አንድ ተከሳሽ በወንጀል ተጠርጥሮ የጣት አሻራ ሰጥቷል በመባለ ብቻ እንደጥፊተኛ ተቆጥሮ የወንጀል ጥፊት ሪከርድ እንዲለበት ተደርጎ ግምት በመውሰድና እንደ ቅጣት ማቅለያ ሳይያዛ የሚሰጥ ውሳኔ መሰረታዊ የህገ መንግስት መርህን የሚጣረስ ስለመሆኑ የወንጀል ህግ አንቀጽ 82 131705 እነ አብርሃም ሰለሞን (ሦስት ሰዎች) እና የፋዳራል ዓ/ህግ ሚያዘያ 16 ቀን 2009 ዓ.ም 68. በወንጀል ጉዲይ በኤግዘቪትነት የተያዖ ንብረት በፍርድ ውሳኔ የሚያገኘው በወንጀለ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ሲሰጥ ለባለንብረቱ ይመለስ ወይም ለመንግስት ገቢ ይሁን ተብል ሲወሰን ወይም ተገቢውን የህግ ስርዓት ተከትል ሥልጣን ባለው አካል ትዔዙዛ ሲተላለፍ የአርሲ ነገላ ከተማ ፖሉስ ጽ/ቤት እና አቶ ተስፊአለም ገ/ሚካኤል ሚያዘያ 26 ቀን 2009 ዓ.ም. XXIX 69. ተከሳሽ በሚያቀርበው ይግባኝ መነሻነት ቅጣትን በማክበድ መወሰን መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለመሆኑ የወንጀል መ/ስ/ስ/ሕ/ቁጥር 196(2
No summary available.
ሚያዛያ 30 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ብርሃኑ አመነው በእውቀት በላይ እንዲሻው አዲነ ሃይለ ነጋሽ እትመት አሰፊ አመልካች፡- አቶ ጎይትኦም ግደይ - ጠበቃ ወይንሸት ከበደ ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን - አልቀረቡም መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የቀረበዉ አመልካች የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመዛገብ የሰጠዉ የጥፊተኝነት እና የቅጣት ዉሳኔ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ መዛገብ የሥር ፍ/ቤት የሰጠዉ የጥፊተኝነት ዉሳኔ በማጽናት እና የቅጣት ዉሳኔ በማሻሻል የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረበዉን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ለመወሰን ነዉ።በሥር መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ተጠሪ ከሳሽ፣ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክሯል። የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ያቀረበዉ የወንጀል ክስ ነዉ።የክሱ ዛርዛርም ሲታይ ተከሳሽ አዋጅ ቁጥር 622/2001 ዓንቀፅ 91(1) በመተላለፍ በግምት ከምሽቱ 3፡00 ሰአት ከማሉ(ባማኮ) በረራ በማድረግ አዱስ አበባ ቦላ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርስ በአየር መንገደ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ሁለት ላይ ሲደርስ ይዜት የገባውን ሻንጣ የጓዛና የአካላዊ ፍተሻ ማድረግ ፣ማስደረግ ሲገባው ሳያስፈትሽ መንገድ በመቀየር ጉዜውን በአየር መንገደ የቀረጥ ነፃ ሱቅ በማድረግ ዋጋ በሚተመንበት በኩል ሉያመልጥ ሲል በቁጥጥር በመዋለ በያዖው ፍለውሚ ሻንጣ በተደረገበት ፍተሻ ተገቢውን የጉምሩክ ስነስርአት ያልተፈፀመባቸው የቀረጥ ታክስ .52 (ሃያ ሶስት ሺህ አራት መቶ አስራ አንድ ከ 52/100) የሆኑ (አርባ ሰባት ሺህ ስድስት መቶ ) ብር የሆኑ አርቴፉሻል ጥንድ የጀሮ ጌጣጌጦች ይዜ ወደ ሃገር ውስጥ ሲያሥገባ በመያዘ በፈፀመው የኮንትሮባንድ ተግባር ፈጽመዋል በማለት ወንጀል ክስ አቅርቦበታል።
