ወንጀል አድራጊው የመጀመሪያውን የጥፊት ዓላማውን ከግብ ለማድረስ ሲል መሰረታዊ ከሆነው ወንጀል በኋላ አከታትል ያደረገው ድርጊት ከቀድሞ ሃሳቡና ሉደርስበት ካቀደው ግብ ጋር የተያያዖ ሆኖ ሲገኝ በዋናው ወንጀል ስር መጠቃለል የሚገባው ስለመሆኑ ፣ የወ/ሕ/ቁ. 61/3/
No summary available.
ታህሳስ 24 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዲኜ መላኩ ተኽሉት ይመሰል ቀነዓ ቂጣታ ሰናይት አድነው ጰውልስ ኦርሺሶ አመልካች፡- የፋዳራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ራቢያ በድሩ ቀርባለች ተጠሪ፡- ሙዐዛ ደስታ ገ/እግዘአበሓር ከጠበቃቸዉ አቶ መኮንን በዙብህ ጋር ቀርበዋል።
መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች በቀን 12/12/2006 ዓ/ም በተጻፈ አቤቱታ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችልት በወ/ይ/መ/ በቀን 29/09/2006 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ ተጠሪን በነፃ መልቀቁን በመቃወም ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን አመልካች በአሁኑ ተጠሪ ላይ ያቀረበው ክስ መሰረታዊ ይዖቱ ሲታይ ተጠሪን ሁለት የወንጀል ህግ ድንጋጌዎችን በመጣስ ወንጀል የከሰሰው ሲሆን የመጀመሪያው ክስ ወላጅ እናቱ ወ/ሮ አወጣሽ አብርሃ ሆና እያለ የማይመለከተውንና በሥጋ ዛምድና ግንኙነት የላላቸውን የአቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ 1,7000.00 (አንድ ሚሉየን ሰባት መቶ ሺህ ብር ) የሚገመት ንብረት ያለአግባብ ለመውረስ ሲል ከላይ የተመለከተውን የወላጅ እናቱን ስም በመለወጥ የእናቱ ስም ወ/ሮ አወጣሽ ወ/ጊዮርጊስ እንደሚባለና የሟች ግርማ ወ/ጊዮርጊስ እህት እንደሆኑ በማስመሰል የወራሽነት ማስረጃ ከፍርድ ቤት ያወጣ በመሆኑ የወንጀል ህግ ቁጥር 696 (ሐ) መሰረት በከባድ የማታለል ወንጀል እንደተከሰሰ የሚገልጽ ሲሆን ሁለተኛው ክስ ተጠሪ በ1996 ዓ/ም የወጣውን የወንጀል ህግ ቁጥር 378 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ በ1ኛ ክስ ላይ እንደተገለጸው ምንም ዓይነት የሥጋ ዛምድና የላላቸውንና አጎቱ ያልሆኑትን ሟች አቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስን የእናቱን ወንድም እና አጎቱ እንደሆኑ እና አጎቱ ለማስመሰል ሀሰተኛ የሆነ የአቤቱታና የቃለ መሃላ ሰነድ በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ንፊስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፍትሐብሕር ችልት በማቅረቡና እንደዘሁም በድሬዲዋ ማዖጋጃ ቤት በ20/02/2002 ዓ/ም የተሰጠው የጋብቻ ምስክር ወረቀት ላይ የእናቱ ስም የሚለው ቦታ ላይ አወጣሽ አብርሃ ተብል የተሰጠውን በተመሳሳይ ማስረጃ ለመውረስ እንዱያመቸው አስቦ ለድሬዲዋ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቤቱታ ፅፍ በማቅረብ የጋብቻ ሰርቲፉኬት ላይ የእናቱ አባት ስም ወ/ጊዮርጊስ ሆኖ እያለ በስህተት አብርሃ ተብሎልና ወ/ሮ አወጣሽ አብርሃ መባለ ቀርቶ ወ/ሮ አወጣሽ ወ/ጊዮርጊስ ተብል ተስተካክል ይሰጠኝ ብል ለፍርድ ቤት አቅርቦ ፍርድ ቤቱም የቀረበውን አቤቱታ እውነተኛ እንደሆነ አድርጎ ቀይሮ የእናቱን አባት ስም አብርሃ መባለ ቀርቶ ወ/ጊዮርጊስ ይባል ብል ውሳኔ በመስጠቱና ፍርድ ቤቱን አታል