No summary available.
ሚያዘያ 16 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ጳውልስ ኦርሺሶ ሰናይት አድነው አመልካች፡- 1ኛ. ወ/ሪት ቅድስት ዮሴፍ 2ኛ. አቶ ኃይለየሱስ ዬሴፍ ጠበቃ ምትክ ኦለማ ቀረቡ ተጠሪ፡-
ጉዲዩ የቤት ይለቀቅልን ክርክርን መሰረት ያደረገ ሲሆን የተጀመረውም በፉንፉኔ ዘሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። በዘህ ፍርድ ቤት ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪዎች ሲሆን ተጠሪዎችና ሓለን አለማየሁ የተባለት ግለሰብ ደግሞ ተከሳሽ ነበሩ። አመልካቾች ባቀረቡት ክስም ወ/ሮ ምንትዋብ አለማየሁ የተባለት ግለሰብ ወላጅ እናታቸው መሆናቸውንና ወራሽነታችን ማረጋገጣቸውን፣ ሟች በሕይወት እያለም ግምቱ ብር 250,000.00 የሆነ ቤት በሰበታ ከተማ አስተዲደር ቀበላ 02 ክልል ውስጥ ያፈሩ መሆኑን፣ ይህንን ቤት ከሕግ ውጪ ተከሳሾች ይዖው እንደሚገኙ ገልጸው ቤቱ እንዱለቀቅላቸው ይወሰን ዖንድ ጠይቀዋል። የሥር ተከሳሾችም ከሳሾች የንብረት ባለቤትነት ክርክርና የውርስ ክርክር አደባልቀው የባለቤትነት መብት ሳይኖራቸው መከራከር ስለማይችለ ክስ ለማቅረብ እንደማይችለ፣ ጉዲዩ በመ/ የታዬና በድጋሚ ክስ ላቀርብበት የማይገባ መሆኑን፣ አውራሻቸው አቶ አለማየሁ በላቸው የውርስ ማስረጃ በስር ፍርድ ቤት በመ/ ያገኙትን በማሻር የተሰጠውን ውሳኔ ይግባኝ ብለው ክርክር ላይ መሆናቸውን፣ ክሱ በሶስት አመት ይርጋ የታገደ መሆኑን የሚመለከቱ ነጥቦችን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት አስነተዋል። በፍሬ ነገሩ ላይም ተገቢ ነው ያለትን ክርክር አቅርበዋል።
የስር ፍርድ ቤትም በተከሳሾች በኩል ከቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ነጥቦች መካከል ይርጋን የሚመለከተውን መቃወሚያ ብቻ ተቀብል ክሱ በሶስት አመት ይርጋ የታገደ ነው በማለት ውድቅ አድርጎታል። በዘህ ብይን የስር ከሳሾች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ አመልካቾች የእናታቸው የወ/ሮ ምንትዋብ አለማየሁ ወራሽ ነን በማለት የሚከራከሩና ተከሳሾች ደግሞ የአቶ አለማየሁ በላቸው ወራሽ ነን በማለት የሚከራከሩ በመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 1000 ለጉዲዩ ተፈፃሚነት የለውም በማለት የአመልካቾች ክስ በይርጋ የሚታገድ አይደለም፣ ፍሬ ነገሩ ተጣርቶ ሉወሰን ይገባል በማለት ጉዲዩን ለዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መልሶ ልኮለታል። በዘህ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሳኔ የአሁኑ ተጠሪዎች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን አቅርበው ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ ጉዲዩን መርምሮ የውርስ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ በገንዖብ ሉገመት በማይቻል ርእስ እንጂ ተገምቶ ላቀርብ አይገባም፣ ስለሆነም በገንዖብ ግምት ላቀርብ የማይቻል ክርክር የማየት ስልጣን የወረዲ ፍርድ ቤት ሆኖ ንብረቱ ተገምቶ በንብረት ግምቱ መሰረት ጉዲዩ ለስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት መቅረቡ ተገቢ በሚል ድምዲሜ ጉዲዩ ከመነሻው የቀረበው የሥረ ነገር ስልጣን በልላቸው ፍርድ ቤቶች ነው በማለት የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በመሻር ውሳኔ ሰጥቷል። እነ ወ/ት ቅድስት ዬሴፍ፤የስር ከሳሾች፣ በሰ/መ/ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩ በዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረበው ያለስረ ነገር ስልጣኑ ነው መባለ ያላግባብ ነው በሚል ሲሆን የስር ተከሳሾች ከነበሩት ውስጥ የአሁኑ ተጠሪዎች በሰ/መ/ የሰበር አቤቱታ ያቀረቡት ደግሞ የስር ከሳሾች ክስ በይርጋ ሉታገድ የሚገባው ነው በሚል ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም በዘህ ችልት እንዱታይ የተደረገ ሲሆን ግራ ቀኙ በሁለቱም መዛገቦች የጽሐፍ ክርክራቸውን አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎቸ ጋር በማገናዖብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የችልቱም ምላሽ የሚያስፈልጋቸው አበይት ነጥቦች፡-
ጉዲዩን የማየት የስረ ነገር ስልጣን የየትኛው ፍርድ ቤት ነው?
