በወንጀል ጉዲይ ፍርድ ከተሰጠ በኋላ ይግባኝ የሚጠይቅ አካል ሉከተላቸው ስለሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎች የወንጀል ሥነ- ሥርዓት ሕግ ቁጥር 187/1
No summary available.
ሰኔ 29 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዲኜ መላኩ ብርሃኑ አመነው ሸምሱ ሲርጋጋ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- የፋዳራል ጠቅላይ ዓቃቤሕግ - ዐ/ሕግ ውብሸት ይመኑ ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የይግባኝ ማስፈቀጃን የሚመለከት ነው። አመልካች በተጠሪዎች ላይ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቦት የነበረውን ክስ በሚመለከት ፍ/ቤቱ 1ኛ ተጠሪን ከ2ኛ ክስ፤ 2ኛ ተጠሪን ከ2ኛ እና ከ6ኛ ክስ በወ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 141 መሰረት በነጻ እንዱሰናበቱ በማለት ሐምል 14 ቀን 2006 ዓ.ም ብይን ሰጥቷል። በልላ በኩል በመዛገቡ ላይ የቀረቡትን ላልች ክሶች በተመለከተ ክርክሩ ቀጥል ታሕሳስ 13 ቀን 2007 ዓ.ም ፍርድ ሰጥቷል። አመልካች የሥር ፍ/ቤት ሐምል 14 ቀን 2006 ዓ.ም በሰጠው ብይን እና በዋናው ጉዲይ ላይ በሰጠው ፍርድ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ጥር 19 ቀን 2007 ዓ.ም ይግባኝ አቅርቧል። ይግባኙ የቀረበለት ፍ/ቤት የሥር ፍ/ቤት ሐምል 14 ቀን 2006 ዓ.ም ብይን ከሰጠ በኋላ አመልካች ይግባኝ ለማቅረብ እንዱችል ሐምል 25 ቀን 2006 ዓ.ም በተጻፈ አቤቱታ ግልባጭ እንዱሰጠው የጠየቀ ሲሆን ለተጠሪዎች የብይኑ ግልባጭ የተሰጣቸው ሐምል 17 ቀን 2006 ዓ.ም በመሆኑ አመልካች የመዛገብ ግልባጭ የተሰጠን ታሕሳስ 22 ቀን 2007 ዓ.ም ነው በማለት ያቀረበው ምክንያት የሚታመን አይደለም፤ አመልካች ሐምል 14 ቀን 2006 ዓ.ም በተሰጠው ብይን ላይ ጊዚው ሳያልፍ የይግባኝ ቅሬታ ማቅረብ ሲገባው ያለበቂ ምክንያት ዖግይቶ ጥር 19 ቀን 2007 ዓ.ም ይግባኙን ያቀረበ በመሆኑ አመልካች በተጠሪዎች ላይ ሐምል 14 ቀን 2006 ዓ.ም በተሰጠው ብይን ላይ ያቀረበው ይግባኝ ጊዚው ያለፈበት ነው በማለት ውድቅ አድርጎታል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህን ውሳኔ በመቃወም ነው።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዖትም፡- የሥር ፍ/ቤት ሐምል 14 ቀን 2006 ዓ.ም የሰጠው ብይን እና በመዛገቡ የተደረገው ሙለ ክርክር ግልባጭ የተሰጠን ታሕሳስ 22 ቀን 2006 ዓ.ም ነው፤ በዘሁ መሰረት የይግባኝ ቅሬታችንን አዖጋጅተን ጥር 15 ቀን 2007 ዓ.ም ባቀረብንበት ሁኔታ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የብይኑ ግልባጭ ለተጠሪዎች የደረሰው ሐምል 17 ቀን 2006 ዓ.ም በመሆኑ አመልካች ያቀረበው ምክንያት የሚታመን አይደለም በማለት አመልካች ሐምል 14 ቀን 2006 ዓ.ም በተሰጠው ብይን ላይ ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ ጊዚ ያለፈበት ነው በማለት የሰጠው ብይን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል የሚል ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በዘህ ችልት መታየት ያለበት ሆኖ ስለተገኘ ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎ ግራቀኙ በጽሐፍ እንዱከረከሩ ተደርጓል።
የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተገለጸው ነው። እኛም የግራቀኙን ክርክር ለጉዲዩ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምረነዋል።
የወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 187/1 ድንጋጌ ይግባኝ ማለቱን ለማስታወቅ የሚጽፈውን ማመልከቻ ይግባኝ ባዩ ወይም ጠበቃው ይግባኝ የሚልበት ፍርድ በተሰጠ በአሥራ አምሥት ቀን ውስጥ ማቅረብ አለበት፤ ይግባኝ ማለቱን ለማስታወቅ የጻፈው ማመልከቻ ለፍርድ ቤት መዛገብ ሹም ሲደርሰው ይግባኝ የተባለበትን ፍርድ አስገልብጦ ለይግባኝ ባዩ ወይም ለጠበቃው ይሰጣል፤
ይግባኝ ባዩ በእሥር ቤት ያለ እንደሆነ ይግባኝ የተባለበትን ፍርድ ግልባጭ የፍርድ ቤት መዛገብ ሹም ለይግባኝ ባይ እንዱሰጥ ለወህኒ ቤቱ ሹም ይልካል፤ ፍርደ ተገልብጦ ያለቀበትን ቀን እና ኋላም ለይግባኝ ባዩ ወይም ለጠበቃው ወይም ለወህኒ ቤቱ ሹም የደረሰበትን ቀን የፍርድ ቤት መዛገብ ሹም በፊርማው ያረጋግጣል በማለት ይደነግጋል። የዘሁ ሕግ ንኡስ ቁጥር 2 ድንጋጌ ይግባኝ ማለት የሚፈልገው ወገን ይግባኙን የፍርደ ግልባጭ በደረሰው በ30 ቀን ውስጥ ፍርደን ለሰጠው ፍ/ቤት መዛገብ ቤት ማቅረብ እንዲለበት ይደረግጋል። ከድንጋጌዎቹ ይዖት መገንዖብ የሚቻለው ይግባኝ መጠየቅ የሚፈልገው ወገን ይግባኝ የሚልበት ፍርድ በተሰጠ በአሥራ አምሥት ቀን ውስጥ ይግባኝ የሚጠይቅ መሆኑን በመግለጽ ማመልከቻ ማቅረብ ያለበት መሆኑን፤ የፍርድ ቤቱ መዛገብ ሹም ይግባኝ መጠየቅ የሚፈልገው ወገን ያቀረበው ማመልከቻ ሲደርሰው ይግባኝ የተባለበትን ፍርድ አስገልብጦ ይግባኝ መጠየቅ ለሚፈልገው ወገን ማድረስ ያለበት መሆኑን፤ ይግባኝ ማለት የሚፈልገው ወገን የፍርደ ግልባጭ በደረሰው በ30 ቀን ውስጥ ይግባኙን ማቅረብ ያለበት መሆኑን ነው።
በተያዖው ጉዲይ አመልካች የሥር ፍ/ቤት ሐምል 14 ቀን 2006 ዓ.ም በተሰጠው ብይን ላይ ይግባኝ ማቅረብ እንደሚፈልግ በመግለጽ በሕጉ የተገለጸው የአሥራ አምሥት ቀን ጊዚ ሳያልፍ ሐምል 25 ቀን 2006 ዓ.ም ይግባኝ መጠየቅ እንደሚፈልግ ገልጾ ግልባጭ የጠየቀ ለመሆኑ በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ፍሬነገር ነው። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሬጅስትራር ጽ/ቤት መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም በተጻፈ ደብዲቤ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሐምል 14 ቀን 2006 ዓ.ም የተሰጠው ብይን ለአመልካች የደረሰው በመዛገቡ ላይ ጠቅላላ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ታሕሳስ 22 ቀን 2007 ዓ.ም መሆኑን አረጋግጧል። የሥር ፍ/ቤት አመልካች ሐምል 14 ቀን 2006 ዓ.