ፍርድ ቤቶች በተከሳሽ ላይ የሚጣለው ቅጣት ከወንጀል አፈጻጸሙ ሆነ ባህሪዉ እንዱሁም ከተፈፀመው ወንጀል ክብደት አንፃር ፍትሃዊ ውሳኔ ለመስጠት በቅጣት አወሳሰን መመሪያዉ መሰረት ለመወሰን የማያስችል ሆኖ በተገኘ ጊዚ በቅጣት አወሳሰን መመሪያው መሰረት ምክንያቱን በማስቀመጥ በመመሪያው ከተቀመጠው በተለየ መልኩ ቅጣት ሉወስኑ የሚችለ ሥለመሆኑ የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 አንቀፅ 21(1) የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 88(2)
No summary available.
ሰኔ 30 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው በእውቀት በላይ እንዲሻው አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- አቶ ሄኖክ ብሩክ አረጋ ጠበቃ እንዲለ ክፍላ ተጠሪ፡- ፋዳራል ዓ/ህግ መሰረት ሙላቱ ቀረቡ መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ወንጀል ሲሆን ክርክሩ የተጀመረውም በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። በዘህ ፍ/ቤት የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ላይ የመሰረተው የወንጀል ክስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወ/ህ/አንቀጽ 539(1(ሐ)) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሳሽ የፈፀመው የአስገድድመድፈር ሙከራ ወንጀል እንዲይገለፅበት ለማድረግ አስቦ ጥር 14 ቀን 2005 ዓ/ም በግምት ከጠዋቱ 2፡50 ሲሆን በን/ላ/ክ/ከ/ቀበላ 12/13 ልዩ ቦታው ሸገር ማህበር ተብል ከሚጠራው አካባቢ ከሚገኘው የመኖሪያ ቤት ውስጥ ሟች መዛገበ ክበበው ወይም አባቷ ባወጣላት ስሟ አለምፀሃይ ብሩክ የተባለችው እድሜዋ 13 አመት የሆነችውን ህፃን አስገድድ መድፈር ሙከራ ወንጀል ከፈፀመባት በኋላ ሟች የፈፀመባትን ድርጊት ለአባትህ እነግርልሃለሁ ስትለው በመጀመሪያ አንገቷን ካነቃት በኋላእጀታው እንጨት በሆነ ቢላዋጨካኝነቱን በሚያሳይ ሁኔታ አንገቷን አርድ በመግደለ ክስ የቀረበበት ሲሆን ሁለተኛው ክስየወንጀል ህግ አንቀፅ 27/620(2(ሀ))የተመለከተውን ተላልፍ በአንደኛው ክስ በተጠቀሰው ጊዚና ቦታ ከግል ተበዲይ ጋር የግብረስጋ ግንኙነት ለመፈፀም አስቦየግል ተበዲይ እድሜዋ 13አመት የሆነችውን ህፃን በእጁ አፍኗት ወለል ላይ ወድቃ ራሷን እንድትስት ካደረጋት በኋላ ለብሳው የነበረው ቱታና ፓንት አንድ ላይ በማውለቅ የግብረስጋ ግንኙነት ሉፈፅምባት ሲል ቆሞ የነበረው ብልቱ በመቀዛቀዘ ፣አመልካች በቀኝ እጁ ጣት ብልቷን በመነካካት የግብረስጋ ግንኙነት ለመፈፀም የሞከረ በመሆኑ 18 አመት ባልሞላት ህፃን ላይ አስገድድ መድፈር ሙከራ ፈፅሟል በሚል ክስ ቀርቦበታል። ሶስተኛው ክስ የወንጀል ህግ አንቀፅ 654 የተመለከተው በመተላለፍ በአንደኛው ክስ በተገለፀው ጊዚና ስፍራ የአጉቱ ልጅ ለሆነችውየግል ተበዲይ ጋር የግብረስጋ ግንኙነት ለማድረግ መሞከርወንጀል ተከሷል በማለት ክስ አቅርቧል።
አመልካች በዓቃቤ ሕግ የቀረበበትን ሶስት ክሶች በጠበቃው እየታገዖ ተቃውሞ አቅርቦበብይን ከታለፈ በኋላ ስለድርጊቱ ሲጠየቅ ድርጊቱን እንደፈፀመ አምኖ ድርጊቱን ሲፈፅም ራሴን ስቼ ስለነበር ጥፊተኛ አይደለሁም በማለት በመከራከሩ ማስረጃዎች ቀረበው ከተሰሙ በኋላ ሶስተኛው ክስ በተመለከተአመልካችና የግል ተበዲይ (ሟች) የስጋ ዛምድና ያላቸው ስለመሆኑ ዓ/ህግ አላስረዲም በማለት አመልካች በአንደኛና ሁለተኛው ክሶች ፍርድቤቱ እንዱከላከለ ትእዙዛ ሰጥቷል።መከለከያ ምስክር አቅርቦም አሰምቷል።ፍ/ቤቱ የተከሳሽ መከላከያ ማስረጃ የዓ/ቃቤ ሕግ ክስና ማስረጃ ማስተባበል ያለቻለ በመሆናቸው አመልካች በተከሰሰበት ሁለቱም የሕግ አንቀፆች ሥር ጥፊተኛ ተብልዋል። በቅጣት ረገድም የግራ ቀኙ የቅጣት አስተያየት እና የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 መሰረት በማድረግ የወንጀለ ደረጃ እና መነሻ ቅጣት እርከን በመለየት ተከሳሹ ሁለት የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች ቀርቦበት፣ሁለት ቅጣት ማቅለያ ምክንያት የተያዘለት በመሆኑ፣ ምክንቶቹ እርስበርሳቸው የሚዋዋጡ በመሆኑ ከተያዖው መነሻ ቅጣት ከፍ ወይም ዛቅ የሚልበት ምክንያት አልተገኘም በማለት አመልካችን በእድሚ ልክ ፅኑ እስራት እንዱቀጣ ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች ይህን ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ ቅሬታው ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረበ ቢሆንም ቅሬታው ባለመቀበል ሰርዜታል። የሰበር አቤቱታ የቀረበው የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ለዘህ ሰበር ችልት ያቀረበው ቅሬታ መሰረታዊ ይዖት ወንጀለ የተፈፀው በነበረኝ የመንፈስ ጭንቀት በድንገተኛ አጋጣሚ አእምሮየን ስቼ እያለሁ የተፈፀመ እንጂ ቂም በቀልበመያዛ ወይም ወንጀል ለመፈፀም አስቤና ተዖጋጅቼ በጨካኝነት የፈፀምኩት ባለመሆኑ ዓ/ህግ ክስ ሲያቀርብ ተገድጄ በሰጠሁት እምነት ቃል ተመስርቶ እንጂ በልላ ማስረጃ የተደገፈ ባለመሆኑ የተጠቀሰብኝ የህግ አንቀፅና የወንጀል ዛርዛሩ ተጣጥሞ ክሱ በወንጀል ህግ አንቀፅ 540(1)ማቅረብ ነበረበት። ወንጀለ በተፈፀመበት ጊዚ የነበረውእድሜዬ 16 አመት እንጂ 19 አመት አልነበረም።የወንጀል ድርጊቱን ከመፈፀሜ በፉት የመንፈስ ጭንቀት በፈጠረብኝ ምክንያት የአእምሮ ችግር ያለብኝ መሆኑ በስርፍርድ ቤት አመልክቼ ሳይታይ ታልፍየተሰጠው ውሳኔ ነው በማለት እንዱታረምለት ጠይቀዋል። ተጠሪ በበኩለ በሰጠው መልስ አመልካች የአእምሮ በሽተኛ መሆኑ ያቀረበው ማስረጃ የለም ። አመልካች ድርጊቱ በተፈፀመበት ጊዚ እድሜው 19 አመት ስለመሆኑ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የቀረበው ማስረጃ ተረጋግጧል። ቅጣት በተመለከተ የቅጣት መነሻው እርከን 39 ከተያዖ በኋላ በማንዋለ መሰረት ለእያንዲንደ የቅጣት ማቅለያ ሶስት እርከን ቢቀነስ ተቃውሞ የለንም በማለት መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዖት ከላይ የተመከለተው ሲሆን እኛም በክርክሩ እልባት ማግኘት የሚገባው፡-
በአመልካቹ ላይ የተሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ የሚነቀፍበት ሕጋዊ ምክንያት አለ ወይስ የለም?
