በአንድ የህብረት ስራ ማህበር ውስጥ አባል የሆነ ሰው በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በአካል ተገኝቶ ድምፅ መሰጠት ያለበት ስለመሆኑ እና ይህ ሁኔታ /አጠቃላይ መርህ/ ሉታለፍ የሚችለው መረጃ ላቀርብበት የሚችል ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥም ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 147/91 /በአዋጅ ቁጥር 402/96 እንደተሻሻለ አንቀጽ 18/2/
No summary available.
ታህሳስ 27 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ ተፈሪ ገብሩ አብዬ ካሣሁን እትመት አሰፊ አመልካች፡- ምድረ ልዙ የጋራ ሕንጻ መኖሪያ ቤት የህብረት ስራ ማህበር -ም/ሉ/መንበር አቶ ኃይላ ገ/ማርያም ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ይሕደጎ ኪዲኔ -ቀረቡ መዛገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ከማህበር አባልነት ማሰናበትን በመቃወም ከቀረበ ክስ ጋር ተያይዜ የተነሳ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን አመልካች አቤቱታውን ለዘህ ችልት ያቀረበው በኀብረት ስራ ማኅበራት አዋጅ ቁጥር 147/1991 መሰረት በተቋቋመው የሽምግልና ጉባኤ በ01/11/2003 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ በ16/03/2007 ዓ.ም የተሻሻለው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ነው።
ተጠሪው በ28/06/2003 ዓ.ም. አዖጋጅተው ለሽምግልና ጉባኤው ያቀረቡት ክስ አጭር ይዖት የማህበሩ መስራች አባል መሆናቸውን፣ማህበሩ አባላት ባልሆኑ ግለሰቦች የሚመራ መሆኑን፣ ወጪና ገቢውም የማይታወቅ መሆኑን፣የቤቶች ዔደላም በማህበሩ ውስጠ ደንብ መሰረት በዔጣ መሆን ሲገባው ከዘህ ውጪ በሆነ አሰራር የታደለ መሆኑን እና ማህበሩ ላልችንም ጥፊቶች እየፈጸመ መሆኑን ገልጸው ተገቢው እርማት እንዱደረግ ለማህበሩ እና ቀጥለውም ማህበሩን ለሚቆጣጠረው የቦላ ክፍለ ከተማ የህብረት ስራ ማህበራት ማደራጃና ማስፊፉያ ጽ/ቤት በ14/06/2000 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ መጠየቃቸውን፣ይህን የመብት ጥያቄ በማቅረባቸውም ምልዓተ ጉባኤው ሳይሟላ እና ምንም ዓይነት ማስጠንቀቂያ ሳይሰጣቸው ማህበሩ በ07/07/2000 ዓ.ም እና በ02/13/2000 ዓ.ም ባደረጋቸው ስብሰባዎች ተጠሪን ከማህበሩ አባልነት ያሰናበተ መሆኑን የሚገልጽ ሆኖ ውሳኔው ተሽሮ ወደ ማህበሩ እንዱመለሱ ይወሰንላቸው ዖንድ ዲኝነት የተጠየቀበት ነው።
አመልካቹ በ23/07/2003 ዓ.ም በፍሬ ጉዲዩ ረገድ በሰጠው መልስ ተጠሪው ከማህበሩ እንዱሰናበቱ የተደረገው በማህበሩ ላይ በፈጸሙት በደል መሆኑን፣ከእነዘህም መካከል በፀሀፉነት ተመርጠው አልሰራም ማለታቸው፣በማህበሩ ላይ የማቴርያል ኪሳራ እንዱደርስ ማድረጋቸው/ለምሳላ በብር 290 የሚገዙን አንድ መኪና ድንጋይ በራሳቸው ፈቃድ በብር 300 መግዙታቸው/፣ክፍያን በወቅቱ አለመፈጸማቸው፣ቤቶቹ ተሰርተው ካለቁ በኃላም ቢሆን እቀያይራቸዋለሁ ብለው መዙታቸው እና ፀሐፉ ሆነው በሰሩበት ጊዚ የያዝቸውን ሰነድች እንዱያስረክቡ ሲጠየቁ ማዖግየታቸው የሚጠቀሱ መሆኑን እና ከአባልነት የማሰናበት ውሳኔው የተላለፈው በተሟላ ምልዓተ ጉባኤ መሆኑን በመግለጽ ክሱ ውድቅ እንዱደረግ ተከራክሮአል።
ጉባኤውምየግራ ቀኙን ክርክር እና ማስረጃ ከመረመረ በኃላ በ07/07/2000 ዓ.ም ውሳኔ የተላለፈው ባልተሟላ ምልዓተ ጉባኤ እንደሆነ በአመልካቹም መታመኑን፣በ02/13/2000 ዓ.ም በተደረገው ስብሰባም ከማህበሩ 24 መስራች አባላት መካከል በአካል ተገኝተው ድምጽ የሰጡት ዖጠኝ አባላት ብቻ መሆናቸውን፣አራቱ መስራች አባላት ድምጽ ሰጥተዋል የተባለው በአዋጅ ቁጥር 147/1991 አንቀጽ 18 ከተመለከተው ውጪ በውክልና በመሆኑ ድምጻቸው ሉቆጠር የማይገባው መሆኑን፣ተተኪ አባላት ናቸው የተባለት ስምንት ሰዎች ስለመተካታቸው ለማህበራት ማደራጃ ጽ/ቤት በደብዲቤ የተገለጸ ቢሆንም በማህበሩ ውስጥ የተተኩበትን አግባብ የሚመለከት ሰነድ እንዱያቀርብ ተጠይቆ ማህበሩ ማናቸውንም ሰነድ ማቅረብ ያልቻለ በመሆኑ ድምጻቸው ሉቆጠር የማይገባው መሆኑን፣በዘህ አግባብ በማህበሩ ውስጠ ደንብ ከተመለከተው ስርዓት ውጪ ቁጥራቸው ከግማሽ በታች በሆነ የማህበሩ አባላት የተሰጠ ውሳኔ አንድን አባል የማሰናበት ውጤት ሉኖረው የማይገባ መሆኑን፣ተጠሪው የፈጸሙት ጥፊት አለ ቢባል እንኳ በማህበሩ ውስጠ ደንብ አንቀጽ 17 እና 23 መሰረት ቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ተግሳጽ በጽሁፍ ሳይሰጣቸው በቀጥታ የስንብት እርምጃ መውሰድ የማይቻል መሆኑን ገልጾ ተጠሪው ወደ ማህበሩ አባልነት ተመልሰው ድርሻቸውን በዔጣ የማግኘት መብትን ጨምሮ መብቶቻቸው እንዱከበሩ እና ግዳታዎቻቸውን እንዱወጡ እና የማህበሩ ሂሳብም በውጪ ኦዱተር እንዱመረመር በአብላጫ ድምጽ ውሳኔ ሰጥቶአል።
በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ባቀረበው ይግባኝ ሳቢያ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የሽምግልና ጉባኤው በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ እንዱሰናበት የተደረገን አባል ወደ ማህበሩ እንዱመለስ የመወሰን ስልጣን እንደላለው እና ክሱም በይርጋ የታገደ እንደሆነ ገልጾ የሽምግልና ጉባኤውን ውሳኔበመዛገብ በ22/08/2004 ዓ.ም ሽሮት የነበረ ቢሆንም የአሁኑ ተጠሪ በተራቸው ባቀረቡት ይግባኝ ሳቢያ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔን ሽሮ የፍሬ ጉዲይ ክርክሩን መርምሮ ውሳኔ እንዱሰጥበት በመዛገብ በ30/07/2005 ዓ.ም በተሰጠ ውሳኔ ጉዲዩን ለከፍተኛ ፍርድ ቤት የመለሰው መሆኑን የመዛገቡ ግልባጭ ያመለክታል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በተመለሰለት መሰረት የፍሬ ጉዲይ ክርክሩን መርምሮ የማህበሩ ሂሳብ እንዱጣራ ውሳኔ የተሰጠው ባልተጠየቀ ዲኝነት መሆኑን ገልጾ በዘህ ረገድ የተሰጠውን የውሳኔ ክፍል በመሻር እና ተጠሪው ወደ ማህበሩ እንዱመለሱ የተሰጠውን የውሳኔ ክፍል ግን በማጽናት የጉባኤውን ውሳኔ አሻሽልአል።