No summary available.
ሰ/መ/ ታህሳስ 26 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሀመድ ተኽሉት ይመሰል ቀነአ ቂጣታ ሰናይት አድነዉ ጳዉልስ አርሺሶ አመልካች፡- ወ/ሮ አልማዛ አሰፊዉ ልጅ መስፍን አስፊዉ ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጲያ ሱማላ ክልል የዐቃቤ ህግ አልቀረቡም መዛገቡን መርምረን የሚከተለዉን ፍርድ ሰጥተናል።
2.አመልካች በተከሳሽነት ቀርባ የወንጀለን ድርጊት አልፈጸምኩም ጥፊተኛ አይደለሁም በማለት ክዲ ተከራክራለች ። ተጠሪ ክሱን ያስረደልኛል በማለት አምስት ምስክሮች አቅርቦ አሰምቷል።
አመልካች መከላከያ ማስረጃ እንድታቀርብ የስር ፍርድ ቤት ትዔዙዛ ሰጥቶ አመልካች የሰዉና የሰነድ ማስረጃ በመከላከያ ማስረጃነት አቅርባለች፡፤ የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች በወንጅል ሕግ አንቀጽ 574(2) እና አንቀጽ 448 የተመለከተዉን በመተላለፍ የወንጀል ድርጊት የፈጸመች ናት በማለት ወንጀለ አንደኛ ደረጃ ላይ የሚወድቅ መሆኑን ገልጾ አመልካች በአምስት ዓመት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ ዉሳኔ ሰጥቷል። አመልካች በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርባለች። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ አጽንቶታል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት አቅርባ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የባታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበትም በማለት አጽንቶታል።
እውነታው ይህ ሆኖ እያለ ተጠሪ አንድ ጊዚ ሟችን ከሞት ለመታደግ የሞከሩትን ሰዎች በግፍ ገድላችኋታል በማለት ክስ አቅርቦ ሰዎቹን በይግባኝ በነፃ ተሰናብተዋል። እኔን ደግሞ ከህግ አግባብ ውጭ አግባብነት የላለው የህግ ድንጋጌ ጠቅሶ ያቀረበውንና ተጠሪ በማስረጃ ያላረጋገጠውን ክስ በመቀበል የበታች ፍረድ ቤቶች የሰጡት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በስበር ታይቶ እንዱታራምልኝ በማለት አመልክታለች።
ተጠሪ ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ/ም የተጻፈ መልስ አቅርቧል። ተጠሪ ባቀረበው መልስ እድሜዋ ለአቅመ ሄዋን ያልደረሰች በአመልካች ቤት ስታድግና ጤናማ አዔምሮ ያልነበራት ልጅ ለአደጋ ስትጋለጥ ማዲን እያቻለች ለማዲን ያልሞከረች መሆኑ ተጠሪ ባቀረበው ማስረጃ ተረጋግጦ ውሳኔ የተሰጠበት በመሆኑ አመልካች ያቀረበችው የሰበር አቤቱታ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል። አመልካች ጥቅምት 23 ቀን 2009 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርባለች።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና ግራ ቀኙ ለዘህ ሰበር ችልት ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ተገቢነት መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች ጥፊተኛ የተባለችው የወንጀል ህግ አንቀጽ 574(2) ተላልፊለች ተብል ነው። የወንጀል ህግ አንቀጽ 574 የወንጀል ህጉ የሰውን ህይወት አካል ወይም ጤንነት ለአደጋ በማጋለጥ የሚፈጸመው ወንጀልች በማለት በምእራፍ አራት ስር ከወንጀል ህጉ አንቀጽ 571 እስከ አንቀጽ 579 በዖረዖረቸው ወንጀልች ውስጥ ተካትቶ የሚገኝ ድንጋጌ ነው።
