No summary available.
ሚያዚያ 9 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ መስፍን Eቁበዮናስ Aሰግድ ጋሻው ሂሩት መለሰ Aመልካች፡- Aቶ Eንዳሻው በቀለ - ጠበቃ Aሰፋ ዝቅAርጋቸው ቀረቡ።
መልስ ሰጭ፡- 1. ወ/ት Aይናለም ያለው - Aልቀረበችም።
በዚህ መዝገብ የቀረበልን ጉዳይ የኑዛዜ Aፃፃፍ ሥርዓትን የሚመለከት ነው።
ለዚሁ የሰበር Aቤቱታ ምክንያት የሆነው የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሟች Aቶ በቀለ ወልድ የሰጡት ኑዛዜ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 881 በሚያዘው መሰረት ኑዛዜው ከተፃፈ በኋላ መነበቡን ስለማይገልፅ ኑዛዜው ፈራሽ ብሎ በመወሰኑ ነው። ኑዛዜው ፈራሽ መሆን Aለበት የሚለውን ጥያቄ ያቀረቡት የAሁን መልስ ሰጪዎች ናቸው።
ተቃውሞውን ያቀረቡት በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቢሆንም የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረቡትን የኑዛዜ ይፍረስልን ተቃውሞ Aልተቀበለውም ነበር። ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለት የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤትም የቀረበለትን ይግባኝ ሳይቀበለው ቀርቷል።
የቀረበው የሰበር Aቤቱታ ኑዛዜው የህጉን መስፈርት የሚያሟላ በመሆኑ ይፍረስ መባሉ ትክክል Aይደለም የሚል ነው። መልስ ሰጪዎች በቃል ክርክር የሰጡት መልስ ደግሞ ኑዛዜው ሕጉ የሚጠይቀውን መስፈርት Eስካላሟላ ድረስ ፈራሽ ነው መባሉ Aግባብ ነው የሚል ነው።
ይህ ችሎት Aከራካሪ የሆነውን ኑዛዜ Aቅርቦ ተመልክቷል። ኑዛዜው በህጉ መሰረት በAራት ምስክሮች የተፈረመ ነው። ትናዛዡ ፈርመውበታል። ይኸው ፊርማ በEርግጥ የተናዛዥ መሆኑም የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ በሰጠው ትEዛዝ መሰረት በፖላስ የቴክኒከ ምርመራ ተረጋግጧል።
ከዚህ በተጨማሪ የኑዛዜው የመጨረሻው ክፍል “Eኛም ከዚህ በላይ ስማችን የተጠቀሰው Eማኞች ይህንን ኑዛዜ Aቶ በቀለ ወልድ በህይወትና በንፁህ AEምሮ Eያሉ Eና በተስተካከለ የጤና Aቋም ላይ Eያሉ ሲናዘዙ ሰምተናል” ይላል። ከዚህ ቀጥሎ “Eኔም ከዚህ በላይ የተገለፀውን የኑዛዜውን ቃል ተፈጻሚ ይሆን ዘንድ በተለመደው ፊርማዬ Aረጋግጣለሁ” የሚል Aረፍተ ነገርና ፊርማ ይገኝበታል።
የፍትሐብሕር ሕጉ ቁጥር 881 ኑዛዜው በተናዛዡና በAራት ምስክሮች ፊት ካልተነበበ ዋጋ Eንደማይኖረው ይደነግጋል። ይህ ሥርዓት መፈፀሙ በኑዛዜው ላይ መገለጽ Eንዳለበትም ይደነግጋል። የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ኑዛዜው ውድቅ ያደረገው ኑዛዜው ምስክሮች ሟቹ ቃላቸውን ሲሰጡ መስማታቸውን ቢገልጽም ኑዛዜው ከተፃፈ በኋላ መነበቡን የሚገልጽ ነገር የለውም በማለት ነው። ሆኖም ከላይ ከተጠቀሰው የኑዛዜው ክፍል መገንዘብ Eንደሚቻለው ምስክሮቹ ሟቹ ሲናዘዝ መስማታቸውን ይገልፃል። ይህ የኑዛዜው Aገላለጽ ሟቹ ሲናገሩ መስማታቸውን ብቻ ሳይሆን የኑዛዜው ይዘት ከንግግሩ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ማረጋገጣቸው Eንደሚገልጽ ሆኖ መወሰድ ይኖርበታል። የኑዛዜው ሂደት ተከታትለው የሟች ንግግር /ቃል/ ከኑዛዜው ይዘት