óD} EÖZ¬ iöqs ðR{ö OŠ}¤p
¡D{ð „MG‰u ¡ºkg| Ñf¬ R¦~U𠡺kg| Ñf¬ ¤Eð iN^M\G ¡¶G
miª§u} ´ðª¦ „^ÑËOFuíEAð iNEp kZ 3830 (_^p óC T^p Mq \FR) M\© iMUμ´¸ð {ð:: „MG‰u i˜óC uEùp N^U° „GdUik‚O ióGO ¡^Z ÖZ¬ iöqu idõ N^U° dZlip ¡\{ð MD{ð} m´}ši|G:: ¦Ge}O „MG‰u d¨O \óG m\ºqp ¡{iU𠡺kg| Ñf¬ MQU˜ð ˆm´EÍEp iíF ¦C} ¬Z´óp MÑÍMð iN\U° mUμ¶»ioG:: iEöF iˆðG „MG‰u ¡MˆFˆG Mkmø „Gm¸idG‚O ióGO m¨μμNô †¬G m\ºqp ¡MˆFˆ¤ N\U°ð} Eó¤dZk „EMtEð ˆMš´ið EM´}˜k uE|G:: mˆRð ¡MˆFˆG Mkn K´M}¶So’õ
Mkp MD{ð j¤ˆXŠZO mˆRb iD{ip ´ðª¦ F¦ im´ióð „ÁZ ´ó˜ö
ð^º ¡MˆFˆ¤ N^U° ‰Eð †}ªó¤dZk ÖZ¬ iöqu m¨μμNô d¸[
ió\¸ðO „MG‰s †¬Eð} jEM¸dMð ÖZ¬ iöqu ¡„MG‰u} K¶
M}¶So’õ Mkp ¹\ð Eó¤\r𠄦uGO:: iMD{ðO „MG‰u i^Z
ÖZ¬ iöp ¡dUiip Š^ iidõ N^U° ¡mUμ´¸ip iMD{ð| ¡m¹Eip
¡AðEp •Mp g¹pO K´ð iNô¤˜ð ŠGG ð^º iMD{ð Bô¨nO D{
ðR{öð MQUo’õ ¡K¶ ^Cmp MÑÍMð} ¡Nô¤R¦ D~ „F´{ðO::
ð R {ö
(1) i˜óC ´ðª¦ ¡dUið ¡\iZ NMGˆt mdj¦{p „F´O::
(2) ¡iö}a´ðG ´ðOš ¡ˆÖm| ¡¸gF¦ ÖZ¬ iöqu ¡\¸ðp
ðR{ö Í}mýG::
115 116
No topics extracted.