No summary available.
ሚያዘያ 25 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- ዓሉ መሐመድ ተኽሉት ይመሰል ተፈሪ ገበሩ ቀነዓ ቂጣታ ፀሐይ መንክር አመልካች፡- አቶ ጌታቸዉ መሸሻ - ጠበቃ አለማየሁ ብርሀኔ ቀርበዋል።
ተጠሪ፡- አቶ ተሾመ ወልዳ - ጠበቃ ገመዲ ስፊው ቀርበዋል።
መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለዉ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር ጉዲይ ለዘህ ችልት ላቀርብ የቻለዉ የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ.232927 በ26/04/2008 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ እንዱታረምልኝ በማለት የአሁን አመልካች ያቀረበዉን የሰበር አቤቱታ መርምሮ ለመወሰን ነዉ።
የጉዲዩ አመጣጥ ሲታይ በአዲማ ልዩ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች ከሳሽ፣ የአሁን ተጠሪ ተከሳሽ ሁኖ ሲከራከሩ የነበረ ሲሆን፣ ከሳሽ ባቀረበዉ ክስ ከሳሽ በ16/3/2006 ዓ.ም በቼክ ቁጥር በሆነዉ /አንድ መቶ ሺህ/ ለተከሳሽ አበድሬዉ ስላልመለሰልኝ ይህን ገንዖብ ከሕጋዊ ወለድ 9% ጋር እንዱከፍለኝ በማለት ከሷል። የሥር ተከሳሽ ባቀረበዉ መልስ ከከሳሽ ገንዖብ አልተበደርኩም እኔን ለመክሰስ መብቱን አላስረዲም በማለት ተከራክሯል።
ከዘህ በኋላ ፍ/ቤቱ ጉዲዩን በመመርመር በሰጠዉ ዉሳኔ ከሳሽ በክስ የተጠቀሰዉን /አንድ መቶ ሺህ/ ለተከሳሽ ስለማበደሩ የፍ/ብ/ሕ/ቁ.2472 በሚደነግገዉ አግባብ ያቀረበዉ ማስረጃ ስለላለ ከሳሽ በዘህ ገንዖብ ተከሳሽን ለመጠየቅ ሕጋዊ መብት የለዉም፣ ቼኩን የተቀበልኩት ከሳሽ ገንዖብ አበድሮኝ ሳይሆን አስቀድሞ የሰጡሁትን ገንዖብ ከፍልኝ ነው በማለት ክሱን ዉድቅ በማድረግ ወስኗል፡ የሥር ከሳሽ በዘህ ዉሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱ ግራ ቀኛቸዉን በማከራከር የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የሥር ከሳሽ አሁንም ይህን ዉሳኔ በመቃወም የሰበር አቤቱታ ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ያቀረበ ቢሆንም ችልቱ የቀረበዉን አቤቱታ ዉድቅ በማድረግ የሥር ፍ/ቤት ዉሳኔ በማጽናት ወስኗል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበዉ ይህን ትዔዙዛ በመቃወም ለማስለወጥ ነዉ።
የአሁን አመልካች የካቲት 17 ቀን 2008 ዓ.ም የተጻፈ ሶስት ገጽ አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን፣ የሥር ፍ/ቤቶች ዉሳኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመመባቸዉ በመሆናቸዉ ተሽረዉ ተጠሪ የተበደረዉን ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ/ ከሕጋዊ ወለድ ጋር እንዱከፍለዉ በዛርዛር ቅሬታቸዉን አቅርቧል።
የሰበር አጣር ችልት ይህን ጉዲይ በማየት ፣አመልካች ለተጠሪ ቼክ ሰጥቷቸዉ ከባንክ ገንዖብ መዉሰዲቸዉ ተረጋግጦ እያለ የብድር ዉል አቅርበዉ አላስረደም በማለት የተከሰሱበትን ገንዖብ እንዲይከፍለ የመወሰኑን አግባብነት ከ
