ለተወሰነና ላልተወሰነ ጊዜ ስለማደረግ የስራ ውል / #### #### የሰ/መ/ቁ 20885 / የኢት/ቴልኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን እና አቶ ገቢሳ የማነ/
No summary available.
የሰ/መ/ቁ/ 2A885 ጥር 3/1999 ዳኞች፡- አቶ ከማል በድሪ አቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ አቶ መስፍን እቁበዮናስ ወ/ት ሒሩት መለሰ አመልካች፡- የኢት/ቴልኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ተጠሪ፡- አቶ ገቢሣ የማነ የስራ ክርክር - ለተወሰነና ላልተወሰነ ጊዜ የሚደረግ የስራ ውል - የስራ ውል መቋረጥ - አዋጅ ቁ.42/85 አንቀጽ 9፣ 10 የፍድራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪው ከስራ የተሰናበቱት በህገ ወጥ መንገድ ስለሆነ ወደ ስራ ላመለሱ ይገባል ሲል የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በማጽናቱ የቀረበ አቤቱታ ነው።
ውሣኔ፡ - የፍድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፍድራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 42/85 አንቀጽ 9 በአንድ አሰሪና ሰራተኛ መካከል የተደረገ የስራ ውል ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ እንደሆነ ግምት ቢወስድም አሰሪ ይህንን ግምት አንቀጽ 10 ላይ የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች በማስረዳት ማፍረስ ይችላል።
አሰሪው ከሰራተኛው ጋር በጽሁፍም ሆነ በቃል ያደረገው ውል ለተወሰነ ጊዜ ወይም ስራ መደረጉን የሚያሳይ ጥቅል ሃሳብ ማስቀመጡ ብቻውን ውሉ በአንቀጽ 10 መሰረት የተደረገ መሆኑን ለማረጋገጥ በቂ አይሆንም።
በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የተደረገውን ውል ለመተርጐም ተዋዋዮች ውሉን ባደረጉበት ጊዜ የነበራቸውን የሃሳብ አንድነት መመርመር አስፈላጊ ነው።
የሰ/መ/ቁ/ 2A885 ጥር 3/1999 ዳኞች፡-
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ ለተወሰነ ጊዜ ወይም ሥራ የተደረገን የሥራ ውል የሚመለከት ነው።
ተጠሪ በፍ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት አመልካች ከሥራ ያላግባብ ያሰናበታቸው መሆኑን በመግለጽ ወደ ሥራ እንዲመልሣቸው ክስ ያቀርባሉ። አመልካች ደግሞ ወቅታዊ ሥራ ለማከናወን ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ሰራተኛ በመሆናቸው የተቀጠሩበት ሥራና ጊዜ ሲያበቃ መሰናበታቸው ተገቢ ነው በማለት ይከራከራል።
ጉዳዩን በመጀመሪያ ያየው ፍ/ቤትም ሥንብቱ ሕገ ወጥ ነው በማለት ተጠሪ ወደ ሥራ እንዲመለሱ ይወስናል። የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤትም ጉዳዩን በይግባኝ አይቶ የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ ያፀናል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታም የቀረበው በዚህ ውሣኔ ላይ ነው። ይህ ችሎትም በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው የሥራ ውል የተወሰነ ሥራ ለመስራት የተደረገ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር ጉዳዩን ለሰበር ችሎት በማስቀረቡ ግራ ቀኙ ክርራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል።