የስር ተከሳሾች ክሱ በይርጋ የታገደ ነው ተብል ሉወሰን ይገባል በማለት ያቀረቡት አቤቱታ በዘህ ችልት ሉስተናገድ የሚችል ነው ወይስ አይደለም የሚለ ሁነው ተገኝተዋል።
የመጀመሪያውን ጭብጥ በተመለከተ፡- ከክርክሩ ሂደት መገንዖብ የተቻለው የሥር ከሳሾች ከወላጅ እናታቸው ሉተላለፍላቸው የሚገባውና ግምቱ ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) የሆነ መኖሪያ ቤት በስር ተከሳሾች ከሕግ ውጪ መያዘን በክሳቸው ገልጸው ይህ ቤት እንዱለቀቅላቸው ይወሰን ዖንድዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ መሆኑን ነው። የሥር ተከሳሾች በቤቱ ላይ ከአመልካቾች እናት ያገኙት የውርስ መብት አለን የሚል ክርክር የላላቸው ከመሆኑም በላይ ቤቱን ለስር ከሳሾች ያስተላለፈት ሟች አቶ አለማየሁ በላቸው ከሕግ ውጪ የሟች ወ/ሮ ምንትዋብ አለማየሁ ወራሽነታቸውን በወረዲው ፍርድ ቤት በመ/ አረጋግጠው የሟች ወ/ሮ ምንትዋብ ሕጋዊ ወራሾች ተቃውሞ አቅርበው የሥር ከሳሾች ወላጅ አባት ያገኙት የወራሽነት ማስረጃ ከመሰረዘም በላይ ይህንኑ የወራሽነት ማስረጃ የተሰረዖበትን ውሳኔ በሕግ አግባብ ስለማስለወጣቸው የሥር ተከሳሾች የሚያቀርቡት ክርክር የላለ መሆኑን ከክርክሩ ሂደት ተመልክተናል። የሥር ከሳሾች አጥብቀው የሚከራከሩት አከራካሪውን ቤት አቶ አለማየሁ በላቸው ከአቶ ካሳሁን ጥላሁን የገዘት ነው የሚለውን ነጥብም በማንሳት ነው። በመሆኑም የስር ከሳሾች ግልፅ የዲኝነት ጥያቄ በውርስ የተላለፈላቸው ቤት ከሕግ ውጪ በስር ተከሳሾች የተያዖ መሆኑን የሚያሳይ የክስ ፍሬ ነገር ተጠቅሶ ቤቱ እንዱለቀቅላቸው ይወሰን ዖንድ የሚጠይቅ በመሆኑ አከራካሪው ቤት የስር ከሳሾች አውራሽ የወ/ሮ ምንትዋብ በላቸው ነው ወይስ የስር ተካሶሾች ወላጅ አባት የሆኑት የሟች አቶ አለማየሁ በላቸው ነው? የሚለውን ጭብጥ በመያዛ ፍሬ ነገሩን በሚገባ አጣርቶ ተገቢውን ዲኝነት መስጠትን የሚጠይቅ እንጂ የውርስ ማጣራት ሑደትን ተከትል በንብረቱ ላይ ወራሾች ያላቸውን የድርሻ መጠን ለይቶ ዲኝነት መስጠትን የሚጠይቅ አይደለም።የሥር ተከሳሾች ቤቱ አንድ መሆኑንና ግምቱ ተለይቶ ክስ መቅረቡን ጠቅሰው ጉዲዩን የማየት የስረ ነገር ስልጣን የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንጂ የወረዲው ፍርድ ቤት አይደለም በማለት የስር ከሳሾችን የሰበር አቤቱታ ደግፈው መልሳቸውን ለዘህ ችልት አቅርበዋል።
ከእነዘህ ነጥቦች አንጻር ጉዲዩን ስንመለከተው የስር ከሳሾች ክስ በማይገመት የውርስ ሃብት ላይ የቀረበ ያለመሆኑን ነው። ይልቁንም ከሳሾቹ በውርስ ሉተላለፍልን የሚገባው ቤት ከሕግ ውጪ ተይዜአል ከአለና ይህ የውርስ ንብረት ተለይቶ የታወቀ እስከሆነ ድረስ ውርስ የሚጣራበት ወይም ሃብቱ የውርስ ስለሆነ ግምቱ ሉታወቅ የሚችል አይደለም ለማለት የሚቻልበት የሕግ አግባብ የለም።ይህ ችልት በሰ/መ/ እና በላልች በርካታ መዙግብት በሰጠው አስገዲጅ የሕግ ትርጉምም የውርስ ሃብቱን የመከፊፈል ጥያቄ ንብረቱ በአይነት ተለይቶና ተገምቶ እስከቀረበ ድረስ በቀረበው ግምት መሰረት የፍርድ ቤቶችን የስረ ነገር ስልጣን ሉወሰንበት የሚገባ መሆኑን ገልጾ ወስኖል። በተያዖው ጉዲይ የስር ከሳሾች የክፍፍል ጥያቄ ያቀረቡበት ጉዲይ ሳይሆን የውርስ ንብረቱ ይለቀቅልኝ ጥያቄ ያቀረቡበትና ንብረቱም ተለይቶ የታወቀ በመሆኑ በንብረቱ ግምት የፍርድ ቤቱ የሥረ ነገር ስልጣን የማይወሰንበት የሕግ አግባብ የለም። በተሻሻለው የኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች ማሻሻያ አዋጅ ቁጥር 141/2000 አንቀጽ 27 (3) መሰረት ግምቱ ከብር 50‚000.00 በላይ የሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት እና ግምቱ ከብር 30‚000.00 በላይ የሆነ የሚንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚነሳ ክርክርንአይቶ የመወሰን ስልጣን ያለው መሆኑንም በግልጽ ተመልክቶአል።ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 18 እንደተደነገገው የገንዖብ ግምት ሉወሰን የማይችል ወይም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 23 ስር እንደሰፈረው የውርስ ማጣራት ስራ የተጀመረበት ነው ለማለት የሚቻልበት አግባብም አላገኘንም።
