በፋደራል የቤተሰብ ህግ መሰረት በአባት በኩል ያለን መወለድ የመካድ ክስ በማቅረብ መቃወም ስለሚችለ ሰዎች የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 177/1-3 ውርስ
No summary available.
ሰኔ 28 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ጳውልስ አርሺሶ ሰናይት አድነው አመልካች፡- አቶ አየለ ወ/አለማው -ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1.ወ/ሮ እመቤት ማሞ ስለሁለቱም ተጠሪዎች 2ኛ ተጠሪ ቀረቡ 2.አቶ ሄኖክ ገ/ጻዱቅ መዛገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ ላቀርብ የቻለው አመልካች ሰኔ 29 ቀን 2008 ዓ/ም በተጻፈ አቤቱታ በመዛገብ በቀን 27/12/2007ዓ.ም የሥር የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የፋደራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዛገብ የካቲት 30 ቀን 2008 ዓ/ም የሰጠውን ውሳኔ በማጽናት የፍደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመዛገብ በ14/8/2008ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ ስህተቱ እንዱታረምልኝ በማለት ዲኝነት በመጠየቃቸው ነው።
የክርክሩ መንሥኤ የውርስ ሀብት ክርክር ነው። ጉዲዩ የተጀመረው በፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካች በ7/11/ 2007 ዓ/ም በተጻፈ በአሁኑ ተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ ከሟች አቶ ገ/ጻዱቅ ደስታ በኑዙዚ የተላለፈልንን በቀድሞ ወረዲ 23 ቀበላ 16 የቤት ቁጥር 207 የሆነ ቤት 1ኛ ተከሳሽ የሟች ሚስት ሳይሆኑ ሚስት ነኝ በማለት እና 2ኛ ተከሳሽም የሟች ልጅ ሳይሆኑ ልጅ ነኝ በማለት በኑዙዚ የተላለፈልኝን ቤት ይዖው ስለሚገኙ 1ኛ ተከሳሽ ሚስት አይደለም 2ኛ ተከሳሽም ልጅ አይደለም በማለት ይወሰንልኝ በማለት ያቀረቡትን የውርስ ሀብት ጥያቄ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ 1ኛ ተከሳሽ የሟች አቶ ገ/ጻዱቅ ደስታ ሚስት 2ኛ ተከሳሽም ልጅ አይደለም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
የአሁን ተጠሪዎች 1ኛተጠሪ የሟች ሚስት አይደለም 2ኛ ተጠሪ የሟች ልጅ አይደለም በማለት በተሰጠው ውሳኔ ቅር በመሰኘት ለፋደራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የሥር ፍርድ ቤት የወሰነውን እና 1ኛ ተጠሪ የሟች ሚስት አይደለም 2ኛ ተጠሪ የሟች ልጅ አይደለም በማለት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የስር ከሳሽ የስር ተከሳሾችን 1ኛ ተከሳሽ ሚስት አይደለም 2ኛ ተከሳሽም ልጅ አይደለም በማለት ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት የላቸውም በማለት ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ይህ ውሳኔ በስር የፋደራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም ተቀባይነት አግኝቷል።
ይህ የሰበር አቤቱታ በአመልካች የቀረበውም ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተሰጥቶ በስር ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጸናውን ውሳኔ ለማስለወጥ ሲሆን የአቤቱታው ይዖትም በአጭሩ፡- የኑዙዚ ተጠቃሚ የሆንኩበትን ንብረት ተጠሪዎች መብት ሳይኖራቸው መያዙቸውን በመግለጽ መብቴ እንዱከበርልኝ ያቀረብኩት ክርክር ውድቅ ተደርጎ በስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ በስር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመጽናት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈጸመበት በመሆኑ እንዱታረም የሚጠይቅ ነው።
የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ አመልካች 1ኛ ተጠሪ ከሟች ጋር ጋብቻ እንደላላቸው እና ከሟች ጋር በጋራ ያፈሩት ንብረት የላለ መሆኑን የሚያስረዲ የሰነድ ማስረጃ አቅርቤያለሁ እያለ ይህ ታልፍ አመልካች በተጠሪዎች ላይ ክስ የማቅረብ መብት የላቸውም በማለት በስር ከፍተኛ እና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት መጣራት ያለበት መሆኑ ስለታመነበት ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው የካቲት 16 ቀን 2009 ዓ/ም በተጻፈ መልስ ለሥር ፍርድ ቤት ያቀረቡትን ክርክር አጠናክረው ተከራክረዋል።
አመልካቹም መጋቢት 19 ቀን 2009 ዓ/ም የተጻፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።የነገሩ አመጣጥና የክርክሩ ሂደት አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ እንደተገለጸው ሲሆን በስር ፍርድ ቤት ከቀረበው ክርክር አንጻር በስር ፍርድ ቤቶች የተሰጡት ውሳኔዎች መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት መሆን ያለመሆኑን አጣሪው ከያዖው ጭብጥ አንጻር ጉዲዩ ተመርምሯል፡ የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአመልካችን ክስ ተቀብል እና የስር ተከሳሾችን ክርክር ውድቅ በማድረግ 1ኛ ተጠሪ የሟች ሚስት 2ኛ ተጠሪ የሟች ልጅ አይደለም በማለት ውሳኔ የሰጠው ሟች ለአመልካች የእህታቸው ልጅ መሆናቸውን በመግለጽ እና የክርክሩ ይዜታ በስተ ግራ ባለው ክፍት ቦታ የተሰራውን ቤት ከሟች ጋር በጋራ የሰሩ መሆናቸውን በመግለጽ ከሞትኩኝ በኃላ አመልካች በስማቸው አዘረው እንዱጠቀሙበት፣ እንዱሸጡ እና እንዱለውጡ ያደረጉት እና ስልጣን ባለው አካል የጸደቀ የቁም ኑዙዚ ማቅረባቸውን እና ሟች ከ1ኛ ተጠሪ ጋር በ23/11/1992ዓ.ም በተጻፈ ከሚያዛያ 12 ቀን 1978ዓ.ም ጀምሮ 1ኛ ተጠሪ እንደ ሚስት በ80 እንደ ሰራተኛ በደመወዛ ልጅ ሳንወልድ አብረን ስንኖር በእድሜ ባለመመጣጠናችን የሰራሁበትን ደመወዛ ብር 3000.00 ተቀብዬ ወደፉት ቀሪ ንብረት እና ሀብት አለኝ በማለት ላልጠይቅ ተስማምቻለሁ በማለት የፈረሙበትን ማስረጃ አቅርበዋል በማለት ሲሆን የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይህንን የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትን ውሳኔ የሻረው አመልካች በተጠሪዎች ላይ ክስ የማቅረብ መብት የላቸውም በመሆኑም ተጠሪዎች ይህንን አስመልክቶ ያቀረቡትን መቃወሚያ የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውድቅ በማድረግ የሰጠው ብይን ተገቢ አይደለም በማለት ሲሆን ይህ ውሳኔ በስር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም ተቀባይነት አግኝቷል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከዘህ በላይ እንደተመለከተው የቀረበ ሲሆን እኛም የሰበር አመልካች 1ኛ ተጠሪ የሟች ሚስት 2ኛ ተጠሪ የሟች ልጅ አይደለም ይባልልኝ በማለት ያቀረቡት አቤቱታ በስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተቀባይነት ቢያገኝም በስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውድቅ በማድረግ መወሰናቸው በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም?
የሚለውን ጭብጥ ይዖን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረነዋል።
አመልካች በስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክስ 1ኛ ተጠሪ የሟች ሚስት አይደለም 2ኛ ተጠሪም የሟች ልጅ አይደለም ይባልልኝ የሚል ሲሆን ለዘህም ምክንያታቸው 1ኛ ተጠሪ ከሟች እንደ ሚስት በ80 እንደ ሰራተኛ በደመወዛ ልጅ ሳይወልደ አብረው ለመኖር ተስማምተው ሲኖሩ ቆይተው 1ኛ ተጠሪ የነበራቸውን ብር 3000.00 ወስደው ከአመልካች ጋር ወደፉት ምንም የቀረ ንብረት እና መብት አለኝ በማለት ላልጠይቅ ብለው የተስማሙበት የሰነድ ማስረጃ አለኝ በማለት አቅርበው በዘህ ምክንያት 1ኛ ተጠሪ የሟች ሚስት 2ኛ ተጠሪም የሟች ልጅ አይደለም ይባልልኝ በማለት ነው።
ከተጠሪዎች በኩል የቀረበው እና ምላሽ ማግኘት የሚገባው መከራከሪያ አመልካች ይህንን ክስ በማቅረብ የመከራከር ህጋዊ መብት የላቸውም የሚለው ነው።
