የህመም ፈቃድ ጊዜ አቆጣጠር / #### #### የሰ/መ/ቁ 21119 / ቃላቲ ምግብ አክሲዮን ማህበር እና ማስተዋል ጫኔ/
No summary available.
ሚያዚያ 18 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ አቶ አሰግድ ጋሻው አቶ መስፍን እቁበዮናስ ወ/ት ሂሩት መለሰ አቶ ተሻገር ገ/ስላሴ አመልካች፡- ወ/ሮ ዓለሚቱ አግዛቸው ተጠሪ፡- እነ ወ/ሮ ዝናሽ ኃይል የውል ክርክር - የውል መፍረስ፣ የቤት ሽያጭ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 1771(1)፣ 1785(2)፣ 1789 የፍድራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ግራ ቀኙ ያደረጉት ውል አመልካች ስም እንዲዛወር ፈቃደኛ ስላልነበሩ ውሉ ፈርሶ ተዋዋይ ወገኖች ወደ ነበሩበት ላመለሱ ይገባል ሲል የሰጠውን ውሣኔ በማጽናቱ በተቃውሞ የቀረበ አቤቱታ ነው።
ውሣኔ፡ - የፍድራል መጀመሪያና ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
ተዋዋይ ወገኖች መሰረታዊ ያልሆኑና ጥቃቅን የሆኑ ምክንያቶችን ብቻ በመስጠት ውል ማፍረስ እንዳይችሉ ዳኞች ውሉ እንዲፈርስ ላያደርጉ የሚችሉት ውሉ ባይፈርስ ከፍ ያለ ችግር የሚያስከትል ከሆነ ብቻ ነው።
የውል አብዛኛው ግድታ በተፈፀመ ጊዜ የተወሰነ ቀሪ ገንዘብ አለመከፈሉ ውሉን ለማፍረስ የሚያበቃ መሰረታዊ የሆነ የግድታ መጣስ የሚያሰኝ ምክንያት አይደለም።
ሚያዚያ 18 ቀን 1999 ዓ.ም ዳኞች፡-
ተጠሪ፡- እነ ወ/ሮ ዝናሽ ኃይል - ቀረቡ።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው የውል መፍረስን የሚመለከት ጉዳይ ነው።
የአሁን ተጠሪዎች በፍ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ በወረዳ 15 ቀበል 26 የሚገኘውን ቁጥር 495 የሆነውን ቤት አሁኗ አመልካች ብር 9.000/ዘጠኝ ሺህ/ ሸጠው ብር 6.000/ ስድስት ሺህ/ ከተከፈላቸው በኋላ ቀሪውን ገንዘብ አመልካች ለመክፈል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ውሉ ቀሪ ሆኖ ግራ ቀኙ ወደነበሩበት እንዲመለሱ ጠይቀዋል።
አመልካችም ቀሪ ገንዘባቸው ያልተከፈላቸው በውሉ ላይ የተመለከተውን ግድታዎች ባለመወጣታቸው በመሆኑ ውሉ ላፈርስ አይገባም በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ በውሉ መሰረት ስም እንዲዛወር ፈቃደኛ ያልነበሩት አመልካች ካልሆኑ ውሉ ላፈርስ ይገባል በማለት አመልካች የገዙትን ቤት እንዲያስረክቡና ተጠሪዎች የተቀበሉትን ብር 6.000 /ስድስት ሺህ/ እንዲመልሱ በማለት ወስኗል።
ጉዳዩን በይግባኝ ያየው የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በድምፅ ብልጫ መዝገቡን በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 337 መሰረት ዘግቶታል።
37 38 የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። ይህ ችሎትም ውሉ ላፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም የሚለውን በመመርመር አቤቱታው ለሰበር እንዲቀርብ በማድረግ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል። ፍ/ቤቱም ጉዳዩን እንደሚከተለው መርምሯል።
የአሁን ተጠሪዎች ለአመልካች ቤት መሸጣቸውን፣ ቤቱንም ማስረከባቸውን ከተዋዋሉት ብር 9.000 /ዘጠኝ ሺህ/ ውስጥ ብር 6.000 /ስድስት ሺህ/ መቀበላቸውን አምነዋል። ውሉ እንዲፈርስ የጠየቁት ከሺያጩ ዋጋ ቀሪው ብር 3.000 /ሦስት ሺህ/ ባለመከፈሉ ነው።
ውልን ስላለመፈፀም በሚመለከተው የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1771/1/ ከተዋዋዮቹ አንዱ የውሉን ግድታ ያልፈፀመ እንደሆነ ውሉ ያልተፈፀመለት ወገን የውሉን መፍረስ ላጠይቅ እንደሚችል ይገልፃል። እንዲሁም የዚሁ ክፍል አንቀጽ 1789 ውሉ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ያልተፈፀመ ከሆነ ዳኞች በአንደኛው ወገን ጠያቂነት ውሉን ላያስቀሩት እንደሚችሉም ተመልክቷል። በአንድ በኩል ህጉ ውል አልተፈፀመልኝም የሚለው ወገን ውሉ እንዲፈርስለት ለመጠየቅ እንዲችል መብት ሰጥቶታል በልላ በኩል ግን ዳኞች በውሉ ላይ አይነተኛ የሆነ የውል መጣስ ካልሆነ በቀር ውሉ እንዳያፈርሱ ህጉ ግድታ ይጥልባቸዋል /የፍ/ህ/ቁ.1785/2/ ይመለከቷል/።
ተዋዋይ ወገኖች መሰረታዊ ባልሆኑና ጥቃቅን የሆኑ ምክንያቶችን ብቻ በመስጠት ውል ማፍረስ እንዳይችሉ ዳኞች ውሉ እንዲፈርስ ላያደርጉ የሚችሉት ውሉ ባይፈርስ ከፍ ያለ ችግር የሚያስከትል ከሆነ ብቻ ነው።
በተያዘው ጉዳይ የከፍተኛው ፍ/ቤት አነስተኛ ድምጽ እንዳሰፈረው የውሉ አመዛኙ ግድታ ተፈጽሟል። ገዥ /አመልካች/ የሽያጩን አብዛኛውን ክፍያ ፈጽመው ቤቱንም ተረክበዋል። አልተፈፀመም የሚባለው ቀሪው የብር 3,000 /ሦስት ሺህ/ ክፍያ ብቻ ነው። ይህ ደግሞ ውሉን ለማፍረስ የሚያበቃ መሰረታዊ የሆነ የግድታ መጣስ የሚያሰኝ ምክንያት አይደለም።
በዚህም መሰረት ቀሪው ገንዘብ አልተከፈለም በማለት ውሉ እንዲፈርስ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት።
ው ሣ ኔ
የፍ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 29696 ሰኔ 4/1996 የሰጠው ውሳኔ እና የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 32497 ጥር 3A/1997 በአብላጫ ድምጽ የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
ለክርክሩ ምክንያት የሆነው የቤት ሽያጭ ውል ላፈርስ አይገባም።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ። መዝገቡ ተዘግቷል። ይመለስ።
No topics extracted.