አመልካች ለዘህ ችልት ያቀረበው አቤቱታ ተመርምሮ በዘህ ጉዲይ ተጠሪን ከማህበሩ ለማሰናበት በውክልና ድምጽ የሰጡት እና ተተኪ አባላት የሆኑትም ጭምር የማህበሩ አባላት ናቸው ወይም አይደለም ሳይባል ድምጻቸው አይቆጠርም ተብል በስር ፍርድ ቤቶች የመወሰኑን አግባብነት ከአዋጁ እና ከማህበራት መተዲደሪያ ደንብ እንጻር ተጠሪው ባለበት ለማጣራት ይቻል ዖንድ ጉዲዩ ለሰበር ክርክር እንዱቀርብ በመደረጉ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክር ተለዋውጠዋል።የጉዲዩ አመጣጥ እና የክርክሩ ይዖት ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን አለመሆኑን ለክርክሩ ከተያዖው ነጥብ አንጻር መርምረናል።
በዘህም መሰረት ተጠሪውን ከማህበር አባልነት ለማሰናበት በውክልና ድምጽ የሰጡት አባላት ድምጽ ሉቆጠር አይገባውም በሚል የተሰጠውን የውሳኔ ክፍል በተመለከተ ማንኛውም የመሰረታዊ ማህበር አባል በስብሰባ ላይ ተገኝቶ ራሱ ድምጽ መስጠት ያለበት ስለመሆኑ በኅብረት ስራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 147/1991 /በአዋጅ ቁጥር 402/1996 እንደተሻሻለ/ በአንቀጽ18 (2) ስር ተመልክቶአል።ማንኛውም አባል በጠቅላላ ጉባኤ ላይ በአካል ተገኝቶ ድምጽ መስጠት ያለበት ስለመሆኑም የአመልካች ማህበር መተዲደሪያ ደንብ በአንቀጽ 8 (1) ስር በግልጽ ያመለክታል።ይህ አጠቃላይ መርህ ሉታለፍ የሚችለው መረጃ ላቀርብበት የሚችል ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥም ስለመሆኑም በዘሁ ደንብ በአንቀጽ 21.1.5 ስር ተመልክቶአል።በተያዖው ጉዲይ ተጠሪውን ከማህበሩ አባልነት ለማሰናበት አራት ሰዎች ድምጽ የሰጡት በውክልና መሆኑ አልተካደም።ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ሲያጋጥም በውክልና ድምጽ መስጠት እንደሚቻል ገልጾ አመልካች በሰበር አቤቱታው የተከራከረ ቢሆንም አራቱ ሰዎች በውክልና ድምጽ እንዱሰጡ የተደረገው ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ስለመሆኑ በ02/13/2000 ዓ.ም. በተያዖው ቃለ ጉባኤ ላይ የተገለጸ ነገር ስላለመኖሩ እና በዘህ ረገድ አመልካቹ በስር ፍርድ ቤቶች ያቀረበው ማስረጃ ስላለመኖሩ ተጠሪው በሰበር መልሳቸው ያቀረቡትን የክርክር ነጥብ አመልካቹ በመልስ መልሱ ማስተባበያ አልሰጠበትም።ጉዲዮችን በውክልና የማስፈጸም መብትን አስመልክቶ በአዋጁ እና በማህበሩ መተዲደሪያ ደንብ ላይ የተመለከቱት ድንጋጌዎች በሕገ መንግስቱ፣በቤተሰብ ሕጉ እና በፍትሐብሕር ሕጉ የተመለከቱትን አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች የሚቃረኑ ናቸው በማለት አመልካች እያቀረበ ያለው ክርክርም የአዋጅ ቁጥር 147/1991 ‛ን“ ዓላማ እና የማህበሩን መተዲደሪያ ደንብ አንቀጽ 8 (1) እና 21.1.5 ግልጽ ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ ባለመሆኑ ተቀባይነት ሉሰጠው የሚገባ ሆኖ አልተገኘም።በመሆኑም ማንኛውም የማህበሩ አባል በጠቅላላ ጉባኤ በሚተላለፈ ውሳኔዎች ላይ ድምጽ መስጠት ያለበት በመርህ ደረጃ በአካል ተገኝቶ ስለመሆኑ በአዋጁ እና በመተዲደሪያ ደንቡ ላይ በግልጽ የተመለከተ እስከሆነ ድረስ እና የዘህን መርህ ተፈጻሚነት የሚያስቀር የተለየ ሁኔታ የነበረ ስለመሆኑ በስር ፍርድ ቤቶች በአመልካቹ የቀረበ ክርክር እና ማስረጃ እስከላለ ድረስ ተጠሪውን ከማህበሩ አባልነት ለማሰናበት በውክልና ድምጽ የሰጡት አባላት ድምጽ ሉቆጠር የሚገባው አይደለም በማለት በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የውሳኔ ክፍል የሚነቀፍበትን ሕጋዊ ምክንያት አላገኘንም።
