በንግድ ምልከት መመሳሰል በአንድ ምርት ወይም አገልግልት ጋር በተገናኘ ሁኔታ የሕዛብ ግንዙቤ ያዙባ ወይም ሉያዙባ የሚችል፤ በሁለት ድርጅቶች መካከል መሳከርን የሚፈጥር ከሆነ ሕብረተሰቡ ሉያገኝ የሚገባው ሕጋዊ ጥበቃና ዋስትና በተሟላ ሁኔታ ተፈፃሚ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ በተመሳሳይ የንግድ ምልክት ላይ ምዛገባ እንዱደረግ የሚቀርብ ጥያቄ ተቀባይነት የላለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 501/1998 አንቀፅ 7 አዋጅ ቁጥር 320/1995
No summary available.
ሕዲር 16 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ቀነዓ ቂጣታ ሰናይት አድነው ጳውልስ አርሺሶ አመልካች፡- ደራታ ባትሪ ካምፓኒ የቀረበ የለም ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ አዔምሯዊ ንብረት ፅ/ቤት የቀረበ የለም መዛገቡ መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ከንግድ ምልክት ምዛገባ ጋር የተያያዖ ክርክር ሲሆን የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ለተጠሪ ፅ/ቤት ያቀረበው የምዛገባ ጥያቄ መሰረት በማድረግ ነው። የአመልካች የንግድ ምልክት ይመዛገብልኝ ጥያቄ በተጠሪ ፅ/ቤት ውድቅ ከተደረገ በኋላ ይግባኝ ቅሬታውን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ ያቀረበውም በተጠሪ ፅ/ቤት እና በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተፈፀመ የተባለውን የሕግ ስህተት አጣርቶ ለመወሰን ነው።
ከስር የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ አመልካች ለተጠሪ ፅ/ቤት ሚያዛያ 21 ቀን 2005 ዓ.ም ባቀረበው ማመልከቻ ‛DURA SUN“ የሚል የንግድ ምልክት እንዱመዖገብለት የጠየቀ ሲሆን የአመልካች ጥያቄ ያስተናገደው በተጠሪ ፅ/ቤት ስር የተደራጀው ኢንደስትራዊ ንድፍ ጥበቃና ልማት ዋና የስራ ሂደት አመልካች እንዱመዖገብለት ያቀረበው ‛DURA SUN“ የንግድ ምልክት በፅ/ቤቱ ‛DURA CELL“ በሚል መጥሪያ ሰርተፍኬት ቁጥር 1987 ከተመዖገበ የንግድ ምልክት ጋር በአዋጅ ቁጥር 501/1998 አንቀፅ 7/1/ መሰረት ተመሳሳይ በመሆኑ የንግድ ምልክት ምዛገባ ጥያቄው ውድቅ ተደርጓአል።
አመልካች በስራ ሂደቱ ውሳኔ ቅር በመሰኘት በፅ/ቤቱ ለተቋቋመው ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ አቤቱታው አቅርበዋል። አመልካች ባቀረበው አቤቱታ ምንም እንኳ ሁለቱ የንግድ ምልክቶች ‛ደራ“ በሚለው ቃል አንድ አይነት ቢሆኑም ‛DURA SUN“ የሚለው የንግድ ምልክት በአነጋገር፣ በትርጉም እና በአቋሙ ጠቅላላ ሲታይ ‛DURA CELL“ ከሚለው የንግድ ምልክትና ምርቶቹን በተመለከተ ጥሩ ስምና እምነት ያገኘበት በመሆኑ የንግድ ምልክቱ እንዱመዖገብለት ጠይቋል። ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው አጠቃላይ የክርክሩን ይዖት ካሰፈረ በኋላ ‛DURA CELL“ ልጎ ያለበት የንግድ ምልክት እ.ኤ.አ በ1996 ዓ.ም በፅ/ቤቱ የተቀማጭነት የምስክር ወረቀት በማግኘት በንግድ ምልክቱ ላይ የቀዲሚነት መብት /priority Right/ ያገኘ መሆኑን፣ የንግድ ምልክት ጥበቃ የሚደረግበት ዋነኛ ምክንያት ዔቃ በማምረት፣ በማከፊፈል ወይም አገልግልት በመስጠት የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መልካም ስምና ዛና ለመጠበቅ እንዱሁም በተመሳሳይ ዔቃዎችና አገልግልቶች መካከል መሳከርን ለማሶገድ ስለመሆኑ፣ በፅ/ቤቱ በቀዲሚነት ከተመዖገቡ የንግድ ምልክቶች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው እና መሳከርን የሚያስከትለ ዔቃዎች ወይም አገልግልቶች ሉመዖገቡ እንደማይገባ፤ ሁለቱም የንግድ ምልክቶች በዔይታ፣ በንባብ፣ በድምጸት ተመሳሳይነት ያላቸውና በህብረተሰቡ ዖንድ መሳከርን ሉፈጥሩ የሚችለ መሆናቸውን ኮሚቴ መገንዖቡን፣ በተመሳሳይ ሁለቱ የንግድ ምልክቶችን ለባትሪ ምርት የሚያገለግለ በመሆኑና ይህንንም ምርት የሚጠቀሙ ሸማቾች ወይም አግባብነት