ቼክ አምጪው በስድስት ወር ጊዚ ውስጥ ባንክ ሣያቀርብ ይህንኑ ጊዚ አሳልፍ አንድ ዓመት ሣያልፍ ባንክ አቅርቦ በቼክ አውጪው ስም በቂ ስንቅ የላለው መሆኑን ያረጋገጠ ቼክ አምጪ ቼኩን መሰረት አድርጎ የሚያቀርበው ክስ አንድ ዓመት አላለፈም በሚል የሚያቀርበው ክስ ተቀባይነት የላለው ስለመሆኑ፣ በንግድ ህግ ቁጥር 881/1/ ስር በተመለከተው የአንድ ዓመት የጊዚ ገደብ ክስ የማቅረብ መብታቸው በህግ ፉት አስማማው በየነ እና አሰፊ ነጋሽ XXVII ሉኖር የሚችለው በን/ሕ/ቁ. 855 ስር ቼኩን በስድስት ወራት ጊዚ ውስጥ ለባንክ የማቅረብ ቅድመ ሁኔታ ሲያሟላ ስለመሆኑ፣ የን/ሕ/ቁ. 855፣881/1 ወንጀል
No summary available.
ሐምል 20 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ጳውልስ ኦርሺሶ ሰናይት አድነው አመልካች፡- አስማማው በየነ -ጠበቃ አዱሱ ወርቄ ቀረቡ ተጠረ ፡- አሰፊ ነጋሽ -የቀረበ የለም መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ ጉዲይ ላቀርብ የቻለው አመልካች መጋቢት 26 ቀን 2009 ዓ/ም በተጻፈ ማመልከቻ በሰሜን ጎንደር መስተዲደር ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 01-31103 ታህሳስ 21 ቀን 2009 ዓ/ም ተሰጥቶ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት 01-00874 የካቲት 28 ቀን 2009 ዓ/ም የጸናው ብይን መስረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወስን ሲባል ነው።
ክርክሩ ሲጀመር የአሁኑ አመልካች ከሳሽ፣የአሁኑ ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ። አመልካች ያቀረቡት ክስም ጥቅምት 04 ቀን 2009 ዓ/ም ባቀረቡት ክስ ተጠሪ 9 የሆነና በላዩ ላይ ብር 500,000.00(አምስት መቶ ሺህ ብር) የያዖ ቼክ የሰጧቸውና ይህንን ቼክ ይዖው ገንዖቡን ወጪ ለማድረግ መስከረም27 ቀን 2009 ዓ/ም ደባርቅ ከተማ ወደሚገኘው የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ሲሄደ ባንኩ በተጠሪ ተቀማጭ ሂሳብ ውስጥ በቂ ገንዖብ ስለላለ በቼኩ ላይ የታዖዖው ገንዖብ ሉከፍል እንደማይችል የገለፀላቸው መሆኑን ዖርዛረው ተጠሪው ገንዖቡን ከወለድ፣ ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዱከፍላቸው ይወሰን ዖንድ ዲኝነት ጠይቀዋል።
የሥር ተከሣሹም መከላከያ መልስ እንዱያቀርቡ ተፈቅድላቸው ህዲር 08 ቀን 2009 ዓ/ም በሰጡት መከላከያ መልስ ክሱ በይርጋ የሚታገድ ነው በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ አነስተዋል። በዘሁ ነጥብ ላይም ግራ ቀኙ እንዱከራከሩ ተደርጓል። የሥር ፍርድ ቤትም በይርጋ መቃወሚያ ላይ ግራ ቀኙ ያቀረቡትን ክርክር መርምሮ አመልካች በንግድ ህግ ቁጥር 855 በተመለከተው የጊዚ ገደብ ውስጥ ቼኩን ባንክ ያላቀረቡ መሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ መሆኑን በመያዛና በስድስት ወር ቼክ ለባንክ አቅርቦ ገንዖቡ ያልተከፈለው ቼክ አምጪ በን/ህ/ቁጥር 881 ስር በተመለከተው የይርጋ ጊዚ መብቱን ለማስከበር የሚችለው ከመጀመሪያውኑ በመብቱ ለመጠቀም እንዱችል ቼኩን ማቅረብ ካለበት የስድስት ወር ጊዚ ሳያበቃ ከአቀረበ ነው በሚል ምክንያት የአንድ አመት የይርጋ ጊዚ ለጉዲዩ ተፈፃሚነት የላለው መሆኑን በመገንዖብ አመልካችን ቼኩን መሰረት በማድረግ ያቀረቡት ክስ በይርጋ የታገደ ነው በማለት ብይን ሰጥቶአል። አመልካች ይህንኑ ብይን በመቃወም