በልላ አገር ህግ እና በኢትዮጵያ የቤተሰብ ህግ መካከል እንደባልና ሚስት አብረው በመኖር ግንኙነት ውስጥ የተፈራ ንብረት የጋራ እንዱሆን ለመወሰን በሁለቱም ህጎች መካከል ግጭት መኖር ያለመኖሩን የላላኛው አገር ህግ እንዱቀርብ በማድረግ መወሰን የሚገባው ስለመሆኑ በዓለም አቀፍ የግለሰብ ህግ /Private International law/ መሰረት በዖርፈ እውቀት ያለ ወይም ምሁር /Scholar/ የሰጠውን አስተያየት በማስረጃነት ሲቀርብ የቀረበውን አስተያየት እንደማንኛውም ማስረጃ የመመዖን ሥልጣን አስተያየቱ የቀረበለት ፍርድ ቤት ስለመሆኑ የኢ.ፉ.ድ.ሪ ቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 5፤102 /1/ 123132 አቶ ከሳሁን ታደሰ እና ወ/ረ ፀዲለ ሀፍታይ ሚያዛያ 30 ቀን 2009 ዓ/ም 56. ለህፃን ልጅ ማሳደጊያ ቀለብ የመስጠት ግዳታ ያለበት ወላጅ፣ የሚከፍለውን የገንዖብ መጠን በተመለከተ ለመወሰን ግምት ውስጥ ሉገቡ ስለሚገባቸው ሁኔታዎች የተሻሻለው ፋዳራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 197 (2) ፣202 XXIV
No summary available.
ሰኔ 19 ቀን 2009 ዓ.ም ዳኞች፡- አልማው ወላ ሙስጠፊ አህመድ አብርሃ መሰለ ጳውልስ አርሺሶ ሰናይት አድነው አመልካች፡- አቶ በላይ ዖለቀ - የቀረበ የለም።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ትዔግስት ዲባ /የህፃን ሀሴት በላይ ሞግዘት/- ቀረቡ መዛገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው።ጉዲዩ ከህፃን ልጅ ማሣደጊያ የሚቆረጥ ገንዖብ መጠን የሚመለከት ክርክር ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩ መነሻ ተጠሪ ያቀረበችው ክስ ነው። ከግራ ቀኛቸው ሕፃን ሀሴት በላይ በጥር 25 ቀን 2004 ዓ.ም የተወለደች መሆኑንና የአመልካች አባትነትም በፍርድ ቤት ውሳኔ የተረጋገጠ መሆኑን፤ ለልጅቷ ቀለብ ብር 5,750.00 (አምስት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ብር) እንዱከፍለና አመልካች ነዋሪነታቸው ስዊዖርላንድ በመሆኑ ቀለቡን በየወሩ ሳያቋርጡ የሚከፈለ ስለመሆኑ በቂ ዋስ ወይም መያዡ እንዱያቀርቡ እንዱታዖዛላቸው፤ ይህ ካልተቻለም የህፃኗ ዔድሜ 18 ዓመት እስኪሞላት ድረስ ያለውን ቀለብ ፍርድ ቤቱ አስልቶ አመልካች በአንድ ጊዚ በህፃኗ ሞግዘት ስም በሚከፈት የባንክ ሂሳብ ገቢ እንዱያደርጉላቸው እንዱወሰንላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል።
አመልካች በተከሳሽነት ቀርበው ተጠሪ የጠየቀችውን ገንዖብ አመልካች በየወሩ ለህፃኗ ማሳደጊያ ለመክፈል አልችልም፤የምችለው በወር ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) መሆኑን ወርሐዊ ገቢያቸው በኢትዮጵያ ብር ከ4,000.00 (አራት ሺህ ብር) እንደማይበልጥ፤ለላላ ልጃቸው ቀለብ እንደሚቆርጡ፤ዔዲ እንደሚከፍለና ላላ ትዲርም መስርተው እየኖሩ በመሆኑ ወጪ ያለባቸው መሆኑን በመግለፅ ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት አመልካች ተጨባጭ ማስረጃ አላቀረቡም የቀለብ መጠን ሲወሰን ለቀለብ ተቀባዩ የሚያስፈልጉ ተጨባጭ ወጭዎች እንዱሁም የቀለብ ክፍያ አቅም ተገናዛቦ መሆን አለበት። በዘሁ መሰረትም አመልካች ከነሐሴ ወር 2007 ዓ.