ማስረጃውን ከወሰደ በኃላ ድሬዲዋ ማዖጋጃ ቤት አቅርቦ የጋብቻው ሰርቲፉኬት ላይ ቀደም ሲል የእናቱ ስም ወ/ሮ አወጣሽ አብርሃ ይባል የነበረው ተቀይሮ ወ/ሮ አወጣሽ ወ/ጊዮርጊስ ተብል ላላ ሀሰተኛ የሆነ የጋብቻ ሰርቲፉኬት አውጥቶ ይህንኑ ሰርቲፉኬት የሟች ንብረትን ለመውረስ በሚደርግ የፍትሐብሕር ክርክር ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርቦ የተጠቀመበት በመሆኑ ተጠሪ በፈጸመው በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል ተከሷል የሚል ነው።
ተጠሪ ወንጀል ያለመፈጸሙን ክድ የተከራከረ ሲሆን ጉዲዩን የተመለከተው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወንጀል ችልት የግራ ቀኝ ማስረጃዎችን ተመልክቶ ተጠሪን በተከሰሰባቸው ሁለቱም ክሶች ጥፊተኛ በማድረግ በ3 ዓመት ከ7 ወር ጽኑ እስራትና በ 1000.00 ብር (አንድ ሺህ ብር) የገንዖብ መቀጮ እንዱቀጣ ሲል ወስኗል።
ተጠሪ በውሳኔው ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፈዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቧል። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችልት ይግባኙን ተቀብል የግራ ቀኙን አከራክሮና ተጨማሪ ማስረጃዎችን ሰምቶ ተጠሪ ወንጀልቹን ስለመፈጸሙ ስላልተረጋገጠበት በነፃ ሉሰናበት ይገባል በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሽሯል።
ይህ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም የጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችልት ተጠሪን በነፃ በመልቀቅ የወሰነውን ውሳኔ ለማስለወጥ ነው። የአመልካች አቤቱታ ይዖትም በአጭሩ፡- ተጠሪ ለፈጸመባቸው ወንጀልች ከመንግሥታዊ አካል የተሰጡ ሰነድች እያለ ይህንን ሳይመለከት ተጠሪ ብቻ ያለውን ሰምቶ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ መስጠቱ ከማስረጃ አመዙዖንና አቀራረብ አንጻር በአንድ ወገን ያለውን ብቻ በመስማት የተሰጠ ውሳኔ አግባብ አይደለም፣ በተጨማሪ ማስረጃነት የሰማውን የተጠሪን አባት ምስክርነት በተመለከተ በሃሰት መስክረው ከሆነ ክስ የሚመሰረት ሆኖ በማለት የሥር ፍርድ ቤት ጠቅሶ ነገር ግን ለአሁን ጉዲይ የሰጡት ቃል አመኔታ የሚጣልበት ነው ማለቱ አግባብነት የላለውና እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነው፣ የተጠሪ እናት ነኝ ብለው የቀረቡት ወ/ሮ አወጣሽ አብርሃ የዱኤንኤ (DNA) ምርመራ እንዱያደርጉ በሥር ፍርድ ቤት ቢጠየቁም ቆራቢ በመሆናቸው በሚል ምርመራውን ለማድረግ አለመፈለጋቸው በተቃራኒው ሉተረጎም ሲገባው ተጠሪን በሚደግፍ ሁኔታ አለመመርመራቸው ጥያቄ ውስጥ ሳይገባና ቆራቢ ናቸው ተብል መታለፍ ያለአግባብ ነው፣ በሥር ፍርድ ቤት እንዱመጣ ያልታዖዖ ሰነድ ተጠሪ በራሱ መነሻነት ያቀረበውን በአንድ የፖሉስ አባል የተጻፈን ሰነድ ብቻ ተቀብል ታማኝነት ያለው ሰነድ ነው በማለት ውሳኔ መስጠቱ አግባብነት የላለው ሲሆን የሥር ፍርድ ቤት በተጠሪ በኩል የቀረበው ማስረጃ በፖሉስ ኮሚሽኑ በምን መነሻነት ሰነደን ላሰጥ እንደቻለ ማጣራት ሳያደርግ ተጠሪን በነፃ ማሰናበቱ አግባብነት የላለውና ምክንያታዊ ያልሆነ በመሆኑ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሳኔ ተሸሮ የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ እንዱጸናልን የሚል ነው።