በአመልካች ላይ በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት አለበት? ወይስ የለበትም?
የሚለ ነጥቦች መሆናቸውን በመገንዖብ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ከእነዘሁ ነጥቦች አንፃር መርምረናል።
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ፡- አመልካች የእምነት ክደት ቃል ሲጠየቅድርጊቱን እንደፈፀመ አምኖ ድርጊቱን ሲፈፅም ራሴን ስቼ ስለነበር ጥፊተኛ አይደለሁም በማለት ቃለን ያስመዖገበ ቢሆንም በወቅቱ በስር ተከሳሽ የሚያቋቋም ነው ተብል ጥፊተኛ የተባለበት በቀረቡት የዓ/ህግ ማስረጃ አመልካች ሟችን በግፍ የገደላት ስለመሆኑ እንዱሁም አስገድድ ለመድፈር የሞከረ ስለመሆኑ፣የአመልካች እድሜ በሚመለከትምየቀረበው የሃኪም ማስረጃ ወንጀለ በተፈፀመበት ጊዚ አመልካች እድሜ 19 አመት የነበረ ስለመሆኑ፣በወቅቱ የአእምሮ ችግርነበረኝ በማለት የተከራከረ ቢሆንም ወንጀለ ሲፈፅም የአእምሮ ችግር የነበረበት ስለመሆኑ በህግ አግባብ ተደግፍ የቀረበ ምንም አይነት ማስረጃ አለመኖሩ ተረጋግጦና የአመልካች የመከላከያ ማስረጃዎችአመልካች ድርጊቱን ስላለመፈፀሙየምስክሮቹ ቃል ያረጋገጣል ሉያስብል የሚችል አለመሆኑን ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዖን ስልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች የተረጋገጠ ጉዲይ ነው።
እንግዱህ የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ድርጊቱን ፈፀመ በማለት ድምዲሜ የደረሱትየአመልካች ድርጊቱን ስለመፈፀሙ የአቃቤሕግ ምስክሮች በሚገባ ተረጋግጧል፣አመልካች በመከላከያ ማስረጃው አልተደገፈም በሚል ምክንያት ነው።አመልካች ከሚከራከርባቸው ነጥቦች ውስጥ የአመልካችን የድርጊት ፈጻሚነት በተገቢው መንገድ አቃቤ ሕግ በማስረጃ ያለማስደገፈንና የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን አመልካች በመከላከያ ምስክሮች የማስተባበላቸው ሁኔታን የሚመለከቱ ነጥቦች የሚገኙ ሲሆን የበታች ፍርድ ቤቶች በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 141 ስር የተመለከተውን የማስረጃ ምዖና መርህ ተከትለው አመልካችን ጥፊተኛ ያደረጉ ስለመሆኑ የክርክሩ ሂደት የሚያሳየን ሁኖ አግኝተነዋል።በመሆኑም ከዘሁ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መገንዖብ የሚቻለው አመልካች ጥፊተኛ የተባለው በጉዲዩ ላይ የቀረቡት ማስረጃዎቸ ተመዛነው መሆኑን ነው።እንደሚታወቀው ይህ ሰበር ሰሚ ችልት አንድ የመጨረሻ ፍርድ ያገኘን ጉዲይ ማረም የሚችለው በውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት መኖሩ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ተመልክቷል።