አመልካች በዓቃቤ ሕግ የቀረበበትን ክስ ክደው በመከራከራቸው ማስረጃዎች ቀርበው ከተሰሙ በኃላ እንዱከላከለ ታዖው አመልካች መከላከያ ምስክሮቻቸው አስቀርበው አሰምተዋል ። ፍ/ቤቱ ተከሳሽ ባቀረቡዋቸው የመከላከያ ማስረጃ የዓቃቤ ሕግ ክስና ማስረጃ ማስተባበል ያልቻለ በመሆናቸው በተከሰሰበት የሕግ አንቀጽ ሥር ጥፊተኛ ተብለዋል። በቅጣት ረገድም የግራ ቀኙ የቅጣት አስተያየት እና የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት በማድረግ የወንጀለ ደረጃ እና መነሻ የእስራት እና የገንዖብ ቅጣት እርከን በመለየት ተከሳሽ በሦስት ዓመት ጽኑ እስራት በተጨማሪም 5000(አምስት ሺህ ብር )የገንዖብ መቀጮ እንዱቀጡ ውሳኔ ሰጥቷል።
የሥር ተከሳሽ ይህን ዉሳኔ በመቃወም ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱ ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር በሰጠዉ ዉሳኔ የጥፊተኛነት ዉሳኔ በማጽናት ቅጣትን በተመለከተ በተሻሻለው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት ደረጃና እርከን የወጣለት ስለሆነ በስር ፍ/ቤት ከተያዘት የቅጣት ማቅለያዎች በተጨማሪ ሁለት ማቅለያዎች በመያዛ በስር ፍርድ ቤት ካረፈበት እርከን 17 ሁለት ማቅለያ ምክንያት ሲቀነስ የእስራት ቅጣት እርከን 15 የሚያርፍ ይሆናል ።የገንዖብ መቀጮም ከእርከን 7 ሁለት ማቅለያ ሲቀነስ እርከን 5 ላይ ያርፊል ስለሆነም አመልካች ከዘህ በፉት የታሰረበት ካለ የሚታሰብለት ሆኖ በ2 አመት ከዖጠኝ ወር ፅኑ እስራት እና 7000 (ሰባት ሺህ ብር) የገንዖብ መቀጮ እንዱቀጡ ውሳኔ ሰጥቷል።አሁን የቀረበው ቅሬታ በዘሁ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች ይግባኝ በጠየቁበት ሁኔታ የስር ፍርድ ቤት የተወሰነው የገንዖብ መቀጮ በማሻሻል ከፍ ተደርጎ የመወሰኑ አግባብነት ለመመርመር ሲባል በሰበር ችልት ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ ቀርበው የጽሁፍ ክርክራቸው ተለዋውጠዋል።
የጉዲዩ አመጣጥና የግራ ቀኙ ክርክር ከፍ ሲል የተመለከተው ሲሆን እኛም ከተያዖው ጭብጥ አንፃር ከሕጉ ጋር አገናዛበን መርምረናል ከክርክሩ ሂደት ለመረዲት የተቻለው አመልካች በስር ፍ/ቤት የቀረበባቸው ክስ የወንጀል ህግ ድንጋጌ አዋጅ ቁ/ 622/2001 አንቀጽ 91/1/ በመተላለፍ ነው።
ቅጣትን በተመለከተ አመልካች ሉቀጡ የሚገባው ጥፊተኛ በተባለባቸው የሕግ ድንጋጌዎች መሰረት ነው። አመልካች በተከሰሱበት የኮንትሮባንድ ወንጀል መፈፀማቸው በሚገባ ተረጋግጧል። በአዋጅ ቁጥር 622/2001 አንቀፅ 91(1) ጥፊተኛ የተባለ አጥፉ ሉቀጣ የሚገባው ከአስራ አምስት አመት በማይበልጥ ጽኑ እስራትና እስከ ብር ሃምሳ ሺህ በማይበልጥ መቀጮ ነው።
በመሰረቱ የኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፖብሉክ የወንጀል ህግ የአገሪቱን የወንጀል ህግ ግብ በአዋጅ ቁጥር 414/1996 አንቀጽ 1 ስር ሲደነግግ ‛የወንጀል ህግ ግብ ወንጀል እንዲይፈፀም መከላከል ሲሆን ይህንን የሚያደርገው ስለወንጀልችና ስለቅጣታቸው በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት፣ ማስጠንቀቂያነቱ በቂ ባልሆነበት ጊዚ ወንጀል አድራጊዎቹ ተቀጥተው ላላ ወንጀል ከመፈፀም እንዱቆጠቡና ለላልች ማስተማሪያ እንዱሆኑ ወይም እንዱታረሙ በማድረግ ወይም ተጨማሪ ወንጀልች እንዲይፈፀሙ እርምጃዎች እንዱወሰደባቸው በማድረግ ነው“ በማለት ያስቀምጣል። ህጉ በአንቀጽ 87 ላይ ቅጣቶችና የጥንቃቄ እርምጃዎች ህጉ ሉደርስበት ያሰበውን ዓላማ ለማረጋገጥ በሚቻልበት ሁኔታ በህጉ መንፈስ መሰረት መፈፀም እንዲለባቸው በመርህ ደረጃ ይደነግጋል። ይኸው አንቀጽ ቅጣቶችና የጥንቃቄ እርምጃዎቹ ምን ጊዚም ሰብዓዊ ክብርን በሚጠብቅ መንገድ መፈፀም እንደሚኖርባቸው ያስገነዛባል። የወንጀል ህጉ አንቀጽ 88 ሲታይም የቅጣቶች እና የጥንቃቄ እርምጃዎች አወሣሰንን በተመለከተ ዖርዖር ያለ ንዐስ ድንጋጌዎችን አካቶ ይዝል። በዘህ አንቀጽ ስር ያለ ንዐስ አንቀጾች የሚያሣዩት ፍርድ ቤቱ ቅጣቶችንና የጥንቃቄ እርምጃዎችን የሚወስነው የወንጀል ህጉን ጠቅላላ ክፍል ድንጋጌዎችን እንዱሁም ስለወንጀልችና ስለቅጣታቸው የሚደነግጉትን የልዩ ክፍለ ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ መሆኑን፣ ቅጣት ሉወሰን የሚገባው የወንጀል አድራጊውን ግላዊ የአደገኛነት መጠን ያለፈ የህይወት ታሪኩን ወንጀል ለማድረግ ያነሣሡትን ምክንያቶችና የሀሣቡን ዓላማ የግል ኑሮውን ሁኔታ፣ የትምህርቱን ደረጃ፣ እንዱሁም የወንጀለን ከባድነትና የአፈፃፀሙን ሁኔታዎች በማመዙዖን መሆኑን፣ የወንጀል ህግ ልዩ ክፍል ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ፍርድ ቤቱ እጅግ ቀላል ከሆነው ቅጣት አንስቶ እስከ ከባደ ድረስ ያለውን በጥንቃቄ በመመርመር ለእያንዲንደ ጉዲይ ተገቢ የሆነውን ቅጣት እንደሚወስን የቅጣት አወሳሳን ደንቡ በግልፅ ያሳያል። ከላይ እንደተገለጸው የወንጀል ቅጣት የሚወሰነው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 88(2) ስር የተመለከቱትን ሁኔታዎችን ግንዙቤ ውስጥ በማስገባት ነው።ይህ ችልትም እነዘህ ሁኔታዎችን ተመልክቷል፤
አመዙዛኗልም።
በያዛነው ጉዲይ በስር ፍርድ ቤት አመልካች ጥፊተኛ በተባለበት የህግ ድንጋጌ ቅጣት ሲወስን የግራ ቀኙ የቅጣት አስተያየት እና የወንጀል ቅጣት አወሳሰን መመሪያ መሰረት በማድረግ የወንጀለ ደረጃ እና መነሻ የእስራት እና የገንዖብ ቅጣት እርከን በመለየት ተከሳሽ በሦስት ዓመት ጽኑ እስራት በተጨማሪም 5000 (አምስት ሺህ ብር ) የገንዖብ መቀጮ እንዱቀጡ ውሳኔ ሰጥቷል።ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት በመቀበል ቅጣቱን በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 መሰረት አስልቶ ወንጀልች በዛቅተኛ ደረጃ በመመደብ፣ለወንጀለ መነሻ ተደርጎ የተያዖው ዛቅተኛው የቅጣት መጠን 5 ዓመት መሆኑን እና ይህም በአባሪ አንድ በእርከን 20 ስር የሚወድቅ መሆኑን በመግለጽ፣በተጠሪ በኩል የቀረበ ማክበጃ ምክንያት ስለላለ በአመልካች በኩል የቀረቡትን ሦስት የማቅለያ ምክንያቶች ተገቢ አድርጎ በመቀበል እርከኑን ወደ 17 ዛቅ ካደረገ በኃላ በእርከን 17 በተመለከተው ፍቅድ ስልጣን መሰረት አመልካቹ በሦስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዱቀጡ ውሳኔ መስጠቱን፣አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት የህግ ድንጋጌ ከእስራት ቅጣት በተጨማሪ የገንዖብ መቀጮ የሚያስቀጣ በመሆኑ የገንዖብ መቀጮው በተመለከተም የህግ ድንጋጌው የሚያስቀጣው ከ50,000 እስከ 150,000 ብር የገንዖብ መቀጮ ስለሆነ በመመሪያው መሰረት ደረጃ በማውጣት ወንጀለ ዛቅተኛ የተያዖ በመሆኑ የገንዖብ ቅጣት መነሻ 50,000 በመያዛ በአባሪ ሁለት እርከን 10 መነሻ እርከን በመያዛ ሶስት የቅጣት ማቅለያ መሰረት ወደ እርከን 7 ዛቅ እንዱል ካደረገ በኋላ አመልካች በ5000 ብር እንዱቀጣ ውሳኔ ሰጥቷል። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ቅጣት ውሳኔ መሰረት አድርጎ ግራቀኙ ካከራከረ በኋላ በአመልካች ቀርበው በስር ፍርድ ቤት ያልተያዘት ተጨማሪ ሁለት የቅጣት ማቅለያዎች በመያዛ የእስራት ቅጣት እርከኑ ወደ እርከን 15 ዛቅ በማድረግ በዘሁ እርከን ባለው ፍቅድ ስልጣን ቅጣቱ በማሻሻል አመልካች ሁለት አመት ከዖጠኝ ወር ፅኑ እስራት እንዱቀጡ የወሰነ ሲሆን የገንዖብ መቀጮ በተመለከተ ግን በቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 2/2006 ላይ ባለው አባሪ ሁለት በተጨማሪነት ለአመልካች ከተያዘለት ሁለት የቅጣት ማቅለያዎች መሰረት ከእርከን 7 ወደ እርከን 5 ዛቅ ካደረገ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ከወሰነው ቅጣት 5,000 (አምስት ሺህ) የገንዖብ ቅጣት በላይ 7000 (ሰባት ሺህ) ብር እንዱቀጣ ውሳኔ ሰጥቷል።