በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ አንድ ጠበቃ የጥቅም ግጭት ሉፈጥር በሚችልበት ሁኔታ የተለያዩ ተከራካሪዎችን በመወከል መከራከር የማይችልና ይሄንኑ ተግባር ፈፅሞ ሲገኝ እንደ ከባድ የሥነ -ምግባር ጥሰት ሉቆጠር የሚችል ስለመሆኑ የኦሮሚያ ክልል የጠበቆች እና ሕግ ጉዲይ ፀሃፉዎች እና ፍቃድ አሰጣጥ አዋጅ ቁ. 182/2005 አንቀፅ 36(3) ደንብ ቁጥር 57/92 አንቀፅ 10፣11፣12 እና 13
No summary available.
የሰ/መ/ ሕዲር 30 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሣሁን እትመት አሰፊ አመልካች፡- አቶ ጉታ ጫካ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1.የኦሮሚያ ፍትሕ ቢሮ አልቀረቡም 2. አቶ አብደልወሃብ ተካ አልቀረቡም መዛገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በጥብቅና አገልግልት ላይ በተፈጸመ የሥነምግባር ጥሰት ምክንያት የተሰጠ የዱስፕሉን ውሳኔን የሚመለከት ነው። የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠበቆች የሥነምግባር ጉዲይ ጉባኤ የአሁን አመልካች የጥብቅና አገልግልት ሲሰጡ ፈጽመውታል በተባለው የሥነምግባር ጥሰት ምክንያት የቀረበባቸውን የዱሲፕሉን ክስ ተመልከቶ ውሳኔ ሰጥቷል።በአመልካች ላይ የቀረበው የዱስፕሉን ክስ በአጭሩ፡-
ሁለተኛ ተጠሪ ንብረትነቱ የወ/ሮ ላቀች ጎሳዬ በሆነ አይሱዘ ተሽከርካሪ እየተጓዘ የሰላዲ ቁጥሩ ኮድ 3-00972 ኢት የሆነ እና አቶ መሐመድ ይመር የተባለ ግለሰብ ሲነዲው ከነበረ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨት እሳቸውን ጨምሮ በአይሱዘ መኪናው ውስጥ በነበሩ ግለሰቦች ላይ ጉዲት የደረሰባቸው በመሆኑ ጉዲቱን አድርሷል በተባለው አቶ መሐመድ ይመር ላይ የወንጀል ክስ ቀርቦበት የነበረ ቢሆንም አመልካች ለግለሰቡ ጥብቅና በመቆም ከወንጀል ክሱ በነጻ እንዱሰናበት በማድረጋቸው፤
ሁለተኛ ተጠሪ ለደረሰባቸው ጉዲት ካሳ እንዱከፈላቸው በማለት ሲጓዘበት የነበረው አይሱዘ ተሽከርካሪ ባለቤት ወ/ሮ ላቀችጎሳዬ ላይ ባቀረቡት ክስ አመልካች ተከሳሽዋን ወክለው የጥብቅና አገልግልት በመስጠታቸው፤
ሁለተኛ ተጠሪ ካሣ እንዱከፈላቸው ባቀረቡት ክስ ላይ ጣልቃ ገብ ሆኖ ለሚከራከረው የመድን ድርጅት አመልካች ጠበቃ በመሆን በመከራከራቸው ምክንያት አመልካች ሁለንም ወገኖች በመወከል መከራከር አይችለም የሚል መቃወሚያ 2ኛ ተጠሪ ያቀረቡ መሆኑን፤ክርክሩን ሲመራ የነበረው ፍ/ቤት አመልካች ተከሳሽን እና ጣልቃገብን በመወከል ክርክሩ እንዱቀጥል ቢደረግ የጥቅም ግጭት ሉኖር አይችልም ለማለት ስለማይቻል እና የጥቅም ግጭቱ ካለ ደግሞ የክርክሩን ሂደት የሚያዙባ በመሆኑ አመልካች ተከሳሽ / የጉዲት አድራሹን መኪና ባለቤት / እና ጣልቃ ገብን / መድን ድርጅትን / ወክል መከራከር አይችልም ተከሳሽ ላላ ሰው በመወከል ወይም በራሷ እንድትከራከር በማለት ብይን የሰጠ መሆኑን፤በዘህ ብይን ላይ በየደረጃው ባለ ፍ/ቤቶች ክርክር ተደርጎበት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.
