አንድ ዲኛ ተግባሩን በሚያከናውንበት ወቅት የፍርድ ስራ ስህተት ተፈጽሟል ከተባለ በይግባኝ ፣ በሰበር ወይም በልላ በህግ በተዖረጋ ስርዓት ከማሳረም በቀር ስልጣንን አላግባብ ተጠቅሟል በሚል ሉቀጣ የማይችል የትግራይ ክልል ዓቃቤ ህግ እና አቶ ገብረሃርያ አሰፊ
No summary available.
ታህሳስ 24 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሀመድ ተኸሉት ይመስል ቀነዓ ቂጣታ ሰናይት አድነው ጳውልስ አርሺሶ አመልካች፡- የትግራይ ክልል ዐቃቤ ህግ ተጠሪ፡- አቶ ገብረአርዔያ አሰፊ መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካት በሥልጣን አላግባብ የመገልገል የደንብ መተላለፍ ጥፊት አልፈፀመም በማለት የትግራይ ክልል ሰበር ችልት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? ሚለውን ጭብጥ በሰበር አጣርቶ ለመወሰን ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ ደረጃ የታየው በሐውዚን ወረዲ ፍርድ ቤት ነው። በወረዲው ፍርድ ቤት አመልካች ተጠሪና ላልች በዘህ ክርክር ተሣታፉ ያልሆኑ ሰዎች በወንጀል ሕግ አንቀጽ 796 የተመለከተውን በመተላለፍ፤ ሐውዚን ከተማ ማህበራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች ሆነው ሲሰሩ መጣራት የሚገባውን ነገር ሣያጣሩና አቶ ሃይላይ ገራስና ወ/ደብረብርሃን አረጋዊ እህታቸው እንደፈረሙ በማሰብ ፈርመናል ብለውናል በማለት ግንቦት 7 ቀን 2009 ዓ.ም ዔርቅ በማፅደቅና የአቶ ሃይላይ ገራስ ጋብቻ ፈርሷል የሚል ማስረጃ ለመቀላ ማዖጋጃ ቤት በመላካቸው በሥልጣን አላግባብ ወንጀልፈፅመዋል የሚል ክስ አቅርቧል።
ተጠሪ በአመልካች የቀረበበትን የወንጀል ክስ ክድ ተከራክሯል። አመልካች ሶስት ምስክሮች በማቅረብ፤ ከተጠሪ ፉት ያልቀረቡት አቶ ሀይላ ገራስና ወ/ደብርሃን አረጋዊ ለማህበራዊ ዳኞች ፉት ቀርበው ሣይፈርሙ፤ የፈረሙ በማስመሰልና የዔርቅ ሰነድ በማፅደቅ ለመቀላ ማዖጋጃ ቤት ማስረጃ ልኳል በማለት የመሰከሩ ሲሆን፤ የፅሐፍ ማስረጃም አመልካች አቅርቧል። ተጠሪ የመከላከያ ማስረጃ አቅርቧል። የወረዲው ፍርድ ቤት ተጠሪ የተጠቀሰበትን የወንጀል ህግ አንቀጽ 796 በመተላለፍ ጥፊት የፈፀመ ነው በማለት በሁለት ወር እስራት ተጠሪ እንዱቀጣና ቅጣቱ በሁለት ዓመት የሙከራ ጊዚ እንዱገደብ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
የወረዲው ፍርድ ቤት የሰጠውን የጥፊተኝነት ውሣኔ የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አፅንቶታል።
ተጠሪ በበኩለ መምህር የማነብርሃን እና ወ/ሮ ምፅላል ሃይላይ የሥጋ ዛምድና ያላቸው መሆኑን በፖሉስ ጣቢያ ከተካሰሱ በኋላ ቤተዖመድ የተራቁ መሆኑን በመግለፅ የሰጠሁት ማስረጃ ስህተት የለበትም በወንጀልም አያስጠይቀኝም በማለት ግንቦት 17 ቀን 2007 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል።
አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