አመልካች ያቀረበው አቤቱታ ተመርምሮ ክሱን በመጀመሪያ ደረጃ ያስተናገደው ፍርድ ቤት ተጠሪ ያለአግባብ ለመውረስ አስቦ ከዖጠኝ ዓመት በፉት ባስመዖገበው የጋብቻ ሰርቲፉኬት ላይ የትክክለኛ የወላጅ እናቱ ስም ወ/ሮ አወጣሽ አብርሃ ሆኖ እያለ በ2002 ዓ/ም ያረፈት የወ/ሮ አወጣሽ ወ/ጊዮርጊስ እናቱ እንደሆኑ አሳስቶ ባገኘው ማስረጃ ስለመገልገለ በዐቃቤ ህግ ምስክሮችና የሰነድ ማስረጃዎች ተረጋግጧል በማለት የወሰነውን ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ከፖሉስ ቀደም ብል የተጻፈው ዲብዲቤ በኃላ በተጻፈው ተሽሯል በማለት በተለይ የሥር ፍርድ ቤት የቀበላ ማኅደር ጭምር አስቀርቤያለሁ በማለት በወሰነው ላይ ምንም ሳይል ማለፈን አግባብነት ለመመርመር ሲባል አቤቱታ ለሰበር ቸልት ይቅረብ ተብል ታዝል።
የሰበር አቤቱታው ለተጠሪ ደርሶት ሟች ወ/ሮ አወጣሽ ወ/ጊዮርጊስ የተጠሪ እናት ስለመሆናቸው በማያመነታ መንገድ በሰውም ሆነ በጽሁፍ ማስረጃ ተረጋግጧል። ወ/ሮ አወጣሽ አብርሃ የተጠሪ እንጀራ እናት እንጂ ወላጅ እናቴ ወ/ሮ አወጣሽ ወ/ጊዮርጊስ መሆናቸውን ወላጅ አባቴ ጭምር በምስክርነት ያረጋገጡት ጉዲይ ከመሆኑ በተጨማሪ የአፅቢ ወንበርታ ፖሉስ ጽ/ቤት ሚያዛያ 29 ቀን 2006 ዓ/ም በጻፈው ዲብዲቤ ቀደም ሲል ወ/ሮ አወጣሽ አብርሃ የተጠሪ እናት እንደሆኑ አድርጎ የጻፈው በተጠናከረ ማስረጃ ተመስርቶ አለመሆኑን የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማረጋገጡ እውነታውን ይበልጥ የሚያሳይ ስለሆነ ተጠሪ ከወንጀል ህግ ቁጥር 23 አኳያ ጥፊተኛ ልባል የሚቻልበት ህጋዊ ምክንያት የለም በማለት ግንቦት 24 ቀን 2007 ዓ/ም የተጻፈ መልስ አቅርቦ ተከራክሯል። አመልካችም ቅሬታውን በማጠናከር በቀን 10/10/2007 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
የክርክሩ ሂደት አጠር ባለ መልኩ ከላይ እንደተገለጸው ሲሆን ጉዲዩን ከስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ፣የግራ ቀኙ በዘህ ችልት ካደረጉት ክርክር እንዱሁም ለሰበር ያስቀርባል ተብል ከተያዖው ጭብጥ አንጻር መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነውም የጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችልት ተጠሪን በነፃ መልቀቁ በአግባቡ ነው ወይ? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው።
በመሆኑም ግራቀኝ ወገኖች ይህን ጭብጥ መሰረት በማድረግ ያሰሙትን ክርክር አቤቱታው ከቀረበበት ውሳኔ እና ከህጉ ጋር አገናዛበን መርምረናል።
ከላይ በዛርዛር እንደተመለከትነው በዐቃቤ ሕግ ክስ የተመለከተውን ድርጊት አልፈጸምኩም በማለት ተጠሪ ቢከራከርም፤ ክሱን የሰማው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግን ድርጊቱን ስለመፈጸሙ በማስረጃ አረጋግጦአል። ጉዲዩን በይግባኝ የሰማው ፍ/ቤት ግን የራሱን ተጨማሪ ማስረጃ በመስማት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሽሯል። እንደሚታየው ድርጊቱ ተፈጽሞአል ወይስ አልተፈጸመም የሚለው የፍሬ ነገር ጭበጥ በመሆኑ የሚነጥረው (የሚጣራው) በማስረጃ ነው።