የተሰጠውን ብይን ያጸናው መሆኑን በመግለጽ አመልካች የጥብቅና ሙያ የሥነ ምግባር ጥሰት የፈጸሙ በመሆናቸው ቅጣት እንዱተላለፍባቸው የሚል ነው።
አመልካች ለቀረበባቸው የዱሲፕሉን ክስ በሰጡት መልስ አመልካች ተከሳሽ እና ጣልቃ ገብን ወክል መከራከር አይችልም በማለት ብይን የተሰጠው ግንቦት 23 ቀን 2004 ዓ.ም በመሆኑ ጉዲዩ በይርጋ የሚታገድ መሆኑን፤ጉዲዩ መታየት ያለበት በአዋጅ ቁጥር 86/96 እንጂ በአዋጅ ቁጥር 182/2005 ላታይ የማይገባ መሆኑን፤ተከሳሽን በመወከል እንዲይከራከሩ የሚያግዲቸው ሕግ የላለ መሆኑን፤ተከሳሽ በፍትሐብሕር ጉዲይ ጥፊት የላለባቸው መሆኑን፤ተከሳሽን ወክለው መከራከራቸው በአመልካች ላይ የሚደርስ ጉዲት የላለ መሆኑን፤ተከሳሽ ለተሽከርካሪዋ መድን ሽፊን ያላቸው በመሆኑ እና ለመድን ድርጅቱ ጠበቃ በመሆናቸው መድን ድርጅቱን ወክለው መልስ መስጠታቸው ጥፊት አለመሆኑን፤በተከራካሪዎች ላይ ሉፈጠር የሚችል የጥቅም ግጭት የላለ መሆኑን በመግለጽ ተከራክረዋል።
ጉዲዩ የቀረበለት የሥነ ምግባር ጉዲይ ጉባኤ ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ በጉዲዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠው ጥር 29 ቀን 2006 ዓ.ም በመሆኑ አመልካች ጉዲዩ በአዋጅ ቁጥር 182/2005 መሰረት መታየት የለበትም በማለት ያቀረቡት መቃወሚያ አመልካች ተከሳሽን እና ጣልቃገብን በመወከል ሉከራከር አይገባም በማለት ታሕሳስ 23 ቀን 2004 ዓ.ም የተሰጠው ብይን በየደረጃው ባለ ፍ/ቤቶች ክርክር ሲደረግበት ቆይቶ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በጉዲዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ የሰጠው ጥር 29 ቀን 2006 ዓ.ም በመሆኑ እና የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠውም አዋጅ ቁጥር 182/2005 ከታወጀ በኋላ በመሆኑ ጉዲዩ በቀድሞ አዋጅ መሰረት መታየት አለበት በማለት የቀረበው ቅሬታ የሕግ መሰረት የለውም፤የይርጋ መቃወሚያውን በተመለከተ የቀረበው ክርክር በጉዲዩ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠው ጥር 29 ቀን 2006 ዓ.ም በመሆኑ እና 2ኛ ተጠሪ ለጉባኤው አቤቱታ ያቀረቡት ነሐሴ 13 ቀን 2006 ዓ.ም በመሆኑ የይርጋ መቃወሚያው ተቀባይነት የለውም በማለት የአመልካችን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ውድቅ አድርጓል።
በዋናው ጉዲይ ላይም አመልካች የአደጋ አድራሹ መኪና አሽከርካሪ በሆነው ግለሰብ ላይ የቀረበበትን የወንጀል ክስ በጥብቅና በመከራከር በነጻ እንዱሰናበት አድርጓል፤2ኛ ተጠሪ ባቀረበው የፍትሐብሕር ክስ ላይ ተከሳሽ ለሆኑት የመኪናው ባለቤት እና ጣልቃገብቶ ለተከራከረው መድን ድርጅት በጥብቅና በመወከል የጥቅም ግጭት ባለው ጉዲይ ላይ በመከራከሩ በ2ኛ ተጠሪ ተቃውሞ ቀርቦበት ጉዲዩን ሲያይ የነበረው ፍ/ቤት አመልካች ተከሳሽን እና ጠልቃገብን በመወከል ክርክሩ እንዱቀጥል ቢደረግ የጥቅም ግጭት ሉኖር አይችልም ለማለት ስለማይቻል እና የጥቅም ግጭቱ ካለ ደግሞ የክርክሩን ሂደት የሚያዙባ በመሆኑ አመልካች ተከሳሽ እና ጣልቃ ገብን ወክል መከራከር አይችልም በማለት ብይን ሰጥቶበታል፤ይህ ብይን እስከ ፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ክርክር ተደርጎበት ጸንቷል፤አመልካች በተሰጠው ብይን ላይ የሕግ ሥሕተት ተፈጽሟል በማለት በየደረጃው