No summary available.
ሚያዘያ 30 ቀን 2009 ዓ/ም ዳኞች፡- ዓሉ መሀመድ ተኽሉት ይመስል ተፈሪ ገብሩ ቀነአ ቂጣታ ፀሀይ መንክር አመልካች፡- አቢሲንያ ባንክ አክሲዮን ማህበር የቀረበ የለም ተጠሪ፡- የኤ.ፋ.ድ.ሪ የግል ድርጅት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጅንሲ የደቡብ ሪጅን ፅ/ቤት - ነገረፈጅ ወንድወሰን ፀጋዬ- ቀረቡ መዛገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል ።
ብለናይል የተባለው ሆቴል ንብረትነቱ የአቶ ታምራት ሙለ ምትኩ የሆነ ድርጅት ህንፃ በአሁኑ አመልካች አማካኝነት በአዋጅ ቁጥር 97/1990 ከፍርድ ቤት ውጪ በ29/07/2007 ዓ/ም የሽያጭ ጨረታ ተከናውኖበታል። ይሁን እንጂ ይህ ድርጅት ከ 82 ሰራተኞች ተሰብስቦ ያልተከፈለ ብር 443,519.57 የጡረታ መዋጮ ዔዲ አለበት። በአዋጅ ቁጥር 715/2003 አንቀፅ 11(12)የጡረታ ዔዲ ከማንኛውም ዔዲ ቅድሚያ የሚሰጠው በመሆኑ የድርጅቱ ህንፃ ሽያጭ እንደፀደቀ ተጠሪ ከሽያጭ ገንዖቡ አስቀድሞ የጡረታ ዔዲውን ለአመልካች ገቢ እንዱያደርግ ትዔዙዛ ይሰጥልን ሲል ዲኝነት ጠይቋል።
የአሁኑ አመልካች በቀረበው የመከላኪያ መልስ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 በተሰጠው ሥልጣን መሰረት የመያዡ ንብረት የመሸጥ መብት እንዲለው፤ የፍ/ሕ/ቁ/3054 የቀድምትነት መብት እንደሚሰጠው፤ አመልካች የመያዛ መብቱ በ2000ዓ.ም ያቋቋመ በመሆኑ እና አዋጅ ቁጥር 715/2003 አንቀፅ 57(1) ቀደም ሲል ሲሰራባቸው የነበሩ እንደመሆናቸውን ሰለሚያመለክት፤ ገንዖቡም ከህዛብ የተሰበሰበ ከመሆኑ አንፃር የማይመለስ ከሆነ ከፍተኛ ተጽዔኖየሚያሳድር ስለመሆኑ፤ የገንዖብ መጠኑም በገለልተኛ ባለሙያ ያልተጣራ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም የሚል ክርክር ያቀረበ ሲሆን የድርጅቱ ባለቤት የተባለት ግለሰብ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት በ20/12/2007 ዓ/ም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/40(2) መሰረት ወደ ክርክሩ እንዱገቡ አዜ በማረሚያ ቤት በኩልመጥሪያ የደረሣቸው ቢሆንም ወደ ክርክሩ መግባት እንደማይፈልጉ የገለጹ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ አልፍታል።
የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙ ክርክር ከመረመረ በኋላ የአሁኑ ተጠሪ የሚጠይቀው የጡረታ መዋጮ ምን ያህል ነው? የሚለው በክሱ 443,519.57 መሆኑን መግለጹን፤
የድርጅቱ ባለቤት ወደ ክርክሩ እንዱገቡ መጥሪያ የተላከ ቢሆንም ወደ ክርክሩ አልገባም ያለ በመሆኑ ተጠሪ ያቀረበው ውዛፍ የጡረታ መዋጮ አልተስተባበለም። የቀደምትነትመብት ያለው ማንነው? የሚለው ነጥብ በተመለከተም የሁለቱም አዋጆች ይዖት እንደመረመረ፤
የጡረታ ዔዲ ከማንኛውም ዔዲ ቅድሚያ ሉከፈል የሚገባ መሆኑን አዋጅ ቁጥር 715/2003 የሚገልጽ ሰለመሆኑ ይህ አዋጅም ከአዋጅ ቁጥር 97/1990 ዓ.ም በኋላ የወጣ ህግ ከመሆኑ አንፃር ተጠሪ በተያዖው ንብረት ላይየቀዲሚነት መብት ያለው መሆኑ የሚያሳይ በመሆኑ የቀደምትነት መብት አለው ሲል ፍርድ ሰጥቷል። የአሁኑ አመልካች በስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኝትለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ ቅሬታውን ያቀረበ ቢሆንም ተቀባይነት አላገኝም ።
የአመልካች አቤቱታ ከተመረመረ በኋላ በዘህ ጉዲይ በግራ ቀኙ እያከራከረ ያለው የቅድሚያ መብት ጥያቄ ላታይ የሚገባው በአዋጅ ቁጥር 97/1990 ነው። ወይሰ አዋጅ ቁጥር 715/2003? የሚለውን ነጥብ ተጠሪ ባለበት ይጣራ ዖንድ ጉዲዩ ለዘህ ችልት ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ተጠሪም በሕጉ አግባብ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ ጨረታ ከተካሄደና ለዔዲ መክፈያ ከዋለ በኋላ የቀረበ ክስ ነው የሚለው በስር ፍርድ ቤት ያልተነሳ አዱስ ክርክር ስለመሆኑ፤ የጡረታ መዋጮ ከማንኛውም ዔዲ ቅድሚያ እንደሚሰጠው፤ዔዲው አልተካደም ተከፍሎል የሚል ማስረጃ ብቻ በማስቀረብ የሚሰተባበል ከመሆኑ አንፃር የአመልካች ክርክር ተገቢነት እንደላለው፤ የክልለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የውክልና ሰልጣንም እንዲልተነሳ በመግለጽ አቤቱታው ውድቅ እንዱደረግ ጠይቋል። የመልስ መልስም ቀርበዋል።
ከሥር የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም ግራ ቀኙ በጽሐፍ ያደረጉት ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ እንዱሁም ጉዲዩ ለዘህ ችልት ላቀርብ ከተያዖው ጭብጥ አንፃርበስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስሕተት መፈጸም አለመፈጸሙን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም አመልካች አጥብቆ የሚከራከረው የቀደምትነት መብት ባደረገው የመያዡ ውል ያረጋገጠ በመሆኑየአሁኑ ተጠሪ የጡረታ መዋጮ ዔዲ የመሰብሰብ የቅድሚያ መብት አለው ተብል የተሰጠው ፍርድ ተገቢ አይደለም በሚል ነው። ተጠሪ በበኩለ አዋጅ ቁጥር 715/2003 ዓ.ም የጡረታ ዔዲ ከማንኛውም ዔዲ ቅድሚያ እንደሚሰጠው በግልፅ የተደነገገ በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የሚነቀፍ አይደለም በማለት መከራከሩን ተገንዛበናል። አመልካች በሰበር አቤቱታው የተጠሪ ክስ ጨረታው ተከናውኖ ዔዲው ከተከፈለ በኋላ የቀረበ ነው በማለት ያቀረበው ክርክር ተጠሪ በሰጠው መልስ ክርክሩ በስር ፍ/ቤት ያልተነሳ አዱስ ክርክር ነው ውድቅ ላደረግ ይገባል ብሎል። ከመዛገቡ እንደተረዲነው አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በዋናነት ያቀረበው ክርክር በአዋጅ ቁጥር 97/1990 የቀደምትነት መብት እንዲለው፤ የአዋጅ ቁጥር 715/2003አንቀጽ 57/(1)ቀደም ሲል ሲሰራባቸው የነበሩ ተፈፃሚ ናቸው ሰለሚል የተጠሪ የቀደምነት መብት አግባብነት የለውም በሚል ነው። ከዘህ አንፃር አመልካች በስር ፍርድ ቤት የክርክር አካል ያላደረገው ጉዲይ በዘህ ሰበር ሰሚ ችልት በአዱስ መልክ ሉያነሳ እንደማይችል የፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ/329/1/ በግልጽ ደንግጓል። የፍርድ ቤት ስልጣንም በተመለከተም የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመጀመሪያ የሚመለከተው /originaljurisdiction/ ስልጣኑ የተነሳ መሆኑ ግልጽ ቢሆንም የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመወከል የሚመለከተው ጉዲይ የውክልና ስልጣን ያልተነሳ በመሆኑ ክርከርሩ የህግ መሰረት የለውም ብለናል።