ም በተሰጠው ብይን ላይ ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ ጊዚው ያለፈበት ነው ከሚል መደሚደሚያ ላይ ሉደርስ የቻለው ተጠሪዎች የብይን ግልባጭ የደረሳቸው ሐምል 17 ቀን 2006 ዓ.ም በመሆኑ አመልካች የብይኑ ግልባጭ የተሰጠኝ ታሕሳስ 22 ቀን 2007 ዓ.ም ነው በማለት ያቀረበው ክርክር የሚታመን አይደለም በማለት ነው። አመልካች በሕጉ በተቀመጠው የጊዚ ገደብ ውስጥ ይግባኝ መጠየቅ እንደሚፈልግ በመግለጽ ግልባጭ እንዱሰጠው በጠየቀበት ሁኔታ የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሬጅስትራር ጽ/ቤት ሐምል 14 ቀን 2006 ዓ.ም የተሰጠው ብይን ለአመልካች የደረሰው በመዛገቡ ላይ ጠቅላላ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ ታሕሳስ 22 ቀን 2007 ዓ.ም ነው በማለት ባረጋገጠበት ሁኔታ፤ አመልካች የክርክሩን ሙለ ይዖት የሚያሳይ የመዛገብ ግልባጭ ሳይደርሰው ይግባኝ መጠየቅ በማይችልበት ሁኔታ፤ አመልካች ግልባጭ እንዱሰጠው በጠየቀበት ቀን እና የመዛገቡ ግልባጭ ለአመልካች በደረሰበት ቀን መካከል ያለት የባከኑ ቀናት በአመልካች ጥፊት ምክንያት ባልባከኑበት ሁኔታ፤ አመልካች የመዛገቡ ግልባጭ ታሕሳስ 22 ቀን 2007 ዓ.ም ደርሶት በሕጉ የተቀመጠው የሰላሳ ቀን የጊዚ ገደብ ሳያልፍ ጥር 19 ቀን 2007 ዓ.ም ይግባኙን አዖጋጅቶ ባቀረበበት ሁኔታ የሥር ፍ/ቤት የብይኑ ግልባጭ ለተጠሪዎች የደረሰው ሐምል 17 ቀን 2006 ዓ.ም ነው በሚል ምክንያት አመልካች ሐምል 14 ቀን 2006 ዓ.ም በተሰጠው ብይን ላይ ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ ጊዚው ያለፈበት ነው በማለት የሰጠው ብይን በወንጀል ሥነ-ሥርዓት ሕጉ የይግባኝ አቀራረብን አስመልክቶ የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ያላገናዖበ እና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ሥሕተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።‛በዘህም ምክንያት ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ. ሕዲር 05 ቀን 2009 ዓ.ም አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሐምል 14 ቀን 2006 ዓ.ም በተጠሪዎች ላይ በሰጠው ብይን ላይ ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ ጊዚው ያለፈበት ነው በማለት የሰጠው ብይን ተሽሯል።
አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ሐምል 14 ቀን 2006 ዓ.ም በተጠሪዎች ላይ በሰጠው ብይን ላይ ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ ጊዚው ያላላፈበት ነው በማለት በወንጀል ሥነ-ሥርዓት 191/4 መሰረት ወስነናል።
አመልካች ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ ጊዚው ያላላፈበት በመሆኑ ይህ ውሳኔ ከደረሰው ቀን ጀምሮ በሚቆጠር አሥር ቀናት ውስጥ ይግባኙን ለሚመለከተው ፍ/ቤት ያቅርብ ብለናል።
መዛገበ ተዖግቷል። ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.