No summary available.
ግንቦት 23 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው በእውቀት በላይ እንዲሻው አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- የአ.ብ.ክ.መ. ፍትህ ቢሮ ዐቃቤ ህግ - ዲግማዊ አገኘሁ ተጠሪዎች፡- 1ኛ አቶ እሸቱ ለላ ንጉሴ - ቀርበዋል።
2ኛ አቶ ደግዋለ ልክነህ ደርሰህ 3ኛ ወ/ሮ ጥሩዬ ደግዋለ አልቀረቡም 4ኛ ወ/ሮ ይሳለሙ ደመቀ መዛገቡ የተቀጠረው መርምሮ ፍርድ ለመስጠት ነው። በመሆኑም መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች የእነማይ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/5 በቀን 02/04/07 ዓ.ም የሰጠውን ፍርድና የቅጣት ውሳኔ የምስራቅ ጏጃም አስተዲደር ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/9 በቀን 21/07/2007 ዓ.ም በመሻሩ እና የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ 02-13131 በቀን ህዲር 29 ቀን 2009 ዓ.ም ይህንኑ በማጽናቱ እና የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት መሰረታዊ የህግ ግድፈት አልተፈፀመም ሲል በሰጠው ትእዙዛ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለታቸው ነው።
ጉዲዩ የወንጀል ክስ እንዱሻሻል የተሰጠ ትእዙዛ ውጤትን ይመለከታል። አመልካች በተጠሪዎች ላይ በስር ፍ/ቤት ባቀረበው ክስ 1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የወንጀል ህግ ቁጥር 32/1/ /ሀ/ 555 /ለ/ የተመለከተውን ተላልፈው በልላ ሰው አካል ላይ ጉዲት ለማድረስ አስበው ነሐሴ 9 ቀን 2006 ዓ.ም በ12፡00 ሰዓት የግል ተበዲይ ላቃቸው ሞገስን ብቸና ከተማ 01 ቀበላ ኪዲነምህረት ቤተክርስቲያን 1ኛ ተከሳሽ በጅንፊ ሽመል እየደጋገመ ሲመታው 2ኛ ተከሳሽ በድንጋይ መሐል ራሱን 3ኛ ተከሳሽ ድንጋይ በመወርወር ግንባሩን በመምታታቸው በአካል ላይ ጉዲት አድርሰዋል 4ኛ ተከሳሽ የወ/ህ/ቁ 27/1/ 556/2/ /ሀ/ የተመለከተውን ተላልፈው በተመሳሳይ ቀንና ቦታ ከ1-3 ያለት ሲመቱት እሷ በድንጋይ ወርውራ የሳተችው በመሆኑ በአካል ላይ ጉዲት ለማድረሰ ሞክራለች የሚል ሲሆን ተጠሪዎች በክሱ ላይ በልላ መዛገብ ታይቶ የተወሰነ ስለመሆኑ መቃወሚያ ያቀረቡ ቢሆንም ፍ/ቤቱ በ01/03/2007 ብይን ተሰጥቶበታል በማለት አልፍ የግል ተበዲይን ጨምሮ የአመልካችን ሁለት ምስክሮች እና የሰነድ ማስረጃዎች ከሰማ በኋላ 1ኛ ተጠሪ የወ/ህ/ቁ 556/2//ሀ/፣ 2ኛ እና 3ኛ ተጠሪዎች የወ/ሕ/ቁ. 555/ለ/ እና 4ኛ ተጠሪ በቀረበበት ክስ እንዱከላከለ ብይን የሰጠ ቢሆንም የተጠሪዎች ጠበቃ ባለመቅረቡ ማስረጃዎቻቸውንም በተከታታይ ቀጠሮዎች አለማቅረባቸውንና ራሳቸውም መሆናቸውን በመግለጽ ጠበቃቸው ሲቀርብ እንዱሰሙ እንዱታዖዛላቸው ተለዋጭ ቀጠሮ የጠየቁ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ህዲር 19፣ ህዲር 29 እና ታህሳስ 1/2007 ተሟልተው አልቀረቡም ጠበቃቸውም አልቀረበም በማለት የመከላከያ ማስረጃ የማሰማት መብታቸውን በማለፍ ተከላከለ በማለት በሰጠው ብይን መሰረት 1ኛ ተጠሪ የወንጀል ህግ ቁጥር 556/2/ /ሀ/ ጥፊተኛ በማለት 4ወር ቀላል እስራት፣ 2ኛ ተጠሪ እና 3ኛ ተጠሪ የወንጀል ህግ ቁጥር 555 /ለ/ ጥፊተኛ በማለት 2 ዓመት ከ4 ወር እና 2ዓመት ከ3ወር እንደቅደም ተከተላቸው እንዱሁም 4ኛ ተጠሪን በ1 ወር ቀላል አስራት እንዱቀጡ በማለት ወስኗል።
