አንድን ጉዲይ በግልግል እንዱያይ የተቀመጠን የግልግል ዲኛ ከተከራካሪ ወገኖች በአንደ እንዱነሳ ጥያቄ ሲቀርብ ዲኛው ገለልተኛ ወይም ነፃ ላይሆን የሚችልበት ግምት ለመውሰድ የሚያስችል ወይም ጥርጣሬን የሚፈጥር አከባቢያዊ ምክንያት መኖሩ ብቻ በቂ ሥለመሆኑ የፍ/ሕ/ቁ. 3340(2)፣3342
No summary available.
ግንቦት 21 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ ኃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች:- አቶ ዲዊት በላይ -- አልቀረቡም ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የግልግል ጉባኤ ዲኛ ሆኖ የተሰየመ ሰዉ ጉዲዩን ከማየት እንዱነሳ የቀረበ አቤቱታን የሚመለከት ሆኖ የተጀመረዉ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነዉ። በአሁኑ 1ኛ ተጠሪ አቤቱታ አቅራቢነት አመልካችና 1ኛ ተጠሪ በመካከላቸዉ የተፈጠረዉ አለመግባባት በግልግል ዳኞች ዉሳኔ እንዱሰጥበት ለማድረግ በአመልካች በኩል አቶ ሚካኤል ጉንታ በ1ኛ ተጠሪ በኩል የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ በመሰየማቸዉ ሁለቱ የግልግል ዳኞች ሰብሳቢ ዲኛዉን እንዱመርጡ ፍ/ቤቱ ትዔዙዛ ሰጥቷል። ሆኖም ሰብሰቢዉ ዲኛ ከመመረጡ በፉት የአሁኑ አመልካች 2ኛ ተጠሪ ጉዲዩን በገለልተኝነት ሉያዩት አይችለም በሚል ከግልግል ዲኝነት ጉባኤ አባልነት ይነሱልኝ ሲለ አቤቱታ ለፍ/ቤቱ አቅርበዋል። የአቤቱታዉ ይዖት፡- 2ኛ ተጠሪ በነጻነትና በገለልተኝነት የመሥራት ኃላፉነት እያለባቸዉ የ1ኛ ተጠሪን ዓላማ ለማሳካት የታሰበ በሚመስል መልኩ የአቶ ሚካኤል ጉንታ ከሳሽ እና በእርሳቸዉ ላይ ያለአግባብ መስካሪ ሆነዉ ተገኝተዋል። አቶ ሚካኤል እና 2ኛ ተጠሪ ሰብሳቢ ዲኛ ለመምረጥ ሞክረዉ አንደ ላላኛዉ ባቀረበዉ ጥቆማ ላይ ባለመስማማታቸዉ 2ኛ ተጠሪ ትልቅ ሥራ ስላገኘሁ የግልግል ዲኝነት ጉባኤ አባል ሆኜ አልሰራም፤ ይህንኑ ለመረጠኝ ድርጅት አሳዉቂያለሁ ማለታቸዉ እና ሐምል 21 ቀን 2007 ዓ.ም ለአመልካች በጻፈት ደብዲቤ የገለጹት አቋም የገለልተኝነት መርህን የሚቃረን ስለሆነ ከግልግል ዲኝነት ጉባኤ አባልነት ይነሱልኝ የሚል ነዉ።
1ኛ ተጠሪ በበኩላቸዉ የቀረበዉ አቤቱታ 2ኛ ተጠሪ ባላቸዉ የትምህርት ደረጃና የሥራ ልምድ እንዱሁም በግልግል ድርጅቶች ዉስጥ ስለሚያበርክቱት አስተዋጽኦ ወቀሳ እንደማይገባቸዉና ግምታዊ በሆነ ሀሳብ ከግልግል ዲኝነት ጉባኤ አባልነት ሉነሱ እንደማይገባ በመግለጽ ተከራክሯል። 