ያላቸው የሕ/ሰቡ ክፍልች በአንፃራዊነት ከላልች ምርቶች አኳያ ሲታይ ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው እና የትምህርት ደረጃቸው ዛቅተኛ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍልች የሚጠቀሟቸው ምርቶች በመሆናቸው ሁለቱም የንግድ ምልክቶች በአግባቡ ለይተው ይገዙለ ብል መናገር አስቸጋሪ ይሆናል። በመሆኑም አመልካች ‛DURA SUN“ በሚል መጥሪያ እንዱመዖገብለት የጠየቀው የንግድ ምልክት ጋር ከዘህ በፉት በፅ/ቤቱ ከተመዖገበው ‛DURA CELL“ ልጎ የንግድ ምልክት ጋር ተመሳሳይና በሕብረተሰቡ ዖንድ መሳከርን ሉያስከትል የሚችል በመሆኑ የንግድ ምልክትና ኢንደስትሪያል ንድፍ ጥበቃና ልማት ዋና የስራ ሂደት የሰጠው ውሳኔ ኮሚቴው ተቀብል አፅንቶታል በማለት ወስኗል።
የፅ/ቤቱ የበላይ ኃላፉም በይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የተሰጠው ውሳኔ በማፅደቅ ለአመልካች አሳውቀዋል። አመልካች በፅ/ቤቱ የተሰጠውን ውሳኔ በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበው ይግባኝ አቤቱታ ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ ያቀረበውም በተጠሪ ፅ/ቤት እና ፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔና ትዔዙዛ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች ሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዖትም ሁለቱም የንግድ ምልክቶች በዓለም ገበያ ተወዲዲሪ እንደሆኑ፣ የመጀመሪያ ሶስት ፉደልች ተመሳሳይ በመሆናቸው ብቻ የንግድ ምልክቶቹ መሳከር ይፈጥራለ ተብል መወሰኑ በአዋጅ ከተቀመጠው ትርጉም ውጭ ስለመሆኑ፣ በንባብ፣ በአተረጓጎምና ድምጸት አንድ ናቸው የተባለውም በአግባቡ አለመሆኑን፣ ፅ/ቤቱ አንድ የህብረተሰብ ክፍል ብቻ መሰረት በማድረግ ምዛገባ መከልከለ የአመልካች መብት በእጅጉ የጣሰ በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው። የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ የአሁኑ አመልካች ለተጠሪ ባቀረበው የይግባኝ አቤቱታ ላይ እንደገለፀው ‛ደራታ“ የሚለውን ምልክት አስቀድሞ ያስመዖገበውና በብዘ ሀገሮች አስመዛግቦ እየተገለገለ የሚገኝበት ከሆነ ‛DURA SUN“ የሚለው ‛DURA CELL“ ከሚለው የንግድ ምልክት ጋር የተመሳሰለ ነው ወይስ አይደለም? ለማለት ‛DURA“ የሚለውን ቃል ለምን ተጠቀመ የሚለውን ምክንያት ለፍርድ ሐተታው እና መነሻ ማድረጉና በዘህም የተነሳ ያሳክራል ከሚል መደምደማያ የደረሰበትን አግባብነት ተጠሪን ባለበት ይጣራ ዖንድ ያስቀርባል ተብሎል። ተጠሪም ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ የበኩለን መልስ የሰጠ ሲሆን ዋናው ፍሬ ጉዲይ የአመልካች የንግድ ምልክት ይመዛገብልኝ ጥያቄ ውድቅ የተደረገው በፅ/ቤቱ ቀደም ከተመዖገበው የንግድ ምልክት ተመሳሳይነት ያለውና መሳከርን የሚፈጥር መሆኑን ተረጋግጦ በመሆኑ የአመልካች የሰበር አቤቱታ ውድቅ እንዱደረግ አመልክቷል። የመልስ መልስም ቀርበዋል።
ጉዲዩ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ግራ ቀኙ በፅሁፍ ያደረጉት ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ ተጠሪ እና የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሰጡት ውሳኔና ትዔዙዛ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈፀም አለመፈፀሙን እንደሚከተለው መርምሮታል።
