No summary available.
ሚያዘያ 30 ቀን 2009ዓ.ም ዳኞች፡- ዲኜ መላኩ ብርሃኑ አመነዉ በዔዉቀት በላይ እንዲሻዉ አዲነ እትመት አሰፊ አመልካች:- አቶ ደስታ ንጉሴ አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ ሐየልም በላይ አልቀረቡም መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ አፈጻጸምን የሚመለከት ሆኖ የተጀመረዉ የሒድነት ወረዲ ፍ/ቤት ሲሆን አመልካች በአቶ ሕንጻ በላይ እና በአሁኑ ተጠሪ ላይ በአንድነትና በተናጠል እንዱከፍለ ካስወሰነዉ ገንዖብ ዉስጥ የአሁኑ ተጠሪ ግማሹን መክፈለን ገልጾ ቀሪዉን ግማሽ ብር 22,165 የመክፈል ግዳታ ያለበት በመሆኑ ተጠሪ እንዱከፍለዉ ሲጠይቅ፤ ተጠሪ በበኩለ በአንድነትና በተናጠል እንድንከፍል ተወስኖ የነበረዉን አቶ ሕንጻ በላይ ይግባኝ ጠይቀዉ ተጠያቂ ሉሆኑ አይገባም ተብል የተወሰነና ከአፈጻጸም ክሱም የተሰናበቱ በመሆነቸዉ በዋናዉ ፍርድ መሰረት ተጠሪ ሙለ ገንዖቡን ብከፍል በአንድነትና በነጠላ ተጠያቂ ነዉ ተብል ከነበነረዉ ሰዉ ግማሹን የማስመለስ መብቴ ስለተነካ የአቶ ህንጻ በላይ ድርሻ የምከፍልበት አግባብ የለም ሲል ተከራክሯል።
የወረዲዉ ፍ/ቤት የአፈጻጸም ክርክሩን መርምሮ ተጠሪ ከአቶ ሕንጻ በላይ ጋር በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ ተወስኖ የነበረዉን አቶ ሕንጻ በላይ ይግባኝ ጠይቀዉ ኃላፉነታቸዉን በተመለከተ ዉሳኔዉን አሽረዋል። ተጠሪ የአቶ ሕንጻ በላይን ድርሻ ለመክፈል ይገደደ የነበረዉ አቶ ሕንጻ በላይ ባለዔዲ ሆነዉ ለመክፈል ፍቃደኛ ባይሆኑ ነበር። አሁን ግን አቶ ሕንጻ በላይ የተወሰነባቸዉን ያሻሩ ስለሆነ ተጠሪ ገንዖቡን ጠቅልለዉ ከፍለዉ ከአቶ ሕንጻ በላይ መልሰዉ ድርሻቸዉን የሚያስከፍለበት የሕግ አግባብ በላለበት ተጠሪ ድርሻዉ ከሆነዉ ግማሽ ገንዖብ በላይ እንዱከፍል ሉገደድ አይገባም በማለት ብይን ሰጥቷል። ይህን ብይን በመቃወም አመልካች ያቀረቡትን ይግባኝ የተመለከተዉ የመቀላ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 337 መሰረት ይግባኙን አሰናብቷል። እንዱሁም አመልካች የሰበር አቤቱታ ለትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረቡ ቢሆንም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኃላ መሰረታዊ የሕግ ስህተት አልተፈጸመም በማለት የስር ፍ/ቤቶችን ዉሳኔ አጽንቶታል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ይህን ዉሳኔ በመቃወም ለማስቀየር ነዉ።
አመልካች ያቀረበዉ የሰበር አቤቱታ ይዖት፡- ዋናዉ ፍርድ በግልጽ የሚያመለክተዉ ተጠሪና አቶ ሕንጻ በላይ በአንድነትና በነጠላ የኮንስትራክሽን ዔቃዎች ዋጋ እና ኪራይ እንዱከፍለኝ ነዉ።
ስለዘህ ዉሳኔዉ ተጠሪና አቶ ሕንጻ በላይ ድርሻ ሳይነጣጠል በጋራ እንዱከፍለኝ የተወሰነ ነዉ።
በዋናዉ ፍርድ ሁለቱም ለከፍተኛ ፍ/ቤት ለየብቻቸዉ ይግባኝ አቅርበዉ በወረዲ ፍ/ቤት የተሰጠዉን ዉሳኔ ቢያሽሩም በተጠሪ መዛገብ በተሰጠዉ ዉሳኔ ስላልተስማማሁ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቤ የከፍተኛዉ ፍ/ቤት ዉሳኔ ተሽሮ የወረዲዉ ፍ/ቤት ዉሳኔ ሙለ በሙለ ጸንቷል። የወረዲዉ ፍርድ ቤት በአፈጻጸም በሰጠዉ ብይን ራሱ የሰጠዉን ዉሳኔ ብቻ ሳይሆን የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ ጭምር ሽሯል። የክልለ ሰበር ሰሚ ችልትም ይህን ብይን ማጽናቱ ስህተት ነዉ። ስለሆነም የስር ፍ/ቤቶች የአፈጻጸም ትዔዙዛ ተሽሮ ተጠሪ ዔዲዉን በሙለ እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ የሚል ነዉ።
የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ ለዘህ አፈጻጸም መሰረት የሆነዉ ፍርድ መነሻ የሆነዉ የክስ ምክንያት ከተጠሪ ጋር ተከሶ የነበረዉን ግለሰብ ጭምር ሳይሆን ተጠሪን ብቻ በግለ የሚመለከት ነዉ ተብል ግለሰቡ በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ከኃላፉነት ነጻ እስከተባለ ድረስ ተጠሪ ፍርደን በሙለ እንዱፈጽም ሉገደድ አይገባም ወይ የሚለዉን ነጥብ ለመመርመር ሲባል ለሰበር ያስቀርባል የተባለ ሲሆን ግራ ቀኙ መልስ እና የመልስ መልስ በጽሁፍ በማቀባበል እንዱከራከሩ ተደርጓል።
ተጠሪ በሰበር መልሳቸዉ ያቀረቡት ክርክር ይዖት፡- አቶ ሕንጻ በላይ ተጠያቂ አይደለም የተባለዉ በድርሻዉ ላለዉ ተጠያቂነት ነዉ። የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የወረዲዉን ፍ/ቤት ዉሳኔ አጽንቻለሁ ማለቱ ሁለቱም በአንድነትና በነጠላ ተጠያቂዎች መሆናቸዉን የሚያሳይ ነዉ። ይህም የአሁኑ ተጠሪ አጠቃላዩን ለመክፈል የሚጠየቅበት አግባብ የለም። ተጠሪ በዉሳኔዉ መሰረት ግማሽ ድርሻዬን የከፍልኩኝ ሲሆን አቶ ሕንጻ በላይ መክፈል ያለባቸዉን ገንዖብ መክፈል አለብህ የሚለዉ ቅሬታ አቶ ሕንጻ በላይ በነጻ ከመሰናበቱ አንጻር የሕግ መሰረት የለዉም። ክፈል ተብዬ ተገድጄ ብከፍል መጨረሻ ላይ ከአቶ ሕንጻ ገንዖቡን ማስመለስ አልችልም። አመልካች በራሳቸዉ ቸልተኝነት በአቶ ሕንጻ በላይ ይግባኝ ሳያቀርቡ ለቀረባቸዉ ግማሽ ክፍያ ተጠያቂ ራሳቸዉ እንጂ ተጠሪ አይደለም። ስለሆነም ተጠሪ ድርሻዉን ግማሹን ገንዖብ ስለከፈልኩ አመልካች ከተጠሪ የሚጠይቁት ተጨማሪ ክፍያ የለም ተብል የስር ፍ/ቤቶች ዉሳኔ ይጽናልኝ የሚል ነዉ።
No topics extracted.
አመልካች አቤቱታቸዉን በሚያጠናክር መልኩ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር ባጭሩ ከላይ የተመለከተዉን የሚመስል ሲሆን እኛም አቤቱታ ከቀረበበት ዉሳኔ እና አግባብነት ካለዉ የሕግ ድንጋጌ ጋር በማገናዖብ መዛገቡን መርምረናል።
የሰበር አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዖዉ ጭብጥ አንጻር መርምረን እንደተረዲነዉ ለአፈጻጸሙ መሰረት የሆነዉን ፍርድ በቅድሚያ የሰጠዉ የመቀላ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት ተጠሪን እና የስር 1ኛ ተከሳሽ የነበረዉን አቶ ሕንጻ በላይን በአንድነትና በነጣል ዔዲዉን እንዱከፍለ የወሰነባቸዉ ሲሆን ሁለቱም ባለዔዲዎች በተናጠል ለመቀላ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበዉ በተለያዬ መዛገብ ዉሳኔዉን አሽረዋል። የአሁኑ አመልካች ተጠሪን በተመለከተ ብቻ ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርቦ ግራቀኙን ካከራከረ በኃላ ተጠሪ ነጻ የተባለበትን ዉሳኔ በመሻር የወረዲዉ ፍ/ቤት የሰጠዉን ዉሳኔ አጽንቶታል። አመልካች ፍርደን ሙለ በሙለ ተጠሪ እንዱፈጽምለት የጠየቀ ሲሆን የስር ፍ/ቤቶች በተመሳሳይ ተጠሪ የፍርደን ግማሽ ገንዖብ በመክፈል ድርሻዉን የተወጣ በመሆኑና በዋናዉ ጉዲይ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቶ ሕንጻ በላይን አስመልክቶ በነጻ እንዱሰናበት በሰጠዉ ዉሳኔ ላይ የአሁኑ አመልካች ይግባኝ ጠይቆ ባለማሻሩ ምክንያት የአሁኑ ተጠሪ ሙለ ገንዖቡን ቢከፍል በድርሻዉ አቶ ሕንጻ በላይን ጠይቆ የማስመለስ መብቱን የሚያሳጣዉ በመሆኑ ተጠሪ ከግማሽ ዔዲ ወይም ከድርሻዉ በላይ እንዱከፍል ሉገደድ አይገባም በማለት ወስነዋል። የአሁኑ አመልካች አጥብቆ የሚከራከረዉ ተጠሪ ለሙለ ዔዲዉ በአንድነትና በተናጠል ኃላፉ ነዉ እስከተባለ ድረስ ተጠሪ ሙለ ገንዖቡን የመክፈል ግዳታ አለበት በሚል ነዉ።
በመሰረቱ የአንድነትና የነጣላ ኃላፉነት ምን ማለት እንደሆነ በሕጋችን ተካትቶ የምናገኘዉ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1896፣ 1897 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ላይ ነዉ። እነዘህ ድንጋጌዎች የሚገኙት ግዳታዎችን በተመለከተዉ የፍትሐብሕር ሕጉ መጽሐፍ በተለይም ስለ ዉልች በጠቅላለዉ በሚለዉ አንቀጽ 12 ስር ቢሆንም መርሁ ግዳታዉ ከዉል፣ ከሕግም ሆነ ከፍርድ የመነጨ ቢሆንም ይህንኑ የሚመለከት የተለዬ የሕግ ድንጋጌ እስካልኖረ ድረስ በተጠቀሱት ድንጋጌዎች የተቀመጠዉ የአንድነትና የነጠላ ኃላፉነት መርህ ተፈጻሚነት ይኖረዋል።
ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 1896፣ 1897 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መገንዖብ የሚቻለዉ ሁለት ባለዔዲዎች በአንድነትና በነጠላ አንድን ዔዲ እንዱከፍለ ከተፈረደባቸዉ ባለገንዖቡ ገንዖቡ እንዱከፈለዉ ሁለቱን ባለዔዲዎች በአንድነት ወይም አንደኛዉ ባለዔዲ ሙለ ገንዖቡን እንዱከፍል ሉጠይቅ ይችላል።
እንዱሁም አንደ የፍርድ ባለዔዲ በዋናዉ ፍርድ ይግባኝ ጠይቆ የራሱን ኃላፉነት አስመልክቶ ፍርደን አሽሮት ከሆነ ሙለ እዲዉን ለመክፈል ኃላፉነት የሚኖርበት ይግባኝ ሳይጠይቅ በመቅረቱ ዋናዉን ፍርድ ባልተሻረለት ወይም ይግባኝ ጠይቆ ፍርደ በጸናበት ሰዉ ላይ ይሆናል።
ፍርድ ያላሻረዉ ወይም የጸናበት ባለዔዲ ዔዲዉን የምከፍለዉ በድርሻዬ ልክ ወይም ግማሹን ነዉ ለማለት አይችልም። ምክንያቱም ሁለት ሰዎች በአንድነትና በነጠላ ኃላፉ ናቸዉ ሲባለ ለእዲዉ አከፊፈል አንዲቸዉ ወይም ሁለቱም በጋራ ለባለገንዖቡ ግዳታ አለባቸዉ ማለት እንጂ ሁለቱ በመካከላቸዉ ዔዲዉን እኩል ለመካፈል ኃላፉነት አለባቸዉ ማለት አይደለም። በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1907 መሰረት የተቀመጠዉ የሕግ ግምት እንደተጠበቀ ሆኖ በሁለቱ ባለዔዲዎች መካከል ያለዉ የኃላፉነት መጠን የሚወሰነዉ እርስ በርሳቸዉ ሲጠያየቁ በሚኖረዉ ኃላፉነት መሰረት አንደ ለሙለ ወይም ለከፉለ ዔዲ ኃላፉ ነዉ ተብል ተለይቶ ሲወሰን ነዉ።
በተያዖዉ ጉዲይ አመልካች የስር ተከሳሾች በአንድነትና በተናጠል ኃላፉነት የሚያስከትልባቸዉ የሕግ ተጠያቂነት አለባቸዉ ብል ቢያምንም ሲፈልግ ሁለቱን ሳይፈልግ አንደን መርጦ የመክሰስ መብት አለዉ። እንዱሁም በይግባኝ ደረጃም ቢሆን በአንደ ላይ ይግባኝ ጠይቆ በልላኛዉ ላይ ይግባኝ ያለመጠየቅ መብት አለዉ። ምክንያቱም አንደን ነጥል መክሰሱ ወይም በአንደ ላይ ብቻ ይግባኝ መጠየቁ ብቻ ገንዖቡን የሚያስከፍለዉ መሆኑን እስካረጋገጠለት ድረስ ሁለቱን በአንድነት የመክሰስ ወይም ይግባኝ የመጠየቅ ግዳታ አይኖርበትም። አመልካች ያቀረበዉ ክስም ሆነ ይግባኝ የስር ተከሳሾች ለአመልካች የሚኖራቸዉን ግዳታ ወይም ኃላፉነት የሚወስን እንጂ በቀጥታ በሁለቱ ተከሳሾች የዔዲ መከፊፈለን