No summary available.
የሰ/መ/ቁ/ 21448 ሚያዚያ 30/1999 ዳኞች፡- Aቶ መንበረጸሐይ ታደሰ Aቶ ፍሰሐ ወርቅነህ Aቶ መስፍን Eቁበዮናስ ወ/ት ሂሩት መለሰ Aቶ ተሻገር ገ/ሥላሴ Aመልካች፡- ወ/ሮ ጎርፍ ወርቅነህ መ/ሰጭዎች፡- Eነ ወ/ሮ Aበራሽ ደባርጌ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል - የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል Aፃፃፍ ፎርም - የሽያጭ ውልን ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው ወይም በፍርድ ቤት ፊት ስለማድረግ - የሽያጭ ውልን በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ መመዝገብ - የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 1723፣ 1727፣ 2877፣ 2878።
የፍድራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመልስ ሰጭዎችና በAመልካች Aውራሽ መካከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል በህጉ ተቀባይነት ያለው ነው ሲል የሰጠውን ውሳኔ በማፅናቱ በተቃውሞ የቀረበ Aቤቱታ ነው።
ውሳኔ፡- የፍድራል መጀመሪያና ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሳኔ ተሽሯል።
የማይንቀሳቀስ ንብረትን የሚመለከቱ ውሎች በህግ ፊት የሚፀኑ Eንዲሆኑ ሁለት መስፈርቶችን ሟሟላት ይጠበቅባቸዋል። የመጀመሪያው መስፈርት ውሉ በፁሁፍ መሆኑ ሲሆን ሁለተኛው ውሉ በAዋዋይ ወይም በፍርድ ቤት መዝገብ ፊት መከናወኑ ነው።
የፍ/ብ/ህግ ቁ.1723(1) የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በAዋዋይ ወይም በፍርድ ቤት ፊት Eንዲደረግ የሚጠይቀው በተዋዋዮች መካከል በሕግ ፊት የሚፀና ውል Eንዲኖር ለማድረግ ነው።
የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 2878 የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ምዝገባ Eንዲከናወን የሚጠይቀው ውሉ በሦስተኛ ወገኖች ላይ ውጤት Eንዲኖረው ለማድረግ ነው።
ልዩ ህግ ከAጠቃላይ ህግ ቅድሚያ ይሰጠዋል (the special prevails over the general) የሚለው የተለመደው የህግ Aተረጓገም ስልት ተግባራዊ የሚሆነው ሁለት የህግ ድንጋጌዎችን Aንድ ላይ ተግባራዊ ማድረግ ሳይቻል ሲቀር ብቻ ነው።