ተተኪ አባላትን በተመለከተ ስምንቱ ተተኪ አባላት በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ተጠሪውን ከማህበር አባልነት በማሰናበት ውሳኔ ላይ ድምጽ የሰጡት በ02/13/2000 ዓ.ም መሆኑ እና አመልካቹ ማህበር ተጠቃሾቹ ግለሰቦች በላልች አባላት ምትክ በማህበሩ የገቡ ስለመሆኑ ለክፍለ ከተማው የማህበራት ማደራጃና ማስፊፉያ ጽ/ቤት የገለጸው ድምጹ ከተሰጠ ከአንድ ወር በኃላ በ27/01/2001 ዓ.ም መሆኑን የሽምግልና ጉባኤው ውሳኔ ያመለክታል።አመልካቹም የእነዘህን ፍሬ ነገሮች ክንውን ቅደም ተከተል አስመልክቶ ያቀረበው የማስተባበያ ክርክር የለም።
ስምንቱ ተተኪ አባላት በማህበሩ አባልነት የተተኩበትን አግባብ በሚያመለክት ማህበሩ ማናቸውንም ዓይነት ሰነድ ማለትም የውርስ፣የስጦታ፣የሽያጭ፣ድርሻ የማስተላለፍ፣በተተኪ አባልነት የመቀበል ቃለ ጉባኤ እና መሰል ሰነድችን እንዱያቀርብ ተጠይቆ ማቅረብ ያልቻለ ስለመሆኑም በጉባኤው ውሳኔ ላይ ሰፍሮ ይገኛል።አመልካቹ እነዘህ ሰነድች ተሟልተው የነበረ ስለመሆኑ በሰበር አቤቱታው ላይ ያቀረበው ክርክር የለም።እንዱህ ከሆነ ደግሞ ተተኪ አባላቱ ተጠሪው ከማህበር አባልነት እንዱሰናበቱ ድምጽ በሰጡበት ቀን በርግጥ የማህበሩ አባላት የነበሩ መሆኑን ማረጋገጥ የሚቻልበት አግባብ አይኖርም።በመሆኑም ተተኪ አባላት ናቸው በተባለት ሰዎች የተሰጠውንም ድምጽ ባለመቀበል በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የውሳኔ ክፍልም የሚነቀፍ ሆኖ አልተገኘም።
ተጠሪን ከማህበሩ ለማሰናበት በውክልና ድምጽ የሰጡት እና ተተኪ አባላት የሆኑትም ጭምር የማህበሩ አባላት ናቸው ወይም አይደለም ሳይባል ድምጻቸው አይቆጠርም ተብል የመወሰኑን አግባብነት ለማጣራት በሚል ለክርክሩ በጭብጥነት የተያዖውን ነጥብ በተመለከተ በመሰረቱ በጉባኤው ዖንድ አከራካሪ ሆኖ የቀረበው እና ውሳኔ ያረፈበት ጭብጥ ተጠቃሾቹ ግለሰቦች ተጠሪውን ከማህበሩ አባልነት ለማሰናበት በተላለፈው ውሳኔ ላይ የሰጡት ድምጽ ሉቆጠር ይገባል ወይስ አይገባም? የሚል እንጂ የማህበሩ አባላት ናቸው ወይስ አይደለም? የሚል ባለመሆኑ የጉባኤው ውሳኔ የድምጽ አሰጣጥ ስርዓቱን በተመለከተ ካልሆነ በቀር በላልች ጉዲዮች ረገድ የተጠቃሾቹን ግለሰቦች መብት የሚነካ አይደለም።በመሆኑም በውክልና ድምጽ የሰጡትም ሆነ ተተኪ አባላት ከማህበሩ ጋር ያላቸውን የግንኙነት ሁኔታ በጭብጥነት መያዘም ሆነ በዘህ ነጥብ ላይ ውሳኔ ማሳረፈ አስፈላጊ የሚሆንበት ምክንያት አልተገኘም።
ሲጠቃለል አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ ስላልተገኘ የሚከተለው ውሳኔ ተሰጥቶአል።
በአብላጫ ድምጽ ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ በ16/03/2007 ዓ.ም. የተሻሻለው ውሳኔ በፍትሐብሕር ስነ ስርዓት ሕግ ቁጥር 348 (1) መሰረት ፀንቶአል።
የሰበር ክርክሩ ያስከተለውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ውሳኔ ያገኘ ስለሆነ መዛገቡ ተዖግቷል።