No summary available.
ሚያዝያ 09 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ አቶ አሰግድ ጋሻው አቶ ተሻገር ገ/ሥላሴ አመልካች፡- አፍሪካ ኢንሹራንስ ተጠሪ፡- አቶ ብስራት ጐላ የኢንሹራንስ ክርክር - የኢንሹራንስ ውል - ከውል ውጪ ኃላፊነት የOሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የOሮሚያ ም/ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ቀረብኝ የሚለውን የተጣራ ገቢ በቀን ብር 250 በድምሩ እንዲከፈለው የሰጠውን ውሣኔ በማፅናቱ በተቃውሞ የቀረበ አቤቱታ ነው።
ውሣኔ፡ - የOሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የOሮሚያ ም/ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የኢንሹራንስ ሽፋን ያለው ተከሣሽ በሶስተኛ ወገን ላይ ጉዳት ባደረሰ ጊዜ ፍርድ ቤቶች የተከራካሪዎችን መብትና ግድታ ለመወሰን ውልንና ከውል ውጪ ያሉ ሕጐችን ተፈፃሚ ማድረግ ይችላሉ።
በመድን ሰጪውና በተከሣሹ መካከል ያለው ግንኙነት በውል ላይ የተመሰረተ በመሆኑ መድን ሰጪው ላገደድ የሚችልበት የካሳ መጠን በመድን ውሉ የተመለከተው ነው።
ሚያዝያ 09 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ አቶ አሰግድ ጋሻው ተሻገር ገ/ሥላሴ አመልካች፡- አፍሪካ ኢንሹራንስ - አልቀረበም ።
መልስ ሰጪ ፡- አቶ ብስራት ጐላ -ቀርበዋል።
በዚህ መዝገብ የቀረበልን ጉዳይ የኢንሹራንስ ጉዳይን የሚመለከት ነው። ተያይዘው ከቀረቡት ፍርዶችና ልሎች ሰነዶች ለመረዳት እንደቻልነው የመልስ ሰጪ መኪና በደረሰበት ግጭት ምክንያት ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ ስለሆነ የመልስ ሰጪ ኢንሹራንስ ኩባንያ የነበረው ህብረት ባንክ በምትኩ አዲስ መኪና ሰጥቶታል። ህብረት ባንክ ደግሞ ሂሳቡን ከአሁን አመልካች ከአፍሪካ ኢንሹራንስ ተረክቧል። የአሁን አመልካች ክፍያውን የፈፀመው ጉዳት ያደረሰው መኪና የመድን ሽፋን ስለነበረው ነው።
ይህ ሁሉ ከተፈፀመ በኋላ የአሁን መልስ ሰጪ መኪናዋ ለቆመችበት ለ112 ቀናት በቀን ብር 25A ሂሳብ ብር 28,000 ላከፈለኝ ይገባል በማለት ጉዳቱን ባደረሰው በቢፍቱ ዲንሽ ማህበር ላይ ክስ መሰረተ። የአፍሪካ ኢንሹራንስም ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከር ፍ/ቤቱ ባዘዘው መሰረት በጉዳዩ ላይ ገብቶ ክርክር ቀጠለ።
ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት ግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ ቢፍቱ ዲንሽ A.ማ ለተቋረጠው ገቢ ኃላፊ መሆኑን በመግለፅ አፍሪካ ኢንሹራንስ ብር 28,000 /ሃያ ስምንት ሺህ ብር/ እንዲከፍል ወሰነ፤ ወጪና ኪሣራ የማቅረብ መብት የተጠበቀ ነውም አለ፤ ጉዳዩ በይግባኝ ወደሚቀጥለው ፍርድ ቤት የቀረበ ቢሆንም የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ አልተለወጠም።
101 102 የሰበር ማመልከቻ የቀረበው ይህን ውሣኔ ለማስለወጥ ሲሆን የአቤቱታው መሰረተ ሃሳብ የሚከተለው ነው፡ -
መልስ ሰጪ ባቀረቡት የአመልካች ቅሬታዎች ላይ የሚከተለውን መልስ ሰጥቷል፡ -
