No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 2A938 ሚያዝያ 11/99 ዓ.ም.
ዳኞች፡- Aቶ መንበረፀሐይ ታደሰ Aቶ ፍስሐ ወርቅነህ Aቶ Aብዱልቃድር መሐመድ Aቶ Aሰግድ ጋሻው ወ/ት ሒሩት መለሰ Aመልካች፡- ወ/ሮ ሸዋዬ ተሰማ ቀርባለች።
መልስ ሰጪ፡- ወ/ሮ ሣራ ልንጋነ Aልቀረበችም።
Aመልካች ለሰበር ችሎት ያቀረቡት ማመልከቻ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መልስ ሰጪ የሟች የAቶ ይልማ ወ/ሃና ሚስት ነበሩ በማለት የሰጠው ውሣኔ Eንዲሻርላቸው የሚጠይቅ ነው። Aመልካች መ/ሰጪ የሟቹ የAቶ ይልማ ወ/ሃና ሚስት Aይደሉም በማለት ተቃውሞ ያቀረቡት ለፍድራል የመጀመሪያ ፍ/ቤት ነው።
ተቃውሞው ለዚህ ፍ/ቤት ያቀረቡት ፍ/ቤት ቀደም ሲል ግንቦት 15/95 በዋለው ችሎት መልስ ሰጪ ወ/ሮ ሣራ ልንጋነ የሟች የAቶ ይልማ ወ/ሃና ሚስት ነች በማለት በመስጠቱ ነው። ተቃውሞው የቀረበለት ፍ/ቤትም Aመልካች ሚስት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ Aቅርበዋል በልላ በኩል መልስ ሰጪ ከሟቹ ጋር ጋብቻ የነበራቸው መሆኑ ስለተረጋገጠና በAመልካቹ በኩል ውላቸው መፍረሱን የሚያሳይ ማስረጃ ባለመቅረቡ ቀደም ሲል መልስ ሰጪ የሟች ሚስት ናት በማለት የተሰጠው ውሣኔ የሚለወጥበት ምክንያት የለም በማለት ውሣኔው Aጽንቶታል።
Aመልካች ይግባኝ ለከፍተኛው ፍ/ቤት ቢያቀርቡም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ማመልከቻውን Aይቶ ይግባኙን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት Aያስቀርብም በማለት ዘግቶታል። የሰበር Aቤቱታ የቀረበውም ይህን ውሣኔ ለማስለወጥ ነው።
የሰበር Aቤቱታ መሰረታዊ ቅሬታ መልስ ሰጪ ከሟች ጋር የነበራት ጋብቻ በገዛ ፈቃዷ Aፍርሳ ከልላ ሰው ጋር ከ1977 በፊት ጀምሮ ትዳር በመመስረቷ የሟቹ ሚስት ፈት ላባል Aይገባም፣ ሟች ከAመልካች ጋብቻ የፈፀመው ልላ ጋብቻ ስላልፈፀመ ነው፣ የመልስ መሰጪን ጋብቻ መፍረስ ያውቁ የነበሩ ምስክር ቀርበው Eንዳይመሰክሩ መደረጉ Eውነቱ Eንዳይወጣ መደረጉን ያሳያል። Aቶ ይልማ የሞቱት በ1989 ሆኖ ሣለ መልስ ሰጪ ግን በ1981 ነው የሞቱት ብላ ለፍ/ቤት ማመልከቷ ጉዳዩን የተቀነባበረና የሚስትነት ጥያቄውን ከ14 ዓመት በኋላ መቅረቡን ያስረዳል የሚል ነው።
በመልስ ሰጪ የቀረበው መልስ ደግሞ መልስ ሰጪና ሟች መጋባታቸው በማስረጃ ስለተረጋገጠና ጋብቻ የሚፈርስባቸው በሕግ ከሚታወቅባቸው ምክንያቶት Aንዱ መኖሩ ስላልተረጋገጠ የሟችና የመልስ ሰጪ ጋብቻ ፈርሷል ላባል Aይችልም፣ የሟችና የAመልካች ጋብቻ መጀመሪያ የተፈፀመውን ጋብቻ Aያስቀርም፣ መልስ ሰጪ ከልላ ሰው ሁለት ልጆች መውለዳቸውም ሆነ የሞቱበትን ቀን 1981 ብለው መጥቀሳቸውም Eንደዚሁ ሚስትታቸውን Aያስቀርም፤
የሚስትነት ማረጋገጫው የተሰጠው ሟቹ በ1989 ዓ.ም. ሞተዋል በማለት በመሆኑ የAመልካች ቅሬታ መሰረት የለውም፣ በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ የሕግ ስህተት ስለልለበት ላፀና ይገባል የሚል ነው።