ከእነዘህ ድንጋጌዎች ይዖትና መንፈስ መገንዖብ የሚቻለው ደግሞ ይህ ሰበር ችልት ፍሬ ነገርን የማጣራት ወይም ማስረጃን የመመዖን ስልጣን የላለው መሆኑን ነው።በተያዖው ጉዲይም አመልካች አጥብቆየሚከራከርባቸው ነጥቦች የመሰረታዊ ሕግ ስህተት መመዖኛን መሰረት ያደረጉ ሳይሆን የፍሬ ነገርንና የማስረጃ ምዖናን መሰረት ያደረጉ በመሆናቸው በዘህ ችልት ሉታዩ የሚችለ ሁነው አላገኘናቸውም።
በመሆኑም አመልካች የአቃቤ ሕግማስረጃዎች በመከላከያ ማሰረጃቸው ባላስተባበለበት ሁኔታ ወንጀል ለመፈፀሜ አልተረጋገጠም በማለት የሚያቀርበው ቅሬታና ክርክር የሕግ መሰረት ያለው ሁኖ አልተገኘም።አመልካች ለድርጊቱ ኃላፉነት አለበት ተብል የተወሰነው ወንጀለ መሰራቱ ወይም መፈጸሙና ተሰራ ወይም ተፈጸመ የተባለው ወንጀል ደግሞ በአመልካች መፈጸሙ በበቂና በአሳማኝ ሁኔታ ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዖን ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች በተረጋገጠበት ሁኔታ በመሆኑና ይህም በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 23(4)፣27(1(ሀ)፣620(2(ሀ))፣58 እና 539(1(ሐ)) ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ይዖትና መንፈስ የሚያሟላ በመሆኑ በዘህ ረገድ የቀረበውን ክርክር የምንቀበለው ሁኖ አላገኘነውም።
ሁለተኛው ነጥብ፡- ቅጣትን መሰረት አድርጎ ወደቀረበውና በአቢይ ጭብጥነት ወደ ተያዖው ጉዲይ ስንመለስም የአመልካች መሰረታዊ ክርክር የበታች ፍርድ ቤቶች ያስተላለፈት የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ቅጣት ውሳኔ የቅጣት አወሣሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 ያስቀመጣቸውን መርሆዎች ያላገናዖበ ነው የሚል ነው። የስር ፍ/ቤት በአመልካች ላይ ቅጣት ሲወስኑ አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት ሁለት ድንጋጌዎች ውስጥ ለወንጀል ህግ ዓንቀፅ 539(1(ሐ))ከባድ የግፍ መግደል ወንጀል የእድሜልክ ፅኑ እስራት በመውሰድ ፣ ለሁለተኛው ክስ አስገድድ መድፈር ወንጀል ሙከራ በ15 አመት ፅኑ እስራት የመነሻ ቅጣት እንዱቀጣ ከወሰነ በኋላ በተከሳሽ ላይ ሁለቱም ክሶች የተወሰነበት ቅጣት በወንጀል ህግ አንቀፅ 184(1(ለ)) ሲደመሩ በህጉ ከተወሰነው ከፍተኛ ቅጣት የሚበልጥ ሆኖ ስላገኘው በአንደኛው ክስ የተወሰነው እድሜ ልክ ፅኑ እስራት የሚጠቃለል በመሆኑ ለሁለቱም የህግ ድንጋጌዎች ይህንኑ መነሻ ቅጣት መወሰኑ መዛገቡ ያመለክታል።