ም ጀምሮ ለልጅቷ ቀለብ በየወሩ ብር 4,000.00 (አራት ሺህ ብር) እንዱከፍለ ክፍያውንም አመልካች በጠየቁት መሰረት የ6 ወርን በአንድ ጊዚ በተጠሪ የባንክ ሂሳብ ገቢ እንዱያደርጉ፤ለዘሁ ክፍያ መፈፀምም ዋስትና የሚሆን ለብር 696,000.00 (ስድስት መቶ ዖጠና ስድስት ሺህ ብር) የሚበቃ የሰው ዋስ ወይንም የንብረት ማስያዡ እንዱያሲይዘ ይህንን ማድረግ ካልቻለ ለቀሪው የ14 ዓመትና 6 ወራት የሚሆን የቀለብ ክፍያ ብር 696,000.00 (ስድስት መቶ ዖጠና ስድስት ሺህ ብር) የህፃን ሞግዘት ለዘሁ ጉዲይ በሚከፍቱት የባንክ ሂሳብ በአንድ ጊዚ እንዱያደርጉ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
በዘህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል።
ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ በስር ፍርድ ቤቱ የተሰጠው ውሳኔ ስህተት ያለበት ሆኖ አልተገኘም በማለት በውሳኔ አጽንቶታል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበውም ይህንኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ሰኔ 20 ቀን 2008 ዓ.ም በፃፈት አቤቱታ በስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዖርዛረው አቅርበዋል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ በዘህ ጉዲይ አመልካች ከኢትዮጵያ ዉጪ ስለሚኖር የገቢውን መጠን የማስረዲት ሸክም በርሱ ላይ ያርፊል ተብል በስር ፍርድ ቤቶች የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልት እንዱቀርብ በመደረጉ ተጠሪ መልስ እንዱሰጡበት በታዖዖው መሰረት ሚያዘያ 17 ቀን 2009 ዓ.ም የተፃፈ መልስ አቅርበዋል። የአመልካች አቤቱታቸውን የመልስ መልስ የማቅረብ መብት በመታለፈ የቀረበ የመልስ መልስ የለም።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም የስር ፍርድ ቤቶች ለህፃን ማሳደጊያ አመልካች እንዱከፍል ውሳኔ የሰጠው በሕግ የተመለከቱትን ሁኔታዎች መሰረት በማድረግ ነው ወይስ አይደለም ? የሚለውን ጭብጥ በመያዛ ጉዲዩን መርምረናል። እንደመረመርነውም የአመልካች ጥያቄ በወር ብዘ ውጭ ማለትም የባንክ ዔዲ፤የልጅ ቀለብ፤የቤተሰብ ማስተዲደር ሁለ ወጭዎች ያለብኝ መሆኑን በማስረጃ አስደግፋ አቅርቤ እያለሁና የምችለውም በወር ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር ) ብቻ መሆኑን እያስረዲሁ ከአቅሜ በላይ የተጋነነ ቀለብ በወር ብር 4,000.00 (አራት ሺህ ብር) እንድከፍልና እና በአንድ ጊዚ በሞግዘት አድራጊዋ በተከፈተ ባንክ ብር 696,000.00 (ስድስት መቶ ዖጠና ስድስት ሺህ ብር) ገቢ እንዲደርግ የስር ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል የሚል ሲሆን ተጠሪ በበኩላቸው ልጅ ወልድ ማሳደግ ከፍተኛ ሀላፉነት የሚጠይቅ እና እንደ አባት እንደ እናት ተንከባክቦ ፍቅርን፤ጊዚን እንዱሁም ገንዖብን ሰውቶ ለቁም ነገር ማብቃትን ይጠይቃል። ተጠሪም እስከ አሁን ድረስ ይህን ሀላፉነት ለብቻቸው በመወጣት ላይ ይገኛለ፤ በአንፃሩ አመልካች ከመኖሪያ ቤት ሽያጭ ከፍተኛ ገንዖብ(ከአምስት ሚሉዮን ብር) በላይ ማግኘታቸው በተረጋገጠበት ሁኔታ ልጅነትን ሳይክደ ከሚጠበቅባቸው የበዙ ሀላፉነት የህፃኗን አስተዲደግ በገንዖብ የመደገፍ ሀላፉነትን ሉወጡ እንደሚገባ በማመን እንዱሁም ኢፋዳሪ ህገመንግስት እና ሀገራችን ባጸደቀቻቸው ዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ሰነድች እንዱሁም የሰበር ችልቱ በተደጋጋሚ በሰጣቸውን ውሳኔዎች ፍርድ ቤቶች ህፃናትን አስመልክቶ የሚወሰኑ ውሳኔዎች የህጻናቱን ጥቅም ከግምት ሉያስገቡ እንደሚገባ የተመለከተውን ግምት ውስጥ በማስገባት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያልተፈጸመበት ስለሆነ የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዖብ የተቻለው አመልካች ለወለዲት ህፃን ሀሴት በላይ ለማሣደግ የሚያስፈልገውን ወጪ የመጋራትና የመሸፈን ግዳታ ያለበት መሆኑ አላከራከረም አመልካችንና ተጠሪ የሚያከራከረው አመልካች ለህፃኗ አስተዲዲግ ሉከፍለው የሚገባው የገንዖብ መጠን ነው።
ለህፃን ልጅ ማሳደጊያ ቀለብ የመስጠት ግዳታ ያለበት ወላጅ፣ የሚከፍለው የገንዖብ መጠን የሚወስነው እንደባለጉዲዩ ሁኔታና እንደ አካባቢው ልምድ የሚስማማውን በመከተል በቀለብ ተቀባዩ ምግብ፣ መኖሪያ፣ ልብስ፣ ጤናውን የሚጠብቅበትና እንደ ሁኔታው ለትምህርት አስፈላጊ የሆኑትን ወጭዎች የሚሸፈን መሆን እንደሚገባው በተሻሻለው የፋዳራል የቤተሰብ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 197 አንቀጽ 2 ይደነግጋል።
ከዘህ አንፃር ሲታይ አመልካች በተወሰነ መልኩ ከኢትዮጵያ ውጭ ገቢ እንዲለቸው ከመታመኑ በላይ በኢትዮጵያ ውስጥም ከመኖሪያ ቤት ሽያጭ ከ2.5 ሚሉዮን ብር ያገኙ መሆኑን ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዖን ሥልጣን ባላቸው ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል።አንድ ወላጅ ህፃን ልጁን በጥሩ ሁኔታ ለመመገብ፤ በጥሩ መኖሪያ አካባቢ ለማኖርና ጤናውን ለመጠበቅ እንዱሁም ጥሩ ትምህርት እንዱያገኝ ለማድረግ የሚያስፈልገውን ወጭ መሰረት በመድረግ ሉወሰን እንደሚገባና ከአመልካች ገቢ አንፃር ሲታይ ከብር 1,ዐዐዐ.00 /አንድ ሺህ ብር/ በላይ ለመክፈል አቅም የለኝም በማለት ያቀረቡትን ክርክር በተሻሻለው የፋዳራል የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 197 እና አንቀጽ 202 ድንጋጌዎችን መሰረት ያላደረገ በመሆኑ አልተበቀልነውም።
ሲጠቃለል የስር ፍርድ ቤቶች አመልካች ለህፃኗ አስተዲደግ እንዱከፍለየሰጡት ውሳኔ የቀለብ ገንዖብ መጠኑ ሆነ የአከፊፈለ ሁኔታ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስላልተገኘ ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ.108713 ነሐሴ 6 ቀን 2007 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 173752 ሚያዘያ 28 ቀን 2008 ዓ.ም በውሳኔ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ስ/ስ/ህ/ቁ.348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዘህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
መዛገቡ ተዖግቷል፤ወደ መዛገብ ቤት ይመለስ ብለናል።
No topics extracted.