ፍርድ ቤቶች የሥም ይቀየርልኝ ጥያቄ በሚቀርብላቸው ጊዚ የአመልካችን ስም መለወጥ አስፈላጊ የሚያደርጉ ሁኔታዎች መኖር አለመኖራቸውን በማስረጃ አጣርተውና የሶስተኛ ወገን ጥቅም የማይጎዲ ለመሆኑ ጭምር ካረጋገጠ በኋላ ወ/ሪት ሐናን እስማኤል አብደልዋሂድ እና የለም XXXIV መወሰን ያለባቸው ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41/1/ /1/
No summary available.
ሕዲር 06 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሳሁን እትመት አሰፊ አመልካች፡- ወ/ሪት ሐናን እስማኤል አብደልዋሂድ ጠበቃ ወርቁ መንገሻ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የለም መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለጉዲዩ መቅረብ ምክንያት የሆነው አዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዛገብ መስከረም 14 ቀን 2008 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ዲኝነት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ስለሆነ በፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ታይቶ ሉታረምልኝ ይገባል በማለት አመልካች በጠበቃቸው አማካኝነት ህዲር 13 ቀን 2008 ዓ.ም የተፃፈ 04 ገጽ የሰበር አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
የአመልካች የሥር አቤቱታ ይዖት በአጭሩ፡-ታህሳስ 10 ቀን 1987 ዓ.ም ከአባታቸው ከአቶ እስማኤል አብደልዋህድና ከእናታቸው ከወ/ሮ ሳባ አልታሰብ አርባ ምንጭ ከተማ ውስጥ ተወልደው ስማቸው ሐናን እስማኤል አብደልዋሂድ በሚል ተፅፍ የምስክር ወረቀት ማግኘታቸውን፤ በኋላም የእናታቸው ወንድም ሚስት የሆኑት ወ/ሮ መአዙ አዲነ አሻሜ ሮሆቦት አካዲሚ በተባለው ት/ቤት ሲያስመዖግቡ ሀና አዲነ አሻሜ በሚል ስም ያስመዖገቧቸውና በሂደትም በዘህ ስም የልደት የምስክር ወረቀት የወጣላቸው መሆኑን፤ ከዘያም ወደ ወላጆቻቸው አካባቢ በመመለስ አስቀድሞ በወጣላቸው ሐናን እስማኤል አብደልዋሂድ በተባለው ስማቸው እየተጠሩ የቀበላ አስተዲደር መታወቂያ ወጥቶላቸውና አዱስ አበባ ዩኒቨርሲቲም ተመዛግበው እየተማሩ እንደሚገኙ ገልፀው የስማቸው መጠሪያ በተለያየ አጋጣሚ በተለያየ ስም የተመዖገበ በመሆኑ ችግር ያስከተለባቸው መሆኑን በመጥቀስ ሐናን እስማኤል አብደልዋሂድ ተብለው እንዱጠሩ እንዱወሰንላቸው አቤቱታ አቅርበው ነበር።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች በትክክለኛው ወላጅ አባታቸው በአቶ እስማኤል አብደልዋሂድ ስም ልጠራ ያለ በመሆናቸው ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት ልጅነትን አረጋግጠው ይቅረቡ በማለት መዛገቡን ዖግቶታል። አመልካች በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የይግባኝ ቅሬታ በኋላም የሰበር አቤቱታ አቅርበው የነበሩ ቢሆንም ተቀባይነት አላገኙም።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ የቀረበው የሥር ፍርድ ቤቶች ዲኝነት መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል በሚል ሲሆን አቤቱታቸው በአጭሩ፡ የአመልካች አቤቱታ የማንንም ጥቅምና መብት የማይነካ፤ በአሳማኝ ማስረጃም ተደግፍ የቀረበ ሆኖ እያለ የሥር ፍርድ ቤቶች ከውልደቴ ጀምሮ በወጣልኝ ስም ለመጠራት ያቀረብኩትን አቤቱታ ውድቅ ያደረጉት ያላግባብ በመሆኑ ሉታረምልኝ ይገባል በሚል ያቀረቡት ነው።
ሰበር አጣሪው ችልቱም መዛገቡን መርምሮ የሥር ፍርድ ቤቶችን ዲኝነት ተገቢነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ሰሚ ችልት እንዱቀርብ በመወሰኑ በጉዲዩ ላይ ተጠሪ የሆነ ተከራካሪ ባለመኖሩ መዛገቡ ለምርመራ የቀረበ ነው።
ክርክሩ በዘህ ዓይነት ሁኔታ ተጠናቋል። እኛም አቤቱታው ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ አንጻር ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል። መዛገቡን እንደመረመረነው ምላሽ ማግኘት ያለበት ነጥብ አመልካች በወላጅ አባታቸው እስማኤል አብደልዋሂድ ስም መጠሪያቸው እንዱሆን የአቀረቡትን አቤቱታ የሥር ፍርድ ቤቶች ውድቅ ያደረጉበት አግባብ ተገቢ ነውን? የሚለው ጭብጥ ሆኖ አግኝተነዋል።
በፍትሐብሕር ህግ አንቀጽ 32(1) ሥር በመርህ ደረጃ እንደተመለከተው አንድ ሰው የቤተዖመድ ስም፤ አንድ ወይም ከዘያ በላይ የግል ስሞች እና የአባት ስም እንደሚኖረው ተደንግጓል። ለልጁ አባት ስም የሚሆነውም የአባቱ የግል ስም ለመሆኑ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 36 ሥር ተመልክቷል። ስለ ልጅ መወለድ መግለጫ ላሰጥ የሚገባው ሰው ልጁ ከተወለደበት ቀን አንስቶ በዖጠና ቀናት ውስጥ ለልጁ የተሰጠውን የግል ስም ልጁ በተወለደበት ቀበላ ለሚገኘው የክብር የመዛገብ ጽ/ቤት መግለጫ የማቅረብ ግዳታ የተጣለበት ለመሆኑም ከፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 37 መገንዖብ የሚቻል ነው። በዘህ ረገድ አመልካች ተወልድኩ በሚለበት በ1987 ዓ.ም በአገራችን ልደት ጋብቻና ሞት የሚመዖገብ የክብር መዛገብ ሹም በህግ አግባብ ተቋቁሞ በተደራጀ መልኩ ሥራ ላይ ያልነበረ በመሆኑ የአንድ ሰው ስምን በተመለከተ ተደራጅቶ የተጻፈ ማስረጃ ማግኘት አስቸጋሪ ይሆናል። በመሆኑም አመልካች በተወለደበት ወቅት ልደትን፤ሞትንና ጋብቻን ባግባቡ መዛግቦ ለመያዛ የሚችል የተደራጀ አካል ባለመኖሩ በወላጆች የወጣላቸው ስም በአጎታቸው ሚስት አማካኝነት ተለውጦ በተለያዩ ጊዘያት በተለያዩ ስሞች መጠራታቸውንና የአባታቸውም ስም በተወለደበት ጊዚ በሆስፒታለ የምስክር ወረቀት የሰፈረውና በአሁኑ ጊዚ በቀበላ መታወቂያቸውና በአዱስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመዛግበው የሚገኘው ለመሆኑ በፍርድ ቤት እንዱነገርላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሥር መዛገቡ ያስረዲል።
አመልካች አሳዲጊያቸው የነበሩት የአጎታቸው ሚስት ባስመዖገቧቸው ሀና አዲነ አሻሜ በሚል ስም ሮሆቦት አካዲሚ ተመዛግበው መማራቸው፤ከአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደርም የልደት ምስክር ወረቀት ማውጣታቸውን ገልፀዋል። በልላ በኩል ደግሞ ወደ ተወለደበት አካባቢ ተመልሰው ሐናን እስማኤል አብደልዋሂድ በሚል ስም የቀበላ መታወቂያ በማውጣት እስከ አዱስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመዛግበው እየተማሩ እንደሚገኙና ይህ ስማቸው አስቀድሞ በተወለደበት ጊዚ የወጣላቸውና በሆስፒታለ ምስክር ወረቀት የተመዖገበ ለመሆኑ እየተከራከሩ ይገኛለ።
አንድ ሰው የቤተዖመድ ስም እንዱለወጥ የመጠየቅ መብት ያለው መሆኑን በዘህ ረገድ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ፍርድ ቤቶች በሶስተኛ ወገኖች ላይ ጉዲት እንዲይደርስ በጥንቃቄ በመመርመር ስሙን ለመለወጥ በቂ ምክንያት ሲኖር መለወጥ እንደሚችለ በፍትሐብሕር ህጉ አንቀጽ 42 ሥር የተደነገገ ሲሆን በዘሁ ህግ አንቀጽ 43 ሥር ደግሞ አንድ ሰው የግል ስሙ እንዱለወጥ ወይም ከብዘዎች የግል ስሞች አንደ እንዱሰረዛ፤ ወይም ላላ ግል ስም እንዱጨመርለት ባለጥቅሙ ጥያቄ ባቀረበ ጊዚ ሉፈቀድለት እንደሚችል ተደንግጓል። በዘህ ረገድ የሚቀረቡ ጥቄዎችን ፍርድ ቤቶች የአመልካቾችን ስም በማስተካከል ሉወስኑ እንደሚገባቸው የፋዳራል ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መዛገብ ላይ አስገዲጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍርድ ቤቶች የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ ያደረጉበት ምክንያት ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት ልጅነት ሳይረጋገጥ የአባትን ስም መለወጥ አይገባንም በሚል መነሻ ለመሆኑ ከመዛገቡ ተረድተናል። አመልካች የጠየቁት ዲኝነት ስሜ ሐናን እስማኤል አብደልዋሂድ ለመሆኑ የሚያመለክቱ ማስረጃዎች ያሎቸው መሆኑን በመግለፅ በተወለደበት ጊዚ በዘህ ስም ተጠርተው እንደነበርና በሂደት የአጎታቸው ሚስት በአሳዲጊነት ዖመናቸው ስማቸውን የለወጡባቸው መሆኑንና በኋላም ሲወለደ ወደ ወጣላቸው ስም ተለውጦ እየተጠሩበት እንደሚገኝ ይህንን የሚያስረደ ማስረጃዎች መኖራቸውን በማጣቀስ እየተከራከሩ ይገኛለ። ስለሆነም ዋናውና መጣራት ያለበት ነጥብ አመልካች በፍሬ ጉዲይነት የሚያነሱት በየጊዚው በተለያዩ ስሞች የመጠራት ወይም ያለመጠራት ጉዲይ ላሆን ይገባል እንጂ የአመልካች ወላጅ አባት ማን ነው የሚል ጭብጥ ላሆን አይችልም። ክርክሩ ያስነሳውን ጭብጥ ፍርድ ቤቶች ምላሽ በሚሰጡበት ጊዚ የሶስተኛ ወገኖችን ጥቅም እንዲይጎዲ ተገቢ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የላላን ሰው ስም ያላግባብ የሚጠቀም ወገን ካለም ህጉ ኃላፉነትን የሚያስከትል ለመሆኑ የደነገገው በመሆኑ ስም ይለወጥለኝ በሚል ጥያቄ የሚያቀርብም ወገን ጥንቃቄ ማድረግ የሚገባው ነው። በመሆኑም የአዱስ አበባ ከተማ ፍርድ ቤቶች ጉዲይን ከቀረበው የዲኝነት ጥያቄ አንፃር በመመልከትና በአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41(1)(ሰ) መሰረት በመቀበል የአመልካችን ስም መለወጥ አስፈላጊ የሚያደርጉ ሁኔታዎች መኖር አለመኖራቸውን በማስረጃ አጣርተውና የሶስተኛ ወገን ጥቅም የማይጎዲ ለመሆኑ ጭምር ካረጋገጡ በኋላ ተገቢውን መወሰን ሲገባቸው ጉዲዩን ከልጅነት ይረጋገጥልኝ ጥያቄ አንፃር በመመልከት ውድቅ ማድረጋቸው አግባብነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም። ስለሆነም የሚከተለውን ወስነናል።
የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዛገብ ቁጥር 4332/07 ሐምል 01 ቀን 2007 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ትዔዙዛ፤የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዛገብ ነሐሴ 11 ቀን 2007 ዓ.ም የሰጠው ትዔዙዛ እንዱሁም የአዱስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችልት በመዛገብ መስከረም 14 ቀን 2008 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሯል።
የአመልካች ጥያቄ የሥም ለውጥ ስለሆነ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 361/1995 አንቀጽ 41(1)(ሰ) መሰረት ስልጣን አለው ብለናል። ጉዲዩን የማየት ሥልጣን አለው ብለናል።
በመሆኑም የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ስማቸው እንዱለወጥላቸው ያቀረቡትን አቤቱታና ማስረጃ አስቀርቦ በመመርመር የአመልካች ስም መለወጥ በሶስተኛ ወገኖች መብት የሚያስከትለው ጉዲት መኖር አለመኖሩን ጭምር ካጣራ በኋላ ተገቢውን እንዱወስን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 341(1) መሰረት መልሰናል።
ይፃፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
የማይነብብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.