“ስለ ውሎች በጠቅላላው” ምEራፍ ስር የሚገኘው የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 1723 Eና “ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ” ስር የሚገኘው የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 2877 ድንጋጌዎች መካከል ልዩነት ቢኖርም በመካከላቸው ግልፅ የሆነ ግጭት የልለ በመሆኑና የማይንቀሳቀስ ንብረትን ባለቤትነት ለማስተላለፍ ከልሎች ውሎች የበለጠ ጥንቃቄና ጥበቃ ስለሚሻ Aንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት የሽያጭ ውልን የAፃፃፍ ፎርም በሚመለከት ገዢ ድንጋጌ መሆን ያለበት የተለየና ጥብቅ መስፈረት የሚያስቀምጠው የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 1723 ነው።
የመ.ቁ. 21448 ዳኞች፡
በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር የማይንቀሳቀስ ሀብት (ቤት) ሽያጭን የሚመለከት ነው። ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ጉዳይ የተጀመረው በፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የAሁን Aመልካች Aቅርበውት በነበረው ከወራሽነት ጋር የተያያዘ የንብረት ክፍፍል ክስ ነው። Aመልካች Aባታቸው Aጋዝ ገ/ሕይወት ወልደየስ ከAንደኛዋ መልስ ሰጪ ጋር በጋብቻ Aብረው ሲኖሩ ያፈሩትና በወረዳ 24 ቀበል 09 የሚገኝና ቁጥሩ 011 የሆነ ቤት የጋራ መሆኑን በመግለጽ የሟቹን የAባታቸውን ድርሻ ያካፍሉኝ የሚል ክስ ለፍርድ ቤት Aቀረቡ። ፍርድ ቤቱም ተጠቃሹ ቤት የጋራ ነው በማለት Aመልካች በቤቱ ላይ ግማሽ ባለድርሻ ናቸው በማለት ውሳኔ ሰጠ። ከዚህ በኋላ የAሁኑ 2ኛ መልስ ሰጪ Aቶ ጌታቸው ነጋ ፍርድ ቤቱ የሰጠው ይኸው ውሳኔ የኔን ይዞታ የሚያጠቃልል በመሆኑ ውሳኔው ይለወጥልኝ በማለት በፍትሐ ብሕር ሥነ ሥርAት ሕግ ቁ. 358 መሰረት የመቃወም ማመልከቻ Aቀረቡ። 2ኛ መልስ ሰጪ ለዚህ ማመልከቻ መሰረት ያደረጉት በ1985 ፈፀምኩ የሚሉት የሽያጭ ውል ነው። 2ኛ መልስ ሰጪ ባቀረቡት ማመልከቻ 1ኛ መልስ ሰጪና ባለቤታቸው Aጋዝ ገ/ሕይወት ወልደየስ በ23/03/85 በተፃፈ የሽያጭ ውል Aንድ ጅምር ቤትና 400 ካሬ ሜትር ቦታ በብር 16,500.00 (Aስራ ስድስት ሺህ Aምስት መቶ ብር) የሸጡላቸው መሆኑን በመግለጽ ፍርድ ቤቱ ቀደም ሲል የሰጠውን ውሳኔ Eንዲለውጥ ጥያቄ Aቅርበዋል።
የAሁን Aመልካች 2ኛ መልስ ሰጪ ባቀረቡት መቃወሚያ ላይ መልስ Eንዲያቀርቡ ተደርገው 2ኛ መልስ ሰጪ ገዛሁ የሚሉት ቤት የቤት ቁጥር ካልተገለፀና ደብተር ከልለው ገዝቻለሁ ላሉ Eንደማይችሉ፣ ክርክር በተነሳበት ቤት ላይ በ1985 ዓ.ም ጅምር ቤት ያልነበረ መሆኑን፣ ሟች ውሉ በተፈፀመበት ወቅት በEድሜ የገፉና ሕመምተኛ ስለነበሩ ውሉ ተቀባይነት Eንደልለው፣ ተፈረመ በተባለው ውል ላይ ያለው የጣት ፊርማ የሟች Aለመሆኑን፣ የፍርድ Aፈጻጸም መምሪያ መሃንዲስ በ1992 ክርክር የተነሳበትን ቤት ማህደር በማስቀረብ የ2ኛ መልስ ሰጪ መሆኑን የሚያመለክት ሰነድ Aለማግኘቱን መግለጹን በመዘርዘር ውሉ ተቀባይነት የለውም ሲሉ ተከራክረዋል።
No specific laws extracted.
No topics extracted.
