የስራ ውል በተቋረጠ ጊዜ ስራ ላልተሰራበት ውዝፍ ደሞዝ የሚከፈልበት ስላለመሆኑ / #### #### የሰ/መ/ቁ 20457 / የኢት/ንግድ ባንክ እና ወ/ሮ አለሚቱ ሞገስ/
No summary available.
መጋቢት 18 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ አሰግድ ጋሻው አቶ መስፍን እቁበዮናስ ወ/ት ሂሩት መለሰ አቶ ተሻገር ገ/ስላሴ አመልካች፡- ወ/ሮ አልማዝ ዓለማየሁ ተጠሪ፡- አቶ ብርሃኑ ተላላ የአፈጻጸም ክርክር - የጋራ ሀብት በፍርድ አፈጻጸም የሚከበርበትና በሐራጅ የሚሸጥበት ሁኔታ - የከተማ ቦታ ይዞታ - የባልና ሚስት የጋራ ሃብት የአፋር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተጠሪው በአፈጻጸም ከአዋሽ ማዘጋጃ ቤት የተረከበው ቦታ የፍርድ ባለእዳው ከነበረው ቦታ የበለጠ ቢሆንም በአፈጻጸሙ አጋጣሚ ቅድሚያ የተመራ ስለሆነ ለእሱ ላደለደል ይገባዋል እንዲሁም በፍርድ ቤቱ ተይዞ የንብረቱ ግምት ግማሽ ገንዘብ ለተጠሪው ላመለስ ይገባል ሲል የወሰነውን ውሣኔ በመቃወም የቀረበ አቤቱታ ነው።
ውሣኔ፡ - የአፋር ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተሽሮ የዞን 3 ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ትእዛዝ ጸንቷል።
ማዘጋጃ ቤት በፍርድ ቤት በታዘዘ የአፈጻጸም ጉዳይ በስህተት ቦታ ለክቶ አስረክቦኛል ግብርና የስም ማዛወሪያ ከፍዬበታለሁ የሚለው መከራከሪያ ነጥብ የቦታ ባለይዞታ ለማድረግ የሚያበቃ አይደለም።
የሰበር መ/ መጋቢት 18 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ አሰግድ ጋሻው መስፍን እቁበዮናስ ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ አመልካች፡- ወ/ሮ አልማዝ ዓለማየሁ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ ብርሃኑ ተላላ አልቀረቡም።
መዝገቡን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዳይ ላቀርብ የቻለው የአፋር ብ/ክ/መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ጉዳይ በይግባኝ ተመልክቶ በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ 15/94 የካቲት 18 ቀን 1996 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ አመልካች ቅር ተሰኝተው የሰበር አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
ጉዳዩም ባጭሩ እንደሚከተለው ነው።
ተጠሪ አቶ ብርሃኑ ተላላ በአሁን አመልካች ባለቤት በአቶ ዮሐንስ ገ/ስላሴ ላይ ብር 18,794.15 አስፈርደዋል። ሆኖም ይህ ፍርድ ከመሰጠቱ በፊት በክርክር ላይ እያለ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ በሚል የእግድ ትእዛዝ የተላለፈበት ንብረት የአቶ ዮሐንስ ገ/ስላሴ ብቻ ሳይሆን ከእኔ ከአመልካች ጋር በትዳር እያለን የተፈራ፤ የተገኘ በመሆኑ የእኔ ድርሻ ላነካብኝ አይገባም በሚል ጣልቃ ገብታ አመልካች በመከራከሯ እንደ አቤቱታዋ እግድ ከተሰጠበት ንብረት ግማሹ የአመልካች መሆኑ የተጠበቀ ነው በሚል ፍርድ አርፎበታል።
