No summary available.
ሚያዝያ 16 ቀን 1999 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ አሰግድ ጋሻው አቶ መስፍን እቁበዮናስ ወ/ሪት ሒሩት መለሰ አቶ ተሻገር ገ/ሥላሴ አመልካቾች፡- እነ ወ/ሮ ደሐብ ሰኢድ ተጠሪ፡- አቶ አብረሃም ካሣ ልጅነትን ስለመካድ - አባትነትን በግምት መወሰን - በማወቅ አባትነት የሚረጋገጥበት መሰረት - የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ቁ/126/1/፣ 143/መ/ና/ሰ/ የፍድራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሟች አቶ እንድሪስ አደም የተጠሪው ወላጅ አባት ናቸው ሲል የሰጠውን ውሣኔ በማፅናቱ በተቃውሞ የቀረበ አቤቱታ ነው።
ውሣኔ፡ - የፍድራል መጀመሪያና ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሸሯል።
በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ ቁ. 143 መሰረት አባትነትን በፍርድ መንገር የሚቻለው አባት ማን ነው የሚለውን ለአባትነት መነሻ የሆኑትን በአንቀጽ 125/1/ መሰረት በህግ ግምት ማወቅ ካልተቻለ ወይም በአንቀጽ 125/2/ መሰረት አባት የተባለው ሰው ልጅነትን ሳይቀበል የቀረበ እንደሆነ ብቻ ነው።
አንድ እናት በህጋዊ ጋብቻ ውስጥ እያለች ልጅ ከተወለደ የልጁ አባት ማን ነው የሚለው ምላሽ የሚያገኘው በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ ቁ. አንቀጽ 128/1/ እና ከአንቀጽ 126 – 128 በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት ህግ ያስቀመጠውን ግምት መነሻ በማድረግ ነው።
በህጉ ግምት አባት የተባለው ሰው ህጉ ያስቀመጠውን ግምት ላያፈርስ የሚችል ክርክር በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ ቁ. 167 ላያቀርበ ይችላል።
87 88
ሚያዝያ 16 ቀን 1999 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ አሰግድ ጋሻው አቶ መስፍን እቁበዮናስ ወ/ሪት ሒሩት መለሰ አቶ ተሻገር ገ/ሥላሴ አመልካቾች፡-
ወ/ሮ ደሐብ ሰኢድ
ወ/ሮ ሶፊያ እንድሪስ ወ/ሮ ሦፍያ እንድሪስ ቀረቡ።
አቶ ኡመር እንድሪስ ተጠሪ፡- አቶ አብረሃም ካሣ - ቀረበ።
መዝገቡን መርምረን ፍረድ ሰጥተናል።
ለዚህ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ውሣኔ የተሰጠው በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው።
የአሁን አመልካቾች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 የተመለከተውን ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ከዚህ በፊት ተጠሪው ለዚህ የመጀመሪያ ደረጀ ፍ/ቤት የአቶ እንድሪስ አደም ልጅ ነኝ በማለት ያስወሰነ መሆኑን ተረድተናል። ሆኖም አቶ እንድሪስ አደም 1ኛ ተቃዋሚን ወ/ሮ ደሐብ ሲይድን አግብተው የኖሩ ከመሆኑ በስተቀር ልላ ሚስትም ሆነ ልጅ የላቸውም። ስለዚህ ውሣኔው ይሻርልን የሚል አቤቱታ አቅርብዋል።
የአሁን ተጠሪም በአመልካቾች በኩል የቀረበው ተቃውሞ ሕጋዊ መሰረት የለውም ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት መልስ ሰጥተዋል።
የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪ አቶ አብርሃም ካሣ የአቶ እንድሪስ አደም ልጅ ናቸው ወይስ አይደሉም የሚለውን ነጥብ ከግራ ቀኙ ክርክርና ማስረጃ ጋር አገናዝቦ ከተመለከተ በኋላ ሰኔ 18 ቀን 1996 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ተጠሪ አቶ አብርሃም ካሣ በተወለዱ ጊዜ እናታቸው እና ሟች አቶ እንድሪስ አደም ቀጣይነት ያለው የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሲፈጽሙ የነበረ በመሆኑና ሟቿም ልጁን /ተጠሪን/ በማሳደግ ሂደት ሲሳተፉ የነበረ ለመሆኑ በተጠሪ ማስረጃዎች የተረጋገጠ ሲሆን የአመልካቾች ማስረጃ ይህንኑ አላስተባበለም። ስለሆነም ተጠሪ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 143/መ/ እና /ሰ/ መሰረት አቶ እንድሪስ አደም የተጠሪው የአብርሃም ካሣ ወላጅ አባት መሆናቸው የተገመተ ስለሆነ በተቃዋሚዎች አማካይነት የቀረበውን የውሣኔ ይሰረዝልን ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል።
ይህም ውሣኔ ጉድለት የልለበት መሆኑን በመግለጽ የፍ/ከፍተኛው ፍ/ቤት በትእዛዝ መዝገቡን ዘግቶታል። የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ ለማስለወጥ ነው። የአቤቱታው ፍሬ ቃልም፡በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 126/1/ በጋብቻ ውስጥ የተፀነሰ ወይም የተወለደ ልጅ አባቱ ነው የሚባለው ባልየው ነው ተብሎ የተደነገገውን በመተው በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የነበረው ጋብቻ ሳይፈርስ ከልላ ጋር ወዳጅነት በመፍጠር ልጅ ወልጃለሁ የሚለውን ተቀብለው የሥር ፍ/ቤት ውሣኔ መስጠታቸው የሕግ ስህተትን ያስከተለ ነው። ለዚሁ ሕግ አንቀጽ 143/መ/ እና /ሰ/ መሰረት ፍ/ቤት አባትነትን በግምት ላወስን የሚቻለው ከዚሁ ድንጋጌ ከፍ ብለው በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት የልጅ አባት ያልታወቀ ወይም የተካዳ ሲሆን ብቻ መሆኑ እየታወቀ ይህ ሁሉ ታልፎ የተሰጠው ውሣኔ የቤተሰብን ሕግ የተከተለ አይደለም የሚል ነው።
ተጠሪም በበኩሉ የተጠሪ እናት ባል ነበራቸው በሚል በአመልካቾች በኩል የቀረበ ክርክር የለም፤ በተጠሪ እናት እና በአቶ ካሣ መካከል ጋብቻ ነበረ እንኳ ቢባል ለረጅም ጊዜ ተለያይተው መተማመንና መረዳዳት በጠፋበት ሁኔታ ትዳር/ጋብቻ አለ ማለት አይቻልም። ትዳር አለ የሚለውን መነሻ በማድረግ የሕግ ግምት የሚወሰድ ከሆነ የተፈጥሮ አባትነት የሚያሰጥ ነው። ስለሆነም ትዳር አለ ቢባል እንኳን የተለያዩት ለረዥም ዓመት በመሆኑ ግላዊ ግንኙነቱ የጠፋ በመሆኑ ፍ/ቤቱ የቤተሰብ ሕጉን ዓላማ በተቃረነ መልኩ ሕጉ መተርጎም ይገባዋል የሚለው ክርክር ተቀባይነት የለውም የሚል ነው።
እኛም ጉዳዩን አግባብነት ካለው ሕግ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
በዚህ ጉዳይ አከራካሪው ነጥብ ተጠሪ የሟች የአቶ እንድሪስ አደም ልጅ መሆኑን ስለአባትነት ማወቅ /Ascertainment of paternity/ ሕጉ በደነገገው መሰረት አስረድቷል ወይስ አላስረዳም? የሚለው ነው።
ይህንን ጭብጥ አስመልክቶ የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ መሰረት ያደረገው በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/92 በአንቀጽ 125/3/ አና 143 /መ/ እና /ሰ/ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች እንደሆነ ከመዝገቡ ግልባጭ ተረድተናል።