2ኛ ተጠሪ በቀረበባቸዉ መቃወሚያ ላይ መልስ እንዱሰጡ የተደረገ ሲሆን ተናግረዋል የተባለዉን ነገር እንዲልተናገሩና ባልተጨበጠ ማስረጃ የቀረበባቸዉ ተቃዉሞ የሥራ ብቃትና ሀላፉነታቸዉን የማይለዉጥ መሆኑን በመግለጽ ዉድቅ እንዱደረግላቸዉ ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተዉ የስር ፍ/ቤት የግራቀኙን ክርክር ሰምቶና መርምሮ 2ኛ ተጠሪ ገለልተኛ አለመሆናቸዉንና የተጠሪን ዓላማ ለማሳካት በሚመስል ሁኔታ አቋማቸዉን አሳይተዋል የተባለዉ በማስረጃ ያልተደገፈና በግልግል ዲኝነት ጉባኤ አባልነት እንዲይቀጥለ የሚያደርግ አይደለም በማለት የአመልካችን አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ ወስኗል። አመልካች ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ቢሆንም ይግባኙን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት ሰርዜታል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለማስቀየር ነዉ።
አመልካች 2ኛ ተጠሪ ገለልተኛ ባለመሆናቸዉ ከግልግል ዲኝነት ጉባኤ አባልነት ሉነሱ ይገባል ያለባቸዉን ምክንያቶች በሰበር አቤቱታቸዉ በዛርዛር አቅርበዋል። አመልካች ያቀረቡት አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች 2ኛ ተጠሪ ከግልግል ዲኝነት እንዱነሱላቸዉ ከገለጽዋቸዉ ምክንያቶች ገለልተኛ አይደለም የሚያስብል አይደለም በማለት እንዱቀጥለ መወሰኑ ሰበር ሰሚ ችልት ከዘህ በፉት በመ/ ከሰጠዉ ዉሳኔ አንጻር አግባብነቱን ለመመርመር ሲባል ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ግራቀኙ መልስ እና የመ/መልስ በማቀባበል እንዱከራከሩ ተደርጓል።
1ኛ ተጠሪ ለአቤቱታዉ በሰጡት መልስ የተመረጡት ገላጋይ ዲኛ ወይም 2ኛ ተጠሪ ገለልተኛ አለመሆኑን የሚያሳይ ምክንያትና ማስረጃ በላለበት ከግልግል ዲኝነት ጉባኤ አባልነት ሉነሱ አይገባም። በሰበር ሰሚ ችልት በመ/ የተሰጠዉ የሕግ ትርጉም ለጉዲዩ አግባብነት የለዉም እንዱሁም አመልካች የጠቀሳቸዉ ምክንያቶች የፈጠራ፣ የሀሰትና በማስረጃ ያልተረጋገጡ በመሆናቸዉ 2ኛ ተጠሪ በጉባኤዉ በዲኝነት ሉያገለግለ ይገባል ተብል እንዱወሰን በመጠየቅ በዛርዛር ክርክራቸዉን አቅርበዋል።
2ኛ ተጠሪ በበኩላቸዉ በሰጡት መልስ በስር ፍ/ቤት በነበረዉ ክርክር ተከራካሪዎች አመልካችና 1ኛ ተጠሪ ናቸዉ። የስር ፍ/ቤት በመቃወሚያዉ ላይ አስተያየት እንድሰጥበት ብቻ ነዉ ያደረገዉ። ስለሆነም የክርክሩ ቀጥተኛ ተሳታፉ ባለመሆኔ በሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በተሰጠዉ ትርጉም መሰረት ከክርክሩ እንድወጣ እንዱደረግ እና ለተከራካሪ ወገኖች ፍትህ የማግኘት የወደፉት ጉዜ የተቃና እንዱሆን ተገቢዉ ዉሳኔ ይሰጥበት ብለዋል። አመልካች አቤቱታቸዉን በሚያጠናክር መልኩ የመልስ መልስ አቅርባል።