ፍርድ ቤቱ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት ቅጣት የወሰነ መሆኑ በመግለፅ የመጨረሻ ቅጣት ሲያስቀምጥም በከሳሽ ዓ/ህግ በኩል የቀረበ ሁለት ቅጣት ማክበጃዎች እንዱሁም በአመልካች በኩል የቀረበና ፍርድ ቤቱ የተቀበላቸው ሁለት የቅጣት ማቅለያዎች እንደተቀበለ በመግለፅ የእድሜ ልክ ፅኑ እስራትአመልካች እንዱቀጣውሳኔ ሰጥቷል።ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አመልካች ያቀረበው ይግባኝ ሲያፀና የስር ፍርድ ቤት ቅጣቱን ከመመሪያው በመውጣት መወሰን የነበረበት መሆኑ በመግለፅ ያፀና መሆኑ ከቀረበው የመዛገብ ግልባጭ ለመረዲት ችለናል።
በመሰረቱ የወንጀል ህግ አንቀጽ 187 ድንጋጌ የሚወሰነው ቅጣት ከወንጀል ሕጉ አላማና ግብ ጋር በተጣጣመ መልኩ የጥፊቱን ከባድነት በማመዙዖን በድንጋጌዉ ከተወሰነዉ የቅጣት ጣራ ሳያልፍ ቅጣት ሉወስን እንደሚገባ ተደንግጓል።እንዱሁም መመሪያው በወንጀል ሕጉ ስለቅጣት አወሳሰን ከተደገጉት ድንጋጌዎች ጋር ተጣጥሞ መተርጎም እንደሚገባው በአንቀጽ 4(9) ስር ተመልክቷል። የኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፖብሉክ የወንጀል ህግ የአገሪቱን የወንጀል ህግ ግብ በአዋጅ ቁጥር 414/1996 አንቀጽ 1 ስር ሲደነግግ ‛የወንጀል ህግ ግብ ወንጀል እንዲይፈፀም መከላከል ሲሆን ይህንን የሚያደርገው ስለወንጀልችና ስለቅጣታቸው በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት፣ ማስጠንቀቂያነቱ በቂ ባልሆነበት ጊዚ ወንጀል አድራጊዎቹ ተቀጥተው ላላ ወንጀል ከመፈፀም እንዱቆጠቡና ለላልች ማስተማሪያ እንዱሆኑ ወይም እንዱታረሙ በማድረግ ወይም ተጨማሪ ወንጀልች እንዲይፈፀሙ እርምጃዎች እንዱወሰደባቸው በማድረግ ነው“ በማለት ያስቀምጣል። ህጉ በአንቀጽ 87 ላይ ቅጣቶችና የጥንቃቄ እርምጃዎች ህጉ ሉደርስበት ያሰበውን ዓላማ ለማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ በህጉ መንፈስ መሰረት መፈፀም እንዲለባቸው በመርህ ደረጃ ይደነግጋል። የወንጀል ህጉ አንቀጽ 88 ሲታይም የቅጣቶች እና የጥንቃቄ እርምጃዎች አወሣሰንን በተመለከተ ዖርዖር ያለ ንዐስ ድንጋጌዎችን አካቶ ይዝል።
በዘህ አንቀጽ ስር ያለ ንዐስ አንቀጾች የሚያሣዩት ፍርድ ቤቱ ቅጣቶችንና የጥንቃቄ እርምጃዎችን የሚወሰነው የወንጀል ህጉን ጠቅላላ ክፍል ድንጋጌዎችን እንዱሁም ስለወንጀልችና ስለቅጣታቸው የሚደነግጉትን የልዩ ክፍለ ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ መሆኑን፣ ቅጣት ሉወሰን የሚገባው የወንጀል አድራጊውን ግላዊ የአደገኛነት መጠን ያለፈ የህይወት ታሪኩን ወንጀል ለማድረግ ያነሣሡትን ምክንያቶችና የአሣቡን ዓላማ የግል ኑሮውን ሁኔታ፣ የትምህርቱን ደረጃ፣ እንዱሁም የወንጀለን ከባድነትና የአፈፃፀሙን ሁኔታዎች በማመዙዖን መሆኑን፣ የወንጀል ህግ ልዩ ክፍል ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ፍርድ ቤቱ እጅግ ቀላል ከሆነው ቅጣት አንስቶ እስከ ከባደ ድረስ ያለውን በጥንቃቄ በመመርመር ለእያንዲንደ ጉዲይ ተገቢ የሆነውን ቅጣት እንደሚወስን የቅጣት አወሳሳን ደንቡ በግልፅ ያሳያል።ከላይ እንደተገለጸው ቅጣት የሚወሰነው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 88(2) ስር የተመለከቱትን ሁኔታዎችን ግንዙቤ ውስጥ በማስገባት ነው።
የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 ደረጃ ላልወጣላቸው የወንጀል ድንጋጌዎች ደረጃ የሚወጣበትን አግባብ በመመሪያው በአንቀጽ 13 ከማስቀመጡ በተጨማሪ በ አንቀጽ 21/1/ መሰረት የወንጀል አፈጻጸሙ ሆነ ባህሪዉ በቅጣት አወሳሰን መመሪያዉ መሰረት ለመወሰን የማያስችል ሆኖ ሲገኝ ወይም ቅጣቱ ፍትሕን የሚያዙባ ነዉ ብል ፍ/ቤቱ ካመነ መመሪያዉን ተግባራዊ ለማድረግ ያልቻለበትን ምክንያት በዛርዛር በማስቀመጥ በመመሪያዉ ላይ ከተቀመጠዉ በተለየ መልኩ ቅጣት ሉወስን ይችላል በማለት አስቀምጧል። ወደተያዖው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች በስር ፍርድ ቤት ጥፊተኛ የተባለበት ሁለት የህግ ድንጋጌዎች ናቸው። እነሱም የወንጀል ህግ ዓንቀፅ 539(1(ሐ)) ተከሳሽ የራሱ ክፈ ስራ እንዲይገለፅ በማሰብ እድሜዋ 13 አመት የሆነችውን ህፃን አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ አንገትዋን አርድ መግደለ ለዘሁ ወንጀል መነሻ ቅጣቱ እድሜ ልክ ፅኑ እስራት ወይም ሞት ቅጣት መሆኑ፣ የወንጀል ህግ ዓንቀፅ 620(2(ሀ))ደግሞ እድሜዋ አስራ ሶስት አመት በሆናት ህፃን ልጅ ላይ የተፈፀመ በመሆኑ ቅጣቱ ከአምስት አመት እስከ ሃያ አመት ለመድረስ በሚችል ፅኑ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ እነዘህ ሁለት የተለያዩ ወንጀልች የፈፀመው አመልካች ላይ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 መሰረት ቅጣት ለመወሰን በወንጀል ህግ አንቀፅ 184(1(ለ)) መደመር የግድ ይላል።
የስር ፍ/ቤት በአመልካች ላይ ቅጣት ሲወስን አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት ሁለት ድንጋጌዎች ለወንጀል ህግ ዓንቀፅ 539(1(ሐ))ከባድ የግፍ መግደል ወንጀል የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት በመውሰድ ለሁለተኛው ክስ አስገድድ መድፈር ወንጀል ሙከራ በ15 አመት ፅኑ እስራት የመነሻ ቅጣት እንዱቀጣ ከወሰነ በኋላ በተከሳሽ ላይ ሁለቱም ክሶች የተወሰነበት ቅጣት በወንጀል ህግ አንቀፅ 184(1(ለ))ሲደመር በህጉ ከተወሰነው ከፍተኛ ቅጣት የሚበልጥ ሆኖ ስላገኘው በአንደኛው ክስ የተወሰነው እድሜ ልክ ፅኑ እስራት የሚጠቃለል በመሆኑ ለሁለቱም የህግ ድንጋጌዎች ይህንኑ መነሻ ቅጣት ይዝል።በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 መሰረት የቅጣቱን ለማስላት የተያዖው የመነሻቅጣት በመመሪያው አባሪ አንድ ላይእርከን 38 ላይ የሚያርፍ ሲሆን ፍርድ ቤቱ በተቀበላቸው ሁለት ማክበጃ ምክንያቶት ሁለት እርከን ሰለሚጨምር እና መመሪያው አባሪ አንድ እስከ እርከን 39 ብቻ እንጂ ከዘህ በላይ እርከን አርባ አልተቀመጠም።
