No summary available.
ሚያዚያ 9 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ መስፍን እቁበዮናስ አቶ አሰግድ ጋሻው ወ/ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- አቶ እንዳሻው በቀለ ተጠሪ፡- እነ ወ/ት አይናለም ያለው ውርስ - ኑዛዜ - የኑዛዜ አፃፃፍ ስርአት - የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 881፣ የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍድራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሟች አቶ በቀለ ወልድ የሰጡት ኑዛዜ ከተፃፈ በኋላ መነበቡን ስለማይገልጽ ፈራሽ ነው ብሎ የሰጠውን ውሣኔ በማፅናቱ በተቃውሞ የቀረበ አቤቱታ ነው።
ውሣኔ፡ - የፍድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የኑዛዜ ስነ ስርአት ጥብቅ መሆን ዋና አላማ ኑዛዜ የሟች ፍላጐት በትክክል የሚገልጽ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው።
ሰነዶች ፎርማላቲውን ያሟሉ እንደሆነ መመርመር የሚገባቸው ከዚህ አላማ አንፃር ነው።
የኑዛዜ እያንዳንዱ መስፈርት መሟላት መመዘን የሚገባው የኑዛዜውን አጠቃላይ ሁኔታ በመመልከትና ተናዛዥም ሆነ ምስክሮች /እማኞች/ በኑዛዜው ባሰፈሩት ቃላትና ሃረጎች ላሰጡ የሚችለውን ትርጉም ግምት ውስጥ በማስገባት ነው።
97 98
ሚያዚያ 9 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ፍስሐ ወርቅነህ መስፍን እቁበዮናስ አሰግድ ጋሻው ሂሩት መለሰ አመልካች፡- አቶ እንዳሻው በቀለ - ጠበቃ አሰፋ ዝቅአርጋቸው ቀረቡ።
መልስ ሰጭ፡- 1. ወ/ት አይናለም ያለው - አልቀረበችም።
በዚህ መዝገብ የቀረበልን ጉዳይ የኑዛዜ አፃፃፍ ሥርዓትን የሚመለከት ነው።
ለዚሁ የሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነው የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሟች አቶ በቀለ ወልድ የሰጡት ኑዛዜ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 881 በሚያዘው መሰረት ኑዛዜው ከተፃፈ በኋላ መነበቡን ስለማይገልፅ ኑዛዜው ፈራሽ ብሎ በመወሰኑ ነው። ኑዛዜው ፈራሽ መሆን አለበት የሚለውን ጥያቄ ያቀረቡት የአሁን መልስ ሰጪዎች ናቸው።
ተቃውሞውን ያቀረቡት በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቢሆንም የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረቡትን የኑዛዜ ይፍረስልን ተቃውሞ አልተቀበለውም ነበር። ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለት የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤትም የቀረበለትን ይግባኝ ሳይቀበለው ቀርቷል።
የቀረበው የሰበር አቤቱታ ኑዛዜው የህጉን መስፈርት የሚያሟላ በመሆኑ ይፍረስ መባሉ ትክክል አይደለም የሚል ነው። መልስ ሰጪዎች በቃል ክርክር የሰጡት መልስ ደግሞ ኑዛዜው ሕጉ የሚጠይቀውን መስፈርት እስካላሟላ ድረስ ፈራሽ ነው መባሉ አግባብ ነው የሚል ነው።
ይህ ችሎት አከራካሪ የሆነውን ኑዛዜ አቅርቦ ተመልክቷል። ኑዛዜው በህጉ መሰረት በአራት ምስክሮች የተፈረመ ነው። ትናዛዡ ፈርመውበታል። ይኸው ፊርማ በእርግጥ የተናዛዥ መሆኑም የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ በሰጠው ትእዛዝ መሰረት በፖላስ የቴክኒከ ምርመራ ተረጋግጧል።