ከተሰጠዉ ትርጉም አንጻር ለመመርመር ሲባል፣ አቤቱታዉ ያስቀርባል በማለት ተጠሪ መልስ እንዱሰጥ በታዖዖዉ መሰረት በ1/2/2009 ዓ.ም የተጻፈ ሶስት ገጽ መልስ አቅርቧል። የመልሱም ይዖት በአጭሩ፡--የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዉሳኔዎች የሕግ ስህተት የላላቸዉ ስለሆነ የቀረበዉ አቤቱታ ዉድቅ ሆኖ የሥር ዉሳኔ እንዱጻናልኝ በማለት በዛርዛር ተከራክሯል። የአሁን አመልካች የሰበር አቤቱታዉን በማጠናከር የመልስ መልስ አቅርቧል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተዉ ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኛቸዉን ክርክር ለሰበር አቤቱታዉ መነሻ ከሆነዉ ዉሳኔ እና አግባብነት ካላቸዉ የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዖብ እንዱሁም አቤቱታዉ ያስቀርባል ሲባል ከተያዖዉ ጭብጥ አንጻር እንደሚከተለዉ መርምሮታል።
የአሁን አመልካች ባቀረበዉ ክስና ክርክር ለተጠሪ በቼክ አንድ መቶ ሺህ ብር አበድሬዉ ስላልከፈለኝ እንዱከፍለኝ በማለት ጠይቋል። ተጠሪ በበኩለ ቼኩን መቀበለን ሳይክድ ቀደም ሲል የሰጠሁትን ገንዖብ መልሶልኝ ነዉ፣ ገንዖብ አልተበደርኩም፣ ገንዖብ የተበደርኩኝ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ/2472 መሰረት የሚያስረዲ ማስረጃ አላቀረበም በማለት ተከራክሯል። ከግራ ቀኛቸዉ ክርክር መገንዖብ እንደሚቻለዉ የአሁን ተጠሪ ከአመልካች ቼኩን ተቀብል ገንዖቡን ከባንክ መዉሰደን ሳይክድ፣ ነገር ግን ገንዖብ ተብድሬዉ አይደለም በማለት /አንድ መቶ ሺህ/ ብድር መኖሩን ክድ ተከራክሯል። ይህ ከሆነ የአሁን አመልካች ለተጠሪ ይህን ገንዖብ በብድር ስለመስጠቱ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.259 /1/ በሚደነግገዉ አግባብ የማስረዲቱ ሸክም የእርሱ ነዉ። አመልካች በዘህ መሰረት አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ብድር መኖሩን ያስረዲ እንደሆነ ተጠሪ ደግሞ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.259 /2/ በሚደነግገዉ መሰረት የመከላከያ ማስረጃ አቅርቦ የማስረዲት ሸክም ይኖርበታል ማለት ነዉ።
No topics extracted.
ይህ ከሆነ የአሁን አመልካች ያቀረበዉን /አንድ መቶ ሺህ/ ብድር ገንዖብ ለማስረዲት አግባብነት ያለዉ ማስረጃ ምንድን ነዉ? የሚለዉ ነጥብ መታየት ያለበት ጉዲይ ነዉ።
አመልካች ባቀረበዉ ክርክር ከክሱ ጋር አያይዜ ያቀረበዉ ቼክ የብድር ዉለን ለማስረዲት አግባብነት እንዲለዉ ነዉ። ነገር ግን በመሰረቱ ቼክ የተወሰነ ገንዖብ ለመክፈል ሐተታ የላለበት ትዔዙዛ የያዖና ቼኩም እንደቀረበ የሚከፈል ስለመሆኑ በንግድ ሕጉ ቁጥር 827 /ሀ/ እና 854 ሥር ተደንግጓል። ከእነዘህ ድንጋጌዎች መገንዖብ የሚቻለዉ ቼክ ክፍያ የሚፈጸምበት ወይም የክፍያ ሰነድ መሆኑን ነዉ። ከዘህ ዉጭ ግን ቼክ የብድር ዉልን ተክቶ ብድር መኖሩን ለማስረዲት አግባብነት ያለዉ ሰነድ ነዉ ለማለት የሚያስችል የሕግ መሰረት የለም። ይህ ከሆነ አመልካች ከክሱ ጋር የቀረበዉ ቼክ የብድር ዉል መኖሩን ያረጋግጣል በማለት ያቀረበዉ ክርክር ተቀባይነት የለዉም።