ስለሆነምአመልካች ጥፊተኛ የተባለበት ሁለት ድንጋጌዎች በወንጀል ህግ አንቀፅ 184(1(ለ)) ሲደመር በህጉ ከተወሰነው ከፍተኛ ቅጣት የሚበልጥ ሆኖ በመገኘቱ ፣ በአንደኛው ክስ የተወሰነው እድሜ ልክ ፅኑ እስራት የተጠቃለለ ከመሆኑ በተጨማሪ ቅጣቱ ሲሰላ በቀረቡት ሁለት የቅጣት ማክበጃ ምክንያቶች በመመሪያው ከተቀመጠው እርከን በላይ ሰለሚሆን ይህንን ጉዲይ የወንጀል አፈጻጸሙ ሆነ ባህሪዉ እንዱሁም ከተፈፀመው ወንጀል ክብደት አንፃር ፍትሃዊ ውሳኔ ለመስጠት በቅጣት አወሳሰን መመሪያዉ መሰረት ለመወሰን የማያስችል በመሆኑ ከላይ በተገለፁት ምክንያቶች መነሻነት የያዛነው ጉዲይ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት ሲወሰን ለተፈፀመው ወንጀል ተመጣጣኝ ቅጣት ለመወሰን ሰለማይቻል፤የሚሰጠው ቅጣትአመልካች የፈፀማቸው ሁለት ከባድ ወንጀልች በመሆናቸው፣ፍትህን ስለሚያዙባእንዱሁም ስለወንጀል ህጉ ግብና አላማ የማያሳካ ስለሚሆን በቅጣት አወሳሰን መመሪያ አንቀጽ 21/1/ መሰረት ከቅጣት አወሳሰን መመሪያው ውጪ ሉወሰን የሚገባ ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ በተገለፀው ምክንያት መነሻነትየስር ፍርድ ቤት የቀረበለት ጉዲይ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት ሉሰላ የማይቻል ሆኖ በሚገኝበት ጊዚ ከቅጣት አወሳሰን መመሪያ ውጪ በመውጣት የቅጣት ውሳኔው መወሰን ሲገባው የሰጠው የቅጣት ውሳኔ በመሆኑ ሉስተካከል የሚገባው ነው ብለናል።ስለሆነም አመልካች ጥፊተኛ ለተባለበትየህግ ድንጋጌዎች፡-የአስገድድ መድፈር ሙከራ ተግባር የተፈፀመው እድሜዋ አስራ ሶስት አመት በሆናት ህፃን ልጅ ላይ በመሆኑ ፣ እንዱሁም አመልካች የራሱ ክፈ ስራ እንዲይገለፅ በማሰብ እድሜዋ 13 አመት የሆነችውን ህፃን አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ አንገትዋንካነቃት በኋላ እጀታው እንጨት በሆነ ቢላ አንገትዋን አርድ መግደለጨካኝነት እና ነውረኝነቱን የሚያሳይ ተግባር ነው። አንድ ሰው በወንጀል ጥፊተኛ ሁኖ ከተገኘ ተገቢውን ቅጣት ማግኘት ያለበት ስለሆነ የሚጣለው ቅጣት የወንጀለን ከባድነትና የአፈፃፀሙን ሁኔታዎች በማመዙዖን መሆኑን የወንጀል ህጉ አላማ የምንረዲው ጉዲይ ነው።አመልካች ባቀረባቸው ሁለት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 አንቀፅ 16(8) መሰረት ለእያንዲንዲቸው ሶስት እርከን ጠቅላላ ስድስት እርከን እንዱቀንስለት ቅሬታ አቅርቧል።