እንዲሁም ይኸው ንብረት በአፈፃፀም ተይዞ በብር 25,000.00 ግምት መነሻ እንዲሸጥ በተባለ ጊዜ ግማሹ የአመልካች መሆኑ ተጠብቆ ንብረቱ 48 49 በሐራጅ እንዲሸጥ ተደርጎ ገዥ ባለመቅረቡ ምክንያት እንደ መጨረሻ አማራጭ የፍርድ ባለመብት የአሁን ተጠሪ ከግምቱ ብር 25,000.00 የሆነበትን /የአመልካችን ግማሽ ድርሻ ብር 12,500.00/አስራ ሁለት ሺህ ከፍሎ ንብረቱን እንዲረከብ ታዟል።
ተጠሪም ይህንኑ ገንዘብ በሞድል 85 አስይዤ ቦታውንም የአዋሽ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ለክቶ አስረክቦኝ አስፈላጊውን የመንግስት ውዝፍ ግብር ከከፈልኩ በኋላ ካርታ እንዲሰጠኝ ሳመለክት እንድረከብ ከተወሰነው ቦታ ተከፍሎ ለአሁን አመልካች እንዲሰጥ ታዝዣለሁ በማለት ማዘጋጃ ቤቱ እንደ ውሳኔው ላያስፈፅምልኝ ስላልቻለ፡-
የከፍተኛው ፍ/ቤትም በዚህ ጉዳይ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የአሁን ተጠሪ በአፈፃፀም ይረከብ የተባለው ይዞታ የፍርድ ባለእዳውን የአቶ ዮሐንስ ገ/ስላሴን ነው።
የፍርድ ባለእዳው ይዞታ ስፋት ደግሞ 600 ካሬ ሜትር እንደሆነ በማዘጋጃ ቤት ተረጋግጧል። ይሁን እንጂ የፍርድ ባለመብቱ ከዚህ ወጭ የፍርድ ባለእዳውን ወንድም የአቶ ገ/እግዚአብሕር ገ/ስላሴን 200 ካሬ ሜትር እና በትርፍነት የሚገኘውን 355 ካሬ ሜትር ጭምር በስህተት ደርቦ እንዲረከብ የተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሐል። ስለሆነም አመልካች የባለቤቷ ወንድም በግንባር ተገኝቶ እስከሚረከብ ድረስ ይህንኑ 200 ካሬ ሜትር በአደራ እንድትይዝ በትርፍነት የሚገኘውንም 358 ካሬ ሜትር ማዘጋጃ ቤቱ በስሟ እንዲያዘዋውርላት ከዚህ በቀር ተጠሪው ላረከብ የሚገባው የፍርድ ባለእዳውን ይዞታ 600 ካሬ ሜትር ላሆን ይገባል በማለት ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ተጠሪ ለክልሉ ጠ/ፍ/ቤት አቤቱታ አቅርቧል።
የጠ/ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙ በተገኙበት ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ በትርፍነት ተገኝቷል የተባለውን ቦታ በሚመለከት ትርፍ እስከሆነ ድረስ ማዘጋጃ ቤቱ ለፈለገው ሰው መደልደል /መስጠት/ ይችላል።ሆኖም ይህንኑ ቦታ ማዘጋጃ ቤቱ በመጀመሪያ ተጠሪው /እንዲረከብ/ ለክቶ እንዲረከብ ካደረገ በኋላ ከአምስት ወር ቆይታ በኋላ ደግሞ ለአመልካች እንዲሰጥ አድርጓል።አንድን ቦታ ለሁለት ሰዎች በአንድ ጊዜ መስጠት አይቻልም። ስለሆነም ለማን ይሰጥ የሚለው ጉዳይ በቅድሚያ ለማን ተስጥቶ ነበረ ከሚለው አንፃር መታየት ስላለበት ይኸው 358 ካሬ ሜትር ቦታ ለተጠሪ ይገባል እንዲሁም በሞድል 85 ተይዞ የነበረው ገንዘብ ለአመልካች መስጠቱ ቀርቶ ለተጠሪው ይመለስ በማለት ወስኗል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ነው። መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል የተባለው የቅሬታ ነጥብም ክርክር ባስነሳው ትርፍ ቦታ ላይ ከተጠሪ በፊት በቦታው ላይ የቆየሁበት በመሆኑ በመሬት ወይም በምሪት አሰጣጥ ላይ የቀዳሚነት መብት የእኔ ሆኖ እያለ ለተጠሪ ይሰጥ በማለት የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት መወሰኑ የህግ አግባብን የተከተለ አይደለም።