የግራ ቀኙ ክርክር ባጭሩ ከላይ የተመለከተዉን የሚመስል ሲሆን እኛም አቤቱታ ከቀረበበት ዉሳኔ እና አግባብነት ካለዉ የሕግ ድንጋጌ ጋር በማገናዖብ መዛገቡን መርምረናል። የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዖዉ ጭብጥ አንጻር መርምረን እንደተረዲነዉ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተዉ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካች 2ኛ ተጠሪ የግልግል ዲኝነት ጉባኤዉ አባልነታቸዉ እንዱነሱ ያቀረቡትን አቤቱታ ዉድቅ ያደረገዉ የአመልካች አቤቱታ በማስረጃ የተደገፈ አይደለም በማለት ነዉ። የስር ፍ/ቤት በርግጥ 2ኛ ተጠሪ አቋማቸዉን አሳይተዉበታል ያለዉን ሐምል 21 ቀን 2007 ዓ.ም ተጻፈ የተባለዉን ደብዲቤ አስቀርቦ እንደተመለከተዉና የደብዲቤዉ ይዖት 2ኛ ተጠሪ የገለልተኝነት መርህን የሚቃረን ሀሳብ ወይም አቋም አንጸባርቋል የሚያስብል አለመሆኑን በፍርደ ገልፅዋል። ሆኖም ላልች ነጥቦችና አቋማቸዉን አንጸባርቀዋል የተባለትን ንግግሮች 2ኛ ተጠሪ ተናግረዋል የተባለት ለአቶ ሚካኤል ጉንታ ከመሆኑ አንጻር ለምን ቀርበዉ እንዲልተሰሙና እንዲልተጣራ ግልጽ አይደለም።
በልላ በኩል አቤቱታዉ ለሰበር ያስቀርባል ሲባል ወደ ተያዖዉ ጭብጥ ስንመለስ 2ኛ ተጠሪ በስር ፍ/ቤት ክርክር ከነበረዉ ሚና እና በሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ከተሰጠዉ አስገዲጅ ትርጉም አንጻር በግልግል ጉባኤ አባልነት ይቀጥለ መባለ በአግባቡ ነዉ? ወይስ አይደለም?
የሚለዉን እንመልከት። ይህ ሰበር ሰሚ ችልት ከዘህን ቀደም በተጠቀሰዉ መዛገብ የሰጠዉ ትርጉም በፍ/ብ/ሕ/ቁ 3342 መሰረት በአንድ የግልግል ዲኛ ላይ መቃወሚያ ሲቀርብበት ተከራካሪ ሆኖ መቅረብ ያለበት ማን እንደሆነ? ከጉባኤዉ እንዱነሳ ጥያቄ የቀረበበት ዲኛ ጥያቄዉን ካነሳዉ ተከራካሪ ወገን ጋር መልስ ሰጭ ወይም ተጠሪ ሆኖ ቀርቦ ዛርዛር ክርክር ካቀረበ በኃላ፤ ፍርድ ቤት ተከራካሪ ሆኖ በቀረበበት ጉዲይና በተከራካሪነት ቀርቦ ሲሞግተዉ የነበረዉን ተከራካሪ ወገን ለግልግል ዳኞች የሚያቀርበዉን ክርክርና ማስረጃ በገለልተኝነት ሰምቶ ሉወስን ይችላል ተብል በግልግል ዲኝነት እንዱሰየም ማድረግ በመርህ ደረጃ የግልግል ዲኝነቱን ዓላማ የማያሳካ መሆኑን፤
የግልግል ዲኛዉ ጉዲዩን ለማስረዲት ከሚቀርብ በቀር ዲኛዉን ከዲኝነቱ የሚያስነሳዉ በቂ ምክንያት አለ ወይስ የለም በሚለዉ ጭብጥ ዘሪያ ተከራካሪ ሆኖ መሰለፈንና ዛርዛር ክርክር የሚቀርብበት ሁኔታ መኖር የላለበት መሆኑን ግልጽና አስገዲጅ ትርጉም ሰጥቶበታል።
በተያዖዉ ጉዲይ ምንም እንኳ 2ኛ ተጠሪ ለሰበር አቤቱታዉ በሰጡት መልስ የክርክሩ አካል ሆኖ መቀጠል ስለማይገባቸዉ ከክርክሩ ዉጭ እንዱደረጉ የጠየቁ ቢሆንም በስር ፍ/ቤቶች የነበራቸዉን ተሳትፍ ምን እንደነበረ መመልከቱ ተገቢ ነዉ። አመልካች ለስር ፍ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታ 2ኛ ተጠሪን በተከራካሪነት የክርክሩ ተካፊይ እንዱሆኑ በአቤቱታቸዉ አልጠቀሱም። የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በራሱ ተነሳሽነት 2ኛ ተጠሪ መልስ እንዱሰጥበት ትዔዙዛ የሰጠ ሲሆን 2ኛ ተጠሪም ዛርዛር ክርክር አቅርበዋል። በርግጥ የዘህ ዓይነት አቤቱታ የቀረበበት የግልግል ዲኛ የበኩለን አጭር አስተያይት እንዱያቀርብ ማድረግ የተለመደ አሰራር ቢሆንም እንደአንድ ተከራካሪ ወገን ተወስድ በመልስ ሰጭነት ተሰይሞ የክርክሩ ሙለ ተካፊይ መደረጉ ተገቢ አይደለም። የስር ፍ/ቤት በፍርደ ላይ 2ኛ ተጠሪን በተከራካሪነት ወይም በመልስ ሰጪነት ከመሰየሙም በላይ 2ኛ ተጠሪ ያቀረበዉን አስተያየት በመደበኛ ተከራከሪ እንደቀረበ ክርክር አድርጎ መዛግቦታል። ይህም በመጀመሪያዉ ክርክር ብቻ ሳይሆን በይግባኝ ሰሚ እና በሰበር ሰሚ ችልት ደረጃ 2ኛ ተጠሪ በመዛገቦቹ በመልስ ሰጭነት ወይም በተጠሪነት የክርክሩ ተሳታፉ እንዱደረግ ምክንያት ሆኗል።
የፍ/ብ/ሕ/ቁ 3340(2) መሰረት እና በሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ከተሰጠዉ አስገዲጅ ትርጉም አንጻር ዲኛዉን ገለልተኛ ወይም ነጻ ላይሆን ይችላል በማለት ከግልግል ዲኝነቱ ለማስነሳት የግድ ዲኛዉ ከአንደኛዉ ተከራካሪ ወገን ጋር ያለዉን ጠንካራ ግንኙነት በጠንካራ ማስረጃ ማረጋገጥ አይጠበቅም። ዲኛዉ ገለልተኛ ወይም ነጻ ላይሆን የሚችልበት ግምት ለመዉሰድ የሚያስችል ወይም ጥርጣሬን የሚፈጥር አካባቢያዊ ምክንያት መኖሩ ብቻ በቂ ነዉ።
ስለሆነም 2ኛ ተጠሪ መ/ሰጪ ወይም ተጠሪ እንዱሆንና ዛርዛር ክርክር እንዱያቀርብ በማድረግ የክርክሩ ተካፊይ በተደረገበት ሁኔታ በአመልካችና በ1ኛ ተጠሪ መካከል ያለዉን ክርክር የግልግል ዲኛ ሆኖ በገለልተኝነትና በነጻነት መመልከት ስለመቻለ ጥርጣሬ የሚፈጥር በመሆኑ 2ኛ ተጠሪ ከግልግል ጉባኤ አባልነቱ እንዱነሱ ማድረግ ተገቢነት ይኖረዋል። በመሆኑም ተከታዩ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ ሚያዘያ 08 ቀን 2008 ዓ.ም ተሰጥቶ፤
በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ ሕዲር 14 ቀን 2009 ዓ.ም በተሰጠ ትዔዙዛ የጸናዉ ዉሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
2ኛ ተጠሪ በአመልካች በቀረበዉ አቤቱታ ላይ አስተያየት ከመስጠት ባለፈ ዛርዛር ክርክር እንዱያቀርበና በመ/ሰጪነት ተሰይሞ የክርክሩ ተካፊይ እንዱሆን በስር ፍ/ቤት የተደረገ በመሆኑ ከዘህ በኃላ ገለልተኛና ነጻ ሆኖ ጉዲዩን ያየዋል የሚል ግምት ባለመኖሩ ከግልግል ዲኝነት አባልነት እንዱነሳ ተወስኗል። 1ኛ ተጠሪ በ2ኛ ተጠሪ ምትክ ላላ የግልግል ዲኛ መምረጥ እንዱችል ተገቢዉ ይፈጸም ተብሎል።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸዉን ይቻለ።
ሰበር/መ/ ሕዲር 21 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሣሁን እትመት አሰፊ አመልካች፡- የመንግሥት ሰራተኞች ማሕበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ …ነ/ፈጅ ሄኖክ መሳው ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ር ቸኮል ሙለጌታ ….. ቀረቡ መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.