እንደመረመርነውም፡- አመልካች እንዱመዖገብለት ያቀረበው የንግድ ምልክት /trade mark/ ‛DURA SUN“ የሚል ነው። ተጠሪ የአመልካች ጥያቄ ውድቅ ያደረገው በፅ/ቤቱ አስቀድሞ የተመዖገበ ‛DURA CELL“ የሚል የንግድ ምልክት እንዲለና አሁን ለምዛገባ የቀረበው ‛DURASUN“ በዔይታ፣ በንባብ እና በድምጸት ተመሳሳይነት ያለው በመሆኑ በህብረተሰቡ ዖንድ መሳከርን ይፈጥራል በሚል መነሻ ነው። የኢትዮጵያ አዔምሯዊ ንብረት ፅ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 320/1995 አንቀፅ 6 ከተሰጡት ስልጣንና ተግባራት አንደ የንግድ ምልክት መመዛገብ ስለመሆኑ መገንዖብ ተችሎል። የንግድ ምልክት ምዛገባና ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 501/1998 የሰጠበት መሰረታዊ ዓላማ ‛ዔቃ በማምረት እና በማከፊፈል ወይም አግለግልት በመስጠት የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን መልካም ስም እና ዛና ለመጠበቅ እንዱሁም በተመሳሳይ ዔቃዎችና አገልግልቶች መካከል መሳከርን ለማሰወገድ የንግድ ምልክት ጥበቃ ማድረግ በማስፈለጉ“ እንደሆነ በአዋጅ መግቢያ በግልፅ ተመልክቷል። በዘህ አዋጅ መሰረት ከቀዲሚ የንግድ ምልክት ጋር አንድ ዓይነት የሆነ ወይም መሳከርን ሉያስከትል የሚችል ተመሳሳይነት ያለው የንግድ ምልክት መመዛገብ እንደማይቻል በአንቀፅ 7 ንዐስ አንቀፅ 1 ተደንግጓአል። በተያዖው ጉዲይ በተጠሪ ፅ/ቤት እ.ኤ.አ በ1996 ዓ.ም ተመዛግቦ የተቀማጭነት የምስክር ወረቀት ያገኘ፣ ‛DURA CELL“ ተ ልጎ ያለበት የንግድ ምልክት መኖሩን ያከራከረ ጉዲይ አይደለም። አመልካች እንዱመዖገብለት ያቀረበው የንግድ ምልክት ‛DURA SUN“ የሚል መሆኑን አልተካደም። እነዘህ ሁለት ምልክቶች የጋራ የሆነ ‛ደራ“ የሚል መነሻ ቃል ያላቸው ከመሆኑ በተጨማሪ በዔይታ፣ በንባብ፣ በድምጸት ተመሳሳይነት ያላቸው ስለመሆኑ የተጠሪ ፅ/ቤት ባደረገው ማጣራት አረጋግጧል። ምዛገባ የተጠየቀበት የንግድ ምልክት አስቀድሞ ከተመዖገበው የንግድ ምልክት በአብዙኛው የሕብረተሰብ ክፍል ወይም ተገልጋዮችና ሸማቾች መሳከርን የሚፈጥር መሆኑን ግንዙቤ ከተወሰደበት ሉመዖገብ እንደማይገባ ከአዋጅ ቁጥር 501/1998 አንቀፅ 7 ድንጋጌ መሰረታዊ ይዖት የምንገነዖበው ነው። አመልካች እንዱመዖገብለት ያቀረበው የንግድ ምልክት ‛DURA SUN“ አስቀድሞ ከተመዖገበው ‛DURA CELL“ ባትሪ ተመሳሳይነት ያለው በመሆኑ በአብዙኛው የህብረተሰብ ክፍል መሳከርን የሚፈጥር ነው። እንዱህ ከሆነ ደግሞ አመልካች ያቀረበው የምዛገባ ጥያቄ በተጠሪ ውድቅ መደረጉ ከላይ የተመለከተውን አዋጅ ዓላማና ግብ በአግባቡ ተፈፃሚ አድርጎአል ከሚባል በስተቀር በጉዲዩ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈፀሙን አያሳይም። ከዘህ ጋር በተያያዖ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ የካቲት 22 ቀን 2003 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ በንግድ ምልከት መመሳሰል በአንድ ምርት ወይም አገልግልት ጋር በተገናኘ ሁኔታ የሕዛብ ግንዙቤ ያዙባ ወይም ሉያዙባ የሚችል፤ በሁለት ድርጅቶች መካከል መሳከርን የሚፈጥር ከሆነ ሕ/ሰቡ ሉያገኝ የሚገባው ሕጋዊ ጥበቃና ዋስትና በተሟላ ሁኔታ ተፈፃሚ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ በተመሳሳይ የንግድ ምልክት ላይ ምዛገባ እንዱደረግ የሚቀርበው ጥያቄ ተቀባይነት እንደላለው አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል። ይህ ችልትም የሰጠው ገዣ የሕግ ትርጉም ደግሞ በተመሳሳይ ጉዲይ ላይ በሁለም ደረጃ ባለ ፍርድ ቤቶች ተፈፃሚነት ያለው ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀፅ 2/1/ ስር ተደንግጓአል። በዘህ ሁለ ምክንያት የአመልካች የንግድ ምልክት ምዛገባ ጥያቄ በተጠሪ ውድቅ መደረጉ እና የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በአመልካች ያቀረበው ይግባኝ ቅሬታ መሰረዘ በአግባቡ ነው ብለናል።
በዘህም ተከታዩን ወስነናል።
የኢትዮጵያ አዔምሯዊ ንብረት ፅ/ቤት የሰጠው ውሳኔ፤ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኮ/መ/ በ3/10/2006 ዓ.ም የሰጠው ትዔዙዛ ፀንቷል።
በዘህ ፍርድ ቤት በተደረገው ክርክር ያስከተለው ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
መዛገቡ ዖግተን ወደ መዛገብ ቤት መልስናል።የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት።
No topics extracted.