ይግባኙን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዖትም ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለው የይርጋ ጊዚ በን/ሕ/ቁጥር 881 ስር የተመለከተው የአንድ አመት ጊዚ ሁኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች ቼኩ ባንክ የቀረበው ስድስት ወር ካለፈ በኋላ ነው በማለት ክሱን በይርጋ ውድቅ ማድረጋቸው የን/ሕ/ቁጥር 885 እና 881 ድንጋጌዎችን ያላገናዖበ ነው የሚል ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በዘህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ይህ ችልትም ግራ ቀኙ በፅሐፍ እንዱከራከሩ አድርጎአል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ብይንና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ እንደሚከተለው መርምሮታል። በዘህም መሰረት አመልካች በተጠሪው ላይ በሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ በይርጋ የታገደ ነው ተብል በመወሰኑ የፈጸመው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለ? ወይስ የለም? የሚለውን ጭብጥ በሚከተለው መልኩ መርምረናል።
ከክርክሩ ሂደት መረዲት የታቸለው አመልካች ለክሱ መሰረት ያደረጉት ቼክ 9 ህዲር 14 ቀን 2008 ዓ/ም የተጻፈ ሁኖ ባንክ መስከረም 27 ቀን 2009 ዓ/ም ቀርቦ ተጠሪ በቂ ስንቅ የላቸውም በሚል ምክንያት አመልካች ገንዖቡ ሳይከፈላቸው ከተመለሰ በኌላ አመልካቹ በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረቱት ጥቅምት 04 ቀን 2009 ዓ/ም ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጡ ነጥቦች መሆናቸውን ነው።
በመሰረቱ ቼክ የንግድ ወረቀት ከሚባለ አንደ ሲሆን እንደቀረበ የሚከፈል፣በባንክ ተቀማጭ ሂሳብ ያለው ሰው ገንዖቡ ለራሱ ወይም ለላላ ወገን እንዱከፈል ሐተታ የላለው ትዔዙዛ የሚሰጥበት፣ገንዖብን ተክቶ ክፍያን የሚያቀላጥፍ የንግድ ወረቀት ወይም ሰነድ ስለመሆኑ ከን/ሕ/ቁጥር 732፣ 827፣828 እና 854 ድንጋጌዎች ይዖት የምንገነዖበው ጉዲይ ነው።ስለሆነም ቼክ እንደቀረበ የሚከፈል የገንዖብ ሰነድ በመሆኑ በቼክ ገንዖብ ለመክፈል አውጭው በባንክ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ የተቀመጠ የቼኩን ዋጋ አጣርቶ የሚከፍል፣በቂ ስንቅ (ገንዖብ) ሉኖረው የሚገባ ስለመሆኑም እርግጠኛ መሆን እንዲለበት የን/ሕ/ቁጥር 830 (2) ድንጋጌ ያስቀምጣል።ይህንኑ በሕግ የተጣለበትን ግዳታ ሳይወጣ የቀረ አውጪ በቼኩ ላይ የተፃፈውን ገንዖብ (እዲ) ለአምጪው እንዱከፍል የሚገደድ ስለመሆኑ የሕጉ ይዖትና መንፈስ የሚያስገነዛበን ጉዲይ ነው።ዔዲ ከፊዩ (አውጪው) ግዳታውን እንዱወጣ የማይገደደው በሕጉ የተቀመጡትን መቃወሚያዎች (መከራከሪያ ነጥቦችን) በአግባቡ ሲያስረዲ ነወ።በሕጉ እዲ ከፊዩ በአምጪው ላይ ሉያቀርብ ይችላል ተብለው የተቀመጡት መቃወሚያዎች በን/ሕ/ቁጥር 717 ስር የተመለከቱት ናቸው። እነዘህም፡-በሁለቱ የግል ግንኙነቶች ላይ የተመሰረቱ፣በሰነድ አጻጻፍ ፍርምና በሰነደ ላይ በተጻፈ ቃልች፣እንዱሁም ፊርማን በማስመሰል የተሰራ፣ ችልታ ወይም ሰነደ ሲወጣ የውክልና ሰልጣን ባለመኖሩ ወይም ክስ ለማቅረብ አስፈላጊ የሆኑት ሁኔታዎች ባለመሟላታቸው የሚነሱ መቃወሚያዎችና አምጭው ይህን ሰነድ ባገኘበት ጊዚ እዲ ከፊዩን ለመጉዲት እያወቀ ያደረገው መሆን ስለመሆናቸው የሚያሳዩ እንደሆነ ሕጉ አስቀምጧል።
