No summary available.
ሚያዚያ 11 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ አሰግድ ጋሻው አቶ መስፍን እቁበዮናስ ወ/ት ሂሩት መለሰ አቶ ተሻገር ገ/ስላሴ አመልካች፡- የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ተጠሪዎች፡- እነ ልእልት ተናኘወርቅ ኃ/ሥላሴ የቤት አበል ክፍያ - የተወረሰ ቤት - የጠቅላይ ሚ/ር ስልጣን - የኢፍዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 74(4) - የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣን ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁ. 4/87 አንቀጽ 11/1/ - አዋጅ ቁ. 47/67 አንቀጽ 21(2) የፍድራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪዎች ቤት የተወረሰባቸው በመሆኑ አበል ላከፈላቸው ይገባል ሲል የሰጠውን ውሣኔ በማፅናቱ በተቃውሞ የቀረበ አቤቱታ ነው።
ውሣኔ፡ - የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚኒስቴር መ/ቤቶችን በበላይነት የመምራትና ስራዎቻቸውንም የመቆጣጠር ስልጣን ተሰጥቶታል።
ሚኒስቴር መ/ቤቶች ስራቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት የፈፀሙትን ስህተት ማረምና ማስተካከል በጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን ስር የሚወድቅ ነው።
ሚያዚያ 11 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡-
መልስ ሰጭ፡- እነ ልእልት ተናኘወርቅ ኃ/ሥላሴ /6 ሰዎች/ - ጠበቃ አቶ ብስራት ሐመልማል ቀረቡ።
ለሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነው ጉዳይ የጀመረው በፍ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ነው።
ተጠሪዎች ለዚህ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ መንግስት የግል መኖሪያ ቤቶቻቸውንና አከራይተው የነበሩትን ልሎች ቤቶች ወርሶ እያስተዳደረ በመሆኑና ምንም ገቢ ስላልነበራቸው አበል እንዲከፈላቸው ለሥራና ከተማ ሚ/ር አመልክተው እንዲከፈላቸው የተወሰነ ቢሆንም ተጠሪ አበሉን ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆኑ ከ1/12/67 - 30/8/87 ያለው ውዝፍ አበልና ወደፊት ያለው አበልም ለዘለቄታው እንዲከፍል እንዲወሰንበት ጠይቀዋል። ጉዳዩን ያየው ፍ/ቤትም ውዝፍ አበሉ እንዲከፈልና ከክሱ በኋላ ያለው ግን ዳኝነት ያልተከፈለበት በመሆኑ ተቀባይነት የልለው መሆኑን ወስኗል። ይግባኝ የቀረበለት የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤትም ጉዳዩን መርምሮ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤቱን ውሣኔ አፅንቷል።
የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። የአመልካች አቤቱታም የሥራና ከተማ ልማት ሚ/ር የሰጠው ውሣኔ በጠቅላይ ሚ/ር ቢሮ ተሽሯል፣ ተጠሪዎች እስር ቤት በነበሩበት ጊዜ መንግስት ወጪ እያደረገ ያኖራቸው በመሆኑ ተጠሪዎች ውጭ አገር ነዋሪዎች በመሆናቸው ከቤት ኪራይ በቀር ልላ ገቢ እንደልላቸው ሣይጣራና ሣይታወቅ የተፈቀደው አበል ተገቢ አይደለም የሚል ነው።
ይህ ችሎትም የሥራና ከተማ ልማት ሚ/ር የሰጠው ውሣኔ በጠቅላይ ሚ/ር ቢሮ ተሽሮ እያለ የተጠራቀመው የቤት ኪራይ ይከፈል መባሉ በአግባቡ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት አቤቱታው ለችሎቱ ቀርቦ እንዲታይ አድርጓል።
ግራ ቀኙም ክርክራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል። ፍ/ቤቱም መዝገቡን አንደሚከተለው መርምሯል።
ከክርክሩ ሂደት ተጠሪዎች ቤታቸው በመወረሱ ምክንያት አበል እንዲከፈላቸው ክስ ለማቅረበ የቻሉት የሥራና ከተማ ልማት ሚ/ር አበሉ እንደከፈላቸው የሰጠውን ውሣኔ መሰረት አድርገው መሆኑን ተገንዝበናል።
የሥራና ከተማ ልማት ሚ/ር በአ/ቁ. 47/67 አንቀጽ 21/2/ መሰረት ትርፍ 105 106 ቤት የተወረሰበት ቤተሰብ ወይም ግለሰብ ከቤት ኪራይ በስተቀር ለመኖሪያ የሚሆን ልላ ገቢ የልለው መሆኑ ሲረጋገጥ በመሥራት ገቢ አስከሚያገኝ ድረስ በየወሩ ለመተዳደሪያ አበል እንዲከፈለው ላወስን እንደሚችል ተደንግጓል። በዚህም መሰረት ህጉ የሰጠውን ስልጣን መሰረት አድርጐ የሥራና ከተማ ልማት ሚ/ር ለተጠሪዎች አበል እንደከፈላቸው ወስኗል። በልላ በኩል ግን ይህ ውሳኔ በጠቅላይ ሚ/ር ቢሮ የተሻረ መሆኑን ከመዝገቡ ተረድተናል። የተጠሪዎች ክርክር የስራና ከተማ ልማት ሚ/ር በአ/ቁ 47/67 የተሰጠውን ስልጣን መሰረት አድርጎ የሰጠውን ውሣኔ የጠቅላይ ሚ/ር ቢሮ ለመሻር የሚያስችል ስልጣን የለውም የሚል ነው።
ከመዝገቡ የጠቅላይ ሚ/ር ቢሮ የሥራና ከተማ ልማት የሰጠውን ውሣኔ የሻረው በ29/12/87 እንደሆነ ተረድተናል። በዚህን ወቅት ደግሞ የኢትዮጵያ ፍድራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብላክ ህገ-መንግስት ከነሐሴ 15/1987 ጀምሮ ስራ ላይ ውሐል። በዚህ ህገ-መንግስት አንቀጽ 74/4/ ሁሉም ሚኒስቴሮች የሚገኙበትን የሚኒስቴሮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደሚመራ፣ እንደሚያስተባብርና እንደሚወክል ተመልክቷል። እንዲሁም ከነሐሴ 17/1987 ጀምሮ ስራ ላይ በነበረው የአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው A/ቁ 4/87 አንቀጽ 11/1/ ሥር እያንዳንዱ ሚኒስትር፣ የሚመራውን ሚኒስቴር መ/ቤት የሚመለከቱ ሥራዎች ፕሮግራሞችና ህጎች አፈፃፀም ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለሚኒስቴሮች ምክር ቤት መሆኑ ተገልጿል። ከነዚህ ህጎች አኳያ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚኒስቴር መ/ቤቶችን በበላይነት የመመራትና ስራቸውንም የመቆጣጠር ስልጣን ተሰጥቶታል።
በመሆኑም ሚኒስቴር መ/ቤቶቹ ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ወቅት የፈፀሙትን ስህተት ማረምና ማስተካከል በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣን ስር የሚወድቅ ነው።
በተያዘው ጉዳይም የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ለተጠሪዎች አበል እንዲከፈል የሰጠው ውሣኔ አግባብ ሆኖ ባለመገኘቱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሣኔው መሻሩ ከስልጣኑ ውጪ ነው የሚያሰኝ አይሆንም። የሥር ፍ/ቤቶችም በአ/ቁ 47/67 ሥር የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር የሚሰጠውን ውሣኔ የጠቅላይ ሚኒስቴር ላሽር፣ ላያሻሽል ወይም ላለውጥ የሚያስችለው ስልጣን በግልጽ አልተመለከተም በማለት ብቻ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ያለውን አጠቃላይ ስልጣን ከግንዛቤ ባለመክተት ውሣኔው የተሻረው ስልጣን በልለው አካል ስለሆነ ውጤት የለውም ማለታቸው የህግ ስህተት መሆኑን ተገንዝበናል።
በመሆኑም ምንም እንኳን አበል ለተጠሪዎች እንዲከፈል ሥልጣን የነበረው አካል ወስኖ የነበረ ቢሆንም ይኸው ውሣኔ ሥልጣን ባለው የበላይ አካል የተሻረ በመሆኑ ተጠሪዎች አበል እንዲከፈላቸው የተሰጣቸውን መብት አጥተዋል።
በመሆኑም ፍ/ቤቶቹ አበሉ እንዲከፈል መወሰናቸው የህግ ስህተት ነው።
ው ሣ ኔ
18942 በ8/8/96 የተሰጡት ውሣኔዎች ተስሯል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ።
ከሥር ፍ/ቤት የመጣው መዝገብ ይመለስ።
No topics extracted.