ሆኖም በዚሁ ሕግ በአንቀጽ 143 መሰረት አባትነትን በፍርድ መንገር የሚቻለው አባት ማነው? የሚለውን በሚመለከት ለአባትነት ማወቅ መነሻ የሆኑትን በአንቀጽ 125/1/ መሰረት በሕግ ግምት አባትነትን ማወቅ ካልተቻለ ወይም በአንቀጽ 125/2/ መሰረት አባት የተባለው ሰው ልጅነት ሳይቀበል የቀረበ እንደሆነ ብቻ ነው። ከዚህ በላይ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት የልጁ አባት ያልታወቀ እንደሆነ ከዚህ በታች የተመለከቱት ሁኔታዎች ሲሟሉ አባትነት በፍርዱ ውሣኔ ላታወቅ ይችላል በሚል በአንቀጽ 143 ተደንግጓል። ከአንቀጽ 143 በላይ ያሉት ድንጋጌዎች ደግሞ በሕግ ግምት ወይም በማወቅ /Acknowledgment/ መሰረት አባትነት የሚረጋገጥበትን መንገድ የሚዘረዝሩ 89 90 ናቸው። ይህም የሚያሳየው በአንቀጽ 125/1/ አባትነት በሕግ ግምት ላታወቅ ከቻለ ወይም 125/2/ መሰረት በማወቅ ከተረጋገጠ ይህንን አልፎ አባትነትን በፍርድ መንገር /Ascertainment of [paternity by Judicial Declaration/ የማይቻል መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው።
አሁን በተያዘው ጉዳይ ተጠሪ የተፀነሰው ወይም የተወለደው የተጠሪ እናት ከልላ ሰው ጋር በሕግ ፀንቶ በቆየ ጋብቻ ተሳስራ በነበረበት ጊዜ የነበረ ስለመሆኑ እራሳቸው የተጠሪ የሰው ማስረጃዎች ያረጋገጡት ጉዳይ ነው። ይህንን በማስመልከት የሰጡትን አግባብነት ያለውን ቃል ለመጥቀስ ያሕልም የተጠሪ እናት ከ196A ዓ.ም.
ጀምሮ ባል አግብተው ይኖሩ ነበረ። ባልየው በሥራ ምክንያት ወደ ክ/ሀገር በሄደበት ጊዜ ከሟች ከእንዱሪስ አደም ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፍጠራቸውን እናውቃለን። በዚህም ግንኙነት ሳቢያ ተጠሪ በ1972 ዓ.ም. ተወለደ። በ1975 ዓ.ም.
የተጠሪ እናት ባል ከሄደበት የሥራ ቦታ ተመልሰው ከተጠሪ እናት ጋር መኖር ቀጠሉ። ድሮውንም ቢሆን አልተፋቱም ነበር። ተጠሪም የሚጠራው በዚሁ ሰው በባልየው ስም ነው የሚለው ይገኝበታል።
እነዚህ ፍሬ ነገሮች እስከተረጋገጡ ድረስ የተጠሪ አባት ማን የሚለውን ጥያቄ ምላሽ የሚያገኘው በአዋጅ ቁጥር 213/92 በአንቀጽ 128/1/ እና ከአንቀጽ 126- 128 በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሰረት ሕግ ያስቀመጠውን ግምት መነሻ በማድረግ ይሆናል። በዚህም መሰረት የተጠሪ አባት የተጠሪን እናት አግብተው የነበሩት የተጠሪ እናት ባል እንጂ ሟች አቶ እንድሪስ አደም ላሆኑ አይችሉም።
በሕጉ ግምት አባት የተባለው ሰው በበኩሉ ሕግ ያስቀመጠውን ግምት ላያፈርስ የሚችል ክርክር በማቅረብ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 167 እና ተከታይ ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ ልጁን የካዱ መሆኑን መነሻ በማድረግ የቀረበ ክርክርም አልተገኘም።
በዚህ ሁሉ ምክንያት የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት በግራ ቀኙ ክርክር አግባብነት የልላቸውን በአንቀጽ 143/መ/ እና /ሰ/ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ ውሣኔ መስጠቱ የሕግ ስህተት መፈፀሙን አረጋግጠናል።
ው ሣ ኔ
የመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 3753 በ18/10/96 የሰጠው ውሣኔ እና የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ25/01/98 የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ ተሽሯል።
ሟች እንድሪስ አደም የተጠሪ የአብርሃም ለማ አባት መሆናቸው አልተረጋገም በማለት ወስነናል።
ይህ የሰበር ክርክር ላስከተለው ኪሣራና ወጭ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ ብለናል። መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.