ተጠሪዎች በዘህ ፍርድ እና የቅጣት ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለምስራቅ ጏጃም አስተዲደር ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም አመልካች የወ/ህ/ቁ 556/2/ /ሀ/ ወደ 555 /ለ/ ለማሻሻል ያቀረበው በብይን ውድቅ ተደርጏ ሳለ በልላ መዛገብ ክስ ማቅረቡን፣ ይህንኑ መሰረት አድርጎ ተጠሪዎች በቀረበባቸው ክስ ተከላከለ የተባለበትን አግባብ እና የመከላከያ ማስረጃ ሳያሰሙ የተሰጠው ፍርድ እንዱሻርልን በማለት ያቀረቡትን ቅሬታ ፍርድ ቤቱ በመመርመር አስቀድሞ ክስ ቀርቦበት ነበር የተባለውን የእነማይ ወረዲ ፍርድ ቤት መ/8 እንዱቀርብ በማድረግ መርምሮ አመልካች በተጠሪዎች ላይ አስቀድሞ በመ/8 በቀላል አካል ጉዲት ማድረስ ወንጀል ክስ አቅርቦ ምስክር ከተሰማ እና እንዱከላከለ ብይን ከተሰጠ በኋላ አመልካች ክሱን በከባድ የአካል ጉዲት ማድረስ ወንጀል ለማቅረብ አሻሸል እንዱያቀርብ ጠይቆ ፍርድ ቤቱ ምክንያቱን ባለመቀበል ውድቅ በማድረግ የአመልካቾች የመከላከያ ማስረጃ እንዱሰማ ያዖዖ ቢሆንም አመልካች ክሱን አንስቶ በልላ መዛገብ 5 አዱስ ክስ አቅርቧል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት ይህንን ጭብጥ በመመርመር ክስ ማንሳትና ማሻሻል ለአመልካች በህግ የተሰጠው ቢሆንም ክሱን መቀጠል ያለበት ግን በተዖጋው መዛገብ ላይ እንዱቀጥል እንጂ አዱስ ክስ መዛገብ ተከፍቶበት የሚቀርብ አይደለም። የስር ፍ/ቤት የተጠሪዎችን ተቃውሞ ያለፈበት ምክንያት የህግ መሰረት የለውም፣ የተጠሪዎች የመከላከያ ምስክሮች መጥሪያ ደርሷቸው ያልቀረቡና በፖሉስ አማካኝነት እንዱቀርቡ ታዜም ካለመቅረባቸውም በላይ ጠበቃቸው ባለመቅረቡ ተለዋጭ ቀጠሮ ተጠይቆ ከወ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 94 አንፃር ማየት ሲገባው ፍ/ቤቱ የመከላከያ ማስረጃ የማሰማት መብታቸውን ማለፊ ተገቢነት የለውም በማለት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ሽሮ አመልካች በቀድሞው መዛገብ እንዱቀጥል አዝል።
አመልካች በዘህ ፍርድ ቅር በመሰኘት ያቀረበው ይግባኝ የተመለከተው የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ በማጽናቱ መሰረታዊ ስህተተ ተፈጽሟል በማለት ለአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ያቀረቡትን አቤቱታ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
የአመልካች የሰበር አቤቱታ ለዘሀ ችልት የቀረበውም በዘሁ ምክንያት ሲሆን ይዖቱም ዐቃቤ ህግ ከውሳኔ በፉት በማናቸውም ጊዚ ክሱን አሻሽል ለማቅረብ የሚከለክለው ህግ ባለመኖሩ ከቀረበው ማስረጃ አንጻር ተመጣጣኝ ድንጋጌ ጠቅሶ ማቅረቡ ተገቢ ነው በሰበር መ/ ተመላክቷል፡ የወረዲ ዐቃቤ ህግ የህክምና የመጨረሻ ውጤት ሳይጠበቅ ተቀራራቢነት በላለው አነስተኛ ድንጋጌ ክስ ማቅረቡ ፍትህን ስለሚያዙባ ድንጋጌው ተሻሽል ክስ መቅረቡ የተጣሰ ህግ የለም ስለመሆኑም የከፍተኛው ፍ/ቤት ውሳኔ ተሽሮ የወረዲው ይጽናልኝ የሚል ነው። የአመልካች አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪዎች ቀርበው መልስ እንዱሰጡበት በታዖዖው መሰረት 1ኛ እና 2ኛ ተጠሪ መልስ የሰጡ ሲሆን 3ኛ እና 4ኛ መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፎል። የመልሳቸው ይዖትም ዓቃቤ ህግ ክሱን ከውሳኔ በፉት በማንኛውም ጊዚ የማንሳት መብት ቢኖረውም ይህንን መብት ግን ያለአግባብ ሉጠቀምበት አይገባም፣ በሰበር መ/ በላለበት የተሰጠ ውሳኔን እንጂ ከዘህ ጉዲት ጋር