No summary available.
ሚያዝያ 16 ቀን 1999 ዓ.ም.
ዳኞች፡- Aቶ መንበረፀሐይ ታደሰ Aቶ Aሰግድ ጋሻው Aቶ መስፍን Eቁበዮናስ ወ/ሪት ሒሩት መለሰ Aቶ ተሻገር ገ/ሥላሴ Aመልካቾች፡- 1. ወ/ሮ ደሐብ ሰIድ 2. ወ/ሮ ሶፊያ Eንድሪስ ወ/ሮ ሦፍያ Eንድሪስ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን ፍረድ ሰጥተናል።
ለዚህ የሰበር Aቤቱታ መነሻ የሆነው ውሣኔ የተሰጠው በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው።
የAሁን Aመልካቾች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 የተመለከተውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ከዚህ በፊት ተጠሪው ለዚህ የመጀመሪያ ደረጀ ፍ/ቤት የAቶ Eንድሪስ Aደም ልጅ ነኝ በማለት ያስወሰነ መሆኑን ተረድተናል። ሆኖም Aቶ Eንድሪስ Aደም 1ኛ ተቃዋሚን ወ/ሮ ደሐብ ሲይድን Aግብተው የኖሩ ከመሆኑ በስተቀር ልላ ሚስትም ሆነ ልጅ የላቸውም። ስለዚህ ውሣኔው ይሻርልን የሚል Aቤቱታ Aቅርብዋል።
የAሁን ተጠሪም በAመልካቾች በኩል የቀረበው ተቃውሞ ሕጋዊ መሰረት የለውም ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት መልስ ሰጥተዋል።
የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪ Aቶ Aብርሃም ካሣ የAቶ Eንድሪስ Aደም ልጅ ናቸው ወይስ Aይደሉም የሚለውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ ጋር Aገናዝቦ ከተመለከተ በኋላ ሰኔ 18 ቀን 1996 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ተጠሪ Aቶ Aብርሃም ካሣ በተወለዱ ጊዜ Eናታቸው Eና ሟች Aቶ Eንድሪስ Aደም ቀጣይነት ያለው የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሲፈጽሙ የነበረ በመሆኑና ሟቿም ልጁን /ተጠሪን/ በማሳደግ ሂደት ሲሳተፉ የነበረ ለመሆኑ በተጠሪ ማስረጃዎች የተረጋገጠ ሲሆን የAመልካቾች ማስረጃ ይህንኑ Aላስተባበለም። ስለሆነም ተጠሪ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ Aንቀጽ 143/መ/ Eና /ሰ/ መሰረት Aቶ Eንድሪስ Aደም የተጠሪው የAብርሃም ካሣ ወላጅ Aባት መሆናቸው የተገመተ ስለሆነ በተቃዋሚዎች Aማካይነት የቀረበውን የውሣኔ ይሰረዝልን ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል።
ይህም ውሣኔ ጉድለት የልለበት መሆኑን በመግለጽ የፍ/ከፍተኛው ፍ/ቤት በትEዛዝ መዝገቡን ዘግቶታል። የሰበር Aቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ ለማስለወጥ ነው። የAቤቱታው ፍሬ ቃልም፡በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ Aዋጅ ቁጥር 213/92 Aንቀጽ 126/1/ በጋብቻ ውስጥ የተፀነሰ ወይም የተወለደ ልጅ Aባቱ ነው የሚባለው ባልየው ነው ተብሎ የተደነገገውን በመተው በAንድ ወንድና በAንዲት ሴት መካከል የነበረው ጋብቻ ሳይፈርስ ከልላ ጋር ወዳጅነት በመፍጠር ልጅ ወልጃለሁ የሚለውን ተቀብለው የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ መስጠታቸው የሕግ ስህተትን ያስከተለ ነው። ለዚሁ ሕግ Aንቀጽ 143/መ/ Eና /ሰ/ መሰረት ፍ/ቤት Aባትነትን በግምት ላወስን የሚቻለው ከዚሁ ድንጋጌ ከፍ ብለው በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት የልጅ Aባት ያልታወቀ ወይም የተካዳ ሲሆን ብቻ መሆኑ Eየታወቀ ይህ ሁሉ ታልፎ የተሰጠው ውሣኔ የቤተሰብን ሕግ የተከተለ Aይደለም የሚል ነው።
ተጠሪም በበኩሉ የተጠሪ Eናት ባል ነበራቸው በሚል በAመልካቾች በኩል የቀረበ ክርክር የለም፤ በተጠሪ Eናት Eና በAቶ ካሣ መካከል ጋብቻ ነበረ Eንኳ ቢባል ለረጅም ጊዜ ተለያይተው መተማመንና መረዳዳት በጠፋበት ሁኔታ ትዳር/ጋብቻ Aለ ማለት Aይቻልም። ትዳር Aለ የሚለውን መነሻ በማድረግ የሕግ ግምት የሚወሰድ ከሆነ የተፈጥሮ Aባትነት የሚያሰጥ ነው። ስለሆነም ትዳር Aለ ቢባል Eንኳን የተለያዩት ለረዥም ዓመት በመሆኑ ግላዊ ግንኙነቱ የጠፋ በመሆኑ ፍ/ቤቱ የቤተሰብ ሕጉን ዓላማ በተቃረነ መልኩ ሕጉ መተርጎም ይገባዋል የሚለው ክርክር ተቀባይነት የለውም የሚል ነው።
Eኛም ጉዳዩን Aግባብነት ካለው ሕግ ጋር Aገናዝበን ተመልክተናል።
