No summary available.
ግንቦት 16 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው በዔውቀት በላይ እንዲሻው አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- አቶ ገ/ኢየሱስ ሃይለ አልቀረቡም ተጠሪ፡- ዲዊት ልዐል አልቀረቡም መዛገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ አፈጻጸምን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በትግራይ ብሓራዊ ክልላዊ መንግሥት በሽሬ እንዲስላሴ ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው።በሥር ፍ/ቤት በተደረገው ክርክር አመልካች የአፈጻጸም ከሳሽ ተጠሪ ደግሞ አፈጻጸም ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል።አመልካች ለአፈጻጸም ችልቱ ባቀረቡት አቤቱታ ተጠሪ በፍርድ ለአመልካች እንዱከፍለ የተወሰነባቸውን ገንዖብ ለማስከፈል ተጠሪ ከአመልካች የገዝት የሰላዲ ቁጥር ኮድ 03-46545 የሆነች መኪና በባለሙያ በተገመተው .05 / ሰባት መቶ ሰላሳ አንድ ሺህ አራት መቶ ሐያ ሥድሥት ብር ከዚሮ አምሥት ሣንቲም / በሐራጅ ተሸጣ የተጠሪ ዔዲ እንዱከፈል በማለት ለሁለት ተከታታይ ጊዚ ጨረታ የወጣ ቢሆንም መኪናዋ በጨረታ ያልተሸጠች መሆኑን፤የመኪናዋ ግምት ከፍ ያለ እና የማይመጥናት ስለሆነ ልትጫረት ያልቻለች መሆኑን፤ተጠሪ በመሰለው ዋጋ መኪናዋን ሸጦ እንዱሰጣቸው የጠየቁት ቢሆንም መኪናዋን ሸጦ ገንዖቡን ሉሰጣቸው ያልቻለ መሆኑን በመግለጽ በውሳኔው መሰረት በብር 430,000 / አራት መቶ ሰላሳ ሺህ / ሑሳብ የመኪናው ሥመሐብት ወደ ሥማቸው እንዱዙወርላቸው ወይም 3ኛ ጨረታ ከታዖዖ በጨረታው እንዱሳተፈ እንዱታዖዛላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተጠሪ በሰጡት መልስ መኪናዋ እስካሁን የምትታወቀው በአመልካች ሥም መሆኑን፤አመልካች መኪናዋን እንዲትሸጣት በማለት ማስጠንቀቂያ የሰጣቸው መሆኑን ፤መኪናዋ በመንገድ ትራንስፖርት ግምት የወጣላት በመሆኑ አመልካች መኪናውን ወስደው ቀሪ ገንዖቡን እንዱመልሱልኝ ይታዖዛልኝ በማለት ተከራክረዋል።ፍ/ቤቱም የግራቀኙን ክርክር መርምሮ መኪናዋ ለሁለት ጊዚ ጨረታ ወጥቶ ልትሸጥ አልቻለችም፤የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 428/2 ሁለተኛ ጨረታ ወጥቶ ተጫራች ካልቀረበ የፍርድ ባለመብት ንብረቱን እንዱረከብ ትዔዙዛ የሚሰጥ መሆኑ ይደነግጋል፤ለአመልካች ሉከፈል የሚገባው ጠቅላላ ገንዖብ ብር 446,098.57 / አራት መቶ አርባ ሥድሥት ሺህ ዖጠና ሥምንት ብር ከሐምሳ ሰባት ሣንቲም / በመሆኑ እና መኪናዋ የተገመተችው ብር 731,426.05 / ሰባት መቶ ሰላሳ አንድ ሺህ አራት መቶ ሐያ ሥድሥት ብር ከዚሮ አምሥት ሣንቲም / በመሆኑ አመልካች ልዩነቱን ብር 285,327.48 /ሁለት መቶ ሰማንያ አምሥት ሺህ ሦስት መቶ ሐያ ሰባት ብር ከአርባ ሥምንት ሣንቲም / ለተጠሪ ከከፈለ በኋላ መኪናዋን ይረከብ በማለት ትዔዙዛ ሰጥቷል።አመልካች በዘህ ትዔዙዛ ቅር በመሰኘት ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኝ ያቀረቡ ቢሆንም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት አቤቱታቸው ውድቅ ተደርጓል።የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዖትም፡-አንድ ንብረት ለፍርድ አፈጻጸም ተብል ለሐራጅ ሲቀርብ መነሻ ዋጋው ወቅታዊ የንብረቱ ዋጋ መሆን ይኖርበታል፤ወቅታዊ የገበያ ግምቱንም በትራንስፖርት ቢሮ በሚገኝ ባለሙያ ማስገመት ይገባል፤የሽሬ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይህን የባለሙያ ግምት ሳያገኝ መኪናው ወደ ሐገር ውስጥ ሲገባ ለግብር አከፊፈል ተብል በኢትዮጲያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን የተቀመጠውን ግምት በመነሻነት መውሰደ ተጫራች እንዲይቀርብ ከማድረጉም በተጨማሪ ከአፈጻጸም ሕግ ድንጋጌዎች ጋር የሚጻረር ነው፤ንብረቱ ለሁለተኛ ጨረታ ቀርቦ ገዠ ከታጣ የፍርድ ባለመብት ንብረቱን እንዱረከብ ተደርጎ ፍርደ በሙለ ወይም በከፉል እንደተፈጸመ ይቆጠራል እንጂ የፍርድ ባለመብት ገዠ ያጣውን ንብረት ከግምቱ በላይ ለፍርድ ባለዔዲው ገንዖብ በመመለስ የፍርድ ባለዔዲው ያለአግባብ እንዱበለጽግ የሚደረግበት የሕግ አግባብ የለም፤በመሆኑም የበታች ፍ/ቤቶች የሰጡት ትዔዙዛ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በዘህ ችልት መታየት ያለበት ሆኖ ስለተገኘ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎ ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከራከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው።እኛም የግራቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና ለጉዲዩ አግብበነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዖብ፡-
ወይስ አይደለም?
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ አመልካች ለሐራጅ የቀረበችው መኪና ዋጋ ወቅታዊ የገበያ ዋጋ አይደለም፤መኪናው ሐገር ውስጥ ሲገባ ለግብር አከፊፈል ተብል በኢትዮጲያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን የተቀመጠለትን ግምት በመነሻነት መወሰደ ተጫራች እንዲይቀርብ ከማድረጉም በተጨማሪ ከአፈጻጸም ሕግ ድንጋጌዎች ጋር የሚቃረን ነው በማለት የሚከራከሩ ቢሆንም የመኪናውን ግምት በተመለከተ መኪናው ጨረታ ከመውጣቱ በፉት የተቃወሙ ለመሆኑ የክርክሩ ሑደት አያሳይም።
በፍርድ አፈጻጸም ጉዲይ ማናቸውም ንብረት በሐራጅ እንዱሸጥ በሚወሰንበት ጊዚ የሚሸጠው ንብረት ከትክክለኛው የዋጋ ግምት አላግባብ ከፍ ወይም ዛቅ ተደርጎ እንዲይገመት ለማድረግ እና በንብረቱ ግምት ምክንያት በፍርድ ባለገንዖቡም ሆነ በፍርድ ባለዔዲው ላይ ሉደርስ የሚችለውን ጉዲት መከላከል እንዱቻል ፍርድ ቤቱ የሐራጁን ሥርዓት አፈጻጸም ለሕዛብ ማስታወቅ እንዲለበት፤የሚሸጠው ንብረት ዓይነት እና ግምት በሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያው ውስጥ ከሚገለጹት ነገሮች ውስጥ አንደ እንደሆነ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 423/1እና2 ድንጋጌ መገንዖብ ይቻላል።አመልካች የመኪናው ግምት ተጋኗል የሚለ ከሆነ የጨረታው ቀን ከመድረሱ በፉት የጨረታውን ትዔዙዛ ለሰጠው ፍ/ቤት ግምቱ ተጋኗል በማለት መቃወሚያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