በመሰረቱ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 177/1-3/ ያለ ድንጋጌዎች በአባት በኩል ያለን መወለድ መቃወም የሚቻለው የመካድ ክስ በማቅረብ ብቻ ሲሆን ክሱንም የሚያቀርበው የልጅ አባት ነህ የተባለ ሰው ነው። ሆኖም በህግ ግምት የልጁ አባት ነህ የሚባለው ሰው የሞት ወይም የመካድ ክስ ለማቅረብ በተወሰነው ጊዚ ውስጥ አባት ነህ የተባለው ሰው ችልታ ያጣ እንደሆነ ከተወላጆች አንደ በእርሱ ፊንታ ሆኖ የመካድ ክስ ማቅረብ እንደሚችል የፍደራል የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 177/1/ ይደነግጋል። ነገር ግን ተወላጆች የላለ እንደሆነ እናት እና አባት የመካድ ክስ የማቅረብ መብት ያላቸው ሲሆን እነዘህም በላለ ጊዚ ደግሞ ወደ ላይ ከሚቆጠሩ ወላጆች አንደ መብቱን ሉሰራበት እንደሚችል ከዘህ በላይ የተጠቀሰው የህግ አንቀጽ 177/2/ ላይ ተመልክቷል። በመጨረሻም ወደ ላይ የሚቆጠሩ ወላጆች የላለ እንደሆነ በመካድ ክስ መብት ሉሰራበት የሚችለው ከወንድሞቹ ወይም ከእህቶቹ አንደ እንደሆነ የቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 177/3/ ይደነግጋል።
ወደ ተያዖው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች የሟች የእህት ልጅ መሆናቸው በኑዙዚ ሰነደ ላይ የተመለከተ በመሆኑ ይህንን ክስ ለማቅረብ ህጋዊ መብት የላቸውም ላላው ሚስትነት በተመለከተ የቀረበው መቃወሚያ እንደመረመርነው አመልካች ሟች አለ የሚለት ኑዙዚ አመልካች የእህቴ ልጅ ስለሆነ በአዱስ ከተማ ወረዲ 23 ቀበላ 16 የቤ.ቁ 207 ከሆነው መኖሪያ ቤቴ በስተግራ ባለው ክፍት ቦታ ወጪ በማውጣት አብሮ ስለሰራ ይህንን የተሰራ ቤት ከህልፈተ ህይወቴ በኋላ በስሙ አዘሮ እንዱጠቀም ተናዛዡለሁ የሚል ነው። በመሆኑም አመልካች ኑዙዚ አለኝ የሚለት ከዋናው ቤት በስተግራ በኩል ባለው ክፍት ቦታ ላይ የተሰራ ቤትን በተመለከተ በመሆኑ የጠቅላላ ሀብት ነኑዙዚ ተጠቃሚ ነኝ በማለት ያቀረቡት ክርክር በላለበት የአሁን 1ኛ ተጠሪ ሚስትነት በመቃወም አቤቱታ ለማቅረብ የሚያስችል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 33 መሰረት መብት ወይም ጥቅም የላቸውም።
በመሆኑም የስር መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠሪዎች በቀረበለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ መሰረት ክሱን ውድቅ በማድረግ ሉወስን ሲገባ መቃወሚያውን ውድቅ በማድረግ በአመልካች ክስ መሰረት 1ኛ ተጠሪ የሟች አቶ ገ/ጻዱቅ ደስታ ሚስት አይደለም 2ኛ ተጠሪም የሟች ልጅ አይደለም በማለት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የስር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ የስር ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በማጽናት የሰጠው ውሳኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት አላገኘንም። በመሆኑም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
በስር የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በ27/12/2007 ዓ.ምተሰጥቶ በስር የፋደራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ በ30/6/2008ዓ.ም ዓ.ም የተሻረው እና በስር የፋደራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ በ14/8/2008ዓ.ም ዓ.ም የጸናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
ይህ ውሳኔ አመልካችን በኑዙዚው መሰረት የውርስ ሃብት ክርክር ከማቅረብ አያግዲቸውም ብለናል።
የዘህን ችልት ወጪና ኪሳራ የግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
በዘህ ክርክር ምክንያት የተሰጠው የእግድ ትዔዙዛ ተነስቷል ለሚመለከተው አካል ይጻፍ።
የውሳኔው ግልባጭ ለሥር ፍርድ ቤቶች ይድረሳቸው።
መዛገቡ ውሳኔ ስላገኘ ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.