ይሁን እንጂ የተፈፀሙት ሁለት ወንጀልች ፤የወንጀል አፈጻጸማቸው ሆነ ባህሪዉ እንዱሁም ከተፈፀመው የወንጀል ክብደት አንፃር ፍትሃዊ ውሳኔ ለመስጠት በቅጣት አወሳሰን መመሪያዉ መሰረት ለመወሰን የማያስችል በመሆኑ ከቅጣት አወሳሰን መመሪያ ውጪ ቅጣቱ እንዱወሰን ድምዲሜ ላይ የተደረሰ ስለሆነ የአመልካች አቤቱታ አልተቀበልነውም። ስለሆነም በቅጣት ማክበጃነትና ማቅለያነት በማስረጃና በሕግ የተደገፈና በችልት ተቀባይነት ያገኙትን ግንዙቤ ዉስጥ በማስገባትና በማመዙዖን ፍትሐዊ ቅጣት ሉወሰን ስለሚገባ የስር ፍርድ ቤት አመልካች ላይ የወሰነው የእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ቅጣት አመልካች እንዱቀጣ መወሰኑን አመልካች ለፈፀማቸው ወንጀልት ተመጣጣኝ ቅጣት ስለሚሆን ላላው ህብረተሰብም የሚያስተምር በመሆኑ በአመልካች ላይ የተወሰነው ቅጣት በውጤት ደረጃ የወንጀል ህጉ መሰረታዊ መርሆዎችን ያልተከተለ ነው ለማለት የሚቻል ሁኖ አልተገኘም። ስለሆነም ፍርድ ቤቶች በተከሳሽ ላይ የሚጣለው ቅጣት የወንጀል አፈጻጸሙ ሆነ ባህሪዉ እንዱሁም ከተፈፀመው ወንጀል ክብደት አንፃር ፍትሃዊ ውሳኔ ለመስጠት በቅጣት አወሳሰን መመሪያዉ መሰረት ለመወሰን የማያስችል ሆኖ በተገኘ ጊዚ በቅጣት አወሳሰን መመሪያው መሰረት ምክንያቱ በማስቀመጥ በመመሪያው ከተቀመጠው በተለየ መልኩ ቅጣት ሉወስኑ ይችላለ።
ሲጠቃለልም በአመልካች ላይ የተሰጠው የጥፊተኝነትና የተጣለው የእድሜልክ ፅኑ እስራት ቅጣት ውሳኔ የወንጀል ሕጉን መሰረታዊ ግብ እንዱሁም የቅጣት አወሳሳን መርሆዎች ከድርጊቱ አፈጻፀም ጋር ያገናዖበ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ውሣኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ግንቦት 24 ቀን 2007 ዓ/ም የሰጠው የጥፊተኝነት ውሳኔ እንዱሁም ሰኔ05ቀን 2007 ዓ/ምየሰጠውየቅጣት ውሳኔ ፣ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝሰሚ ችልት በመ/ ታህሳስ 13 ቀን 2008 ዓ.ም የጸናው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በወ/መ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ 195(2)(ለ-2) መሰረት በአብላጫ ድምፅ ጸንቷል።
አመልካች በእድሜ ልክፅኑ እስራት እንዱቀጣ ተብል መወሰኑ በአግባቡ ነው ብለናል።
የበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ የፀና መሆኑን እንዱያውቀው ለክፍለ ማረሚያ ቤት ይፃፍ ብለናል።
ይህ ውሳኔ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 አንቀፅ 21(1) መሰረት መመሪው ከሚያስቀምጠው በተለየ ከመመርያው በመውጣት የቅጣት ውሳኔ የተሰጠ በመሆኑ በቅጣት አወሳሰን መመሪያ አንቀፅ 21(2) መሰረት ለሚመለከተው አካል እንዱያውቀው ይደረግ ብለናል።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.