አመልካች የጨረታው ቀን ከመድረሱ በፉት ግምቱ ተጋኗል በማለት ያቀረቡት መቃወሚያ ሳይኖር በጨረታው ቀን በቀረበው ግምት መሰረት ተጫራች ስላልቀረበ አስቀድሞ የተያዖው ግምት የገበያን ዋጋ መሰረት አላደረገም በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ተገቢ አይደለም።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 428/2 በሁለተኛው የጨረታ ማስታወቂያ በተወሰነው ቀን ተጫራች ያልቀረበ እንደሆነ ማናቸውም ተቃራኒ ድንጋጌ ቢኖርም እንኳን ለጨረታ የቀረበውን ንብረት የፍርድ ባለገንዖቡ ተረክቦ እንዱይዛ ትዔዙዛ ላሰጥ እንደሚችል፤ይህም በሆነ ጊዚ ፍርደ በሙለ ወይም በከፉል እንደተፈጸመ እንደሚቆጠር ይደነግጋል።ከድንጋጌው ይዖት መገንዖብ የሚቻለው የፍርድ ባለገንዖቡ ለጨረታ የቀረበውን ንብረት እንዱረከብ ትዔዙዛ ላሰጥ የሚችለው የፍርድ ባለገንዖቡ ንብረቱን ለመረከብ ፈቃደኛ ከሆነ እንጂ ከፈቃደ ውጪ ንብሩቱን እንዱረከብ የማይደረግ መሆኑን ነው።የፍርድ ባለመብት ንብረቱን ለመረከብ ፍቃደኛ ከሆነ ምላሽ ሉሰጠው የሚገበው ቁልፍ ነጥብ ለጨረታ የቀረበው ንብረት ግምት ለፍርድ ባለገንዖቡ ሉከፈለው ከሚገባው የገንዖብ መጠን የሚበልጥ ከሆነ የፍርድ ባለመብት ልዩነቱን የመክፈል ሀላፉነት አለበት? ወይስ የለበትም?
የሚለው ነው።
በተያዖው ጉዲይ ለጨረታ የቀረበችው መኪና ግምት ብር 731,426.05 / ሰባት መቶ ሰላሳ አንድ ሺህ አራት መቶ ሐያ ሥድስት ብር ከዚሮ አምሥት ሣንቲም / በመሆኑ እና ለአመልካች ሉከፈል የሚገባ አጠቃላይ የገንዖብ መጠን ብር 446,098.57 / አራት መቶ አርባ ሥድሥት ሺህ ዖጠና ሥምንት ብር ከሐምሳ ሰባት ሣንቲም / በመሆኑ ለጨረታ በቀረበችው መኪና ዋጋ ግምት እና ለአመልካች ሉከፈል በሚገባው የገንዖብ መጠን መካከል የብር 285,327.48 /ሁለት መቶ ሰማንያ አምሥት ሺህ ሦስት መቶ ሐያ ሰባት ብር ከአርባ ሥምንት ሣንቲም / ልዩነት አለ።
ከላይ በአንደኛው ጭብጥ እንደተገለጸው ንብረት በሐራጅ እንዱሸጥ በሚወሰንበት ጊዚ የሚሸጠው ንብረት ከትክክለኛው የዋጋ ግምት አላግባብ ከፍ ወይም ዛቅ ተደርጎ እንዲይገመት ለማድረግ እና በንብረቱ ግምት ምክንያት በፍርድ ባለገንዖቡም ሆነ በፍርድ ባለዔዲው ላይ ሉደርስ የሚችለውን ጉዲት መከላከል እንዱቻል የሚሸጠው ንብረት ዓይነት እና ግምት በሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያው ውስጥ የሚገለጽ በመሆኑ እና አመልካች የጨረታው ቀን ከመድረሱ በፉት ግምቱን በሚመለከት ያቀረቡት መቃወሚያ የላለ በመሆኑ አስቀድሞ የቀረበውን የዋጋ ግምት እንደተቀበለት ግምት የሚወሰድበት ነው።
አመልካች ለጨረታ የቀረበውን የመኪናዋን ዋጋ ግምት ከጨረታው ቀን በፉት ባልተቃወሙበት ሁኔታ በሁለተኛው ጨረታ ተጫራች ስላልቀረበ ተጠሪ ለአመልካች ሉከፍለው በሚገባው የገንዖብ መጠን ልክ መኪናዋን ልረከብ ይገባል በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 423 እና 428 ድንጋጌዎች ዓላማ ውጪ በመሆኑ በዘህ አግባብ ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም።