እንዲሁም በሞድል 85 የተያዘው ብር 12,500.00 የእኔ የሚስት ድርሻ ሆኖ እንዲከፈል የተወሰነው ለጠ/ፍ/ቤቱ ይግባኝ ምክንያት በሆነው የትእዛዝ ፋይል መዝገብ በአለመሆኑ በይግባኝ መዝገቡ ላይ በዚህ አኳኋን መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ፈፅሟልና ይሻርልኝ የሚል ነው።
ተጠሪም ቀርቦ የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት በይግባኝ አይቶ የሰጠው ውሳኔ የህግ ግድፈት የለበትም የሚልበትን ምክንያት በመዘርዘር መልስ ሰጥቷል።
እኛም ጉዳዩን ተመልክተናል።
እንደተመለከትነውም ለዚህ ክርክር መነሻ የሆነው የአሁን ተጠሪ ከሳሽ የአመልካች ባለቤት አቶ ዮሐንስ ገ/ስላሴ ደግሞ ተከሳሽ ሆነው በፍ/ብ/መ/ቁ 8/90 በከፍተኛው ፍ/ቤት በመከራከር ላይ እያሉ የአሁን አመልካች ባለቤቴ አመጣው በተባለው እዳ ምክንያት የእኔ የጋራ ሀብት በሆነው ቤት ላይ የእግድ ትእዛዝ መተላለፉ ተገቢ አይደለም። ስለሆነም ጣልቃ ገብቼ ልከራከር በማለት ባቀረበቺው ጥያቄ የክርክሩ ተካፋይ ከሆነች በኋላ የከፍተኛው ፍ/ቤት የአመልካች ባለቤት በሥራው ምክንያት ላጐደለው ብር 18,794.15 ባለእዳ ነው። የእግድ ትእዛዝ የተላለፈበትን ቤት አመልካች በሚስትነታቸው አብረው የሰሩት መሆኑን በማስረጃ ስላረጋገጠ ድርሻቸው ላነካባቸው አይገባም በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ መሰረት እንዲፈፀም በአፈፃፀም መ/ቁ 3/93 የአፈፃፀም ክሱ ቀጥሎ በብር 25,000.00 ግምት መነሻ ይህንኑ የጋራ ቤት የሚገዛ ገዥ 51 52 ባለመገኘቱ አመልካች ግማሹን መክፈል ከቻለች ቤቱን እንድታስቀር ተብሎ ቢታዘዝም ይህንን መፈፀም ባለመቻሐ ተጠሪው ብር 12,500.00 የአመልካችን ድርሻ በሞድል 85 አስይዞ ንብረቱን ስለእዳው እንዲረከብ በሚል የታዘዘ ስለመሆኑ ከመዝገቡ ግልባጭ ተገንዝበናል።
ይህም ከሆነ የፍርድ ባለመብቱ የአሁን ተጠሪ ስለእዳው ላረከበው የሚገባው ቤትና ይዞታው ይህንኑ በአፈፃፀም ምክንያት ይሸጥ የተባለውንና በባለእዳው በአቶ ዮሐንስ ገ/ስላሴ ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን ነው። ይህ ቦታ እና ይዞታ ደግሞ በፊቱ 650 ሜትር ካሬ ብቻ እንጂ ከዚያ ያልዘለለ ስለመሆኑ በባለሙያ በማዘጋጃ ቤቱ ተረጋግጧል። ይህንኑ ቤት ከእነ ትክክለኛ ይዞታው ተለክቶ እንዲረከብ ማድረግ ሲገባ በእዳ ከተያዘው ንብረት ውጭ መሰራቱ እና እንዲረከብ ጥረት መደረጉ ተገቢ ሆኖ አላገኘውም። የማዘጋጃ ቤቱ ይህንኑ 600 ሜትር ካሬ፣ የአቶ ገ/እግዚአብሕር ገ/ስላሴን ይዞታ 200 ሜትር ካሬ እና ክርክር ያስነሳውን ትርፍ ቦታ እንድረከብ ለክቶልኛል። ግብር ና የስም ማዛወሪያ ከፍዬበታለሁ የሚለው መከራከሪያ ነጥብ የዚህ ሁሉ ቦታ ባለይዞታ ለማድረግ የሚያበቃ አይደለም። የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ፍርዱን በአፈፃፀም ተከካሹ ወይም በፍርድ ባለእዳው ንብረት ላይ ብቻ ማስፈፀም ሲገባው የማዘጋጃ ቤቱ የፈፀመውን ስህተት እንደ መነሻ በመውሰድ ይህንኑ ትርፍ ቦታ በቅድሚያ የተመራው የፍርድ ባለመብቱ የአሁን ተጠሪ ነው። ስለሆነም ለእርሱ ላደለደል ይገባል ሲል የሰጠው ውሳኔ የአፈፃፀም ሥርዓቱን የተከተለ ሆኖ አላገኘነውም።
በልላ በኩል የአመልካች ባለቤት በተከሰሰበት ጉዳይ አመልካች ጣልቃ ገብታ ተከራክራ በክሱ ምክንያት ቦታ በታገደው ንብረት ላይ ያላት ድርሻ የተጠበቀ ነው በሚል ፍርድ አርፎበታል። የጣልቃ አግባብ ሥርዓቱ ተገቢ አይደለም በሚል የይግባኝ አቤቱታ ቀርቦ የታረመ ስለመሆኑም አልተመለከተም። ከዚህ በላይ በአፈፃፀም መ/ቁ 3/93 ከንብረቱ ሽያጭ ግማሹ ብር 12,500.00 የሚስት/የአመልካች ድርሻ ሆኖ በሞድል 85 እንዲያዝ ተደርጓል። ይህ መሆኑ እየታወቀ በአፈፃፀም ምክንያት ልረከብ የሚገባው ይዞታ ምን ያህል ላሆን ይገባል የሚለውን በሚመለከት ክስ ላይ የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት ይኸው በአደራ ተይዞ የነበረው ገንዘብ ወጭ ሆኖ ለተጠሪው ይመለስ ሲል የሰጠው ዳኝነት ህጋዊ መሰረት ያለው አይደለም። ለምን ቢባል ይሸጥ ከተባለው ንብረት ላይ ግማሹ የአመልካች ድርሻ መሆኑ ለአፈፃፀሙ ምክንያት በሆነው በዋናው ጉዳይ በመ/ቁ 8/90 ውሳኔ ያረፈበት ከመሆኑም በላይ ጠ/ፍ/ቤቱ በይግባኝ ለተመለከተው ጉዳይ መነሻ በሆነው በመ/ቁ 11/94 በሞድል 85 የተያዘው ገንዘብ የይዞታው መጠን ታይቶ ውሳኔ እስኪሰጠው ድረስ ይህ ገንዘብ ሳይከፈል ታግዶ ይቆይልኝ በሚል እንጂ ይመለስልኝ በሚል ዳኝነት አልተጠየቀበትም። ይህን ሳይረዳ የክልሉ ጠ/ፍ/ቤት በሞድል 85 የተያዘው ገንዘብ ይመለስ ሲል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው።
የአፋር ብሕራዊ ክልላዊ መንግስት ጠ/ፍ/ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ቁ 15/94 ታህሳስ 28 ቀን 1996 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው ውሳኔ የተሻረ ሲሆን በአንፃሩ የዞን ሦስት ከፍተኛ ፍ/ቤት በት/ፋ/መ/ቁ 11/94 የካቲት 19 ቀን 1994 ዓ.ም በዋለው ችሎት የሰጠው ትእዛዝ የፀና ስለሆነ፡
ተጠሪ ገዥ ባለመገኘቱ ምክንያት በአፈፃፀም ላረከበው የሚገባው ንብረት የፍርድ ባለእዳውን የአቶ ዮሐንስ ገ/ስላሴን እና የአመልካችን ቦታና ይዞታ ብቻ በመሆኑ በማዘጋጃ ቤቱ እንደተረጋገጠው 600 ሜትር ካሬ ብቻ ላረከብ ይገባል።
ይህም ይሸጥ የተባለው ቤትና ቦታ የፍርድ ባለእዳውና የአመልካች የጋራ ሀብት መሆኑ ታይቶ ለአፈፃፀሙ መነሻ በሆነው ውሳኔ ላይ ዳኝነት የተሰጠበት በመሆኑና ይህም በይግባኝ ያልተሻረ ስለሆነ እንዲሁም በአፈፃፀም መዝገቡም ላይ ቢሆን ይኸው መብት የተጠበቀ በመሆኑ በሞድል 85 ተይዞ የሚገኘው ብር 12,500.00 /አስራ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር/ የአመልካች ድርሻ በመሆኑ ለአመልካች ላከፈል ይገባል በማለት ወስነናል።
ይህ ክርክር ላስከተለው ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸው
No topics extracted.