ስለሆነም የሥር ከሳሾች በጠየቁት ግምት መሰረት ጉዲዩ የቀረበለት የዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የማየት ስልጣን ማየቱና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም የስረ ነገር ስልጣኑን ማለፈ ተገቢ ሁኖ እያለ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የስር ፍርድ ቤቶችን ውሳኔ በመሻር ጉዲዩ በወረዲ ፍርድ ቤት የስረ ነገር ስልጣን የሚውድቅ ነው በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ሁለተኛውን ጭብጥ በተመለከተ፡- ከላይ እንደተገለፀው የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ክሱ በይርጋ የሚታገድ አይደለም በማለት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በሰጠው ውሳኔ ላይ የቀረበለትን የስር ተከሳሾችን ቅሬታ አልተመለከተውም። ይህም የሆነው ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የማየት የስረ ነገር ስልጣን ያለው ፍርድ ቤት የወረዲው ፍርድ ቤት ነው በሚል ድምዲሜ ችልቱ በመያዘ ምክንያት ነው። ይህ ስለመሆኑ የክርክሩ ሂደት እያሳዬ የስር ተከሳሾች ክሱ በይርጋ ሉታገድ ይገባል፣ ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ይርጋም በውርስ ሕጉ የተመለከተው ነው በማለት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የመጨረሻ ፍርድ ሳይሰጥበት ነው። ከክልል ፍርድ ቤቶች የተነሳ ጉዲይ የሰበር ስርዓት በተዖረጋባቸው ክልልች በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ሳይታይ ለዘህ ችልት የሚቀርብበት የሕግ አግባብ የላለ መሆኑን ይህ ችልት በሰ/መ/ እና በላልችም በርካታ መዙግብትበአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀፅ 2(1) መሰረት አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። በመሆኑም በአንደኛው ጭብጥ ጉዲዩ በዜን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሥረ ነገር ስልጣን የሚወድቅ ነው ከተባለና በዜኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ከጸና ወይም ከተለወጠ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቀርቦ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት መሆን ያለመሆኑ ተለይቶ ሳይወሰን ለዘህ ችልት የሰበር አቤቱታ የሚቀርብበት ስነ ስርዓታዊ አግባብ የላለ በመሆኑ የሥር ተከሳሾች የይርጋ ክርክርን አስመልክቶ ያቀረቡት አቤቱታ በቅድሚያ በክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ቀርቦ መታየት ያለበት ሁኖ አግኝተናል። በእነዘህ ሁለ ምክንያቶች በመሆኑም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
በአሮሚያ ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመዛገብ ቁ. 199980 በ04/04/2008 ዓ/ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሮአል።
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ክርክሩ እንዱቀጥል በማድረግ ከስረ ነገር ውጪ ባለት ላልች ክርክሮች እነ ምስራቅ አለማየሁ (ሶስት ሰዎች) ያቀረቡትን አቤቱታ መርምሮ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በ27/01/2007 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔመሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት መሆን ያለመሆኑን መርምሮ ተገቢውን ውሣኔ ይሰጥ ዖንድ ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 341/1/ መሰረት መልሰንለታል።
በዘህ ችልት በሁለቱም መዙግብት ለተደረጉት ክርክሮች ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ግራ ቀኙ ወገኖች የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
መዛገቡ ተዖግቶአል፤ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ ብለናል።
No topics extracted.