የፍሬ ነገር ጭብጥን በማስረጃ የማጣራት እና የተሰማውን ማስረጃ የመመዖን ሥልጣን ያላቸው የፍደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ክርክሩን ተመልክተው የተለያየ መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል። በዐቃቤ ህግ ክስ የተመለከተው ድርጊት በተጠሪ መፈጸሙን ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በማረጋገጡም ድርጊቱን ከተጠቀሰው የወንጀል ሕጉ ድንጋጌ ጋር አገናዛቦ የጥፉተኛነት ውሳኔ ሰጥቷል። የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችልት ደግሞ በሰማው ተጨማሪ ማስረጃ ተጠሪ ወንጀል ስላለመፈጸሙ ተረጋግጧል በማለት ተጠሪን በነፃ እንዱሰናበት ወስኗል።
በበኩላችንም እንደምናየው ተጠሪ በዐቃቤ ህግ ክስ የተመለከተውን ድርጊት ፈጽሞአል ወይስ አልፈጸመም የሚለውን የፍሬ ነገር ጭብጥ የማጣራት ሥልጣን ለሰበር ችልቱ የተሰጠ ባለመሆኑ በዘህ ደረጃ የምንመረምረው አይደለም። በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠው እውነታ በክሱ በተጠቀሰው ድንጋጌ የተመለከተውን ወንጀል ያቋቁማል ወይ? የሚለው ነጥብ ግን የህግ ጭብጥ በመሆኑ ተመልክተነዋል።
ተጠሪ የተከሰሰው የመጀመሪያው ክስ በወንጀል ህጉ በአንቀጽ 696 (ሐ) የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፍ ወንጀል ፈጽሞአል ተብል እንደሆነ ከላይ ተመልክተናል። ድንጋጌው የሚለው "ወንጀለ የተፈጸመው በህዛብ አስተዲደር ወይም በህዛብ አገልግልት ላይ እንደሆነ ነው።" በዘህ ድንጋጌ ሥር ጥፊተኛ ሲባል ከአስራ አምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራትና እስከ ብር ሃምሳ ሺህ በማይበልጥ መቀጮ ያስቀጣል።
በያዛነው ጉዲይ እንደምናየው የተጠሪ ወላጅ እናቱ ወ/ሮ አወጣሽ አብርሃ ሆና እያለ የማይመለከተውንና በሥጋ ዛምድና ግንኙነት የላላቸውን የአቶ ግርማ ወ/ጊዮርጊስ 1,7000.00 (አንድ ሚሉየን ሰባት መቶ ሺህ ብር ) የሚገመት ንብረት ያለአግባብ ለመውረስ ሲል ከላይ የተመለከተውን የወላጅ እናቱን ስም በመለወጥ የእናቱ ስም ወ/ሮ አወጣሽ ወ/ጊዮርጊስ እንደሚባለና የሟች ግርማ ወ/ጊዮርጊስ እህት እንደሆኑ በማስመሰል የወራሽነት ማስረጃ ከፍርድ ቤት አውጥቷል።ለፍርድ ቤቱ ወራሽ መሆኑ እንዱረጋገጥለት አቤቱታውን በቃለ መኽላ አረጋግጦ አቀርቧል። በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 92 እንዱሁም ቁጥር 205 መሰረት አንድን አቤቱታ በቃለ መሃላ እንዱቀርብ ህግ አውጪው የፈለገበት በሁለት ምክንያቶች ነው።
የመጀመሪያው ሀሰተኛ አቤቱታዎች በፍትህ ሥርዓቱ ውስጥ የሚያስከትለትን የፍትህን መጓደል ለመከላከል ሲሆን ሁለተኛው ምክንያት ሀሰተኛ አቤቱታ የሚያቀርቡ ተከራካሪዎች በህግ እንዱጠየቁ ለማድረግ ነው። ተጠሪ ሀሰተኛ አቤቱታ በማቅረብ ፍትህ እንዱዙባ ከማድረጉም ባሻገር በህግ በተቋቋመ የተከራካሪዎችን መብትና ጥቅም በሚያስከበር አካል ፉት እንደዘህ ያለውን ሀሰተኛ የሆነ አቤቱታ አቅርቦ ማስወሰኑ በወንጀል ህግ ቁጥር 696 (ሐ) የተደነገገውን ድንጋጌ የጣሰ ሆኖ አግኝተነዋል።በመሆኑም በተያዖው ጉዲይ በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠው እውነታ በክሱ በተጠቀሰው ድንጋጌ የተመለከተውን ወንጀል የሚያቋቁም ሆኖ ተገኝቷል። የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ይግባኝ ሰሚ ችልት ይህንን እውነታ በአግባቡ ሳያጤን አልፍ ተጠሪን በነፃ እንዱሰናበት በማለት መወሰኑ የማስረጃ ህግ መርህን ጭምር የሚጥስ ውሳኔ በመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
ሁለተኛውን ክስ በተመለከተ በ1ኛው ክስ ሥር ሉጠቃለል የሚችል ነው ወይስ አይደለም?