የAሁንዋ Aንደኛ መልስ ሰጪ በልላ በኩል ከባለቤታቸው ጋር በመሆን ውሳኔ ያረፈበትን ቤት በከፊል ለAሁን 2ኛ መልስ ሰጪ ሸጠው በውሉ መሰረት ለ2ኛ መልስ ሰጪ ያስረከቡ መሆናቸውን በመግለጽ ወደ ክርክሩ ቢገቡ ተቃውሞ Eንደልላቸው ገልጸዋል።
ጉዳዩ የቀረበለት ፍርድ ቤት በ2ኛ መልስ ሰጪ በቀረበው የሽያጭ ውል ላይ ያለው ፊርማ የሟች የAጋዝ ገ/ሕይወት መሆን Aለመሆኑን ለማጣራት ጉዳዩን ለፖላስ የቴክኒክ ምርመራ ከላከ በኋላ ተመርማሪው የጣት ፊርማ በውስጡ በቂ ዝርዝር ማስረጃ የለውም በማለት ለመለየት መቸገሩን Eንደገለፀለት በፍርዱ መዝግቧል። ይህ ሪፖርት ከቀረበለት በኋላ በግራ ቀኙ የቀረቡትን ምስክሮች ሰምቶ በ2ኛ መልስ ሰጪ የቀረበው የሽያጭ ውል ተቀባይነት ያለው ነው በማለት ቀደም ሲል የሰጠውን ውሳኔ በከፊል Aሻሽሐል።
የAሁን Aመልካች በዚሁ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፍድራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ ይግባኙን ውድቅ Aድርጐታል። የሰበር Aቤቱታ የቀረበውም ይህን ውሳኔ ለማስለወጥ ነው። የAሁን Aመልካች ባቀረቡት የሰበር Aቤቱታ የስር ፍርድ ቤት የሽያጭ ውሉ ይፀናል ሲል የሰጠው ውሳኔ Eንዲሻርላቸው ጠይቀዋል።
መልስ ሰጪዎች የAመልካች የሰበር Aቤቱታ Eንዲደርሳቸው ከተደረገ በኋላ በዚህ ችሎት ፊት የቃል ክርክር ተካሂዷል።
በዚህ በቀረበልን ጉዳይ መፍትሄ የሚፈልገው ዋነኛ ጥያቄ የማይንቀሳቀስ ሀብት ሽያጭ ላከተለው የሚገባው የውል Aጻጻፍ ፎርም ምን ዓይነት ነው የሚለው ነው። በዚህም መሰረት ይህ ችሎት የቤት ሽያጭን በሚመለከት በIትዮጵያ ሕግ ማEቀፍ Aግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች ዳስሷል። የማይንቀሳቀስ ሀብትን የሚመለከቱ የAጻጻፍ ፎርም ድንጋጌዎች በፍትሐብሕር ሕጉ የተለያዩ ክፍሎች የሚገኙ በመሆናቸው የነዚህን ድንጋጌዎች ግንኙነትና ልዩነትም ተመልክቷል።
ለዚህ ሰበር Aቤቱታ መነሻ የሆነው ውሳኔ የተሰጠው የቤት ሽያጭ ውል በጽሑፍ መሆኑን በቂ ነው ከሚል Aጠቃላይ መንደርደሪያ የተነሳ መሆኑ ከውሳኔው Aጠቃላይ ይዘት ለመገንዘብ ችለናል። ጉዳዩ የቀረበለት የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሉ በEርግጥ ተፈጽሟል ወይስ Aልተፈጸመም የሚለውን ጥያቄ ለማጣራት ማስረጃ Eንዲቀርብ ከማድረጉ በስተቀር ውሉ በEርግጥ ሕጉ የሚጠይቀውን መስፈርት Aሟልቷል ወይስ Aላሟላም የሚለውን የሕግ ነጥብ Aልተመለከተም። በመሆኑም ፍርድ ቤቱ የቤቱን ሽያጭ በሚመለከት በሁለቱ ወገኖች መካከል መስማማት ነበር ወይስ Aልነበረም የሚለውን የፍሬ ነገር ጉዳይ ከማጣራት Aልፎ በመካከላቸው መስማማት Aለ Eንኳን ቢባል ሕጉ የሚፈቅደውን ሥርAት ተከትሎ የተፈጸመ ውል ነው ወይስ Aይደለም የሚለውን ዋነኛ ነጥብ Aልተመለከተም። ይህ የሰበር ችሎት ለፍርድ ቤቱ ቀርቦ የነበረውን የጣልቃ ገብነት ጥያቄ ለማስተናገድ ጣልቃ ልግባ ብሎ የጠየቀው 2ኛ መልስ ሰጪ በሕግ የሚፀና የሽያጭ ውል ነበረው ወይስ Aልነበረውም የሚለው የሕግ ነጥብ ይበልጥ Aግባብነት የነበረው መሆኑን ተገንዝቧል። ይህን የሕግ ነጥብ ለመፍታት ደግሞ ውሉ ላይ የነበሩ ምስክሮችን Aስቀርቦ ከመስማት 41 42