የአሁን አመልካች በክሱ የጠቀሰዉ ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ/ ለተጠሪ በብድር ሰጥቼዋለሁ የሚል ከሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2472 የተመለከተዉን አግባብነት ያለዉን ማስረጃ በማቅረብ የማስረዲት ሸክም አለበት። የዘህ ድንጋጌ ንዐስ አንቀጽ 1 እንደሚደነግገዉ ፣በብድር የተሰጠዉ ገንዖብ 500 /አምስት መቶ/ የኢትዮጵያ ብር በላይ ሲሆን የብድሩ ዉል በጽሐፍ ወይም በፍ/ቤት በተደረገ የእምነት ቃል ወይም መሐላ ካልሆነ በቀር ለማስረዲት አይቻል፣ በማለት ደንግጓታል። በዘህ አግባብ ሲታይ የአሁን አመልካች ለተጠሪ ብር 100,000 ስለማበደሩ ወይም የብድር ዉል ስለመኖሩ በዘህ ድንጋጌ አግባብ በሚቀርብ ማስረጃ ማስረዲት ይጠበቅበታል። ነገር ግን አመልካች ደግሞ በዘህ መሰረት ያቀረበዉ የብድር ዉል ሰነድ ስለላለ ለተጠሪ ገንዖቡን ስለማበደሩ የማስረዲት ሸክሙን ተወጥቷል ለማለት አይቻልም። የአሁን አመልካች ከጀምሩ በሕጉ አግባብ የብድር ዉል መኖሩን ባላስረዲበት ሁኔታ ተጠሪ የመከላከያ ማስረጃ አቅርቦ ገንዖቡን እንዲልተበደረዉ የሚያስረዲበት የሥነ ሥርዓት ሕግ አካሄድ ስለላለ በዘህ ረገድ ያቀረበዉ ቅሬታ ተቀባይነት የለዉም። የሰበር አጣር ችልት አቤቱታዉ ያስቀርባል በሚልበት ጊዚ የጠቀሰዉ
/ቅጽ 5/ ላይ የተሰጠዉ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሲታይ በመጀመሪያ ደረጃ ጉዲዩ የሚመለከተዉ የሐዋላ ወረቀት እንጂ ቼክን ስላልሆነ በዉሳኔዉ የተጠቀሱት ፍሬ ነገሮችም ተመሳሳይነት ስለላላቸዉ ተፈጻሚነት የለዉም ብለናል።
ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች የአሁን አመልካች ለተጠሪ /አንድ መቶ ሺህ/ ያበደረ ስለመሆኑ አግባብነት ባለዉ ማስረጃ ስላላስረዲ ክሱ ተቀባይነት ያለዉም በማለት ክሱን ዉድቅ በማድረግ የሰጡት ዉሳኔ በሕጉ አግባብ የተሰጠ ነዉ ከሚባል በስተቀር በዘህ ችልት ሉታረም የሚችል መሰረታዊ የሕግ ስህተት ስለላለዉ የሚከተለዉ ዉሳኔ ተሰጥቷል።
የአዲማ ልዩ ዜን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.20647 በ15/11/2007 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እና ይህን ዉሳኔ በማጽናት የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ.ቁ.226770 በ07/04/2008 ዓ.ም የሰጠዉ ዉሳኔ እንዱሁም የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ.ቁ.232927 በ26/4/2008 ዓ.ም የሰጠዉ ትዔዙዛ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያልተፈጸመባቸዉ ስለሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348 /1/ መሰረት ጸንቷል።
የዘህ ዉሳኔ ግልባጭ ለሥር ፍ/ቤቶች ይድረስ ብለናል።
ግራ ቀኛቸዉ በዘህ ችልት የደረሰባቸዉን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸዉን ይቻለ ብለናል።
በ27/12/2008 ዓ/ም እና ጥቅምት 16 ቀን 2009 ዓ/ም የተሰጠው የእግድ ውሳኔ ተነስቷል ይፃፍ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።