ከላይ እንደተመለከተው አመልካች የተጠሪን የሥራ ውል ያቋረጠው ውሉ የተደረገው ወቅታዊ ሥራን ለማከናወን በመሆኑ የተቀጠሩበት ሥራና ጊዜ በማለቁ መሆኑን ገልጿል። በመሆኑም ተጠሪ የተቀጠሩት ላልተወሰነ ጊዜ ነው ወይስ ለተወሰነ ሥራና ለተወሰነ ጊዜ ነው የሚለው ላታይ የሚገባው ነጥብ ነው።
የሥራ ውል ስለሚቆይበት ጊዜ የሚመለከተው የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 42/85 አንቀጽ 9 በአንድ አሰሪና ሰራተኛ የሚደረገው የሥራ ውል ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ መሆኑን የሕግ ግምት ይወስዳል። ሆኖም ይህ የሕግ ግምት ላፈርስ የሚችልባቸው ሁኔታዎች ደግሞ በአንቀጽ 1A ሥር 1 2 ተመልክተዋል። በመሆኑም አንድ አሰሪ ሰራተኛው የተቀጠረው ላልተወሰነ ጊዜ ሣይሆን ለተወሰነ ጊዜ ወይም ሥራ መሆኑን በማስረዳት በአንቀጽ 9 ሥር የተመለከተውን የሕግ ግምት ማፍረስ ይችላል። ይሁን እንጂ አሰሪው ከሰራተኛው ጋር በጽሁፍም ሆነ በቃል ያደረገው ውል ለተወሰነ ጊዜ ወይም ሥራ መደረጉን የሚያሣይ ጥቅል ሃሣብ ማስቀመጡ ብቻውን ውሉ በአንቀጽ 1A መሰረት የተደረገ መሆኑን ለማረጋገጥ በቂ አይሆንም። ከዚህ በተጨማሪ ውሉ በአንቀጽ 1A ሥር በተዘረዘሩት ሁኔታዎች በአግባቡ መደረጉን ማረጋገጥ ይኖርበታል። በሁለቱ መሃከል የተደረገውን ውል ለመተርጎምም ተዋዋዮቹ ውሉን ባደረጉበት ወቅት የነበራቸው የሃሣብ አንድነት መመርመር አስፈላጊ ይሆናል። በአጠቃላይ ለተወሰነ ጊዜ ወይም ሥራ የተደረገን የሥራ ውል በተመለከተ ይህ ችሎት የሰጠውን የሕግ ትንታኔ ከመ/ መመልከት ይቻላል።
በተያዘው ጉዳይ ተጠሪ ወቅታዊ ሥራ ለማከናወን E.ኤ.A. ከ14/4/2AAA- 15/1A/2AAA የተቀጠሩ መሆኑን በሁለቱ መሃከል የተደረገው የጽሁፍ ውል ያመለክታል። ከዚህ በተጨማሪ ተጠሪ የተቀጠሩት ሰልጣኞች ሥልጠና አጠናቀው እስኪወጡ የማሰልጠኛው ምግብ ቤት ምግብ አዘጋጅ ሆነው እንዲሰሩ መሆኑን በአመልካች በኩል በሥር ጀምሮ የቀረበውን ክርክር ተጠሪ በዚህ ሁኔታ አልተቀጠርኩም በማለት ክደው አልተከራከሩም። ማሰልጠኛው ወደ ኮልጅ ያደገ በመሆኑ ሥራው ቀጣይነት ስላለው ልሰናበት አይገባም በማለት ነው የሚከራከሩት። ነገር ግን አንድ አሰሪ ሥራው ቀጣይነት ቢኖረውም እንኳን የሥራ ብዛትን ለማቃለል፣ እየተቋረጠ የሚሰራ ሥራ ወይም ቋሚ ሣይሆን አንዳንድ የሚሰራን ሥራ ለማሰራት ሰራተኛን ለተወሰነ ጊዜ ወይም ሥራ ለመቅጠር የሚችል መሆኑ በአዋጅ አንቀጽ 1A ሥር ተመልክቷል።
በመሆኑም አመልካች ተጠሪን የቀጠረው በወቅቱ ለነበሩት ሰልጣኞች ምግብ እንዲያዘጋጅ በመሆኑና ሰልጣኞቹ ሥልጠናውን ጨርሰው ስለወጡና ተጠሪ የተቀጠሩበት ወቅታዊ ሥራና ጊዜ ሲጠናቀቅ መሰናበታቸው ሕጉን መሰረት ያደረገ ነው። ስለዚህም የሥር ፍ/ቤቶች ተጠሪ ከሥራ የተሰናበቱበት ሁኔታ ከሕግ ውጪ ነው በማለት የደረሱበት መደምደሚያ የሕግ ሥህተት ያለበት ነው።
ው ሣ ኔ 1/ የፍ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 1774 በ14/A6/97 እና የፍ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ23/1A/97 የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
2/ ተጠሪ ከሥራ የተሰናበቱት በአግባቡ በመሆኑ ወደ ሥራ እንዲመለሱ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም።
3/ ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ።
No topics extracted.