በወንጀል ህግ አንቀጽ 57/2/ የተደነጋገውን ወንጀል ፈጽሟል ተብል አንድ ሰው በኃላፉነትን የሚጠየቀው በወንጀል ህግ አንቀጽ 574 ንዐስ አንቀጽ 1 የተዖረዖሩትን ወንጀለን የሚያቋቋሙ መሰረታዊ ፍሬ ነገሮች በአንቀጽ 574 ንዐስ አንቀጽ (2) የተመለከቱት የማክበጃ ምክንያት መኖራቸው በማስረጃ ሲረጋገጥ ነው።
የወንጀል ህግ አንቀጽ 574 ‛ሰውን ለአደጋ ማጋለጥ ወይም መተው“ በእንግሉዖኛው ቅጅ Exposure or Abandonment of Another የሚል ርእስ ያለው ሲሆን የአንቀጹ ንዐስ አንቀጽ 1 ቃል በቃል ሲነበብ“ በጤናው በእድሜው በሁኔታው ወይም በማናቸውም ላላ ምክንያት ራሱን ለመጠበቅ የማይችለውን ላላ ሰው የማናቸውም ምክንያት ይሁን በጠባቂነት ወይም በኃላፉነት ለማኖር የተቀበለ ማንም ሰው የተባለውን ሰው አስቦ (ሀ) በሕይወቱ ወይም በጤናው ላይ በቅርብ መድረሱ ለማይቀር አደጋ ያገለጠው እንደሆነ ወይም (ለ) ይህን በመሰለ ሁኔታ ላይ በሚገኝበት ጊዚ ጥልት የሄደ እንደሆነ ወንጀለን እንደፈጸመ ተቆጥሮ ቅጣት የሚጣልበት መሆኑን የሚደነግግ ሲሆን የአንቀጽ 574 ንዐስ አንቀጽ 2 ወንጀለ የተፈጸመው በህጻን ልጅ ላይ የሆነ እንደሆነ ቅጣቱ ከሰባት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ይሆናል። በማለት ይደነግጋል።
የአንቀጽ 574 የእንግሉዖኛው ቅጅ ይዖት ሲታይም ‛የአንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 1‛ who ever Having the custody or charge, on no matter what grounds of a person in capable of protecting Himself= whether on account of his health, his age, his situtation any other circumstances intentionally (a) Exposes him there by putting him imminent danger of life or heath or (b) Abandons him when in like situation የሚል ይዖት ያለው ሲሆን ንዐስ አንቀጽ 2 ‹‹where the crime is committed against infant, the punishment shall be rigorous imprisonment not exceeding seven years›› የሚል ይዖት ያለው ነው።
ከላይ ከጠቀስነው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 574 ድንጋጌ የምንረዲው፣ በመጀመሪያ ደረጃ ሰውን ለአደጋ የማጋለጥ ወይም የመተው ወንጀል ሆነ ተብል የሚፈጸም ወንጀል መሆኑን ነው። በዘህ ድንጋጌ ተጠያቂ የሚሆን ሰው፣ ሰውየውን ለአደጋ ያጋለጠው ወይም ህይወቱ በአደጋ ላይ እንደሚወድቅ እያወቀ የተወው፣ ተጎጅው በአደጋው ህይወቱን እንዱያዲጣ ሆነ ብል አስቦበት የፈጸመው ሆኖ ሲገኝ ነው። በሁለተኛ ደረጃ ወንጀለን የፈጸመው ሰው ከአደጋ ካልጠበቀው በስተቀር የተጎጅውን ህይወት ከአደጋ ውስጥ የሚጥል እርግጠኛና በፍጥነት ሉደርስ የሚችል አደጋ መኖሩን እያወቀ ሆኖ ሲገኝ ነው። በሶስተኛ ደረጃ የላላውን ህይወት ከአደጋ የመጠበቅ ሃላፉነት ያለበት ሰው፣ ህይወቱ ለአደጋ የተጋለጠውን ሰው በማናቸውም ምክንያት ለመጠበቅና በእሱ ቁጥጥርና ክትትል ስር ለማኖር ሃላፉነቱን የተቀበለ ሰው መሆን ያለበት መሆኑ ሲሆን፣ በአራተኛ ደረጃ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 574 ንዐስ አንቀጽ 2 የአማረኛው ቅጅ ‛ህጻን“ የሚለውን አነጋገር፣ ማናቸውም አስራ ስምንት ዓመት ያልሞላው ሰው ማለት እንዲልሆነ ከእንግሉዖኛው ቅጅ ‛where the crime is committed against infant“ በማለት በደነገገው አገላለጽ ግልጽ ያደረገው መሆኑን የሚያሳይ ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ የተደነገገውን የሕጉን ይዖት ተጠሪ በአመልካች ላይ ካቀረበው ክስና ማስረጃ ጋር ስናገናዛበው በመጀመሪያ ደረጃ ተጠሪ አመልካች የአስራ ሁለት አመት ህጻን የሆነችው ኤደን፣ በላልች ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ስትገደል አመልካች ምንም እርዲታ አላደረገችም በማለት ለዜኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ባቀረበው የወንጀል ክስ የገለጸ ሲሆን፣ ሟች ህጻን ኤደን በሰዎች ያልተገደለች መሆኑና አመልካች መታጠቢያ ክፍል ውስጥ ገብታ ራሷን በጨርቅ በመስቀሎ ምክንያት የሞት አደጋ የደረሰባት መሆኑን ተጠሪ ባቀረበው የወንጀል ክስ ሁለተኛው ፓራግራፍ እና በበታች ፍ/ቤቶች የተረጋገጠ መሆኑን ተገንዛበናል። ይህ የሚያሳየው ተጠሪ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 574 ይዖት በአግባቡ ሳይረዲና የወንጀል ክሱን የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 111 እና የወንጀል ሕግ ቁጥር 112 በሚደነግገው መሰረት አዖጋጅቶ ያላቀረበ ፣ ተጠሪ ያቀረበው የወንጀል ክስ ይዖት ተቃራኒ ይዖት ያለው መሆኑን ነው።
ተጠሪ አመልካች የወንጀል ሕግ ቁጥር 574 ንዐስ አንቀጽ 2 በመጣስ ሟች ኤደንን ለአደጋ አጋልጣለች ወይም ትታለች በማለት ባቀረበው የወንጀል ክስ ውስጥ ሟች የሞተችው በአመልካች የገላ መታጠቢያ ክፍል ውስጥ ራሷን በጨርቅ በመስቀል መሆኑን፣ አመልካች በወቅቱ ከዘያው ግቢ ውስጥ ስለነበረች ሟች የታነቀችበትን ጨርቅ በጥሳ ከሞት ልታድናት እየቻለች ይህን ያላደረገች መሆኑን ገልጿል። ተጠሪ ይህንን ክስ ለማስረዲት ያቀረባቸው ምስክሮች ሚያዘያ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ኤደን የተባለች ልጅ ታንቃ፣ ሰዎች የታነቀችበትን ጨርቅ በጥሰው አመልካችና ላልች ሰዎች ወተት ለማጠጣት ሲሞክሩና በኋላም በባጃጅ ሟችን ይዖው ወደ ሃኪም ቤት ሲወስደ ያዩ መሆናቸውን እንደመሰከሩ ከበታች ፍ/ቤቶች ውሳኔ ይዖት ለመረዲት ችለናል።