የሚለውን ከተጠሪ ድርጊት አንጻር መርምረናል። የተጠሪ ሀሳብና ፍላጎት የሟች ግርማ ወ/ጊዮርጊስን ንብረት ለማግኘት ነው። ለዘህ ግብ ያስችለው ዖንድ እናቱን የሟች እህት አድረጎ ማስወሰን ስላለበት በ1989 ዓ/ም ጋብቻ ሲመሰርት የእናቱን ስም አወጣሽ አብርሃ በማለት በጋብቻ ሰርቲፉኬት የመዖገበውን ወ/ሮ አወጣሽ ወ/ጊዮርጊስ ተብል እንዱቀየር በድሬዲዋ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቅርቦ ካስወሰነ በኃላ ለማዖጋጃ ቤት በማቅረብ የጋብቻ ሰርቲፉኬቱ እንዱቀየር አድርጓል።ይህንን ማስረጃ ለአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በማቅረብ የሟች ወራሽ መሆኑን አስወስኗል።ይህን ሰነድ የተጠቀመውም ዋናው ግብ የሆነውን የሟች ንብረት የማግኘት ዓላማውን ከግቡ ለማድረስ ስለሆነ ላታይ የሚገባው ከወንጀል ህግ አንቀጽ 61 (3) አንጻር ነው። በመሆኑም ተጠሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 378 ድንጋጌን በመተላለፍ የተከሰሰበት ወንጀል በወንጀል ህግ ቁጥር 61 (3) መሰረት በወንጀል ህግ ቁጥር 696 (ሐ) የሚጠቃለል ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም ተጠሪ በወንጀል ህግ ቁጥር 378 መሰረት የጥፊተኝነትም ሆነ የቅጣት ውሳኔ ሉወሰንበት አይገባም ብለናል።
በመጨረሻም ከላይ በዛርዛር እንደተገለጸው ተጠሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 696 (ሐ) በመተላለፍ ጥፊተኛ ሆኖ ስለተገኘ ሉወሰን የሚገባውን ቅጣት ከወንጀል ህግ እንዱሁም ወንጀለ በተፈጸመበት ጊዚ በሥራ ላይ ከነበረው የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ቁጥር 1/2002 አንጻር ተመልክተናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪን በወንጀል ህግ ቁጥር 696 (ሐ) መሰረት ጥፊተኛ ነው ካለ በኃላ የወንጀል ደረጃውን መካከለኛ ሲል ይዝል። በእኛም በኩል ይህ ተገቢ እንደሆነ ተመልክተናል። ይህም እርከን 19 ሥር የሚያርፍ በመሆኑ በዘህ እርከን ያለው ፍቅደ ሥልጣን ከ4 ዓመት እስከ 4 ዓመት ከ10 ወር በመሆኑ መነሻ ቅጣት 4 (አራት) ዓመት ተይዝል። በከፍተኛ ፍርድ ቤት ለተጠሪ የተያዘለት ሁለት የቅጣት ማቅለያዎች እያንዲንዲቸው ሁለት እርከን የሚያስቀንሱ በመሆናቸው 4 (አራት) እርከን ተቀንሶ መጨረሻ ቅጣት ሉወሰን የሚገባው እርከን 15 ሥር በመሆኑ ተጠሪ በ2 ዓመት ከ9 ወር ጽኑ እስራት እንዱቀጣ ብለናል።
ሲጠቃለልም የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በወ/ይ/መ/ቁ. 96602 በቀን 29/09/2006 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 195 (2) (ለ) (2) መሰረት ተሸሯል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኮ/መ/ ህዲር 3 ቀን 2006 ዓ/ም የሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 195 (2) (ለ) (2) መሰረት ተሸሽሎል፡፤
ተጠሪ ጥፊተኛ በተደረገበት የወንጀል ህግ ቁጥር 696 (ሐ) መሰረት ቀደም ሲል የታሰረው ካለ ታሳቢ ተደርጎ በሁለት ዓመት ከዖጠኝ ወር ጽኑ እስራትና በብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) መቀጮ እንዱቀጣ ተወስኗል።
በተጠሪ ላይ የተወሰነውን የ2 ዓመት ከ9 ወር ጽኑ እስራትን ቀደም ሲል የታሰረ ካለ ታሳቢ ተደርጎ የተወሰነበትን ቅጣት ተከታትል እንዱያስፈጽም ለአዱስ አበባ ማረሚያ ቤት የመሰሪያ ወራንት ይጻፍ፡፤የብር 1000.00 (አንድ ሺህ) መቀጮ ለመንግሥት ገቢ ይደረግ፤የገንዖብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስቴር ያስፈጽም፤ይጻፍ።
የውሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይድረስ።
መዛገቡ ተዖግቷል። ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.