ባለ ፍ/ቤቶች ቅሬታ በማቅረብ ክርክሩን አሳግድ የ2ኛ ተጠሪ ጉዲይ በወቅቱ ውሳኔ እንዲይሰጥበት በማድረግ ላልተገባ ወጪ የዲረገው እና ከፍተኛ መጉላላት እንዱደርስበት ያደረገው በመሆኑ በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት የጠበቆች እና ሕግ ጉዲይ ጸሐፉዎች እና የፈቃድ አሰጣጥ አዋጅ ቁጥር 182/2005 አንቀጽ 36/3/15 መሰረት ከባድ የሥነምግባር ጥፊት ፈጽመዋል በማለት አመልካች / አሥር ሺህ ብር / የገንዖብ መቀጮ እንዱቀጡ እና የጥብቅና ፈቃዲቸው ለ6 ወር ታግድ እንዱቆይ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበዋል። ይግባኙ የቀረበለት ፍ/ቤት ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የሥነ ምግባር ጉባኤው የሰጠውን ውሳኔ አጽንቶታል።በመቀጠል አመልካች ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ ያቀረቡ ቢሆንም አቤቱታቸው ተቀባይነት አላገኘም።የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዖትም፡-ጉባኤው አመልካች ተከሳሽን እና ጣልቃገብን በመወከል መከራከር አትችልም በማለት ግንቦት 23 ቀን 2004 ዓ.ም በተሰጠው ብይን ላይ ይግባኝ መጠየቅ አልነበረብህም፤ክርክሩንም ማሳገድ አልነበረብህም በማለት ቅጣት የጣለብኝ ቢሆንም ለቅጣቱ መነሻ ያደረገው ምክንያት በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 37 ላይ የተደነገገውን ፍትሕ የማግኘት መብት የሚቃረን ነው፤በጉባኤው እና በበታች ፍ/ቤቶች ያቀረብኩት የይርጋ መቃወሚያ መታለፈም ተገቢ አይደለም፤ጉዲዩ መታየት የነበረበት ቅጣቱን በሚያከብደው አዋጅ ቁጥር 182/2005 ሳይሆን በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 22 መሰረት በአዋጅ ቁጥር 86/96 መሆን ነበረበት፤2ኛ ተጠሪ ለ3ኛ ወገን ጥቅም የሥነ ምግባር ክስ ማቅረብ ይችላል መባለ የሰዎችን የመዋዋል ነጻነት የሚነካ ነው፤በሥነምግባር ጉባኤውም ሆነ በየደረጃው ባለ ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል የሚል ነወ።የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች ጉዲት አድርሷል ተብል በወንጀል የተከሰሰውን ግለሰብ በጥብቅና ወክል ተከራክሮ በነጻ እንዱሰናበት ካስወሰነ በኋላ በተሽከርካሪው ባለቤት ላይ የጉዲት ካሣን ማስከፈል በቀረበው ክስ ተከሳሽን እና የመድን ድርጅቱን በመወከል መከራከሩ የጥቅም ግጭት ያስነሳል በማለት መወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ በዘህ ችልት እንዱታይ ተደርጓል።ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎ 2ኛ ተጠሪ መጥሪያ ደሷቸው ባለመቅረባቸው መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፎል።አመልካች እና 1ኛ ተጠሪ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው።ይህ ችልትም እንዱጣራ የተያዖውን ነጥብ ብቻ ለጉዲዩ መነሻ ምክንያት ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዖብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሑደት መገንዖብ የተቻለው በአመልካች ላይ ጉዲት ሉደረስ የቻለው አመልካች ሲጓዘበት የነበረው መኪና እና የወ/ሮ ዖይነባ መሐመድ መኪና በመጋጨታቸው ምክንያት መሆኑን፤አመልካች የጉዲት ካሣ እንዱከፈላቸው ክስ የመሰረቱት ሲጓዘበት በነበረው መኪና ባለቤት ላይ መሆኑን፤የኢትዬጲያ መድን ድርጅት 1ኛ ጣልቃገብ መሆኑን፤ወ/ሮ ዖይነባ መሐመድ 2ኛ ጣልቃገብ መሆናቸውን እና አመልካች የወ/ሮ ዖይነባ መሐመድ መኪናአሽከርካሪ ነው በማለት በወንጀል ተከሶ ለነበረው ግለሰብ፤ለተከሳሽ እና ለ1ኛ ጣልቃገብ ጠበቃ በመሆን መከራከራቸውን ነው።የሥነምግባር ጉባኤው አመልካች የጥብቅና ሙያ ሥነምግባር ጥሰት ፈጽመዋል በማለት የቅጣት ውሳኔ ሉያስተላልፍ የቻለው አመልካች ጉዲት አድርሷል የተባለውን ተሽከርካሪ ሲያሽከረክር በነበረው ግለሰብ ላይ የቀረበውን የወንጀል ክስ ለግለሰቡ ጠበቃ ሆነው በመከራከር በነጻ እንዱሰናበት አድርገዋል፤ተጠሪ ለደረሰባቸው ጉዲት ካሣ እንዱከፈላቸው ተሳፍረው ሲጓዘበት በነበረው ተሽከርካሪ ባለቤት ላይ ባቀረቡት ክስ አመልካች ተከሳሽዋን በመወከል ተከራክረዋል፤በክርክሩ ጣልቃገብ ሆኖ ለሚከራከረው መድን ድርጅትንም በመወከል ተከራክረዋል፤ተጠሪ ጠበቃው ለተከሳሽ እና ለጣልቃገብ በጥብቅና በመወከል መከራከር አይችለም በማለት ባቀረቡት ተቃውሞ ጉዲዩን ሲመራ የነበረው ፍ/ቤት የጥቅም ግጭት ሉፈጠር ስለሚችል አመልካች ተከሳሽን እና ጣልቃገብን በመወከል መከራከር አይችለም ተከሳሽ ራሳቸው ወይም ላላ ጠበቃ በመወከል ይከራከሩ በማለት ብይን ሰጥቷል፤አመልካች በዘህ ብይን ላይ እስከ ፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ተከራክረውበት ብይኑ ጸንቷል፤አመልካች ክርክሩን በማሳገድ እና በየደረጃው ባለ ፍ/ቤቶች በተሰጠው ብይን ላይ ይግባኝ በማቅረብ 2ኛ ተጠሪን ላልተገባ ወጪ ዲርገውታል ከፍተኛ መጉላላትም አድርሰውበታል በሚል ነው።ጉባኤው ውሳኔ ለመስጠት በዋነኝነት የሰጠው ምክንያት አመልካች የጥቅም ግጭት በሚፈጥር ሁኔታ ጉዲዩን በአግባቡ የሚያውቁ ሆኖ ሳላ በጉዲዩ በወንጀል ተከሳሽ ለነበረ እና የፍ/ብሓር ክስ ለቀረበባቸው ተከራካሪ ወገኖች ጥብቅና በመቆም ተከራክረዋል።ይህም የጥቅም ግጭት የሚፈጥር መሆኑ ተረጋግጦባቸው እስከ ፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ ተወስኖባቸዋል የሚል ምክንያት ነው።ጉባኤው አመልካች ለተከሳሽ እና ለጣልቃገብ መከራከር አትችልም በማለት በሰጠው ብይን ላይ በየደረጃው ባለ ፍ/ቤቶች ይግባኝ በመጠየቅ እና ክርክሩን በማሳገድ ጉዲዩ በጊዚ እንዲይወሰን በማድረግ 2ኛ ተጠሪን ለአላስፈላጊ ወጪ ዲርገዋል በማለት የሰጠው ምክንያት በአመልካች ላይ ለተጣለው የዱስፕሉን ቅጣት ብቸኛ ምክንያት ሳይሆን ተጨማሪ ምክንያት በመሆኑ አመልካች ጉባኤው ለውሳኔው መሰረት ያደረገው ምክንያት ለተጣለባቸው የዱስፕሉን ቅጣት ብቸኛ ምክንያት እንደሆነ በመውሰድ በጉባኤው የተሰጠው የዉሳኔ ምክንያት የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 37 ላይ የተሰጠውን ፍትሕ የማግኘት መብት የሚጻረር ነው በማለት ያቀረቡት አቤቱታ ተገቢ አይደለም።
አመልካች በ2ኛ ተጠሪ የጉዲት ካሣን በተመለከተ የፍ/ብሓር ክስ በቀረበባቸው ተከሳሽ እና ጣልቃገብን በመወከል መከራከር አይችለም፤ተከሳሽ ራሳቸው ወይም ላላ ጠበቃ በመወከል ይከራከሩ ተብል በተሰጠው ብይን ላይ ባቀረቡት ቅሬታ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የመድን ውለን መነሻ በማድረግ በስር ተከሳሿ ላይ ጭምር ክርክር ሉያቀርብ የሚችልበት አጋጣሚ ሉኖር ስለሚችል የስር ተከሳሿ እና የኢትዮጵያ መድን ኢንሹራንስ ጥቅም ሉጻረር የሚችልበት አጋጣሚም ሉኖር የሚችል