ተጠሪ ያቀረበው የወንጀል ክስ፣ ሟች ህጻን ኤደን ራሷን በራሷ ለማጥፊት እንደምትሞክርና በዘህም ምክንያት የሟች ኤደን ህይወት አደጋ ላይ ሉወድቅ እንደሚችል አመልካች እያወቀች፣ አመልካች ሆንብላና ህጻን ኤደን ራሷን በማነቅ እንድታጠፊ በማሰብ ተገቢውን ጥንቃቄ ሳታደርግ የተወቻት መሆኑን የሚገልጽ አይደለም። አመልካች ህጻን ኤደን ህይወቷን በገዙ እጇ ለማጥፊት በሚያስችላት በእርግጠኝነት ሉደርስ በሚችል አደጋ ውስጥ የነበረች መሆኑን እንደምታውቅ የተጠሪ ምስክሮች አላስረደም። ከዘህ በተጨማሪ አመልካች ህጻን ኤደን ትምህርቷን አቋርጣ ወደ እሷ ቤት የመጣች መሆኑን ያየችና የምታውቅ መሆኑን ተጠሪ ያቀረባቸው ማስረጃዎች የሚገልጹ እንዲልሆኑ ተረድተናል። ተጠሪ ህጻኗ ከንግድ ቤቱ ራቅ ብል ከተሰራው መጸዲጃ ቤት ውስጥ ገብታ በጨርቅ ራሷን ስታንቅ፣ አመልካች በዘያው ግቢ ውስጥ ሆና ሳለ ቀድማ አልደረሰችም በማለት የሚያቀርበው ክርክር በወንጀል ህግ አንቀፅ 574 የተደነገገው ወንጀል የሚፈፀመው ሆን ተብል እንደሆነ ከሚገልፀው ጋር አብሮ የሚሄድ ሆኖ አላገኘነውም።ተጠሪ አመልካች ሆነብላ እና አስባ ህፃን ኤደን ራስዋን በራስዋ እንድታጠፊ ለአደጋ ያጋለጠቻት ወይም ትታት የሄደች መሆኑን የማስረዲት ግዳታውን የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 20 ንኡስ አንቀፅ 3 በሚደነግገው መሰረት አልተወጣም።በልላ በኩል አንድ ወንጀል ወንጀለን በቸልተኝነት የሚያስጠይቀው በህጉ በተለየ ክፍል ያስቀጣል ተብል በግልፅ በተደነገገ ግዚ እንደሆነ የወንጀል ህጉ አንቀፅ 59 ንኡስ አንቀፅ 2 የተደነገገ በመሆኑ አመልካች ሟች ራሷን ባነቀችበት ቤት ግቢ ውስጥ እያለች የሟችን የሲቅና የጣር ድምፅ ባለመስማቷ ምክንያት በወንጀል ህግ ቁጥር 574 ንኡስ አንቀፅ 2 ተጠያቂ የምትሆንበትን የህግ ምክንያት አላገኘንም።
ከላይ በዛርዛር በገለፅናቸው ምክንያቶች ተጠሪ አመልካች የወንጀል ህግ 574 የተዖረዖረውን ወንጀል የፈፀመች ስለመሆኑ በህጉ አነጋገር እና የድርጊቱን አፈጻፀም የሚገልፅ |የወንጀል ክስ በወ/መ/ስ/ስ/ሕግ ቁጥር 111 እና በወንጀል ህግ ቁጥር 112 መሰረት አላቀረበም።የበታች ፍ/ቤቶች ተጠሪ የወንጀል ክሱን በማሻሻል አመልካች የወንጀል ሕግ አንቀፅ 574 (2) የተገለፀውን የወንጀል ድርጊት የፈጸመች መሆኑን የሚያሳይ የአመልካችን የሀሳብ ክፍል ሆን ብላ ወንጀለን የፈፀመች በመሆኗ የአመልካችን ግዘፍ ድርጊትና ተሳትፍ ግልፅ አድረጎና ዖርዛሮ እንዱያቀርብ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ቁ 119(1) መሰረት ትእዙዛ ሳይሰጡ የወንጀል ክሱን ማየታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።ከዘህ በተጨማሪ አመልካች ሟች ህፃን ኤደን ከመፃዲጃ ቤት ታንቃ ላልች ሰዎች የታነቀችበትን ጨርቅ በጥሳው ከወጣች በኃላ ፈፅማዋለች በማለት በተጣራ ምስክሮች የተዖረዖረው ግዘፍ ተግባር አመልካች የሟችን ሂወት ለመታድገ የቻለችውን ጥረት ማድረጓንና በወንጀል የሚያስጠይቅ የወንጀል ተግባር ያልፈፀመች መሆኑን የሚያረጋግጥ ሆኖ እያለ የበታች ፍ/ቤት አመልካች የወንጀል ሕግ ቁጥር 574(2) በመተላለፍ ወንጀል ፈፅማለች በማለት የሰጡት የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ ከላይ በዛርዛር የጠቀስናቸውን የህግ ድንጋጌዎች የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የስር ፍርድ ቤት አመልካች በወንጀል ህግ አንቀጽ 448 በመተላለፍ ጥፊት፣ፈጽማለች በማለት የጥፊተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል። ሆኖም ተጠሪ አመልካች በወንጀል ህግ አንቀጽ 448 የተዖረዖሩትን ድርጊቶች ስለመፈጸሙ በግልጽና የወ/መ/ስ/ስ/ህግ/ቁ/111/ እና የወ/መ/ስ/ስ/ህግ/ቁ/ 112 በሚደነግግበት መሰረት አላቀረቡም። ተጠሪ ያቀረበችው ምስክሮቹም አመልካች በወንጀል ህግ አንቀጽ 448 የተመለከተውን ወንጀል ስለመፈጸሟ የሰጡት የምስክርነት ቃል የላለ መሆኑን ተረድተናል። ከዘህ አንፃር ሲታይ ተጠሪ በአግባቡ የወንጀል ክሱን ባላቀረበበትና ክሱን የሚያስረዲ ማስረጃ ባላቀረበበት ሁኔታ የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች በወንጀል ህግ አንቀጽ 448 በመተላለፍ ወንጀል ፈጽማለች በማለት የሰጠውን ውሳኔ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት ማፅናታቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በአጠቃላይ ሲታይ አመልካች የወንጀል ህግ አንቀጽ 574/2/ እና አንቀጽ 448 የተደነገጉትን በመተላለፍ የወንጀል ተግባር የፈጸመች መሆኑን በተሟላ ሁኔታ የሚያሳይ የወንጀል ክስ ተጠሪ ያላቀረበበት ሆኖ እያለና ተጠሪ ያቀረበውን የወንጀል ክስ የማስረዲት ግዳታውን በአግባቡ ባልተወጣበት ሁኔታ አመልካች በወንጀል ህግ አንቀጽ 574/2/ እና አንቀጽ 448 የተመለከተውን በመተላለፍ ወንጀል ፈጽማለች በማለት በአምስት ዓመት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና የሰበር ችልት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት በወንጀለኛ መቅጫ ስነ-ስርዓት ህግ ቁጥር 195 ንዐስ አንቀጽ 2/ለ/1 መሰረት በመሻር አመልካች በነፃ ልትሰናበት ይገባል በማለት ወስነናል።
የኢትዮጲያ ሱማላ ክልል የፊፈን ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ ቁጥር 711/06 ሰኔ 10 ቀን 2005 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔና ፍርድ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዛገብ ቁጥር 05/1/201/06 መጋቢት 1 ቀን 2007 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት በመዛገብ ቁጥር 05/01/125/07 ሰኔ 15 ቀን 2008 ዓ/ም የሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በወ/መ/ስ/ስ/ህግ/ቁ/ 195 ንዐስ አንቀጽ 2/ለ/1/ መሰረት ሙለ በሙለ ተሽሯል።
አመልካች የወንጀል ህግ አንቀጽ 574/2/ እና የወንጀል ህግ 448 በመተላለፍ ወንጀል የፈጸመች ስለመሆኑ ተጠሪ የማስረዲት ግዳታውን ያልተወጣ በመሆኑ አመልካችዋ ከቀረቡቧት ሁለት የወንጀል ክሶች በነፃ እንድትሰናበት በማለት ወስነናል።
በአመልካች ላይ ተወስኖ የነበረው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ ሙለ በሙለ ተሽሮ አመልካች በነፃ እንድትሰናበት ከዘህ ሰበር ችልት የተወሰነ መሆኑን አውቆ አመልካችን በዙሬው ዔለት ከእስር እንዱለቃት ለክፍለ ማ/ቤት የመፍቻ ትዔዙዛ ይፃፍ።
መዛገቡ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.