ይህ ችሎት የግራ ቀኙን ክርክር Aግባብ ካላቸው ሕጎች ጋር በማያያዝ ተመልክቷል። ከመዝገቡ Eንደተረዳነው Aመልካችም ሆነ መልስ ሰጪ ከሟች Aቶ ይልማ ወ/ሃና ጋር ጋብቻ መፈፀማቸው ተረጋግጦAል። መ/ሰጪ ሚስት መሆናቸውን ለማረጋገጥ በ1966 የተጋቡበት የጋብቻ ውል በ6/6/72 የተሞላ የሕይወት ታሪክ /ሟች ይሰሩበት ከነበረው የቡና ገበያ ድርጅት ማኀደር የተገኘ/ Eንዲሁም ጥር 19/1974 በጡረታ ቅጽ ላይ ሚስት ተብለው የተሞላበት ሰነድ ቀርቦAል። Aመልካቹ በበኩላቸው በ1987 ዓ.ም. ከሟች ጋር መጋባታቸው ማስረጃ ቀርቦ ሚስትታቸው በልላ ተረጋግጧል።
በልላ በኩል Aመልካች ባቀረቡት መቃወሚያ መነሻነት የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባደረገው ማጣራት መልስ ሰጪ ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ቃል ሟቹና መ/ሰጪ Eስከ 1985 Aብረው ከኖሩ በኋላ በ1985 ዓ.ም. ተጣልተው መ/ሰጪ ወደ Aዲስ Aበባ መምጣታቸውን በኋላ ደግሞ ሟቹ Aቶ ይልማ Aመልካቿን ወ/ሮ ሸዋዬን Aግብተው Aጋሮ መሄዳቸውን Eንደሰሙ በፍርዱ ቤቱ Aስረድተዋል። ከዚህ በተጨማሪ ከሟች ጋር የነበረው ጋብቻ በፍቺ Aለመፍረሱም ገልፀዋል በቃል በተደረገው ማብራሪያ የAሁን Aመልካች ስለፍቺው ያውቁ Eንደሆነ ተጠይቀው ሟቹ ከመልስ ሰጪ ጋር ጋብቻ የነበረው መሆኑን ስለማናውቅ ስለፍቺው Aናውቅም ብለዋል።
ከዚህ መገንዘብ የቻልነው የAሁንዋ መልስ ሰጪ ምንም Eንኳ ከሟቹ ጋር ቀደም ብሎ የተፈፀመ ጋብቻ የነበራቸው ቢሆንም በመካከላቸው በተፈጠረ Aለመግባባት ምክንያት በነበረው ጋብቻ መቀጠል Aለመቻላቸውንና ሁለቱ በየፊናቸው የየራሳቸው ሕይወት መጀመራቸውን ነው። የAሁን መልስ ሰጪ ጋብቻው በፍቺ ምክንያት Aልፈረሰም ይባል Eንጂ ለፍርድ ቤቱ የሰጡት ማረጋገጫ ጋብቻው መፍረሱን የሚያረጋግጥ ነው። ጋብቻ የሚፈርሰው ሕጉ ባስቀመጣቸው ውሱን ምክንያት መሆኑን ይህም ፍ/ቤት ይቀበለዋል። በልላ 85 86 በኩል ለጋብቻ መፍረስ ምክንያቶች የሆኑ ነገሮች መኖር Aለመኖራቸውን የሚረጋግጠው Eንድት ነው የሚለው ጥያቄና ነጥብ በሁለቱም ተጋቢዎች ከነበረው ሁኔታ ጭምር መረዳት የሚችል ነው። ጋብቻ የሚፈርስበትን ምክንያት መፍረሱን ከማስረዳት መለየትም ያስፈልጋል። Aሁን በቀረበልን ጉዳይ የመልስ ሰጪ መከራከሪያ ፍቺ መፈፀሙን Aመልካች Aላስረዳችም የሚል ነው። ነገር ግን የመልስ ሰጪና የሟች ግንኙነት ማንም ልላ ማስረጃ ላያስረዳ ከሚችለው ከሚገልፀው በላይ በመካከላቸው የነበረው የጋብቻ ግንኙት መፍረሱ ሁለቱም ልላ ሕይወት ጀምረው ሟቹ የAሁንዋን Aመልካች ማግባታቸውን፣ ይህንንም ጋብቻ የAሁኗን መልስ ሰጪ ያውቁ Eንደነበር ያስረዳል። ይህ በመሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ የAሁንዋን መልስ ሰጪ ቀደም ሲል የፈፀመችውን ጋብቻ መሰረት በማድረግ ብቻ ሚስት ናት ብሎ መወሰኑ ትክክለኛ የሕግ Aተረጓጎም Aይደለም።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ የፍድራል መጀመሪያት በመ/ቁ 4796 ሚያዝያ 18 ቀን 1997 ዓ.ም.
የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
ወ/ሮ ሣራ ልንጋነ የሟች የAቶ ይልማ ወ/ሃና ሚስት Aይደለችም በማለት ወስነናል፣ ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ።