ሰራተኛው በየአመቱ ውሉ እየታደሰ ሲሰራ መቆየቱና የሰራተኛው የቅጥር ውል በጊዜ የተገደበ መሆኑ ብቻ ለተወሰነ ጊዜ ተቀጣሪ የሚያደርገው ስላለመሆኑ / #### #### የሰ/መ/ቁ 25526 / መምህር ጥላሁን አስፋው እና አዲስ ኮልጅ/ ውል
No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 2A938 ሚያዝያ 11/99 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ አቶ አሰግድ ጋሻው ወ/ት ሒሩት መለሰ አመልካች፡- ወ/ሮ ሸዋዬ ተሰማ ተጠሪ፡- እነ ወ/ሮ ሣራ ልንጋነ ጋብቻ - የጋብቻን መፍረስ ስለማስረዳት የፍድራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ የሟች የአቶ ይልማ ወ/ሃና ሚስት ናቸው ሲል የሰጠውን ውሣኔ በማፅናቱ በተቃውሞ የቀረበ አቤቱታ ነው።
ውሣኔ፡ - የፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
ጋብቻ የሚፈርሰው ህጉ ባስቀመጣቸው ውሱን ምክንያቶች ነው።
ጋብቻ የሚፈርስበትን ምክንያት መፍረሱን ከማስረዳት መለየት ያስፈልጋል።
ተጋቢዎች ምንም እንኳን ቀደም ብሎ የተፈፀመ ጋብቻ የነበራቸው ቢሆንም በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት መቀጠል አለመቻላቸውና ሁለቱ በየፊናቸው የየራሳቸውን ሕይወት መጀመራቸው እያለ ፍቺ መፈፀሙን አንደኛው ተጋቢ አላስረዳም የሚል ውሣኔ ትክክለኛ የህግ አተረጓጎም አይደለም።
83 84 የሰ/መ/ቁ. 2A938 ሚያዝያ 11/99 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ አቶ አሰግድ ጋሻው ወ/ት ሒሩት መለሰ አመልካች፡- ወ/ሮ ሸዋዬ ተሰማ ቀርባለች።
መልስ ሰጪ፡- ወ/ሮ ሣራ ልንጋነ አልቀረበችም።
አመልካች ለሰበር ችሎት ያቀረቡት ማመልከቻ የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መልስ ሰጪ የሟች የአቶ ይልማ ወ/ሃና ሚስት ነበሩ በማለት የሰጠው ውሣኔ እንዲሻርላቸው የሚጠይቅ ነው። አመልካች መ/ሰጪ የሟቹ የአቶ ይልማ ወ/ሃና ሚስት አይደሉም በማለት ተቃውሞ ያቀረቡት ለፍድራል የመጀመሪያ ፍ/ቤት ነው።
ተቃውሞው ለዚህ ፍ/ቤት ያቀረቡት ፍ/ቤት ቀደም ሲል ግንቦት 15/95 በዋለው ችሎት መልስ ሰጪ ወ/ሮ ሣራ ልንጋነ የሟች የአቶ ይልማ ወ/ሃና ሚስት ነች በማለት በመስጠቱ ነው። ተቃውሞው የቀረበለት ፍ/ቤትም አመልካች ሚስት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ አቅርበዋል በልላ በኩል መልስ ሰጪ ከሟቹ ጋር ጋብቻ የነበራቸው መሆኑ ስለተረጋገጠና በአመልካቹ በኩል ውላቸው መፍረሱን የሚያሳይ ማስረጃ ባለመቅረቡ ቀደም ሲል መልስ ሰጪ የሟች ሚስት ናት በማለት የተሰጠው ውሣኔ የሚለወጥበት ምክንያት የለም በማለት ውሣኔው አጽንቶታል።
አመልካች ይግባኝ ለከፍተኛው ፍ/ቤት ቢያቀርቡም የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ማመልከቻውን አይቶ ይግባኙን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት አያስቀርብም በማለት ዘግቶታል። የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህን ውሣኔ ለማስለወጥ ነው።
የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ቅሬታ መልስ ሰጪ ከሟች ጋር የነበራት ጋብቻ በገዛ ፈቃዷ አፍርሳ ከልላ ሰው ጋር ከ1977 በፊት ጀምሮ ትዳር በመመስረቷ የሟቹ ሚስት ፈት ላባል አይገባም፣ ሟች ከአመልካች ጋብቻ የፈፀመው ልላ ጋብቻ ስላልፈፀመ ነው፣ የመልስ መሰጪን ጋብቻ መፍረስ ያውቁ የነበሩ ምስክር ቀርበው እንዳይመሰክሩ መደረጉ እውነቱ እንዳይወጣ መደረጉን ያሳያል። አቶ ይልማ የሞቱት በ1989 ሆኖ ሣለ መልስ ሰጪ ግን በ1981 ነው የሞቱት ብላ ለፍ/ቤት ማመልከቷ ጉዳዩን የተቀነባበረና የሚስትነት ጥያቄውን ከ14 ዓመት በኋላ መቅረቡን ያስረዳል የሚል ነው።
በመልስ ሰጪ የቀረበው መልስ ደግሞ መልስ ሰጪና ሟች መጋባታቸው በማስረጃ ስለተረጋገጠና ጋብቻ የሚፈርስባቸው በሕግ ከሚታወቅባቸው ምክንያቶት አንዱ መኖሩ ስላልተረጋገጠ የሟችና የመልስ ሰጪ ጋብቻ ፈርሷል ላባል አይችልም፣ የሟችና የአመልካች ጋብቻ መጀመሪያ የተፈፀመውን ጋብቻ አያስቀርም፣ መልስ ሰጪ ከልላ ሰው ሁለት ልጆች መውለዳቸውም ሆነ የሞቱበትን ቀን 1981 ብለው መጥቀሳቸውም እንደዚሁ ሚስትታቸውን አያስቀርም፤
የሚስትነት ማረጋገጫው የተሰጠው ሟቹ በ1989 ዓ.ም. ሞተዋል በማለት በመሆኑ የአመልካች ቅሬታ መሰረት የለውም፣ በመሆኑም የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ የሕግ ስህተት ስለልለበት ላፀና ይገባል የሚል ነው።
ይህ ችሎት የግራ ቀኙን ክርክር አግባብ ካላቸው ሕጎች ጋር በማያያዝ ተመልክቷል። ከመዝገቡ እንደተረዳነው አመልካችም ሆነ መልስ ሰጪ ከሟች አቶ ይልማ ወ/ሃና ጋር ጋብቻ መፈፀማቸው ተረጋግጦአል። መ/ሰጪ ሚስት መሆናቸውን ለማረጋገጥ በ1966 የተጋቡበት የጋብቻ ውል በ6/6/72 የተሞላ የሕይወት ታሪክ /ሟች ይሰሩበት ከነበረው የቡና ገበያ ድርጅት ማኀደር የተገኘ/ እንዲሁም ጥር 19/1974 በጡረታ ቅጽ ላይ ሚስት ተብለው የተሞላበት ሰነድ ቀርቦአል። አመልካቹ በበኩላቸው በ1987 ዓ.ም. ከሟች ጋር መጋባታቸው ማስረጃ ቀርቦ ሚስትታቸው በልላ ተረጋግጧል።
በልላ በኩል አመልካች ባቀረቡት መቃወሚያ መነሻነት የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባደረገው ማጣራት መልስ ሰጪ ለፍርድ ቤቱ በሰጡት ቃል ሟቹና መ/ሰጪ እስከ 1985 አብረው ከኖሩ በኋላ በ1985 ዓ.ም. ተጣልተው መ/ሰጪ ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን በኋላ ደግሞ ሟቹ አቶ ይልማ አመልካቿን ወ/ሮ ሸዋዬን አግብተው አጋሮ መሄዳቸውን እንደሰሙ በፍርዱ ቤቱ አስረድተዋል። ከዚህ በተጨማሪ ከሟች ጋር የነበረው ጋብቻ በፍቺ አለመፍረሱም ገልፀዋል በቃል በተደረገው ማብራሪያ የአሁን አመልካች ስለፍቺው ያውቁ እንደሆነ ተጠይቀው ሟቹ ከመልስ ሰጪ ጋር ጋብቻ የነበረው መሆኑን ስለማናውቅ ስለፍቺው አናውቅም ብለዋል።
ከዚህ መገንዘብ የቻልነው የአሁንዋ መልስ ሰጪ ምንም እንኳ ከሟቹ ጋር ቀደም ብሎ የተፈፀመ ጋብቻ የነበራቸው ቢሆንም በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት በነበረው ጋብቻ መቀጠል አለመቻላቸውንና ሁለቱ በየፊናቸው የየራሳቸው ሕይወት መጀመራቸውን ነው። የአሁን መልስ ሰጪ ጋብቻው በፍቺ ምክንያት አልፈረሰም ይባል እንጂ ለፍርድ ቤቱ የሰጡት ማረጋገጫ ጋብቻው መፍረሱን የሚያረጋግጥ ነው። ጋብቻ የሚፈርሰው ሕጉ ባስቀመጣቸው ውሱን ምክንያት መሆኑን ይህም ፍ/ቤት ይቀበለዋል። በልላ 85 86 በኩል ለጋብቻ መፍረስ ምክንያቶች የሆኑ ነገሮች መኖር አለመኖራቸውን የሚረጋግጠው እንድት ነው የሚለው ጥያቄና ነጥብ በሁለቱም ተጋቢዎች ከነበረው ሁኔታ ጭምር መረዳት የሚችል ነው። ጋብቻ የሚፈርስበትን ምክንያት መፍረሱን ከማስረዳት መለየትም ያስፈልጋል። አሁን በቀረበልን ጉዳይ የመልስ ሰጪ መከራከሪያ ፍቺ መፈፀሙን አመልካች አላስረዳችም የሚል ነው። ነገር ግን የመልስ ሰጪና የሟች ግንኙነት ማንም ልላ ማስረጃ ላያስረዳ ከሚችለው ከሚገልፀው በላይ በመካከላቸው የነበረው የጋብቻ ግንኙት መፍረሱ ሁለቱም ልላ ሕይወት ጀምረው ሟቹ የአሁንዋን አመልካች ማግባታቸውን፣ ይህንንም ጋብቻ የአሁኗን መልስ ሰጪ ያውቁ እንደነበር ያስረዳል። ይህ በመሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ የአሁንዋን መልስ ሰጪ ቀደም ሲል የፈፀመችውን ጋብቻ መሰረት በማድረግ ብቻ ሚስት ናት ብሎ መወሰኑ ትክክለኛ የሕግ አተረጓጎም አይደለም።
ው ሣ ኔ የፍድራል መጀመሪያት በመ/ቁ 4796 ሚያዝያ 18 ቀን 1997 ዓ.ም.
የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
ወ/ሮ ሣራ ልንጋነ የሟች የአቶ ይልማ ወ/ሃና ሚስት አይደለችም በማለት ወስነናል፣ ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ።