No summary available.
ሕዲር 22 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ አብዬ ካሳሁን እትመት አሰፊ አመልካች፡-
ጉዲዩ የፍርድ አፈጻጸምን የሚመለከት ክርክር ሲሆን አመልካቾች አቤቱታቸውን ለዘህ ችልት ያቀረቡትም ለፍርድ አፈጻጸሙ ምክንያት የሆነው መኖሪያ ቤት ክፍፍል መፈጸም የሚገባው በሀራጅ ተሽጦ ነው በሚል በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠውን የአፈጻጸም ትዔዙዛ በፍርድ በማጽናት በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዛገብ 9 በ16/06/2008 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ነው።
የጉዲዩን አመጣጥ በተመለከተ፡-የ1ኛ አመልካች ባለቤት የነበሩት አቶ ሞገስ ጌታሁን በሞት መለየታቸውን ተከትል በተነሳው የውርስ እና የጋራ ንብረት ክፍያ ክርክር በዋግኽምራ ዜን በሰቆጣ ከተማ በቀበላ 02 ክልል በሟች ስም ተመዛግቦ ይታወቅ ከነበረው ቤት ውስጥ ግማሹ የአሁኗ 1ኛ አመልካች ድርሻ ሆኖ ቀሪው ግማሽ ደግሞ ከሟች ለሚወለደት ሰባት ልጆች እንዱከፊፈል ውሳኔ የተሰጠ መሆኑን፣ይህንን የስረ ነገር ፍርድ ለማስፈጸም 1ኛ አመልካች በፍርድ ባለመብትነት ተሰይመው ባደረጉት እንቅስቃሴ በከተማው አስተዲደር በቀረበው የዋጋ ግምት መሰረት የቀሪዎቹን ወራሾች ድርሻ 1ኛ አመልካች ከፍለው እና ከወራሾቹ መካከል የአሁኑ ተጠሪ ቤቱ በጨረታ መሸጥ ከሚገባው በቀር ግምቱን ለመቀበል አልስማማም በማለታቸው ድርሻቸው በሞዳል 85 እንዱያዛ ተደርጎ የቤቱ ስመሀብት አፈጻጸሙን በያዖው የሰቆጣ ወረዲ ፍርድ ቤት ትዔዙዛ ወደ 1ኛ አመልካች የተዙወረ መሆኑን፣1ኛ ተጠሪ በዘህ ትዔዙዛ ባለመስማማት በየደረጃው ያቀረቡት ክርክር በመጨረሻ የቀረበለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የስርፍርድ ቤቶችን የአፈጻጸም ትዔዙዛ ሽሮቤቱ ከተቻለ በዓይነት፣ካልተቻለ ግራ ቀኙ እርስ በእርስ በሚያደርጉት ጨረታ፣ይህም ካልተቻለ ለ3ኛ ወገን በጨረታ እንዱሸጥ በመዛገብ ቁጥር 03-08523 በ26/04/2007 ዓ.ም ውሳኔ የሰጠ መሆኑን፣የወረዲው ፍርድ ቤትም በዘሁ አግባብ ቤቱ በጨረታ እንዱሸጥ ለማስቻል የጨረታ ማስታወቂያ እንዱወጣ ትዔዙዛ የሰጠ መሆኑን፣በዘህ ትዔዙዛ ቅር በመሰኘት 1ኛ አመልካች ያቀረቡት ይግባኝ በዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ በ02/10/2007 ዓ.ም.
በትዔዙዛ የተዖጋ እና አቤቱታቸውም በክልለ ሰበር ችልት በመዛገብ ቁጥር0311349 በ16/06/2008 ዓ.ምበተሰጠ በፍርድ ተቀባይነት ያጣ መሆኑን የመዛገቡ ግልባጭያመለክታል።
አመልካቾች ለዘህ ችልት ያቀረቡት አቤቱታ ተመርምሮ አመልካቾቹ በአከራካሪው ቤት ላይ ያላቸው የጋራ ድርሻ በጣም ብዘ ሆኖ እያለ እና የተጠሪው ድርሻ ግን በድርሻቸው ብቻ የታጠረ ሆኖ እያለ፣ይህንኑ ከግምት በማስገባትም 1ኛ አመልካች ከአሁኑ ተጠሪ በቀር ለቀሪው እያንዲንደ ወራሽ ግምቱን ከፍለው ቤቱን በስማቸው አዙውረው እያለ የአሁኑ ተጠሪ ግምቱን ለመቀበል ባለመስማማታቸው ብቻቤቱ በሀራጅ እንዱሸጥ የመታዖዘን አግባብነት ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዖንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዖት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም በጉዲዩ እልባት ማግኘት የሚገባቸው፡-
በስረ ነገሩ ፍርድ መሰረት ለማስፈጸም ይቻል ዖንድ በቤቱ ላይ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ እንዱወጣ በወረዲው ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ያገኘው የአፈጻጸም ትዔዙዛ የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አለ ወይስ የለም?
አመልካቾቹ ከአከራካሪው ቤት ላይ አለን የሚለትን አብላጫ ድርሻ መሰረት በማድረግ ቤቱን ማስቀረት የሚችለበት የሕግ አግባብ አለ ወይስ የለም?
የሚለ ነጥቦች መሆናቸውን በመገንዖብ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ከእነዘሁ ነጥቦች አንጻር መርምረናል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ 1ኛ አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩት ከአከራካሪው ቤት በሚስትነታቸው ያላቸው ድርሻ ግማሽ ሆኖ እያለ እና የሰባት ወራሾች ድርሻ ከሆነው የቤቱ አጋማሽ ውስጥ ደግሞ 1ኛ አመልካች ሞግዘት የሆኗቸው 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾችእያንዲንዲቸው አንድ ሰባተኛ ድርሻ ያላቸው ሆኖ እያለ እንዱሁም ከተጠሪው ውጪ ላለት ቀሪ ወራሾች 1ኛ አመልካች ድርሻቸውን ከፍለው እያለ ከቤቱ አጋማሽ ውስጥ አንድ ሰባተኛ ድርሻ ብቻ ላላቸው የአሁኑ ተጠሪ ጥቅም ብቻ ሲባል ወደ 1ኛ አመልካች ስም ተዙውሮ የነበረው ቤት በሀራጅ እንዱሸጥ የተሰጠው ትዔዙዛ ፍትሐዊ አይደለም የሚል መሆኑን የአቤቱታቸው ይዖት ያመለክታል።ይሁን እንጂ የክልለ ሰበር ችልት የአፈጻጸም ሂደቱን አስመልክቶ ቀደም ሲል ቤቱ ከተቻለ በዓይነት፣ካልተቻለ ግራ ቀኙ በመካከላቸው በሚያደርጉት ጨረታ፣ይህም ካልተቻለ ደግሞ ለ3ኛ ወገን በጨረታ እንዱሸጥ በመዛገብ ቁጥር 03-08523 በ26/04/2007 ዓ.ም. ውሳኔ የሰጠው 1ኛ አመልካች ከአሁኑ ተጠሪ ውጪ ላለት ላልች ወራሾች ድርሻቸውን ሰጥተው ቤቱን በስማቸው ካዙወሩ በኃላ በመሆኑ የተጠሪው ድርሻ ከቤቱ አጋማሽ ውስጥ አንድ ሰባተኛ ብቻ ሆኖ እያለ ቤቱ በሐራጅ ይሸጥ መባለ ተገቢ አይደለም የሚለ ከሆነ የሰበር አቤቱታቸውን በወቅቱ በስርዓቱ መሰረት ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት አቅርበው ተገቢውን ውሳኔ ማሰጠት ይገባቸው የነበረ ከመሆኑ በቀር በክልለ ሰበር ችልት ውሳኔ መሰረት ጉዲዩ ወደ ወረዲው ፍርድ ቤት ተመልሶ የአፈጻጸም ሂደቱ ከቀጠለ በኃላ ወደኃላ ተመልሰው ቤቱ በሀራጅ እንዱሸጥ የተሰጠው የአፈጻጸም ትዔዙዛ ፍትሀዊ አይደለም በማለት አሁን እያቀረቡ ያለት ክርክር ስነ ስርዓታዊ ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም።በመሆኑም አፈጻጸሙን የያዖው የሰቆጣ ወረዲ ፍርድ ቤት ቀደም ሲል በክልለ ሰበር ችልት በመዛገብ ቁጥር 03-08523 በ26/04/2007 ዓ.ም.
No topics extracted.