ተጠሪና ላልች የማህበራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች አፀደቁት የተባለው የዔርቅ ሰነድ መነሻው በሐውዚን ከተማ ፖሉስ ጣቢያ ያቀረበን የወንጀል ክስ ቀሪ ለማድረግ፤ የወንድና የሴት ቤተዖመድች ሶስት ሽማግላዎች ባለበት የታረቁ መሆኑን የሚገልፅናከአንደኛ እስከ አምስተኛ ስማቸው የተገለፀው ሰዎች የፈረሙ መሆኑን የሚገልፅና 6ኛ ምፅላል ሃይላይ አልፈረመችም የሚልና የአስታረቁትን ሶስት ሰዎች ስም የያዖ መሆኑንና ተጠሪ ከላልች የማህበራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች ጋር በመሆን የምስክሮችን ቃል ሰምቶ፤ ማስረጃ የሰጠ መሆኑ ተረጋግጧል።
አመልካች የሚከራከረው ተጠሪ ከላልች ማህበራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች ጋር ሆኖ ማጣራት የሚገባውንና ፍሬ ነገር ሣያጣራ በወቅቱ የዔርቅ ሰነደን ለማፅደቅ በማህበራዊ ፍርድ ቤት ያልቀረቡ የወ/ሮ ምፅላል ሃይላይ ወላጆች፣ ችልት የቀረቡ መሆኑን በአግባቡ ሣያረጋግጥ፣ በችልት እንዱቀርቡ በማስመሰል ማስረጃ ሰጥቷል በማለት ነው። ተጠሪ ከላልች የሀውዚን ከተማ ማህበራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች ጋር በመሆን፣ ምስክሮችን በመስማት መምህር የማነብርሃን ወ/ሮ ምፅላል ሀይላይ በትግራይ ክልል የቤተሰብ ህግ መሰረት ጋብቻ እንዲይፈፅሙ የሚከለክል የሥጋ ዛምድና ያላቸው መሆኑን በመግለፅ፣ የዔርቅ ሰነደን የምስክሮች ቃል ያረጋገጡ መሆኑን ገልፀው ለመቀላ ማዖጋጀ ቤት ማስረጃ መስጠታቸው ተረጋግጧል።
ተጠሪ ማስረጃውን አጣርቶ የሰጠው ከላልች የሀውዚን ማህበራዊ ፍርድ ቤት ዳኞች ጋር በመሆንና በችልት በመሰየም እንደሆነ በመከላከያ ማስረጃ ተረጋግጧል። የሀውዚን ከተማማህበራዋ ፍርድ ቤት ዳኞች /ተጠሪን ጨምሮ /ይህንን ማስረጃ የሰጡት የኢ.ፋ.ዳ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 37 ንዐስአንቀጽ 1 1985 በወጣው የትግራይ ክልል ሕገ መንግስት 89 እንደተሻሻለ እና በትግራይ ክልል ምክር ቤት ባወጣው የቤተሰብ ሕግ መሰረት በተሰጣቸው የዲኝነት ነክ ሥልጣን መሰረት በማድረግ ነው። ይህ ከሆነ፣ ተጠሪ በሕግ የተሰጠውን የዲኝነት ነክ ተግባሩን ከላልች ዳኞች ጋር በሚወጣበት ወቅት፤ የፍርድ ሥራ ስህተት በይግባኝ፤ በሰበር ወይም በልላ በሕግ በተዖረጋ የፍርድ ሥራ ስህተት ማረሚያ መንገድች የሚመለከታቸው ግለሰቦች አቅርበው እንዱያሳርሙ ከሚደረግ በስተቀር፣ ተጠሪ በተናጠል የወንጀል ህግ አንቀጽ 796 በመተላለፍ በሥልጣን አላግባብ የመገልገል ወንጀል ፈፅሟል በማለት የወንጀል ክስ የሚቀርብበትና ኃላፉ የሚሆንበት ህጋዊ ምክንያት የለም።
ከዘህ አንፃር የትግራይ ክልል ሰበር ችልት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡትን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ በመሻር ተጠሪ በነፃ እንዱሰናበት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
መዛገቡ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ። የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.