ሐምል 27 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት ባቀረበው አቤቱታ መነሻነት ነው።ተጠሪ ከነሐሴ 01 ቀን 1990 ዓ.ም እስከ ሚያዛያ 30 ቀን 2001 ዓ.ም ድረስ በወንጀል ጥፊተኛ ተብለው በእስር ላይ የቆዩ መሆናቸውን በመጥቀስ ተቋርጦ የቆየው የጡረታ አበል ይከፈላቸው ዖንድ ለአመልካች አቤቱታ አቅርበዋል፤አመልካች በጉዲዩ ላይ የሕግ አስተያየት እንዱሰጥበት አድርጓል፤የአመልካች መሥሪያ ቤት የሕግ ጉዲዮች ዲይሬክቶሬት ተጠሪ የጡረታ አበል በመቀበል ላይ ያለት በአስገድድ መድፈር ወንጀል ጥፊተኛ ተብለው 12 ዓመት ከተቀጡ በኋላ በመሆኑ እየተከፈላቸው የነበረው የጡረታ አበል አግባብ አይደለም፤ለወደፉትም መቋረጥ አለበት የሚል አስተያየት በመስጠቱ አመልካች የተጠሪን የጡረታ አበል ክፍያ አቋርጧል።
ተጠሪ በአመልካች መሥሪያ ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለማሕበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ይግባኝ አቅርበዋል።ይግባኝ ሰሚው ጉባኤ ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ ተጠሪ በወንጀል ጥፊተኛ ተብለው 12 ዓመት ጽኑ እሥራት የተፈረደባቸው በመሆኑ እና የቀድሞ የጡረታ አዋጅ ቁጥር 5/1967 አንቀጽ 34 የመንግሥት ሰራተኛ በወንጀል ተከሶ ጥፊተኛ መሆኑ በሕግ በተቋቋመ ፍ/ቤት ከተረጋገጠበት እና ቢያንስ የሦስት ዓመት ጽኑ እሥራት ቅጣት ከተወሰነበት የጡረታ መብቱን ያጣል ወይም በመከፈል ላይ ያለው የጡረታ አበል ይቋረጥበታል የሚል በመሆኑ አመልካች የሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው በማለት አጽንቶታል።
ተጠሪ በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ አቅርበዋል።ይግባኙ የቀረበለት ፍ/ቤት ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ አመልካች እና የማሕበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የተጠሪን የጡረታ አበል ለማቋረጥ መሰረት ያደረጉት የአዋጅ ቁጥር 5/1967 አንቀጽ 34 ድንጋጌን ነው፤ሆኖም ይህ አዋጅ በአዋጅ ቁጥር 424/97 እና 714/2003 ተሽሯል፤አዋጅ ቁጥር 714/2003 በወንጀል የተቀጣ ሰው የጡረታ መብት እንደሚያጣ አይደነግግም፤የዘህ አዋጅ አንቀጽ 49/1 ውዛፍ ክፍያ በሦስት ዓመት ይርጋ እንደሚቋረጥ የሚደነግግ በመሆኑ ውዛፍ ክፍያ ለመክፈል አዋጁ ይከለክላል በማለት የተሰጠው ውሳኔ ተገቢ ነው ሆኖም ተጠሪ የጠየቀው ውዛፍ ክፍያ እንዱከፈለው ሆኖ ሳለ አመልካች የተሻረን አዋጅ በመጥቀስ ተጠሪ ባልጠየቀው ዲኝነት ላይ እየተከፈለ ያለው የጡረታ አበል እንዱቋረጥ በማለት መወሰኑ ተገቢ አይለም በማለት አመልካች እና የማሕበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የሰጡትን ውሳኔ በመሻር የተጠሪ የጡረታ አበል ሉቋረጥ አይገባም፤የተጠሪ የጡረታ አበል ከተቋረጠበት ጊዚ ጀምሮ ይከፈላቸው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ዋና ይዖት፡-ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የአመልካች ውሳኔ ተገቢ ነው?
ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዛ ውሳኔ መስጠት ሲገባው ተጠሪ በጠየቁት የውዛፍ የጡረታ አበል ይከፈለኝ መነሻነት በመከፈል ላይ ያለው የጡረታ አበል እንዱቋረጥ መደረጉ ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ መስርቶ ውሳኔ መሰጠቱ ተገቢ አይደለም፤በአዋጅ ቁጥር 714/2003 አመልካች መሥሪያ ቤት ተጠየቀም አልተጠየቀም በራሱ ተነሳሽነት ምርመራ ካደረገ በኋላ አላግባብ ሲከፈል የተገኘን የጡረታ አበል ሉያስቆም ይችላል፤በጽኑ እሥራት ምክንያት ተከልክል የነበረው የጡረታ መብት የተፈቀደው በአዋጅ 907/2007 ነው፤ሆኖም ይህ አዋጅ ውዛፍ የጡረታ አበልን ሳይጨምር ለወደፉት የጡረታ አበል የማግኘት መብት ይኖረዋል በሚል የሚደነግግ እንጂ ውዛፍ ክፍያን የሚፈቅድ አይደለም፤አመልካች የተጠሪን የጡረታ አበል በማቋረጥ ውሳኔ የሰጠው ይህ አዋጅ ከመውጣቱ በፉት ነው፤ተጠሪ የጡረታ አበል መቀበል የሚችለት አዋጁ በሥራ ላይ ከዋለበት ጊዚ ጀምሮ በመሆኑ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የተጠሪ የጡረታ አበል ተቋርጦ ከነበረበት ጊዚ ጀምሮ እንዱከፈላቸው በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት ነው።በልላ በኩል አዋጅ ቁጥር 345/95 እና አዋጅ ቁጥር 714/2003 አዋጆቹ ከመውጣታቸው በፉት የነበሩት ሕጋዊ ሁኔታዎች ተፈጻሚነታቸው እንደሚቀጥል የሚደነግጉ በመሆኑ አመልካች እና ይግባኝ ሰሚው ጉባኤ የሰጡት ውሳኔ የሕግ መሰረት አለው የሚል ነው።የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ለተጠሪው እንዱከፈላቸው የተወሰነው የጡረታ አበል ክፍያ ከአዋጅ ቁጥር 907/2007 አንጻር ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዘህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል።ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎም ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው።ይህ ችልትም እንዱጣራ የተያዖውን ነጥብ በጭብጥነት በመያዛ የግራቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምሮታል።
አመልካችም ሆነ የማሕበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤው የተጠሪ የጡረታ አበል ሉቋረጥ ይገባል ከሚል መደምደሚያ ላይ ሉደርሱ የቻለት የጡረታ ሕግን አስመልክቶ በወቅቱ ሥራ ላይ የነበሩትን የሕግ ማእቀፍች መሰረት በማድረግ በመሆኑ ተጠሪ በወንጀል ተከሰው ጥፊተኛ ተብለው ከሦስት ዓመት በላይ ጽኑ እሥራት ቅጣት የተወሰነባቸው በመሆኑ የጡረታ መብታቸው ሉቋረጥ ይገባል በማለት መወሰናቸው ተገቢ ነው።በልላ በኩል የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አዋጅ ቁጥር 907/2007 ከመውጣቱ በፉት አሥቀድመው ሥራ ላይ የነበሩት የጡረታ ሕግ ማዔቀፍች በወንጀል ጥፊተኛ የተባለ እና ከሦስት ዓመት በላይ ጽኑ እስራት የተፈረደበት ሰው የጡረታ መብቱን እንደሚያጣ የሚደነግጉ ሆነው ሳላ በሥራ ላይ የነበሩት አዋጆች ከሦስት ዓመት በላይ በጽኑ እስራት የተቀጣ ሰው የጡረታ መብቱን እንዱያጣ አይደነግጉም በማለት የደረሰበት መደምደሚያ ተገቢ ኖኖ አላገኘነውም።