የክልለ ፍ/ቤቶች በሁለተኛው ጨረታ ተጫራች ስላልቀረበ በመኪናዋ ዋጋ እና ለአመልካች ሉከፈለው በሚገባ የገንዖብ መጠን መካከል ያለውን ልዩነት አመልካች ሉከፍለ ይገባል በማለት የደረሱበት መደምደሚያ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 423 እና 428 ድንጋጌዎች ዓላማ አኳያ ተቀባይነት ያለው ቢሆንም በሁለተኛው ጨረታ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት የፍርድ ባለመብቱ ለጨረታ የቀረበውን ንብረት እንዱረከቡ ትዔዙዛ ላሰጥ የሚችለው የፍርድ ባለመብቱ ለጨረታ በቀረበው የገንዖብ መጠን መሰረት ንብረቱን ለመረከብ ፈቃደኛ መሆኑ በቅድሚያ ከተረጋገጠ በኋላ ነው።የክልለ ፍ/ቤቶች አመልካች ንብረቱን ለጨረታ በቀረበው የገንዖብ መጠን መሰረት ለመረከብ ፈቃደኛ መሆናቸውን በቅድሚያ ሳያረጋግጡ አመልካች በመኪናዋ ዋጋ እና ለአመልካች ሉከፈል በሚገባው የገንዖብ መጠን መካከል ያለውን ልዩነት ከፍለው መኪናዋን ይረከቡ በማለት የሰጠው ትዔዙዛ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 428/2 ድንጋጌን ያላገናዖበ እና መሰረታዊ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።በዘህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
ሕዲር 09 ቀን 2008 ዓ.ም ተሰጥቶ፤በክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. የካቲት 30 ቀን 2008 ዓ.ም በትዔዙዛ የጸናው ትዔዙዛ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1 መሰረት ተሻሽሎል።
የክልለ ፍ/ቤቶች አመልካች ለጨረታ በቀረበው የዋጋ መጠን እና ሉከፈላቸው በሚገባው የገንዖብ መጠን መካከል ያለውን ልዩነት ከፍለው መኪናዋን ለመረከብ ፈቃደኛ መሆናቸውን በቅድሚያ ሳያረጋግጡ አመልካች ልዩነቱን ከፍለው መኪናዋን እንዱረከቡ በማለት የሰጡት ውሳኔ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 428/2 ድንጋጌን ያላገናዖበ ነው ብለናል።
በሁለተኛው ጨረታ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት አመልካች ለጨረታ በቀረበው የዋጋ መጠን እና ሉከፈላቸው በሚገባው የገንዖብ መጠን መካከል ያለውን ልዩነት ከፍለው መኪናዋን እንዱረከቡ ሉገደደ አይገባም በማለት ወስነናል።
የሽሬ እንዲስላሴ ከፍተኛ ፍ/ቤት አመልካች በጨረታ መነሻ ዋጋ ተሽከርካሪውን ለመረከብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው አፈጻጸሙ በፍርድ ባለዔዲው ላላ ንብረት ላይ እንዱቀጥል በማድረግ ወይም ለጨረታ በቀረበው ተሽከርካሪ ላይ አፈጸጸሙ የሚቀጥልበት አግባብ ካለም ተገቢውን በመፈጸም አፈጻጸሙን እንዱቀጥል ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343/1 መሰረት ጉዲዩ ተመልሶለታል።
በዘህ ፍ/ቤት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
ሚያዛያ 19 ቀን 2009 ዓ.ም በመዛገቡ የተሰጠው የዔግድ ትዔዙዛ ተነስቷል።ይጻፍ።
መዛገቡ ተዖግቷል።ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.