እንግዱህ ቼክ እንደቀረበ የሚከፈል እንደመሆኑ መጠን አውጪው ለቼኩ መውጣት ምክንያት የሆነውን ነገር የማስረዲት እና የማስተባበል ሸክም ያለበት ስለመሆኑ ከሕጉ ቅርፅ፣ይዖትና መንፈስ በቀላለ የምንገነዖበው ጉዲይ ሲሆን በቼኩ የተጻፈውን ገንዖብ ለመክፈል አልገደድም የሚለው አውጪው ከላይ በን/ሕ/ቁጥር 717 ስር የተመለከቱትን ሁኔታዎች በበቂ እና አሳማኝ መንገድ ማስረዲት ግዳታውን ሲወጣ ስለመሆኑ ግልጽ ነው። እነዘህ በሕጉ የተመለከቱት ሁኔታዎች ቼኩን በቼክነቱ መሰረታዊ የሆኑ መብቶችን ማስገኘትና ግዳታዎችን ደግሞ ለማስከትል የሚያስችለ መሆናቸውን የሚያስገነዛቡ ነው። በመሆኑም ቼክ በቼክነቱ የሚያስገኘውን መብት ለመጠቀም በህጉ የተመለከቱ ሁኔታዎች ተሟልተው መገኘት አለባቸው። ቼክ በቼክነቱ የሚያስገኛቸው መብቶች ቀሪ ከሚሆንባቸው ምክንያቶች አንደ የይርጋ ጉዲይ ነው።
ከይርጋ አንፃር ጉዲዩ ሲታይም አንድ ቼክ ከተፃፈበት ቀን ጀምሮ ባለት 6 ወራት ጊዚያት ውስጥ ወደ ባንክ ለክፍያ መቅረብ ያለበት ስለመሆኑ የን/ሕ/ቁጥር 855 አስገዲጅነት ባለው መልኩ የሚደነገግግ ሲሆን በስድስት ወር ጊዚ ውስጥ ለባንክ ቀርቦ ክፍያው ካልተፈፀመም ቼክ አምጪው ቼኩ ለባንክ የቀረበበት ጊዚ ካለፈ ጀምሮ ባለት ስድስት ወራት ውስጥ ፍርድ ቤት ክስ በማቅረብ መብቱን ማስከበር የሚችል መሆኑን በን/ሕ/ቁጥር 881(1) ስር በግልጽ ተመልክቶአል።
የን/ሕ/ቁጥር 855 እና 881(1) አንድ ላይ ሲነበቡ የክስ ማቅረቢያ ጊዚ በቼኩ ላይ ከተፃፈበት ጊዚ ጀምሮ በሚቆጠር አንድ አመት ጊዚ መሆኑን ያስገነዛባለ። ይሁን እንጂ ይህ ጊዚ መያዛ ያለበት ቼኩ በን/ሕ/ቁጥር 855 ስር ሕግ አውጪው በአስገዲጅነት በደነገገው አግባብ ቼኩ ከተፃፈበት ጊዚ ጀምሮ በስድስት ወራት ጊዚ ውስጥ ባንክ መቅረቡ ሲረጋገጥ ነው። በመሆኑም በን/ሕ/ቁጥር 855 ስር በተመለከተው የስድስት ወር ጊዚ ውስጥ ባንክ ሳያቀርብ ይህንኑ ጊዚ አሳልፍ አንድ አመት ሳያልፍ ባንክ አቅርቦ በቼክ አውጪው ስም በቂ ስንቅ የላለው መሆኑን ያረጋገጠ ቼክ አምጪ ቼኩን መሰረት አድርጎ የሚያቀርበው ክስ አንድ አመት አላለፈበትም በሚል ክሱ ተቀባይነት የሚያገኝበት አግባብ ሉኖር አይችልም። አመልካች በን/ሕ/ቁጥር 881(1) ስር በተመለከተው የአንድ አመት የጊዚ ገደብ ክስ የማቅረብ መብታቸው በሕግ ፉት ተቀባይነት ሉኖር የሚችለው በን/ሕ/ቁጥር 855 ስር ቼኩን በስድስት ወራት ጊዚ ውስጥ ለባንክ የማቅረብ ቅድመ ሁኔታ ሲያሟለ ነው። ይህ ቅድመ ሁኔታ ሳይሟላ ቼኩን መሰረት አድርገው የሚያቀርቡት ክስ በን/ሕ/ቁጥር 855 እና 881(1) ድንጋጌ አግባብ ይርጋው የሚቆጠርበት ህጋዊ ምክንያት የለም።
በእነዘ ሁለ ምክንያቶች ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በሰሜን ጎንደር መስተዲደር ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 01-31103 ታህሳስ 21 ቀን 2009 ዓ/ም ተሰጥቶ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት 01-00874 የካቲት 28 ቀን 2009 ዓ/ም የጸናው ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
የአመልካች የቼክ ክስ በይርጋ የታገደ ነው ተብል ክሱ ውድቅ በመደረጉ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለም ብለናል።
በዘህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣ ወጪና ኪሳራ ግራ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻቻለ ብለናል።
መዛገቡ ዖግቷል፤ ወደ መዛገብ በት ይመለስ ብለናል።
No topics extracted.