አመልካች እና የማህበራዊ ዋስትና ይግባኝ ሰሚ ጉባኤው ውሳኔ ከሰጡ በኋላ አዋጅ ቁጥር 907/2007 ወጥቶ ሥራ ላይ ውሎል። የዘህ አዋጅ አንቀጽ 11/9 የጡረታ አበል ተጠቃሚ ሆኖ በወንጀል ጥፊት ምክንያት ከሦስት ዓመት ያላነሰ ጽኑ እስራት ቅጣት ተፈርድበት የዖለቄታ የጡረታ አበል መብቱን ያጣ ባለመብት ማሻሻያ አዋጁ ከጸናበት ጊዚ ጀምሮ ውዛፍ አበል ሳይጨምር የጡረታ አበል የማግኘት መብት እንደሚኖረው የሚደነግግ በመሆኑ አዋጁ ከመውጣቱ በፉት ለነበሩ የማሕበራዊ ዋስትና ጉዲዮች ተፈጻሚነት ያለው ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች ለዘህ ችልት ባቀረበው ክርክርም አዋጅ ቁጥር 907/2007 ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለው ሕግ መሆኑን አምኖ የተከራከረ በመሆኑ ተጠሪ በወንጀል ጥፊተኛ ተብለው ከሦስት ዓመት በላይ ጽኑ እስራት ተፈርድባቸው የነበረ እና አስቀድመው በሥራ ላይ በነበሩት ሕጎች የጡረታ መብታቸው የተቋረጠ ቢሆንም በአዋጅ ቁጥር 907/2007 መሰረት የጡረታ ክፍያ የማግኘት መብት አላቸው።ሆኖም የአዋጅ አንቀጽ 11/ 9 የጡረታ ባለመብቱ የጡረታ ክፍያ የማግኘት መብት የሚኖረው ማሻሻያ አዋጁ ከጸናበት ጊዚ ጀምሮ ውዛፍ አበል ሳይጨምር እንደሆነ የሚደነግግ በመሆኑ የተጠሪ የጡረታ ክፍያ ከተቋረጠበት ጊዚ ጀምሮ እንዱከፈላቸው በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።በዘህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ሐምል 27 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ተሻሽሎል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የተጠሪ የጡረታ አበል በተጠሪ የቋረጠበት ጊዚ በሥራ ላይ የነበሩት የጡረታ ሕግ ማዔቀፍች በወንጀል ጥፊተኛ ተብል ከሦስት ዓመት በላይ ጽኑ እስራት የተፈረደበት ሰው የጡረታ መብቱን እንደሚያጣ አይደነግጉም በማለት የሰጠው የውሳኔ ክፍል እና የተጠሪ የጡረታ አበል ክፍያ ከተቋረጠበት ቀን ጀምሮ እንዱከፈላቸው በማለት የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ተሽሯል።
የተጠሪ የጡረታ አበል ሉቋረጥ አይገባም በማለት የተሰጠው የውሳኔ ክፍል ጸንቷል።
ተጠሪ የጡረታ አበል ክፍያ የመንግሥት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅን ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 907/2007 ከጸናበት ከሐምል 01 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ይከፈላቸው ብለናል።
በዘህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ኪሣራ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል።ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.