መሆኑን፤በ2ኛ ተጠሪ ላይ ለደረሰው አደጋ ምክንያት የሆኑት 2ኛ ተጠሪ ሲጓዘበት የነበረው መኪና ባለቤት እና ከዘህ መኪና ጋር የተጋጨው መኪና ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ዖይነባ መሐመድ ጉዲቱ በልላው መኪና አሽከርካሪ ጥፊት ምክንያት የደረሰ ስለሆነ ኃላፉነቱ እኔን አይመለከተኝም በሚል አንደ የላላውን ጥቅም በሚፃረር መልኩ አንዲቸው በልላኛው ላይ ክርክር ሉያቀርቡ የሚችለበት አጋጣሚም ያለ መሆኑን፤አመልካች ወ/ሮ ዖይነባ መሐመድን መኪና አሽከርካሪ ነው ተብል ተከሶ የነበረውን ግለሰብ ወክል በወንጀል ሲከራከር በነበረበት ጊዚ በወ/ሮ ዖይነባ መሐመድ በኩል ሉነሱ የሚችለትን ክርክሮች እና እንዱሁም ከሙያው ጋር ተያይዜ ሉያገኛቸው የሚችለትን ላልች መረጃዎችንም አጋጣሚውን በመጠቀም ማወቁ ወይም ማግኘቱ የማይቀር መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ከወ/ሮ ዖይነባ መሐመድ ጋር ተፃራሪ ጥቅም ሉኖራቸው ከሚችለት 2ኛ ተጠሪ ተሳፍረው ሲጓዘበት የነበረው መኪና ባለቤት እና ለመኪናዋ የመድን ሽፊን የሰጠውን መድን ድርጅት ወክል መከራከሩ እና በተከሳሽዋ እና በመድን ድርጅቱ መካከል የጥቅም ግጭት ሉኖር የሚችልበት አጋጣሚ እያለ ሁለቱን ወክል መከራከሩን የሙያውን ስነ-ምግባር መርሆዎችን የሚጥስ ከመሆኑም ባሻገር የጠበቆች ስነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 57/92 አንቀጽ 10፣11፣12 እና 13 ድንጋጌዎች ይዖት ፣አላማ እና መንፈስ ጋርም የተጣጣመ አይደለም በማለት አመልካች ተከሳሽን እና ጣልቃገብን ወክል መከራከር አይችልም በማለት የተሰጠውን ብይን አጽንቶታል።
የሥነምግባር ጉባኤው ከላይ የተገለጸውን የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ መሰረት በማድረግ አመልካች የጥቅም ግጭት ሉፈጠር በሚችልበት ሁኔታ የተለያዩ ተከራካሪዎችን በመወከል መከራከራቸው በፍ/ቤት ውሳኔ የተረጋገጠባቸው መሆኑን፤ይህ ድርጊታቸውም በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት የጠበቆች እና ሕግ ጉዲይ ጸሐፉዎች እና የፈቃድ አሰጣጥ አዋጅ ቁጥር 182/2005 አንቀጽ 36/3/15 ድንጋጌን የሚጥስ እና ከባድ የሥነምግባር ጥሰት መሆኑን በማረጋገጥ ውሳኔ የሰጠ በመሆኑ የጉባኤው ውሳኔ አመልካች ባቀረቡት ቅሬታ ላይ ይህ ችልት የሰጠውን ውሳኔ መሰረት ያደረገ እና የአመልካች ድርጊትም የጥብቅና ሙያ አገልግልት የሥነምግባር ደንብ የሚጥስ በመሆኑ ጉባኤው በሰጠው ውሳኔም ሆነ በየደረጃው ባለ ፍ/ቤቶች በሰጡት ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሕግ ሥሕተት አላገኘንበትም።በዘህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠበቆች የሥነምግባር ጉዲይ ጉባኤ በ16/06/07 ዓ.ም ተሰጥቶ በኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ሚያዘያ 01 ቀን 2007 ዓ.ም በውሳኔ፤በኦሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰበር ሰሚ ችልት በመ. ሚያዘያ 13 ቀን 2007 ዓ.ም በትዔዙዛ የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ጸንቷል።
በዘህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዛገቡ ተዖግቷል።ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።