No summary available.
መጋቢት 13 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- አቶ ከማል በድሪ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ አቶ ጌታቸው ምህረቱ አቶ መስፍን እቁበዮናስ አመልካች፡- የኢት.ጉምሩክ ባለስልጣን ተጠሪ፡- እነ አቶ አበሮ ኢርጋኖ የመንግሥት ሰራተኞች የስራ ክርክር - የፍድራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስተዳደር ፍርድ ቤት ስልጣን - የጉምሩክ ሰራተኞችን አስተዳደር በተመለከተ የገቢዎች ሚኒስትር የሚያወጣው መመሪያ - አዋጅ ቁ. 368/95 አንቀጽ 6/2/ለ የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍድራሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስተዳደር ፍርድ ቤት የተጠሪዎቹን ክርክር ተቀብሎ ያስተናግድ ሲል የወሰነውን ውሣኔ በመቃወም የቀረበ አቤቱታ ነው።
ውሣኔ፡ - የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የጉምሩክ ሰራተኞች የመንግሥት ሰራተኞች ቢሆኑም ከልሎች የፍድራል መ/ቤቶች ተለይተው የሚተዳደሩት የገቢዎች ሚኒስትር በሚያወጣው መመሪያ እንጂ በፍድራል መንግሥት ሰራተኞች አዋጅ ቁ. 262/1994 አይደለም።
107 108
13/7 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡-
የአሁኑ የሰበር ቅሬታ ማመልከቻ የቀረበው በዚሁ ነጥብ ላይ ነው። የአሁኑ አመልካች በሰበር ቅሬታ ማመልከቻው ላይ እንደገለፀው፣ በአዋጅ ቁጥር 368/95 አንቀጽ 6/2/ /ለ/ መሰረት የባለሥልጣኑ መ/ቤት ሰራተኞች ሚኒስትሩ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት የሚተዳደር መሆኑ እየታወቀና፣ የገቢዎች ሚኒስቴርም የባለሥልጣኑን ሰራተኞች አስተዳደር አስመልክቶ ቁ.01/22/41/3 በ23/02/98 የሰራተኞች አስተዳደር አጠቃላይ መመሪያ አውጥቶ እና በሥራ ላይ አውለው እያለ የፍድራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የአመልካች መ/ቤት ሰራተኞች የሥራ ክርክር በፍድራሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ይታይ ማለቱ የህግ ሥህተት ያለበት ነው ብለዋል።
ጉዳዩ ለሰበር ይቀርባል ተብሎ የግራ ቀኙ ክርክር ሰኔ 5 ቀን 1998 ተሰምቷል። በዚህ ጉዳይ በዋነኛነት የተያዘው ጭብጥ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ሰራተኞች የሆኑት የተጠሪዎች ጉዳይ በአዋጅ ቁጥር 262/94 መስተናገድ ይገባዋል ወይስ አይገባውም? የሚለው ይሆናል። በአዋጅ ቁጥር 368/1995 በአንቀጽ 6/2/ /ለ/ መሰረት “የፍድራል መንግስት አዋጅ ቁጥር 262/1994 ቢኖርም እንኳን የባለሥልጣኑ ሰራተኞች አስተዳደር ሚኒስቴሩ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት ይሆናል።” በማለት የደነገገ መሆኑ ይታወቃል። ይህንንም ተከትሎ በገቢዎች ቦርድ የሰራተኞቹን አስተዳደር በሚመለከት መመሪያ ወጥቶ ከጥቅምት 23 ቀን 1996 ጀምሮ በሥራ ላይ መዋሉ ተረጋግጧል። ይህ በዚህ ሁኔታ ተከናውኖ እያለ የሥር ፍ/ቤት “---የባለስልጣኑን ሰራተኞች አስተዳደር የሚኒስቴር መ/ቤቱ የሚያወጣው መመሪያ መሰረት ይሆናል የሚለው ቢተረጐም ስለሰራተኞቹ አስተዳደር ነክ ጉዳዮችን የሚመለከት መመሪያ ይሆን እንደሆን እንጂ በሰራተኞቹ በኩል የሚኖረው የዳኝነት ጥያቄ የት ቦታ? በማን ይታይ? የሚለውን በመመሪያ ላወሰን ይችላል የሚል ትርጉም ላሰጥ አይችልም።” በማለት የደረሰበት መደምደሚያ ከህጉ ዓላማና መንፈስ የራቀ ትርጉም የተሰጠበት መሆኑን ያመለክታል።
የአመልካች መ/ቤት የፍድራል መንግሥት መ/ቤት መሆኑ ቢታወቅም፣ ሕግ አውጭው የአመልካች መ/ቤት ከሚያከናውናቸው ተግባራት አኳያ ከልሎቹ የፍድራል መ/ቤቶች ተለይቶ እንዲተዳደር በአዋጅ በግልጽ አመላክቶ እያለ የሥር ፍ/ቤቱ የባለሥልጣኑ ሰራተኞች አስተዳደርን በተመለከተ የሚኒስቴር መ/ቤቱ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት ይሆናል የሚለው የሰራተኞቹን አስተዳደር ነክ ጉዳዮች ብቻ በመመሪያው መሰረት ይታያሉ በማለት የሰጠው ትርጉም መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ብለናል።
109 110
ሚያዚያ 18 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ አሰግድ ጋሻው አቶ መስፍን እቁበዮናስ ወ/ት ሂሩት መለሰ አቶ ተሻገር ገ/ስላሴ አመልካች፡- በምስራቅ ቀጠና ጉምሩክ የሐረር ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ተጠሪ፡- አቶ አብዲ አላ ሳዬ የጉምሩክ ክርክር - ኮንትሮባንድ - የተቋረጠ ጥቅም ክፍያ - አዋጅ ቁ. 60/89 አንቀጽ 5 - 6 የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 2010/2/ የOሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የOሮሚያ ም/ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች የ393 ቀናት የተቋረጠ ገቢ ለተጠሪ እንዲከፍልና መኪናውን ወይም ዋጋውን እንዲተካ የሰጠውን ውሳኔ በማፅናቱ በተቃውሞ የቀረበ አቤቱታ ነው።
ውሣኔ፡ - የOሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የOሮሚያ ም/ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የጉምሩክ ባለሥልጣን በኮንትሮባንድ ወደ አገር የሚገቡትን ወይም ከአገር የሚወጡትን እቃዎች እንቅስቃሴ የመቆጣጠር፣ የሚንቀሳቀሱ እቃዎችንና ማጓጓዣዎችን የመያዝና አስፈላጊ እርምጃዎችን የመውሰድ ስልጣን ተሰጥቶታል።
የጉምሩክ ባለሥልጣን በሕገ ወጥ መንገድ መገልገያ የሆኑ መጓጓዣዎችን ጭምር ይዞ ለምርመራ በጥበቃ ሥር ለማቆየት ግልፅ ስልጣን ተሰጥቶታል።
የመንግሥት መ/ቤት ባለሥልጣን ራሱ የመረመራቸውን ሰነዶች ቃላት መቃወም የሚቻለው ዳኞች በተለይ ከፈቀዱ ብቻ ነው።
No topics extracted.