በሰበር አጣሪ ችልት ለክርክር የተያዖው ጭብጥም አመልካች ባቀረቡት ይግባኝ መነሻነት ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የገንዖብ ቅጣቱን የመጨመሩ አግባብነት የሚመለከት ነው። ከተያዖው ጭብጥ አንፃር የወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 196(2) ስር እንደተደነገገው ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ቅጣቱን ያፀናል ፣ይጨምራል፣ወይም ይቀንሳል በማለት ተደንግጓል። ከዘህ ድንጋጌ ለመረዲት የሚቻለው ተከሳሽ ይግባኝ የሚለው ቅጣቱ ለመለወጥ ወይም ለማሻሻል እንደሆነ አከራካሪ አይሆንም ወደ ተያዖው ጉዲይ ስንመለስ የስር ፍርድ ቤት አመልካች (ተከሳሽ )ባቀረቡት ይግባኝ ቅሬታ መነሻነት የገንዖብ ቅጣት መጨመሩ የወንጀል ህጉ አላማ አይደለም። ስለሆነም አመልካች ባቀረቡት ቅሬታ መነሻነት በስር ፍርድ ቤት ያልተያዖላቸው ሁለት የቅጣት ማቅለያዎች በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተያዖላቸው ስለሆነ ይህንን ይግባኝ ተብል ያልተሻረ ስለሆነ በእርከን 5 ስር ካለው ፍቅድ ስልጣን በወንጀል ህግ ቁጥር 90 መሰረት በማስላት መወሰን ሲገባው አመልካች ባቀረቡት ይግባኝ መነሻነት የገንዖብ ቅጣት በማክበድ መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው ብለናል።
ስለሆነም አመልካች ጥፊተኛ በተባለበት የህግ ድንጋጌ በቅጣት አወሳሰን መመሪያው መሰረት በማስላት የእስራት ቅጣቱ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ በአግባቡ ሆኖ የገንዖብ ቅጣት በተመለከተ ግን ሉወሰን የሚገባው ቅጣት በእርከን 5 ስር ካለው ፍቅድ ስልጣን በወንጀል ህግ ቁጥር 90 መሰረት መሰላት ስላለበት አመልካች 2000 (ሁለት ሺህ) ብር የገንዖብ መቀጮ ሉቀጣ ይገባል ብለናል።
ሲጠቃለል በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የጸናው የጥፊተኝነት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ ስላልተገኘ እና በቅጣት ውሳኔው ላይ ግን ከላይ በተገለጸው ምክንያት ተገቢው ማስተካከያ ላደረግበት የሚገባ ሆኖ በመገኘቱ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቶአል።
በአመልካቹ ላይ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዛገብ በ03/09/2008 ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዛገብ በ05/11/2008 ዓ.ም. የጸናው የጥፊተኝነት ውሳኔ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 195(2)(ለ)(2) መሰረት ፀንቶአል።
በአመልካቹ ላይ በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የተወሰነው የሁለት አመት ከዖጠኝ ወር ፅኑ እስራት ቅጣት እንዲለ ተቀብለን ፣ተጥል የነበረውን የብር 7,000 (ሰባት ሺህ) መቀጮ የቅጣት ውሳኔ በማሻሻል አመልካቹ ከፅኑ እስራቱ በተጨማሪ 2000 (ሁለት ሺህ ) ብር መቀጮ እንዱቀጡ ወስነናል።
ይህንኑ ተገንዛቦ የተሻሻለውን የገንዖብ ቅጣት መሰረት እንዱያስፈጽም ለሚመለከተው አካል የዘህ ውሳኔ ግልባጭ ከመሸኛ ትዔዙዛ ጋር ይላክ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዛገቡ ተዖግቶአል።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
No topics extracted.