ከዚህ በተጨማሪ የኑዛዜው የመጨረሻው ክፍል “እኛም ከዚህ በላይ ስማችን የተጠቀሰው እማኞች ይህንን ኑዛዜ አቶ በቀለ ወልድ በህይወትና በንፁህ አእምሮ እያሉ እና በተስተካከለ የጤና አቋም ላይ እያሉ ሲናዘዙ ሰምተናል” ይላል። ከዚህ ቀጥሎ “እኔም ከዚህ በላይ የተገለፀውን የኑዛዜውን ቃል ተፈጻሚ ይሆን ዘንድ በተለመደው ፊርማዬ አረጋግጣለሁ” የሚል አረፍተ ነገርና ፊርማ ይገኝበታል።
የፍትሐብሕር ሕጉ ቁጥር 881 ኑዛዜው በተናዛዡና በአራት ምስክሮች ፊት ካልተነበበ ዋጋ እንደማይኖረው ይደነግጋል። ይህ ሥርዓት መፈፀሙ በኑዛዜው ላይ መገለጽ እንዳለበትም ይደነግጋል። የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ኑዛዜው ውድቅ ያደረገው ኑዛዜው ምስክሮች ሟቹ ቃላቸውን ሲሰጡ መስማታቸውን ቢገልጽም ኑዛዜው ከተፃፈ በኋላ መነበቡን የሚገልጽ ነገር የለውም በማለት ነው። ሆኖም ከላይ ከተጠቀሰው የኑዛዜው ክፍል መገንዘብ እንደሚቻለው ምስክሮቹ ሟቹ ሲናዘዝ መስማታቸውን ይገልፃል። ይህ የኑዛዜው አገላለጽ ሟቹ ሲናገሩ መስማታቸውን ብቻ ሳይሆን የኑዛዜው ይዘት ከንግግሩ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ማረጋገጣቸው እንደሚገልጽ ሆኖ መወሰድ ይኖርበታል። የኑዛዜው ሂደት ተከታትለው የሟች ንግግር /ቃል/ ከኑዛዜው ይዘት ጋር ለማመሳከር እድል የነበራቸው እንደሆነ በመገመት “ሲናዘዙ ሰምተናል” የሚለው ቃል ኑዛዜው ሲፃፍ የነበረውን ሂደት በአጠቃላይ በሚገልጽ ሁኔታ መረዳት ያስፈልጋል። በመሆኑም በዚህ ረገድ የከፍተኛው ፍ/ቤት ከተፃፈ በኋላ ኑዛዜው መነበቡን አይገልጽም የሚለው መደምደምያ ከኑዛዜው ይዘት ጋር የሚጣጣም አይደለም። ኑዛዜ ጥብቅ የሆነ ሥርዓት እንዲከተል የሚፈለግ መሆኑ ከፍትሐብሕር ሕጉ ቁጥር 881 መገንዘብ የሚቻል ቢሆንም የእያንዳንዱ መስፈርት መሟላት መመዘን የሚገባው ግን የኑዛዜውን አጠቃላይ ሁኔታ በመመልከትም ጭምርና ተናዛዥም ሆነ ምስክሮች /እማኞች/ በኑዛዜው ባሰፈሩት ቃላትና ሀረጐች ላሰጡ የሚችለውንም ትርጉም ግምት ውስጥ በማስገባት ነው። የኑዛዜ ሥነ ሥርዓት ጥብቅ መሆን ዋና አላማ ኑዛዜ የሟች ፍላጐት በትክክል የሚገልጽ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው። ሰነዶች ፎርማላቲው ያሟሉ እንደሆነ መመርመር የሚገባቸውም ከዚሁ አንፃር ነው።
አሁን በያዝነው ጉዳይ ምስክሮች ኑዛዜው ሟቹ በትክክለኛ አእምሮ እያሉ ሲሰጡ መስማታቸውን ገልፀዋል። የኑዛዜ መሰጠት ሥርዓት ተናዛዥ ሲናገር ማድመጥ ብቻ ሳይሆን የተባለውን ሁሉ በጽሁፍ ማስፈርን የሚያጠቃልል ነው። በመሆኑም ይኸው አገላለጽ ምስክሮች ኑዛዜው ሲነበብ መስማታቸውን ለመግለጽ ጭምር እንደተጠቀሙበት መገንዘብ የተሻለ የኑዛዜው አተረጋጐም ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመዝገብ ጥቅምት 18 ቀን 1998 እንዲሁም የፍድራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 22174 ታህሣሥ 26 ቀን 1998 የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የፍድራል መጀመሪያ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 373/93 በ4/11/94 የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
No topics extracted.