ከመዝገቡ ለመረዳት አንደቻልነው የመልስ ሰጪ መኪና ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ በመሆንዋ መልስ ሰጪ ከራሱ መድን ሰጪ ከነበረው ከህብረት ኢንሹራንስ ልላ መኪና ተረክቧል።መልስ ሰጪ ክስ ያቀረበው መኪናዋ በደረሰው አደጋ ምክንያት ከ11/09/96 እስከ 2/13/96 ዓ.ም.ድረስ ለ112 ቀናት በመቆምዋ ሳይገኝ የቀረበው የተጣራ ገቢ ላከፈለኝ ይገባል በማለት ነው።መልሰ ሰጪው ቀረብኝ የሚለው የተጣራ ገቢ በቀን ብር 25A በድምሩ 28,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ነው። ጉዳዩ የቀረበለት የምሥራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት መልስ ሰጪ አዲሱን መኪና እስኪረከብ ድረስ የ112 ቀናት ገቢ ስለተቋረጠበት ለዚሁ ጉዳት ቢፍቱ ዲንሽ ኃላፊ ነው ካለ በኋላ አፍሪካ ኢንሹራንስ ከቢፍቱ ዲንሽ ጋር ባለው የመድን ውል መነሻነት ቀረ የተባለውን ብር 28,000 /ሃያ ስምንት ሺህ/ እንዲከፍል ወስኗል።
ለመልስ ሰጪ ክስ መነሻ የነበረው በመኪናው ላይ የደረሰው ጉዳት በመሆኑ ጉዳዩ ከውል ውጪ ለሚደርስ ኃላፊነት አግባብ ባለው ህግ መሰረት መታየቱ አመልካች እንደሚለው ከህግ ያፈነገጠ አሰራር አይደለም። አመልካች ከቢፍቱ ዲንሽ ጋር ያለው ግንኙነት በውል ላይ የተመሰረተ ቢሆንም ጉዳት ደረሰብኝ የሚል ሦስተኛ ወገንን በሚመለከት የኃላፊነቱም ሁኔታም ሆነ የግምቱ መጠን በሚመለከት የውል ህግ ብቻ ተፈፃሚ ይሆናል የሚለው ክርክር የሚያስኬድ አይደለም። ጉዳቱ የደረሰው በውል ግንኙነት ውስጥ ባለመሆኑ የመልስ ሰጭ ጉዳይ በውል ሕግ ብቻ ላስተናገድ አይችልም። በልላ በኩል አመልካች ኃላፊ የሚሆነው ከቢፍቱ ዲንሽ ጋር በነበረው የመድን ውል መነሻነት በመሆኑ ላከፍል የሚገደደው የካሣ መጠን በመድን ውሉ በተመለከተው ሁኔታ ውስጥ መሆኑ የሚቀር አይደለም። በዚህ መሰረት አመልካች በምትክ የተሰጠውን የመኪና ዋጋ ለህብረት ኢንሹራንስ መተካቱ ከውሣኔው ለመገንዘብ ችለናል። ኢንሹራንስ ኩባንያው ከዚህ በተጨማሪ በመኪናው መውደም ምክንያት ለደረሰው ጉደት /Consequential loss/ ተጠያቂ አይደለም። መልስ ሰጪ የደረሰው ኪሣራ በአመልካች ጥፋት ምክንያት የደረሰ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ አላቀረበም። ይልቁንም መልስ ሰጪ የ112 ቀናት ሂሳብ አስልቶ ያቀረበው የመድን ሽፋን ሰጥቶት የነበረው የሕብረት ኢንሹራንስ መኪናውን ለመተካት 112 ቀናት በመውሰዱ ነው። በመሆኑም የአሁን አመልካች አፍሪካ ኢንሹራንስ በጉዳት ምክንያት የቀረ ገቢን ለመተካት ግድታ ስለልለበት ጥፋት መፈፀሙ የሚያሳይ ማስረጃም ስላልቀረበ መኪናው ለቆመበት 112 ቀናት የቀረውን ገቢ ብር 28,000 /ሃያ ስምንት ሺህ/ ላከፍል ይገባል ተብሎ መወሰኑ አግባብ ሆኖ አላገኘነውም።
ው ሣ ኔ
የምሥራቅ ሀረርጌ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁጥር 2A73 በ13/10/97 የሰጠው ውሣኔ እንዲሁም የOሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመዝገብ ቁ.20745 በ16/2/98 የሰጡት ውሳኔ ተሽሯል።
አመልካች ኡንሹራንስ ኩባንያ የተጠየቀውን የጉዳት ካሳ ብር 28,000 /ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ለመልስ ሰጪ ላከፍል አይገባም ብለናል።
No topics extracted.