ወይም አንደ ሙለ እዲ ከፍል ከላላዉ የሚጠይቅበት ፍርድ ወይም የዲኝነት ጥያቄ አይደለም። ተጠሪ ለሙለ እዲዉ በአንድነትና በተናጠል ኃላፉ ነዉ ተብል የተወሰነበትን በይግባኝ ወይም የሰበር አቤቱታ አቅርቦ እስካላሻረ ድረስ ወይም ኃላፉነቱ በድርሻዉ እንዱቀንስ እስካላደረገ ድረስ ሙለ እዲዉን ለአመልካች ለመክፈል ይገደዲል። አመልካች የመቀላ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቶ ሕንጻ በላይን በነጻ ሲያሰናብት ይግባኝ አለመጠየቁ ወይም ይግባኝ ተይቆ የጸናበት መሆኑ ተጠሪ ዔዲዉን በሙለ ለመክፈል ባለዉ ኃላፉነት ላይ ለዉጥ አያመጣም።
ስለሆነም የስር ፍ/ቤቶች አመልካች የመቀላ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቶ ሕንጻ በላይን በነጻ ሲያሰናብት ይግባኝ ጠይቆ ባለማሻሩ ተጠሪ ሙለ ክፍያ ከፍል ግማሹን ከአቶ ሕንጻ በላይ የማስመለስ መብቱን የሚነካ በመሆኑ ተጠሪ ድርሻዉን ወይም ግማሹን ፍርድ እንጂ ግማሹን ለመክፈል አይገደድም በማለት የሰጡት የአፈጻጸም ዉሳኔ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነዉ።
ሲጠቃለል በዋናዉ ፍርድ በወረዲዉ ፍ/ቤት ከተጠሪ ጋር በአንድነትና በተናጠል ለሙለ ዔዲዉ ኃላፉ ተደርጎ የነበረዉ አቶ ሕንጻ በላይ ይግባኝ ጠይቆ ራሱን ከኃላፉነት ነጻ ባደረገበትና በተጠሪ ላይ በወረዲዉ ፍ/ቤት የተሰጠዉ ዉሳኔ ባልተሻሻለለት ወይም ባልተሻረለት ሁኔታ፤ የስር ፍ/ቤቶች ተጠሪ ግማሹን እስከከፈለ ድረስ ግማሹን ወይም የአቶ ሕንጻ በላይን ድርሻ ለመክፈል አይገደድም በማለት የሰጡት የአፈጻጸም ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም የሚከተለዉ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የመቀላ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት የሒድነት ምድብ ችልት በመ/ ሕዲር 22 ቀን 2007 ዓ.ም ተሰጥቶ፤ በመቀላ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ መጋቢት 11 ቀን 2007 ዓ.ም በተሰጠ ትዔዙዛ እና የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ነሐሴ 07 ቀን 2007 ዓ.ም በተሰጠ ዉሳኔ የጸናዉ የአፈጻጸም ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
የተጠሪ ኃላፉነት አስመልክቶ የወረዲዉ ፍ/ቤት የሰጠዉ ዋና ፍርድ በይግባኝ የጸና በመሆኑና በይግባኝ የተሻረዉ የአቶ ሕንጻ በላይ ኃላፉነት ብቻ በመሆኑ ተጠሪ የሚከፍለዉን ገንዖብ ግማሽ ከአቶ ሕንጻ ማስመለስ መቻል አለመቻለ ግምት ዉስጥ ሳይገባ ለአመልካች እንዱከፈል የተወሰነዉን ሙለ ገንዖብ ተጠሪ የመክፈል ወይም እንደፍርደ የመፈጸም ኃላፉነት አለበት ተብል ተወስኗል። የመቀላ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት የሒድነት ምድብ ችልት መዛገቡን በማንቀሳቀስ ለአመልካች ያልተፈጸመለትን ቀሪ ገንዖብ ተጠሪ እንዱከፍል በማድረግ ፍርደን እንዱያስፈጽም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343(1) መሰረት ጉዲዩ ይመለስለት ተብሎል። ይጻፍ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለዉን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸዉን ይቻለ።
መዛገቡ ዉሳኔ ያገኘ ስለሆነ ተዖግቷል። ይመለስ።