የሰጠውን ውሳኔ ተከትል በስረ ነገሩ ፍርድ መሰረት ለማስፈጸም ይቻል ዖንድ በቤቱ ላይ የሀራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ እንዱወጣየሰጠው እና በክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ያገኘው የአፈጻጸም ትዔዙዛ የሚነቀፍበትን ሕጋዊ ምክንያት አላገኘንም።
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ ከአከራካሪው ቤት 1ኛ አመልካች ግማሽ ድርሻ፣2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ደግሞ ከቤቱ አጋማሽ ውስጥ እያንዲንዲቸው አንድ ሰባተኛ ድርሻ ያላቸው መሆኑ አላከራከረም።ይህም 1ኛ አመልካችም ሆኑ 2ኛ እና 3ኛ አመልካቾች ከቀሪዎቹ ወራሾች ጋር የአከራካሪው ቤት የጋራ ባለሀብቶች መሆናቸውን መገንዖብ የሚያስችል ነው።በፍርድ አፈጻጸም ምክንያት ተይዜ የሚሸጠው የማይንቀሳቀስ ንብረት ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ሰዎች በሕብረት የያዘት እና ያልተከፊፈለት በሆነ ጊዚ ከተካፊዮቹ አንደ ንብረቱን ለመግዙት በጨረታ ተወዲዲሪ ሆኖ የቀረበ እንደሆነ የፍርድ ባለዔዲው እንደቀረበ ተቆጥሮ የተቀዲሚነት መብት የሚሰጠው ስለመሆኑ የፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 443 ይደነግጋል።ከስነ ስርዓት ሕጉ በተጨማሪም የጋራ ባለሀብቶች የሆኑ ሰዎች ያልተከፊፈለውን የጋራ ንብረት ከማንኛውም ሶስተኛ ወገን በፉት ቀዲሚ ሆነው በግዣ የማስቀረት ሕጋዊ መብት ያላቸው ስለመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1261 (1) የተደነገገ ሲሆን ይህ መብት ተግባራዊ የሚደረግበት ስርዓትም በዘሁ ሕግ ከቁጥር 1386 እስከ 1409 ተደንግጎ ይገኛል።በመሆኑም አመልካቾቹ አከራካሪውን ቤት ለማስቀረት የሚችለት በቤቱ ላይ በሚከናወነው ጨረታ መሰረት ከፍተኛ ዋጋ በማቅረብ አሸናፉ የሆነው ተጫራች ጨረታውን ያሸነፈበትን ዋጋ መሰረት በማድረግ ከላይ በተጠቀሱት ድንጋጌዎች በተጠበቀላቸው የቀዲሚነት መብት በመገልገል ነው።በቀጣይ የአፈጻጸሙ ሂደት አመልካቾቹ ከፍተኛ ዋጋ በማቅረብ አሸናፉ የሆነው ተጫራች ጨረታውን ያሸነፈበትን ዋጋ መሰረት በማድረግ የቀዲሚነት መብታቸውን ተግባራዊ የሚያደርጉ ከሆነ በሰበር አቤቱታቸው እንደሚከራከሩት ከአሁኑ ተጠሪ ውጪ ላለት ላልች ወራሾች ድርሻቸውን ከፍለው በቤቱ ላይ ያላቸውን ድርሻ ከፍ ያደረጉ መሆን አለመሆኑ፣ጨረታውን ካሸነፈበት የዋጋ መጠን ውስጥ የራሳቸው ድርሻ ተቀንሶ ገቢ ማድረግ የሚገባቸው የገንዖብ መጠን ምን ያህል እንደሆነ እና መሰል የአፈጻጸም ጉዲዮች ፍርደን በሚያስፈጽመው ፍርድ ቤት ተስተናግደው ተገቢው ትዔዙዛ የሚሰጥባቸው ይሆናል።
ሲጠቃለል አመልካቾቹ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 443 እንዱሁምበፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1261 (1)፣1386 እስከ 1409 በተደነገገው የቀዲሚነት መብታቸው የመገልገል መብታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ አከራካሪው ቤት በሀራጅ እንዱሸጥ በወረዲው ፍርድ ቤት የተሰጠው እና በክልለ የበላይ ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ያገኘው ትዔዙዛ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ስላልተቻለ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
በሰቆጣ ወረዲ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በዋግኽምራ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ 3 በ02/10/2007 ዓ.ም. በትዔዙዛ የጸናውን የአፈጻጸም ትዔዙዛ በፍርድ በማጽናት በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዛገብ 9 በ16/06/2008 ዓ.ም. የተሰጠው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ጸንቷል።
የስረ ነገሩ ፍርድ ያረፈበት ቤት በሀራጅ ይሸጥ መባለ በአግባቡ ነው በማለት ወስነናል።
አከራካሪው ቤት በሀራጅ በሚሸጥበት ጊዚ አመልካቾቹ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 443፣እንዱሁም በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1261 (1)፣1386 እስከ 1409 በተደነገገው የቀዲሚነት መብት የመገልገል መብት አላቸው በማለት ወስነናል።
እንዱያውቁት የዘህ ውሳኔ ግልባጭ ለሰቆጣ ወረዲ ፍርድ ቤት፣ለዋግኽምራ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ለአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ይላክ።
በአማራ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በመዛገብ 9 በ16/06/2008 ዓ.ም. የተሰጠው ውሳኔ አፈጻጸም ታግድ እንዱቆይ በዘህ መዛገብ በ06/07/2008 ዓ.ም. ተሰጥቶ የነበረው ትዔዙዛ ተነስቷል።ይጻፍ።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዛገቡ ተዖግቷል።