አይያያዛም። ከፍተኛው ፍ/ቤት ወረዲው የሻረው የወንጀል ህግ አንቀጽ 556 ወደ 555 ለምን ተቀየረ በሚል ሳይሆን በተለየ መዛገብ ክስ መቅረቡን መሰረት በማድረግ ነው ስለሆነም የአመልካች አቤቱታ የህግ መሰረት የላለው በመሆኑ ይሻርልኝ የሚል ነው። አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ፍርድ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ መርምረነዋል እንደመረመርነውም በዋናነት ምላሸ የሚሻው የክርክሩ ጭብጥ ዐቃቤ ህግ አመልካች በተጠሪዎች ላይ አቅርቦት የነበረው ክስ የተጠሪዎች የመከላከያ ማስረጃ ከመሰማቱ በፉት ክሱን እንዱያሻሽል የቀረበው አቤቱታ በፍርድ ቤቱ ተቀባይነት በማጣቱ ክሱን ካነሳ በኋላ በልላ መዛገብ ለማሻሻል ባቀረበው ምክንያት ውጤት መሰረት አዱስ ክስ ማቅረብ የሚችልበት አግባብ ከወንጀል ሥነ ሥርዓት ህግ ድንጋጌዎች ዓላማ አንጻር መርምረናል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዖብ የሚቻለው አመልካች በተጠሪዎች ላይ በስር ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/8 የወ/ህ/ቁ 556 ተላልፈው ቀላል የአካል ጉዲት አድረሰዋል በማለትበቀረበው ክስ ማስረጃዎቹን አሰምቶ እንዱከላከለ ብይን ከተሰጠ በኋላ አመልካች ክሱን ለማሻሻል ያቀረበውን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ባለመቀበለ የመከላከያ ምስክሮች ከመሰማቱ በፉት ክሱን በማንሳቱ ፍርድ ቤቱ መዛገቡን ዖግቷል። አመልካች በልላ መዛገብ በስር ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/5 በተጠሪዎች ላይ የወ/ህ/ቁ555 እና 27/1/ /ሀ/ 556 የተመለከተውን ተላልፈዋል በማለት አዱስ ክስ አቅርባል። ተጠሪዎቹ መቃወሚያ ቢያቀርቡም ውድቅ ሆኖ ለዘህ ሰበር አቤቱታ ምክንያት የሆነው ውሳኔ በየደረጃው ባለ ፍርድ ቤት ተሰጥቷል።
በመሰረቱ በተከሳሽ ላይ በቀረበ የወንጀል ክሰ ዋና ስህተት ወይም ያልተጠቀሰ ነገር ሲኖር ይህም ክሱ የቀረበበትን ተከሳሽን የሚያሳስት ወይም ያሳሳተ በመሰለ ጊዚ /የወ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 118/ በክሱ መሰማት ወቅት ፍርድ ከመስጠቱ በፉት በማናቸውም ጊዚ ፍርድ ቤቱ በራሱ ጊዚ ወይም ከተከራካሪ ወገኖች በሚነሳ አስተያየት ቀርቦ የነበረው የወንጀል ክስ እንዱለወጥ ወይም እንዱጨመር ወይም አዱስ ክስ እንዱዖጋጅ ፍርድ ቤቱ ትእዙዛ ለመስጠት እንደሚችል በወ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 119/1/ ተመልክቷል፣፣ ከዘህ ድንጋጌ መረዲት እንደሚቻለው ፍርድ ቤቱ በራሱ ወይም ከተከራካሪ ወገኖች በአንደ በሚያቀርበው ማመልከቻ መሰረት እንደነገሩ ሁኔታ ክሱ እንዱለወጥ እንዱጨመር ወይም አዱስ ክስ እንዱዖጋጅ ትእዙዛ የሚሰጥ ስለመሆኑ ነው። ይህ ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ትእዙዛ የማሻሻል ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ የተሰጠ ከሆነ ደግሞ የመጨረሻ በመሆኑ ይግባኝ ልባልበት የሚገባ ስለመሆኑ በሰበር መ/ አስገዲጅ ትርጉም ተሰጥቶበታል።
በዘህ በያዛነው ጉዲይ አመልካች በተጠሪዎች ላይ በቅድሚያ በመ/8 በወረዲው ፍርድ ቤት በቀረበው ክስ ላይ ክሱን ለማሻሻል ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት ሲያጣ አመልካች ይግባኝ በማለት በበላይ ፍርድ ቤት ሉያሳርም አልሞከረም። በይግባኝ በበላይ ፍርድ ከማሳረም የቀረበውን ክስ በወ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ 122/ለ/ መሰረት ክሱን የማንሳት እና ለዘያው ፍርድ ቤት በልላ መዛገብ በመ/5 አዱስ ክስ በማቅረብ ለማሻሻል ለፍርድ ቤቱ አቅርቦ ያጣውን መብት ክሱን በማንሳት አዱስ ክስ በማቅረብ ክርክሩ እንዱቀጥል የሆነ መሆኑን ነው መዛገቡ የሚያስረዲው።