ጋር ለማመሳከር Eድል የነበራቸው Eንደሆነ በመገመት “ሲናዘዙ ሰምተናል” የሚለው ቃል ኑዛዜው ሲፃፍ የነበረውን ሂደት በAጠቃላይ በሚገልጽ ሁኔታ መረዳት ያስፈልጋል። በመሆኑም በዚህ ረገድ የከፍተኛው ፍ/ቤት ከተፃፈ በኋላ ኑዛዜው መነበቡን Aይገልጽም የሚለው መደምደምያ ከኑዛዜው ይዘት ጋር የሚጣጣም Aይደለም። ኑዛዜ ጥብቅ የሆነ ሥርዓት Eንዲከተል የሚፈለግ መሆኑ ከፍትሐብሕር ሕጉ ቁጥር 881 መገንዘብ የሚቻል ቢሆንም የEያንዳንዱ መስፈርት መሟላት መመዘን የሚገባው ግን የኑዛዜውን Aጠቃላይ ሁኔታ በመመልከትም ጭምርና ተናዛዥም ሆነ ምስክሮች /Eማኞች/ በኑዛዜው ባሰፈሩት ቃላትና ሀረጐች ላሰጡ የሚችለውንም ትርጉም ግምት ውስጥ በማስገባት ነው። የኑዛዜ ሥነ ሥርዓት ጥብቅ መሆን ዋና Aላማ ኑዛዜ የሟች ፍላጐት በትክክል የሚገልጽ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው። ሰነዶች ፎርማላቲው ያሟሉ Eንደሆነ መመርመር የሚገባቸውም ከዚሁ Aንፃር ነው።
Aሁን በያዝነው ጉዳይ ምስክሮች ኑዛዜው ሟቹ በትክክለኛ AEምሮ Eያሉ ሲሰጡ መስማታቸውን ገልፀዋል። የኑዛዜ መሰጠት ሥርዓት ተናዛዥ ሲናገር ማድመጥ ብቻ ሳይሆን የተባለውን ሁሉ በጽሁፍ ማስፈርን የሚያጠቃልል ነው። በመሆኑም ይኸው Aገላለጽ ምስክሮች ኑዛዜው ሲነበብ መስማታቸውን ለመግለጽ ጭምር Eንደተጠቀሙበት መገንዘብ የተሻለ የኑዛዜው Aተረጋጐም ሆኖ Aግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ ጥቅምት 18 ቀን 1998 Eንዲሁም የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 22174 ታህሣሥ 26 ቀን 1998 የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የፍድራል መጀመሪያ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 373/93 በ4/11/94 የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
ሚያዝያ 09 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- Aቶ መንበረፀሐይ ታደሰ Aቶ ፍስሐ ወርቅነህ Aቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ Aቶ Aሰግድ ጋሻው Aቶ ተሻገር ገ/ሥላሴ Aመልካች ፡- Aፍሪካ Iንሹራንስ ተጠሪ፡- Aቶ ብስራት ጐላ የIንሹራንስ ክርክር - የIንሹራንስ ውል - ከውል ውጪ ኃላፊነት የOሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የOሮሚያ ም/ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ቀረብኝ የሚለውን የተጣራ ገቢ በቀን ብር 250 በድምሩ Eንዲከፈለው የሰጠውን ውሣኔ በማፅናቱ በተቃውሞ የቀረበ Aቤቱታ ነው።
ውሣኔ፡ - የOሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የOሮሚያ ም/ሐረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የIንሹራንስ ሽፋን ያለው ተከሣሽ በሶስተኛ ወገን ላይ ጉዳት ባደረሰ ጊዜ ፍርድ ቤቶች የተከራካሪዎችን መብትና ግድታ ለመወሰን ውልንና ከውል ውጪ ያሉ ሕጐችን ተፈፃሚ ማድረግ ይችላሉ።
በመድን ሰጪውና በተከሣሹ መካከል ያለው ግንኙነት በውል ላይ የተመሰረተ በመሆኑ መድን ሰጪው ላገደድ የሚችልበት የካሳ መጠን በመድን ውሉ የተመለከተው ነው።
No topics extracted.