በዚህ ጉዳይ Aከራካሪው ነጥብ ተጠሪ የሟች የAቶ Eንድሪስ Aደም ልጅ መሆኑን ስለAባትነት ማወቅ /Ascertainment of paternity/ ሕጉ በደነገገው መሰረት Aስረድቷል ወይስ Aላስረዳም? የሚለው ነው።
ይህንን ጭብጥ Aስመልክቶ የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ መሰረት ያደረገው በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ Aዋጅ ቁጥር 213/92 በAንቀጽ 125/3/ Aና 143 /መ/ Eና /ሰ/ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች Eንደሆነ ከመዝገቡ ግልባጭ ተረድተናል።
ሆኖም በዚሁ ሕግ በAንቀጽ 143 መሰረት Aባትነትን በፍርድ መንገር የሚቻለው Aባት ማነው? የሚለውን በሚመለከት ለAባትነት ማወቅ መነሻ የሆኑትን በAንቀጽ 125/1/ መሰረት በሕግ ግምት Aባትነትን ማወቅ ካልተቻለ ወይም በAንቀጽ 125/2/ መሰረት Aባት የተባለው ሰው ልጅነት ሳይቀበል የቀረበ Eንደሆነ ብቻ ነው። ከዚህ በላይ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት የልጁ Aባት ያልታወቀ Eንደሆነ ከዚህ በታች የተመለከቱት ሁኔታዎች ሲሟሉ Aባትነት በፍርዱ ውሣኔ ላታወቅ ይችላል በሚል በAንቀጽ 143 ተደንግጓል። ከAንቀጽ 143 በላይ ያሉት ድንጋጌዎች ደግሞ በሕግ ግምት ወይም በማወቅ /Acknowledgment/ መሰረት Aባትነት የሚረጋገጥበትን መንገድ የሚዘረዝሩ 89 90 ናቸው። ይህም የሚያሳየው በAንቀጽ 125/1/ Aባትነት በሕግ ግምት ላታወቅ ከቻለ ወይም 125/2/ መሰረት በማወቅ ከተረጋገጠ ይህንን Aልፎ Aባትነትን በፍርድ መንገር /Ascertainment of [paternity by Judicial Declaration/ የማይቻል መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው።
No topics extracted.
Aሁን በተያዘው ጉዳይ ተጠሪ የተፀነሰው ወይም የተወለደው የተጠሪ Eናት ከልላ ሰው ጋር በሕግ ፀንቶ በቆየ ጋብቻ ተሳስራ በነበረበት ጊዜ የነበረ ስለመሆኑ Eራሳቸው የተጠሪ የሰው ማስረጃዎች ያረጋገጡት ጉዳይ ነው። ይህንን በማስመልከት የሰጡትን Aግባብነት ያለውን ቃል ለመጥቀስ ያሕልም የተጠሪ Eናት ከ196A ዓ.ም.
ጀምሮ ባል Aግብተው ይኖሩ ነበረ። ባልየው በሥራ ምክንያት ወደ ክ/ሀገር በሄደበት ጊዜ ከሟች ከEንዱሪስ Aደም ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፍጠራቸውን Eናውቃለን። በዚህም ግንኙነት ሳቢያ ተጠሪ በ1972 ዓ.ም. ተወለደ። በ1975 ዓ.ም.
የተጠሪ Eናት ባል ከሄደበት የሥራ ቦታ ተመልሰው ከተጠሪ Eናት ጋር መኖር ቀጠሉ። ድሮውንም ቢሆን Aልተፋቱም ነበር። ተጠሪም የሚጠራው በዚሁ ሰው በባልየው ስም ነው የሚለው ይገኝበታል።
Eነዚህ ፍሬ ነገሮች Eስከተረጋገጡ ድረስ የተጠሪ Aባት ማን የሚለውን ጥያቄ ምላሽ የሚያገኘው በAዋጅ ቁጥር 213/92 በAንቀጽ 128/1/ Eና ከAንቀጽ 126- 128 በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት ሕግ ያስቀመጠውን ግምት መነሻ በማድረግ ይሆናል። በዚህም መሰረት የተጠሪ Aባት የተጠሪን Eናት Aግብተው የነበሩት የተጠሪ Eናት ባል Eንጂ ሟች Aቶ Eንድሪስ Aደም ላሆኑ Aይችሉም።
በሕጉ ግምት Aባት የተባለው ሰው በበኩሉ ሕግ ያስቀመጠውን ግምት ላያፈርስ የሚችል ክርክር በማቅረብ በዚሁ Aዋጅ Aንቀጽ 167 Eና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ ልጁን የካዱ መሆኑን መነሻ በማድረግ የቀረበ ክርክርም Aልተገኘም።
በዚህ ሁሉ ምክንያት የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት በግራ ቀኙ ክርክር Aግባብነት የልላቸውን በAንቀጽ 143/መ/ Eና /ሰ/ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ ውሣኔ መስጠቱ የሕግ ስህተት መፈፀሙን Aረጋግጠናል።
ው ሣ ኔ
የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 3753 በ18/10/96 የሰጠው ውሣኔ Eና የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ25/01/98 የሰጠው ትEዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ ተሽሯል።
ሟች Eንድሪስ Aደም የተጠሪ የAብርሃም ለማ Aባት መሆናቸው Aልተረጋገም በማለት ወስነናል።
ይህ የሰበር ክርክር ላስከተለው ኪሣራና ወጭ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ ብለናል። መዝገቡ ተዘግቷል።