አመልካች ከስር ፍርድ ቤት ጀምሮ ባነሳው ክርክር በአዋጅ ቁጥር 97/1990 የቀደምነት መብት ያቋቋመ በመሆኑ የተጠሪ ጥያቄ ውድቅ ሉያደርግ ይገባል ብሎል። ተጠሪም የአዋጅ ቁጥር 715/2003 አንቀጽ 11/12/ የቀደምትነት መብት እንደሚሰጠው ተከራክሯል።
አመልካች በውል የቀደምትነት መብት ማቋቋሙ ያከራከረ ጉዲይ አይደለም። ተጠሪም ብለናይል ከተባለው ሆቴል ያልተሰበሰበ የሰራተኞች የጡረታ መዋጮ እዲ እንዲለው አረጋግጧል። አመልካች እና ተጠሪ ብለ ናይል በተባለው ሆቴል ላይ የፍርድ ባለመብት መሆናቸው ያከራከረ ነጥብ አይደለም። አከራካሪ የሆነውን መሰረታዊ ነጥብ የዔዲው አከፊፈል ቅደም ተከተል ነው። አመልካች ከውል የመነጨ የመያዞ መብት ያለው ሲሆን ተጠሪም በህግ የተረጋገጠ የቀደምትነት መብት አለው። የስር ፍርድ ቤት አዋጅ ቁጥር 715/2003 ከአዋጅ ቁጥር 97/1990 በኋላ የወጣ መሆኑን የተጠሪ ቀደምትነት መብት ለመወሰን እንደአንድ መነሻ የወሰደው ቢሆንም ጉዲዩ መታየት ያለበት ህጎች ከወጡበት ጊዚ አንፃር ሳይሆን በክርክሩ ለተያዖው ጉዲይ ልዩ ህግ /special law/ የትኛው ነው? በሚል መሆን ይገባው ነበር። የስር ፍርድ ቤት በዘህ ረገድ የደረሰበት መደምደሚያ ተገቢነት ያለው አይደለም። ወደ አከራካሪው ነጥብ ስንመለስ አዋጁ ቁጥር 97/1990 ባንኮች በመያዛ የተያዡ የተያዘ ንብረቶች የሚሸጡበት ስርዓት የሚደነግግ ነው። አዋጅ ቁጥር 715/2003 የግል ድርጅትሰራተኞቸ ጡረታ አዋጅ የሚመለከት ሲሆን በአዋጅ አንቀጽ 11/12/“ የጡረታ መዋጮ ክፍያ ከማንኛዉም እዲ ክፍያ ቅድሚያ ይኖርዋል። በማለት የደነገገ ሲሆን የእንግሉዖኛ ትርጉም the payment of contribution shall have priority over any debt``በማለት ተገልጸዋል። ከዘህ የምንረዲው የተጠሪ የቀደሞትነት መብት በግልጽ በልዩ ህግ የተመለከተ መሆኑ ነው። አመልካች የአዋጅ ቁጥር 715/2003 አንቀጽ 57/1/ በመንቀስ የተከራከረ ቢሆንም አቋቋምኩት የሚለው የቀድምትነት መያዡ መብት የሚደግፍ ድንጋጌ ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም የአሁኑ ተጠሪ በልዩ ህጉ የጡረታ መዋጮ ክፍያ ከማንኛውም እዲ ቅድሚያ እንደሚሰጠው መሰረት በማድረግ ያቀረበው ክርክር የህግ መሰረት ያለው ነው ብለናል። የአሁኑ አመልካች በመያዞ ውል አቋቆምኩት ከሚለው የቀደምትነት መብት ይልቅ በልዩ ህግ የተቋቋመው የቀደምትነት መብት ለተጠሪ ቅድሚያ የሚሰጠው ነው። በዘህ ሁለ ምክንያት የስር ፍርድ ቤቶች የአሁኑ ተጠሪ ብር 443,519.57 የጡረታ መዋጮ እዲ በቅድሚያ እንዱከፈለው የሰጡት ፍርድ ህጉን በአግባቡ ተፈጻሚነት አድርጓል ከሚባል በስተቀር መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አልተገኘም። በዘህም ተከታዩን ወስነናል።
በደ/ብ/ብ/ህ/ክልል የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ በ11/02/2008 ዓ/ም የሰጠው ፍርድ፤ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዛገብ ቁ/67034 በ19/04/2008 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ ጸንቷል።
የዘህ ፍርድ ቤት ክርክር ያስከተለው ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸው ይቻለ ብለናል።
የዘህ ፍርድ ቤት ውሳኔ ግልባጭ ለስር ፍርድ ቤቶች ይተላለፍ ብለናል።
በዘህ ፍርድ ቤት በ16/05/2008 ዓ/ም የተሰጠው የዔግድ ትዔዙዛ ተነስቷል።
ለሚመለከተው ይፃፍ።
መዛገቡ ዖግተን ወደ መ/ቤት መልሰናል። የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.