የወንጀል ሥነ ሥርዓት ህግ ዋነኛ ዓላማ የወንጀል ህጉ በተግባር የሚተረጏምበትን ሥርዓት በመዖርጋት በህጉ ላይ የተመለከቱ ወንጀልች ተፈጽመው በሚገኙ ጊዚ እውነት በማውጣት ውጤታማ፣ ቀልጣፊና ፍትሐዊ የወንጀል ፍትህ ሥርዓት እንዱኖር ማስቻል ነው። ከሥነ- ሥርዓት ሕጉ ውጪ በሆነ አካኋን ተመርምሮና ክርክር ተካሂድ የሚሰጥ ፍርድ በህገመንግስታችን አንቀጽ 20 የተረጋገጠውን በተገቢ አጭር ጊዚ ፍትህ የማግኘት መብት ያጓደለ ነው የሚሆነው።
አመልካች ክሱን ለማሻሻልም ሆነ ለማንሳት ብልም በልላ መዛገብ አዱስ ክስ ለመቅረብ ምክንያት የሚያደርገው የወረዲው ዐቃቤ ህግ የህክምና የመጨረሻ ውጤት ሳይቀርብ ክሱን በማቅረቡ በቀላል አካል ጉዲት ክስ የቀረበ ቢሆንም አሁን የህክምና ማስረጃ የደረሰ በመሆኑ ነው ክሴን ላሻሽል የሚል ነው፣ ይህ ሁኔታ አይኖርም ባይባልም መፈጸም ያለበት ግን በሕግ በተዖረጋ ሥርዓት ነው፣ በመሰረታዊነት ያላለቀ ምርመራ ላይ ክስ አይቀርብም.፣ ከወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 40/1/ ዐቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ ክስ ለማቅረብ በቂ ምክንያት መኖሩን ከተረዲ ክስ የሚያቀረብና ከዘህ በፉት ግን ተመሳሳይ ሁኔታዎች እንዲያጋጥሙ በወ/ህ/ሥ/ሥ/ቁ. 38፣ 41 እና ተከታዮቹ መሰረት መፈጸም የሚገባው ነው።
ስለሆነም አመልካች በቅድሚያ ያቀረበው ክስ ላይ ማስረጃዎቹን ካሰማና እንዱከላከለ ታዜ የክሱ መሰማት በቀጠለበት ሂደት ላይያቀረበው ክስ ማሻሻል አቤቱታ ተቀባይነት ሲያጣ ይህንን በህጉ አግባብ በይግባኝ ከማሳረም ክሱን በማንሳት በልላ መዛገብ አዱስ ክስ ማቅረቡ ምክንያቱ ምንም ይሁን ምንም የሥነ-ሥርዓት ህጉን ዓላማ ያልጠበቀ እና የፍርድ ቤቱን ትእዙዛ ያላከበረ በመሆኑ ተገቢውን ፍትህ ሉያሰጥ የሚችል ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም የምስራቅ ጏጃም አስተዲደር ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠውና በበላይ ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ያገኘው ውሳኔ መሰታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ያላገኘነው በመሆኑ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
1/ የእነማይ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/5 በቀን 02/04/07 ዓ.ም የሰጠውን ፍርድ በመሻር የምስራቅ ጏጃም አስተዲደር ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/9 በቀን 21/07/2007 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ እና የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ 02-13131 ህዲር 29 ቀን 2008 ዓ.ም እና አብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት መ/ መጋቢት 5 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጡት ትእዙዛ በወ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 195/ለ/ /2/ መሰረት ፀንቷል።
መዛገቡ ተዖግቷል ።
No topics extracted.